🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 136.25K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 190

2021-11-29 08:25:52 Credit for poetery Debebe Seyfu
................................
በምን ጠፋ ቢሉ

የፊቱን እያየ የኋላውን ትቶ
ማንነቱ ጠፍቶት እልህ ጋ ተጋብቶ
ጎጆውን ቀልሶ
ማን እንደነበረ ረስቶት ጨርሶ
የገዛ እልሁ ደፋው ከፊት ደርሶ።

ብላችሁ ንገሩ
ላገር ለመንደሩ
ንገሩ ለሁሉ
በምን ጠፋ ቢሉ


ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
326 views05:25
Open / Comment
2021-11-28 22:40:24
አዲስ አልበም በዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ቀን አውጣላት ተለቀቀ።ከታች ባለው ሊንክ ገብታቹ ማውረድ ትችላላቹ።
950 views19:40
Open / Comment
2021-11-28 19:18:25 እርሶ የተወለዱበትን ወር ይምረጡ። የሚወስዶት ወደ መንፈሳዊ እና ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ወዳዘለ የቴሌግራም ቻናል ነው። እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ያስተምራል። ኑ የእግዚአብሔርን ቃል አብራችሁን ተካፈሉ።

መስከረም ጥቅምት ህዳር

ታህሳስ ጥር የካቲት

መጋቢት ሚያዝያ ግንቦት

ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ

ጷጉሜ
367 views16:18
Open / Comment
2021-11-28 17:38:35
#4_3_3_Challenge


ሰላም ውድ የ4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ ቤተሰቦች ፣ እንደሚታወቀው 575ሺህ ተከታይ የነበረው ቻናላችን በምንለቀው የጎል ቪዲዮ መክኒያት BEIN SPORT ማዘጋቱ የሚታወስ ነው። ቻናሉ ለማስመለስ አሁንም እየሰራን ነው እናም እስኪመለስ ድረስ አዲስ ቻናል ከፍተን ብዙዎች እየተቀላቀሉን ነው።

በዚህም መክኒያት #4_3_3_Challenge በሚል መሪ ቃል አዲስ ቻሌንጅ ጀምረናል። ይህን ቻሌንጅ ሁላችን ለምናውቀው 10 ሰው ይህንን ፖስት ሼር ማድረግ፣ Facebook Account ያላችሁ Facebook አካውንታችሁ ላይ እይሄንን ፖስት ሼር ማድረግ ነው!

ይህም በፍጥነት የቀድሞ ቦታችን እንድንመለስ ያድርገናል ፣ ሌላው ለ10 ሰው በላይ ሼር ካደረጋችሁ እንዲሁም ፈስቡክ ላይ ፖስት ካደረጋችሁ Screenshot በማድረግ በዚህ Bot ( @Simerabot ) ይላኩልን።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/joinchat/RU8rzd2SuDnHu0Id
https://t.me/joinchat/RU8rzd2SuDnHu0Id

