Get Mystery Box with random crypto!

#ሊብራዎች ለምን ይከፋሉ  ------------------------------------- Episode | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

#ሊብራዎች ለምን ይከፋሉ 
-------------------------------------
Episode 11
»» ሊብራዎች ሲያዝኑ ሚዛናቸውን ይስታሉ፣ ስሜታቸው ይዋዥቃል፣ ደስታቸውንም ለመመለስ ሚዛናቸውን ማስተካከል አስፈላጊ ነው። ብዙ ነገራቸው ስለሚዛባ በፊት በጣም ሚወዱትን ነገር ሳይቀር ፍላጎት ያጡበታል፣ ተነሳሽነታቸው ይጠፋል፣ ተስፋቸውም ይመነምናል። ተስፋ ሰጪ ንግግሮችን አውሯቸው፣ ለመነሳት ቅርብ ናቸው። ያልተለመዱ ዲርጊቶችን መሞከር፣ አዳዲስ ቦታዎችን ማየት ወደ ቀድሞ ግዜያቸው እንዲመለሱ ያግዛቸዋል፣ በራሳቸውም መተማመን ሲጀምሩ በቶሎ ወደ ቀድሞ ሰለማቸው መመለስ ይጀምራሉ።

»» ስሜታዊያኑ ሊብራዎች ነገሮች ከእጃቸው ሚወጡ ከሆነና መቆጣጠር ከከበዳቸው፣ ወዲያው ወደ መሰላቸትና ተስፋ መቁረጥ ይሄዳሉ፣ በተቻላቸው አቅም ምንም እንዳልተፈጠረ አክት ያደርጋሉ። ጥሩ አፅናኝ ካገኙ ሀዘናቸው እድሜ አይኖረውም ወዲያው ደና ይሆናሉ፣ እንደዛውም የቅርብ ጓደኛቸው ድጋፍ ካላገኙ ሀዘናቸው ይበረታል። ካጠፉም ለይቅርታ ወደ ኋላ ሚሉ አይደለም፣ ሀላፊነቱን ማይወጣ ሰው ካገጠማቨው ግን በደንብ ይበሳጫሉ፣ ንዴታቸውን ከመገለፅ ወደ ኋላ አይሉም።

»» የማንም ሰው ሀዘን ሚከብደው፣ ክብደት በሰጡት ልክ ነው፣ ምንም እንዳልተጎዱ ሳይሆን ለነገሮች ያላቹን ክብደት መቀነስ አስፈላጊ ነው። ሀዘናቸው እድሜ ባይኖረውም፣ ሀዘን ላይ ሲሆኑ ድምፃቸውን ያጠፉና ሲብስባቸው ያፈነዱታል፣ ፣አይረጋጉም፣ በፊት ሚፈልጉትን ከሰዎች መጫዎት አይፈልጉትም፣ ግድም አይሰጣቸውም፣ በሌሎች የመገፋትና የመተው ስሜት ይሰማቸዋል።







የሌሎችም ጥምረት ይቀጥላል