የ በረዶ ሊዮፓርድ ( Snow Leopard )
- የበረዶ ሊዮፓርዶች የሚገኙት ተራራማ የ ኤዥያ ክፍል ውስጥ ነው።
- የሚመገቡት የተራራ በጎች ፣ አጋዘኞችን ፣ አጥቢ እንስሳቶችን እና ወፎችን ነው
- የበረዶ ሊዮፓርዶች ከሌሎች የነብር ዝርያዎች በሙሉ ለየት የሚያደርጋቸው አያገሱም ( አስፈሪ ወፍራም ጩኸት አያወጡም)
- በ አሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው 8478 ብቻ በመሆኑ ቁጥራቸው ከ 10,000 በታች የሆኑ እንስሳቶች ውስጥ ተመድበው ጥበቃ እየተደረገላቸው ይገኛል።
- የ ሴቷ የ እርግዝና ጊዜ ከ 90 እስከ 105 ቀን ይቆያል
- የበረዶ ሊዮፓርዶች -40 ድግሪ የሚደርስ ቅዝቃዜ ውስጥ መኖር ይችላሉ።
- ደረታቸው ከሌሎች የነብር ዝርያዎች በተለየ መልኩ ይሰፋል። ምክንያቱ ደግሞ ተራራ ላይ ብዙም ኦክስጅን ስለማይገኝ ሳምባቸው በደንብ አየር ወስዶ ለመጠቀም ይረዳቸዋል። በተጨማሪም የደረታቸው ስፋት የተለየ ግርማ ሞገስን ይሰጣቸዋል።
- ጭራቸው ረጅም እና ወፍራም በመሆኑ የሰውነታቸውን ሚዛን ጠብቀው ከታራራ ላይ ቁልቁል መሮጥ ያስችላቸዋል።
- በ አማካኝ የእድሜ ጣሪያቸው 21 ነው