#4_3_3_Challenge
825 views14:38
Open / Comment
2021-11-28 12:57:09 መጠናናት
(በእውቀቱ ስዩም)
አንድ በድሜና በምጣኔ ሀብት የሚበልጠኝ ወዳጅ ነበረኝ ፤ አንዳንዴ በግድግዳ ስልክ ደውየ “ ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልግህ እንገናኝ” ስለው " ጋብዘኝ፥ ሊፍት ስጠኝ፥ ገንዘብ አበድረኝ፥ ዋስ ሁነኝ፥ ሽማግሌ ሆነኝ አትበለኝ እንጂ ለጥብቅም ሆነ ለላላ ጉዳይ ልታገኘኝ ትችላለህ ” ብሎ ይመልስልኝ ነበር ፤ እና እኔንም ፖለቲካ ጻፍ አትበሉኝ እንጂ ፌስቡክ ላይ ለማንዣበብ ቃል እገባለሁ::
“እስቲ አንዴ እንደማመጥ !” አለ የዳምጠው ሹፌር፤
ድሮ ከትዳር በፊት መጠናናት የሚባል ነገር ነበር፤ አባቶቻችን ውሃ አጣጫቸውን ሲያጠኑ “ ሙሽራዋ የማን ልጅ ናት? ዶሮ መበለት ትችላለች? ቤተእግዚሀር ትስማለች ?” በሚሉ ጉዳዮች ላይ ብቻ ይወሰኑ ነበር፤ የሙሽራዋ መልክ ራሱ በጫጉላው ቀን ብቻ የሚገለጥ “Top secret ነበር :: ዛሬ ከትዳር ቀርቶ ከድርያ በፊት ያለው መጠናናት እጅግ በጣም ተራቋል፤
ባለፈው ባለቀ ሰአት ትዳር ውል ብሎብኝ እዚህ ጎረቤት አገር ካለች ቀንበጥ ጋራ እንዴት ነሽ እንዴት ነህ ስንባባል ባጀን:: ባንድ ምሽት ድንገት “ ከወገብህ በታች አወላልቀህ ፎቶ ተነስተህ ላክልኝ አለችኝ” ፤ ተገረምሁ፤ ብሎም ደነገጥሁ፤ ግን ስሜቴን ዋጥ አድርጌ ” ከወገቤ በታች ያለው ጓዝ ባንድ የሞባይል ፎቶ የሚወሰን አይደለም፤ ራሱን የቻለ የናሺናል ጆግራፊ ዶከመንተሪ የሚፈልግ ፕሮጀክት ነው፤ ባይሆን ከወገቤ በላይ አወላልቄ ልላካልሽና ገምግሚኝ” አልኳት::
በስንት ልምምጥ ተስማማች ::
አምሳ ፎቶ ተነስቼ፤ አርባ ዘጠኙን ደምስሼ አንዱን ሰደድኩላት::
“ ሲክስ ፓክ አለኝ ብለኸኝ ነበርኮ”
“ ከራት በፊት ሲክስ ፓክ ነበረኝ፤ ከራት በሁዋላ ሲክስ ባግ ሆኗል “ አልኳት::
“No way ! ሆድህ ትልቅ ያፈር ገንፎ ነው እሚመስለው “
“ ደረቴ ላይ ብታተኩሪ ደስ ይለኛል ”
“ ደሞ ሁለት እምብርት ነው ያለህ እንዴ ? ”
‘አንደኛው ትርፍ አንጀት ያስወጣሁበት ጠባሳ ነው ! ምናለ ደረቴ ላይ ብናተኩር”
“ ኦኬ! ደረትህ ከየት ነው እሚጀምረው?”
ይሄንን አሳዛኝ ጭውውት ለቀጣዩ ላሳድርና ሌላ ገጠመኝ ላውጋችሁ::
በቀደም ዲሲ ኡበር ታክሲ እየነዳሁ አለምአቀፉን ማህበረሰብ ሳገለግል አንዱ አበሻ ተሳፈረ፤ ሰውየውን የት ነው የማውቀው እያልሁ እያሰበኩ ፊቱን ለጥቂት ደቂቃ አጠናሁት፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የሸግግር መንግስት ለመመስረት ተሰባስበው ፎቶ ከተነሱት አንዱ ወጣት መሆኑን ተገነዘብኩ ፤ ሰውየው ከሁዋላ ወንበር ለጠጥ ብሎ ተቀመጠ፤ አቀማመጡን በማየት ብቻ ለንግስና የተፈጠረ መሆኑን መገመት ይቻላል :: ረጅም ሎጋ ከመሆኑ የተነሳ በቂጡ የቆመ ነው እሚመስለው፤ ጭራሽ በwhite house በዋይታ-ውስ በኩል ስናልፍ እጁን በመስኮት አውጥቶ አውለበለበ :: ለአሜሪካ አቻው ሰላምታ ማቅረቡ መሰለኝ :: ሰፈሩ ሲደርስ ቀልጠፍ ብየ ወረድሁና በሩን እንደ ጋሻጃግሬ ከፍቼ “ እንግዲህ በመንግስትህ አትርሳኝ “ ብየ አሰናበትኩት:: ቤቴ ደርሼ መኪናየን ስፈትሽ ሰውየው ሳምሶናይቱን ጥሎ መሄዱን ተረዳሁ ፤ ቦርሳውን ከፍቶ የማየት አሳብ መጥቶብኝ ትንሽ ከራሴ ጋራ ታገልኩ፤ ኢትዮጵያን እጣ ፈንታ የሚወስን ነገር በጄ ገብቶ ቢሆንስ ? የመጣው ይምጣ! ሳምሶናይቱን ስከፍተው ያገኘሁት ገረመኝ- አንድ ፌስታል ድርቆሸ፥ ስድስት ብልቃት ሚጥሚጣ; አንድ ፌስታል ኤልሳ ቆሎ፤ፌርሙስ የሚያክል የብብት ፊሊት… ከስር አንድ ወረቀት አየሁ፤ አሃ! ይሄ የሽግግር መንግስቱ ሰነድ ፥ አለዚያም የአዲሱ ህገ -መንግስት ረቂቅ መሆን አለበት ብየ ገለጥ አደረኩት፤ የኪራይ ቤት ውል መሆኑን ሳውቅ ግን እጢየ ዱብ አለ፤ እጢየን ወደ ነበረበት ሰቅየ ውሉን በጥሞና ማንበብ ጀመርኩ ፤ No shoe inside the house ይላል የመጀመርያው አንቀጽ፤
ከጥቂት ሰአታት በሁዋላ ሰውየው ሳምሶናይቱን ሊቀበለኝ ሲመጣ “ ዠለስ! የሽግግር መንግስት ነው ፤ወይስ የችግር መንግስት ያሰብክልን? እስቲ ኢትዮጵያን ከመግዛትህ በፊት መጀመርያ ቤት ግዛ “ ብየ ገሰጽኩት !
ፖለቲካ አልጽፍም ያልኩትን ከምኔው ዘነጋሁት በሞቴ !

