🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 134.59K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 186

2021-12-09 08:30:02 * እስያ*

አስያ ጨብራሬ
አሰያ ጨብራሪት
ፈንገል ፈንገልጋሊት፣
የዛራማ ጉሪት
የቅኔ ዥንጉርጉሪት፤
የዳመና ቅሪት
ውሽል ውሽልሽሊት፣
በዝናብ ምትመጣ
ዘመን ዘመንማኒት።

ሽው ~ንጥፍ
ንጥፍ ~ሽው ፣
ምታስከጎነብሽው
ከነፍስ የምትደርሽው፣

የሌለሽ ~አምሳያ

እስያ..~.አስያ
ከወዲህና ፣ ወዲያ
አካልሽን ~እየናጥሽው
እያንቀጠቀጥሽው

እየተንጎማለልሽ
እየተፍገመገምሽ
ጅብ ለማይበላው ሰው
ብቻ የተገለጥሽ፣

እየተንጎማለልሽ
ወደፊት ምጭና
ድፍቅ እንደገና፣
ወደኃላ መለስ
ጉሪቱን ማስታወስ፣
ዛርና ፣ ርቢን
ውቃቤን ማወደስ
አስያም እንድትነግስ

ከወገብ ማጎብደድ
ማጎብደድ
ማጎብደድ
ከዛም መንጎራደድ፣
ከቀኝ ወደግራ
አንገት ማንገዳገድ
ከቀልብ ያላረፈ
በእሳት ሊማገድ።

ማጫጫስ~ ሉባንጃ
በከሰል~ ምድጃ፣

ቡንን ~ቡንንንንን
እቴ ባንችው መጀን

ቦለል ~ ቦለለለለል......
ምረቃት ~ልቀበል
ከራማው~ ቁጭ ይበል

ሀዬ ና ተነሳ
ቄጠማ ነስንሳ
ሰንደሉን አጢሳ፣

አቦ! አብሽር መርሀባ
እስያ እንድትገባ
በወረብ ሽብሸባ፣
በጌታው ሙሀባ

ጀማው ~ተሰይሞ
አባ ሊቁም ቆሞ፣

እሱስ የኔ መውደድ
እሱስ የኔ መላ
እሷስ አትጠጣ
እሷስ አትበላ፣
ለነፍስ ነው እንጅ
ለአይንስ አትሞላ

የነፍስያ ~ዘምዘም
ለጥንቡ ~ስጋ ደም!

የምታፍለቀልቅ!
የምታስረቀርቅ!

እስያ....... አስያ.......

ሲደቦሩ ሜዳ
ሱገኙ በጋራ ፣
ሙጋድ ሆና ቀረች
የሱስ ገረገራ።

እምቡር
እምቡር
እምቡር
ከነፍስ ተጣብቆ
ልብ ላይ ለመኖር።

እስያ..... አስያ....

አስያ ጨብራሬ
አሰያ ጨብራሪት
ፈንገል ፈንገልጋሊት፣
የዛራማ ጉሪት
የቅኔ ዥንጉርጉሪት፤
የዳመና ቅሪት
ውሽል ውሽልሽሊት፣
በዝናብ ምትመጣ
ዘመን ዘመንማኒት

እስያ አስያ
እስያ ጨብራሬ
እስያ ጨብራሪት


ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ አለም ጣኦት


።።።።።።።።። ።።።።።።።
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.5K views05:30
Open / Comment
2021-12-08 20:08:08 (በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ክፉም ንጉስ መጣ
ደግም ንጉስ መጣ
ብቻ ግን ያልፋሉ ፣ ሁሉም እንደመልኩ
ይብላኝ ከህዝብ ጋር
ለሚጣሉ ህዝቦች ፣ መሪ እያመለኩ !!!


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.0K views17:08
Open / Comment
2021-12-08 18:20:23
Cervical Neck Traction Device

Adjustable Neck Support Pillow for Spine Alignment Chronic Neck Pain Relief Three Layers U Shaped


ዋጋ፦ 1500 ብር


               አድራሻችን
                  አዲስ አበባ



ስልክ:
0911468394
@abela1987
822 views15:20
Open / Comment
2021-12-08 15:53:40 #የአዋቂ ሰው ፀሎት

(ሚካኤል አስጨናቂ)

ምን ብሆን ተስፈኛ ምንም ብሆን ፅኑ

ሁሌ በየ ቀኑ

አዲስ ቀን አምጣልን ብዬ አልፀልይም

ዛሬ ነው መልካም ቀን ነገን አልመኝም።

ሞኝ ነው ተላላ !

የዘመኑን ማብቂያ አንብቦ ሳያውቀው

የምሳሌህ ፍቺ ... እያደናበረው

መቅደስህ ፊት ቁሞ ...የሚጨቃጨቀው

ይሻል ቀን ላይ ሳለ

ትብስን አምጣልኝ ... ብሎ 'ሚፀልየው

እሱ ሰው ሞኝ ነው!

ዘመን እየገፋ ፀሀይ ሲገልፅልን

አደዩ ሲፈካ ምድር ስትነግስልን

አዝማሪ ሲጨፍር ዜማ እየቀመረ

ሁሉ እየመሰለው የነገው ያማረ

ትከሻውን ሰብቆ የደከረ ሁላ አፍሮ ነው የቀረ!

እኔስ አልቦርቅም

ስለ ነገ ተስፋ

ነገን የሚል ሰው ነው ዛሬን የሚገፋ ...

ይልቅ የኔ ፀሎት

እንዲህ ነው መሻቴ

ዛሬዬን አባዛው ሶስቴ ና አራቴ

ደግሞም ከተቻለ መልሰኝ ከትናንት

እንደዚህ ሲሆን ነው

ይህችን ስጉ ነፍሴ ...ተስፋህ የሚሞላት !

