2022-11-22 17:25:58
**ሳውዲ አረቢያ 2 - 1 አርጀንቲና (የሙሉ ሰዓት ውጤት)**
በሳውዲ አረቢያ እና በአርጀንቲና መካከል የተደረገው የ2022ቱ የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ሳውዲ አረቢያ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
ዓለም ዋንጫው በዛሬ ዕለት ያልተጠበቀ ውጤት ተመዝግቦበታል።
በአሰልጣኝ ሄርቬ ሬናልድ ለምትመራው ሳውዲ አረቢያ ግቦችን አል ሼህሪ በ48ኛው ደቂቃ፣ አል ዶውሰሪ በ53ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል።
ለአርጀንቲና ሊዮኔል ሜሲ በ10ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
በዓለም ዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጣት አርጀንቲና 88ሺህ 12 ተመልካቾች በሉሳይል ስታዲየም በታደሙት መርሐ ግብር በሳውዲ አረቢያ 2ለ1 ተሸንፋለች።
አርጀንቲና በዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ ሁለት ጎሎች ከተቆጠሩባቸው አርባ አራት ዓመታት ተቆጥረዋል።
የምድቡ ሁለተኛ ቀጣይ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሲደረጉ ፖላንድ ከ ሳውዲ አረቢያ እንዲሁም አርጀንቲና ከሜክሲኮ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
1.3K viewsFiker Assefa, 14:25