Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን •ቤተሰቦችህ በምንም ነገር ልትተካቸዉ የማትችላቸዉ ልዩ ማንነቶችህ ናቸዉ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ሰላም ለእናንተ ይሁን

•ቤተሰቦችህ በምንም ነገር ልትተካቸዉ የማትችላቸዉ ልዩ ማንነቶችህ ናቸዉ፡፡

•የጤናህ ጉዳይ ከምንም ነገር በላይ ጠቃሚ ነዉ፡፡ የምትበላዉን ምግብ ምረጥ፣ ታትረህ ስራ፣ በህይወትህ አላማ ይኑርህ እንዲሁም ሃብትህን በብልሃት ያዘዉ፡፡

•ለራስህ ክብርና ስርአት አታመቻምች፡፡ ለማንም ሰዉ ብለህ የራስህን ክብር አትጣል፡፡ የራስህን መስመር አስምር፣ አይሆንም ማለትን ተማር ሲያስፈልግ ብቻ ማንነትህን ግለጽ፡፡

•የነፍሴ ክፋይ እና እዉነተኛ ፍቅር የሚባሉ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነቶች በዘፈንና በፊልም ታጅበዉ የሚኖሩ ነገር ግን ዉሸትና ግነት የሞላባቸዉ ሃሳባዊ ድርሰቶች መሆናቸዉን ተረዳ፡፡

•ከአምላክህ ቀጥሎ ለሕይወትህ ትኩረት መስጠት የምትችለዉ አንተ ራስህ መሆንህን እወቅ፡፡ ህይወትህን አትቀልድበት! መስራት ባለብህ ነገር ስራ..መዝናናት በሚኖርብህ ጊዜም እንዲሁ፡፡

•'አንዴና አንዴ' ብቻ እንደምትኖር አዉቀህ ጊዜህንና ጉልበትህን በማይጠቅም ቦታና ማንነት ዉስጥ አታባክነዉ፡፡

ቸር የሰማን