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.6K views12:53
Open / Comment
2021-12-08 12:42:04 ይሉኝታ ጠፍንጎ አስሮ ሚያንገላታን
ከደስታችን ይልቅ የሰው አፍ ሚያሰጋን
ከሆነው ገዝፎብን ሃሜት የሚያስፈራን
ምን አሉ ምን አዩ ገንኖ የሚያጋፋን
መንገድ የጠፋብን አሳዛኝ ተጓዦች
እጣችንን ያልኖርን ምስኪን ተቅበዝባዦች

Nuniyat
@yetyelele1

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.2K views09:42
Open / Comment
2021-12-08 09:30:44 መጽሐፈ ሔኖክ ብራና.pdf
#shaer
#share #share
#ሼር #ሼር #ሼር
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.5K viewsedited  06:30
Open / Comment
2021-12-07 21:42:37
ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል፡፡ ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል ከመስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው:ሰው ይገልጽለታል። በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁ ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ .. ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ " በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ ይተርክለታል! ...

በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ
አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው የተቀመጠው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን ጠርታ አዘዘቻቸቸው!

ያ ብቻውን የቀረው በጀርባው የተኛው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ እንዲወስዱለት ጠየቀ። ወሰዱለት። ሟች የነገርውን በሙሉ በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!

"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ።

"ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት።

"ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር" ስትል በመገረም መለሰችለት፡፡

ልብ የሚነካ ነገር.. ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው። አንዱን ለማጠንከር ወይም ለማበርታት የኛ ጥንካሬና ብርታት አስፈላጊ ነው። ለሰወች ደግ ነገር በማድርግ የተጨነቀ አምሮአቸውን እረፍት እንስጠው::

መልካም ምሽት!
1.4K views18:42
Open / Comment
2021-12-07 18:05:33 አንድ አዝማሪ ነበር
ማሲንቆውን ሚገርፍ ስንኝ እያጀበ
የከበበው ጠጪ ብሶት ገረበበ
ሚስቱ የፈታችው ተቀበል በሚል ቃል
ብሶቱን ሲያበርደው ቤቱ ግን ይሞቃል

ተቀበልልል
.
.
ሚስቴ የሰው ገፊ መሄድ ነው ሚደላት
እንደ ቀልድ ፈታችኝ አርግዢልኝ ብላት
ከጎኑ ሚገችም አንድ ቀለም ቀቢ
ደግሞ ያሽሟጥጣል ምን ጉድ ነው በረቢ

እሱም እንዲህ አለ

ክብር ጠለቀብን አዳም ደበዘዘ
ሄዋን በምትሰራው ወንዱ እያረገዘ
(ህመም አይደል ፅንሱ )
.
.
ስካር የጀመረው ሳይገባው ይስቃል
ከሆደ ከደረሰ ብቅል ያሳቅቃል
ከቀቢው ፊት ለፊት ስራ የፈታ ወጣት
ተበድሮ ይጠጣል ቀፋፊ ነው ማጣት

እሱም አቀበለ...
.
.
ሆዴን ይብሰኛል ብሶቴን ስደግመው
እኔን መሳይ የታል
ተመረኩኝ ቢልም ትምህርት የረገመው
.
.
ትካዜን ሲያጣጥም ከእንባው ተናንቆ
ችግር ያስተጋባል ቢቸገር ማሲንቆ
ያንሳል አትልቆ!
.
እኔ እንዳለሁ አለ

አንዴ ሰካራሙን ሲልም አዝማሪውን
ስገረም ስታዘብ መከራ ሲተውን
ወጣት ሽማግሌው ቃል እየተራጨ
ስንቱ ነው ያለፈው
ባ'ለም መቅጫ እድሜው ባ'ለም 'የተቀጨ

#እኔ_እንዳለሁ_አለሁ....

ናታን ኤርሚያስ
@UniqueDy
2.4K views15:05
Open / Comment
2021-12-07 10:46:51 በመጀመሪያ እንኳን ለዚች ቀን አደረሰን አደረሳችሁ የአመቱን ህዳር 28ን አስመልክቶ አንዴ ፅዋችንን እናንሳ

#ችርስ

እውነት ስንናገር ለሚገለምጡን
የታባቱ ብለው አውተው ለሚጥሉን

.....................ችርስ..................

በየስራ ጣቢያው ዘመድ ላሰማሩት
እድሜ ለቀበሌ ትግስት ላስተማሩት

.....................ችርስ..................

ለፖለቲካ ቅስቀሳ ማልደው ለሚያነቁን
በሀገረ እረፍት እንቅልፍ ለሚያሳጡን

...................ችርስ..................

ወደድናቹ ስንል ሚገፉን ቀልባችን
ቅናት ላስተማሩን ለሴት ልጆቻችን

...................ችርስ..................

ራሱን ሳይዳኘው እኛን ለሚዳኘን
በተሳሳተ ፍርድ ዘብጥያ ለጣለን

.....................ችርስ.................

ይቀጥላል

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
441 viewsedited  07:46
Open / Comment
2021-12-06 19:00:05 ሀዘን ሲበዛ
።።።።።።።
ሀዘን ሲበዛ ሮሮአችን ከፍቶ
እምባውም ሲያልቅብን ከውስጣችን ወጥቶ
የመከፋት ጥጉ ጫፉ ላይ ሲደረስ
ወዲም ወዲያ ተብሎ የጠፋብን ለት መልስ
የሀዘኑ ሲቃ በዜማችን ታጥፎ
ሳቃችን ተሰማ ከጣሪያችን አልፎ

Nuniyat
2.0K views16:00
Open / Comment