Get Mystery Box with random crypto!

ካነበብኩት ትንሽ ላጋራቹ ¹.⁸k ንስር ቁራ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ካነበብኩት ትንሽ ላጋራቹ ¹.⁸k

ንስር ቁራ

ታላቁን ንሥር አሞራ (Eagle) የሚደፍረው ቁራ ብቻ ነው። ቁራ በንሥሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና ማጅራቱን ደጋግሞ በሹል መንቁሮቹ ይነክሰዋል።

ንሥሩ የቁራው ንክሻ ቢያሳምመውም ከቁራው ጋር በመታገል ጊዜውንና ጉልበቱን አያባክንም። ንሥሩ ክንፎቹን ዘርግቶ ወደ ላይ ከፍ ከፍ ከፍ እያለ ይበራል። በቃ ከፍታውን እየጨመረ ወደ ሰማይ ያሻቅባል። ንሥሩ ከፍታውን በጨመረ ቁጥር ቁራው የመተንፈስ ችግር ያጋጥመዋል።

በመጨረሻም ቁራው በሚያጋጥመው #የኦክስጅን_እጥረት ይሞትና ሬሳ ሆኖ ወደ መሬት ይወድቃል።

ዝም ብለህ ወደ ላይ ወደ ከፍታህ ውጣ። ቁራዎቹ ከአቅማቸው በላይ መሄድ ስለማይችሉ ተመልሰው ይወድቃሉ።

በተስፋዬ ሃ/ማርያም