Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን • ሰዉ በነገሮች መሳካትና አለመሳካት ላይ በሚያደርጋቸዉ መስተጋብሮች | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ሰላም ለእናንተ ይሁን

• ሰዉ በነገሮች መሳካትና አለመሳካት ላይ በሚያደርጋቸዉ መስተጋብሮች ሃሳቡ፣ ህልሙ ወይ ይሳካለታል አለበለዚያ ይከሽፍበታል፡፡ በህይወትህ ዉስጥ በምትኖረዉ የተገደበ ጉዞ እያንዳንዷን ዉሳኔህን እንደ ብስለትህ መጠን ትተገብራቸዋለህ፡፡

• አእምሮህ ከምንም በላይ የተሳለና 'ግራና ቀኝ' አስተሳሰብን ያዳበረ እንዲሆን ሁልጊዜ ኮትኩተዉ፣ መግበዉ፣ አሳድገዉ፡፡

• በእድሜ ብዛት ወይም በሃብት ከፍታ አእምሮህ ሊያድግ አይችልም፡፡ ይልቁንስ በየቀኑ የምትሰማዉ፣ የምታዳምጠዉና የምታሰላስለዉ ነገር ዛሬህን እየቀረፀ የነገዉን አንተነትህን ያሳይሃል፡፡

• ብስለት መፅሃፎችን በማንበብ፣ ከሰዎች ጋር አብረህ በማሳለፍ፣ በህይወትህ ከሚገጥሙህ ችግሮች፣ ከህብረተሰቡ ደስታና ሃዘን ወዘተ.ልትቀስማቸዉ የምትችላቸዉ ናቸዉ፡፡

• ብስለት ባገኙት አጋጣሚና ቦታ ሁሉ ማዉራት ሳይሆን፣ ጆሮን ከፍቶ የሰዎችን ሃሳብ በመገንዘብና ጠቃሚ የሆኑትን በመለየት የሚዳብር ነዉ፡፡

• ሰዎችን በአለባበሳቸዉና በዘመናዊ ስታይላቸዉ 'የበሰሉ' እንደሆኑ ልትገምት አይገባም፡፡ እኔም ሆንኩ አንተ የተለያየ ባህሪ፣ እምነት፣ ቋንቋ ወዘተ...ሊኖረን ይችላል ግን ሃሳብህ በኣካባቢህ ላሉት ወሳኝ ነዉ ብዬ ካመንኩ በትዉልድ መካከል አስፈላጊዉ ጉዳይ ሃሳብህ ነዉ፡፡

• ትዉልዶች በአንድ ላይ በሚኖሩባት በኛ ሀገር ፣ሰዎች ከተለያዩ የህይወት መስመሮቻቸዉ ተነስተዉ የበሰሉ እንደሆኑ ከነሱ ትዉልድ በኋላ የመጣዉ ግን ነገሮችን እንዳበለሻሸ ሲናገሩ ትሰማለህ፡፡ ይሄ የኛ የሃበሾች ትልቁ ችግራችን ነዉ ብዬ አስባለሁ፡፡

• የበሰለ ሰዉ በበዛ ቁጥር የበሰለ ትዉልድን ያፈራል፤ያ የበሰለ ትዉልድ ደግሞ ከጊዜያዊ ጥቅምና ጉራ ባለፈ ነገን የሚናፍቅ አዲስና ብርቱን ትዉልድ ይፈጥራል፡፡

• እራስህን ከትንሹ እስከትልቁ ዉሳኔ እንዴት መብሰል እንዳለብህና ጠቃሚዉ ጎን የቱ እንደሆነ እየለየህ አስተምረዉ፣ ገስፀዉ፣ መንገድ ምራዉ፣ አሳርፈዉ፣ አስኪደዉ፡፡ በል ይመችህ! ይመችሽ!

ቸር ያሰማን

kogoese