Get Mystery Box with random crypto!

እናትነት ².⁸k እናትነት የሚጀመረው ነፍስ በሆዷ ውስጥ ካበቀለችበት ቀን ጀምሮ አይደለ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

እናትነት ².⁸k

እናትነት የሚጀመረው ነፍስ በሆዷ ውስጥ ካበቀለችበት ቀን ጀምሮ አይደለም......እናት መሆን የሚጀመረው ልክ 9ወር ሙሉ በሆዷ ተሸክማ ወደዚህ አለም ልታመጣው እእ.........ብላ ከምታምጥበ exት ቀን ጀምሮ ነው። 9ወር ሙሉ በሆዷ ስታስቀምጠው እያንዷንዷን ቀን ልጇን በእጇ ምትታቀፍበትን ቀን በጉጉት ትጠብቀዋለች። በእያንዳንዱ ደቂቃ ስለልጇ ጤንነት....ስለ ልጇ ትንንሽዬ እጆች....ስለ ልጇ አስተዳደግ ታስባለች...ትልቅ የስቃይ ሰዓታትን አሳልፋ.....ደሟን አፍስሳ......''እናት'' ለሚባለው ክብር ትበቃለች።
እናትነት እንዲህ ነው:-

....ልክ በእጆቿ አቅፋ እነዛን ትንንሽዬ እጆች እየነካቻቸው ጡት ስታጠባው
....ከዛም እነዛ የሚያማምሩ ትንንሽዬ ጣቶቹ ደረቷን ሲነካት
....በራሷ ጉያ ውስጥ ታቅፋ እሹሩሩ ብላ ስታስተኛው
....ከዛም ከፍ ሲል በእጁም በእግሩም ዳዴ ማለት እየጀመረ ሲጫወት
....እየጠነከረ ሲመጣ መራመድን በነዛ በትንንሽዬ እግሮቹ መንገድ እየሳተ ትንሽ እየተወላገደ በኋላም ላይ መራመድን ሲችል
....ትንሽ ከፍ ብሎም በዛ ማር በሆነ አንደበቱ እማዬ እማ እያለ ሲጠራት
....ት/ቤት ገብቶም እኔ መሆን ምፈልገው ብሎ የመጀመሪያ ምኞቱን ሲነግራ
....ከዛም ከፍ ብሎ ምኞቱን ሊያሳካ ሲጥር እናትም ስታግዘው
....ከዛም ከፍ ብሎላት የልጅነት ምኞቱን አሳክቶ ተመሮቆ ስራ ይዞ እናትም በልጇ ስትደሰት
....ከዛም ከፍ ብሎ ለወግ ለማዕረግ በቅቶላት የሚፈልገው ስኬት ላይ ደርሶ የራሱን ቤተሰብ መስርቶ አያት የሚባለውን ማዕረግ ሲሰጣት
.......አነዚህ ሁሉ ሂደቶች ውስጥ <<እናትነት>> አለ ትልቅ ልጅ ሆኖላት እንኳን እንቅፋት ቢመታው ''እኔን ልጄ'' ትለዋለች።

እናትነት ልጅ ከወለደችበት ቀን ነው የሚጀመረው....አው....ሴት ልጅ በነዛ 7 ወይም 8 ቀናት ውስጥ ደም እየፈሰሳት እያመማት ''እናት'' የምትሆንበትን ቀን ትጠብቃች እነዛ የህመሟ ቀናቶች አልፈው ወደፊት ''እናት'' እንደምትሆን ይነግራታል......ሴት ልጅ 9 ወር በሆዷ ልጇን ስትሸከም ደከመኝ፣ ከበደኝ፣ አሳመመኝ ሳትል ታግሳ ያቺን ቀን ናፍቃ ልጇን በስቃይ ትወልደዋለች....... 6ወር ኧረ ከዛም በላይ ጡቴ ደረቀብኝ፣ ነከሰኝ ሳትል ሳትሰስት በጡቷ ትመግበዋለች.... ልጇን እንዲመቸው በጀርባዋ አዝላ እሹሩሩ እያለች ታስተኛዋለች.....ሳዝለው ወገቤን አመመኝ፣ እሹሩሩ ስለው ጉሮሮዬ ደረቀ ሳትል ህመም ቢሰማት እንኳን ችላ አልፋ የራሷን ኑሮ ትታ ለልጇ ትኖራለች.... በሱ ሳቅ የምትስቀው....በሱ ለቅሶ የምታለቅሰው....ልጇ ሰው ስለሆነ ብቻ አይደለም ''እናት'' ስለሆነች ነው.... አው እናት እንዲህ ናት....ታድያ እናት መሆን መታደል አይደል?

StEpHeN17