Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን አንድ ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ሰላም ለእናንተ ይሁን

አንድ ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደ መኪናው ሲመለስ የአንዱ ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል፡፡ ይህኔ ይበሳጭ እና አከባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ ያጣል፡፡

ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሳለ አከባቢው ላይ ያለ አንድ እብድ ነገሩን ተከታትሎ ኖራልና "ምን ሆነህ ነው?" ይለዋል፡፡ ሰውየውም በንቀት አይን አየት እያደረገው "የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ አከባቢው ላይ የለም" ይለዋል በብስጭት ስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡

ይህኔ እብዱ "ነው እንዴ? ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም" አለው፡፡

ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተውና አንዳለውም አደረገ፡፡

"ቆይ አንተ እብድ አይደለህ እንዴ! አንዴት ይህ ሀሳብ ሊመጣልህ ቻለ?" ብሎ ጠየቀው፡፡

እብዱም ቀበል አድርጎ "ታዲያ እኔ እብድ ነኝ እንጂ ደደብ አይደለሁም" ብሎ ይመልስለታል፡፡

ዝቅ በል፤ ዝቅ ስትል ከፍ ትላለህ፤ ተናነስ፤ ራስህን አትቆልል፤ ሁሌም እኔ አዋቂነኝ አትበል።
,10th fun ✓

kogoese