2021-12-01 13:31:12
"
አዋቂና የነቃን ሰው በባርነትም ሆኖ ሊታዘዙት ይገባል "--የዲዮጋን
ዲዮጋን በአንድ ወቅት ተይዞ ለባርነት ተሽጦም ነበር ። ሚኒፐስ የተባለው የአቴና
ሰው "Sale of Diogenes" በሚለው መጽሐፉ ሲነግረን ፦
" ዲዮጋን በምርኮ ተይዞ ለሽያጭ ሲቀርብ ምን መስራት እንደሚችል ተጠይቆ
ነበር ። እሱም ሲመልስ 'ሰዎችን ማስተዳደር' አለ ። የሽያጩን ጨረታ
ለሚመራውም ሰው ምናልባት ጌታ የሚፈልግ ሰው ካለ ስለእሱ ይኽንኑ
እንዲነግር ካዘዘው በኋላ ዲዮጋን ለመቀመጥ ሲሞክር እንዲቆም አዘዙት ።
ዲዮጋንም ፦
<< እንደኔ እምነት ግን መቀመጤ ልዩነት አያመጣም ። ለገበያ ያቀረብከውን አሣ
በማንኛውም አቅጣጫ ብታስተኛው ገዢ ማግኘቱ አይቀርም >> ብሎታል ።
ዲዮጋን ሲናገር ፦
<< ለቤታችን የምንገዛው ደምበጃን ወይም ብርጭቆ በሚገባ ይሰራ እንደሆነ
እንፈትሸዋለን ፤ የምንገዛው የሰው ልጅ ከሆነ ግን እሱን በመመልከት ብቻ
ለመርካት ነው >> ብሏል ።
ዜናይዴስ ዲዮጋንን ከገዛ በኋላ ዲዮጋን እንዲህ ብሎታል ፦
<< እኔን ልትታዘዝ የግድ ነው ፤ ምንም እንኳ ባርያህ ብሆንም አዋቂና የነቃ ሰው
በባርነት ሆኖም ሊታዘዙት ያስፈልጋል ። >>
ምንጭ፦ጥበብ ከጲላጦስ
1.0K views10:31