2022-06-18 15:56:19
#ፀሀይ
፡
፡
፡
ወዲያ ማዶ ያየሽ ጊዜ፣ቁንፅል ብርሃን ድንግዝ ላምባ፤
የኔ ምለው አንድ ልብሽ፣ድንገት ከድቶኝ ገሌ ገባ።
ነቁጥ ጨረር ለሚያክለው፣ለማይባል እሩብ ሲሶ፤
ስንቁን ጭኖ ገሰገሰ፣ልብሽ ልቤን ጥሎ ምሶ።
፡
፡
የቤታችን ክዳን ጣሪያው፣ያስገባትን ተሸንቁሮ፤
ንዑስ ፀዳል ያየ ጊዜ፣ገፍቶኝ ቢሄድ ልብሽ ዞሮ፤
እንዳልከረምሽ በወገግታ፣ፋኖስ ሆኜሽ ስታበሪ፤
ብልጭ ድርግም የሚል ኮከብ፣አሸፍቶሽ ተወርዋሪ፤
መስዬበት ጠፍጨረቃ፣የወረሰው ድቅድቅ ጭልም፤
ብርቅርቅታን ከሩቅ አይቶ አለ ልብሽ ጥሎኝ እልም።
፡
፡
አቤት ልቤን ሰነበጠው፣
ሀቅ እያደር እስኪገልጠው።
፡
፡
ያኔማ፣
ሀቅ ጮሀ ስትሰማ፣
ፅልመት ሌሊት እየተባልኩ፣ባንቺ ዘንዳ እንዳልነበር፤
ፍቅር ፈርዶ ልቤን ሲክስ፣ስትመሰክር ለ'ውነት ጀንበር፤
ፍክት ስል ባደባባይ፣እኔው በኔው ተማምኜ፤
የዛን ለታ ምን ሊውጥሽ፣ስታገኚኝ ፀሀይ ሆኜ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.6K viewsAbela, 12:56