🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቢቨር ( beaver ) - ተፈጥሮ ቢቨሮችን ኢንጅነር አድርጋ ፈጥራቸዋለች ። ቢቨሮች የሚታ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ቢቨር ( beaver )

- ተፈጥሮ ቢቨሮችን ኢንጅነር አድርጋ ፈጥራቸዋለች ።
ቢቨሮች የሚታወቁት ግድብ በመስራት ነው። የተለያዩ ዛፎችን በሹል ጥርሳቸው በመቁረጥ ከገነደሱ በኋላ የዛፉን እንጨቶች በመጠቀም ከወንዙ የታችኛው ክፍል ጀምረው ቀስ በቀስ በመደርደር ወንዙን ይገድቡታል። ግድቡ ከተለያዩ ጠላቶች ራሳቸውን ለመከላከል ይረዳቸዋል።
እስካሁን ድረስ ቢቨሮች ከገነቡት ግድቦች በሙሉ በትልቅነቱ በ 1ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው " Alberta's wood Buffalo" የተባለ ፓርክ ውስጥ የተገነባ ሲሆን ቁመቱ 804 ሜትር ነው።
ይሄን ግድብ በ ትውልድ ቅብብሎሽ ነው የጨረሱት። በሚገርም ሁኔታ የሰው ልጅ ከ ህዋ ላይ ሆኖ ማየት ከሚችላቸው ጥቂት ምስሎች መሀል አንዱ ይህ ግድብ ነው።
ቢቨሮች በህይወት ዘመናቸው 1 ፍቅረኛ ነው የሚኖራቸው። በፍቅር አርጅተው እስኪሞቱ አይለያዩም። ነገርግን አንዳንዴ ባል ወይም ሚስትየዋ ከሞቱ ከሌላ ቢቨር ጋር ግንኙነት ሊጀምሩ ይችላሉ።
የ ቢቨሮች የእድሜ ጣርያ 15 አመት ነው።