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
456 views09:57
Open / Comment
2021-11-28 10:40:28 ከዱባይ እቃወችን ገዝቶ መላክ የሚችል ሰው በውስጥ ያናግረን።
@abela1987
1.2K views07:40
Open / Comment
2021-11-28 09:17:54
የልጅ ነገር
ቶሎ በስሎ ለመጋገር፣




ሏ.....

ጥሬነቷን አላወቀች
በሀሳብ ላይ
ቡኮ ሀሳብ ለቀለቀች፣

ልምሻ አእምሮ
ልምሻ እጅ እግሯ
ቢደነድን ቢጠነክር
የእናቷን ጡት መጋተሯ፣

እሷነቷስ ወተት
መጋት ተጠይፋ
ጥሬ ስጋ ትሸጣለች
በዓደባባይ ተሰልፋ።

የአፍላ ነገር.........
ቶሎ በስሎ ለመበላት
ተበልቶ አልቆ ለመጋገር።

*


አዝጎ : የብስል : መሀል : ጥሬ : መሆን። የበሰለው : ወርቀዘቦን :ሲጎናፀፍ: ያልበሰለው :ትድግና : ልብስና ትራሱ የሱ እንደሆኑ : ለመገመት : አያዳግትም።

እህልን: በማጭድ : ገዝግዞ : ጎተራ የሚከምር : ገበሬ : ይመስል አገቦአተውን
እንደህል : ለሚወቁ ወፈሰማይ አንበጦች
ሽቅብ : አንጋጠን : ብናይ : ማጠጣተው
ቁልጭ : ብሎ : ይታይ : ነበር።

እሷም : አንገቷን : ቀና አድርጋ ብታማትር
ቢራቢሮ : በአክናፉ : ነፋስን ሰንጥቆ ሲቀዝፍ : ተመለከተችና: በቀለሙ ተሳበች
የመጣበትን : መንገድም : ቢያሳያት : አባጨጓሬነቱ : ኮሰኮሳት። ህመሙንም : በወርቅ ቅብ ደጉሶት ነበርና... ደመመራራነቱ : ገዘፈባት።
መች :እሱ ቆዳውን : ሊያስወድዳት :ሻተና

እሱ ቋንጣ
እሷ ለንቋንጣ

ሆነው እንጂ!!

ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ አለም ጣኦት
1.6K views06:17
Open / Comment
2021-11-27 22:32:28 እርሶ የተወለዱበትን ወር ይምረጡ። የሚወስዶት ወደ መንፈሳዊ እና ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ወዳዘለ የቴሌግራም ቻናል ነው። እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ያስተምራል። ኑ የእግዚአብሔርን ቃል አብራችሁን ተካፈሉ።

መስከረም ጥቅምት ህዳር

ታህሳስ ጥር የካቲት

መጋቢት ሚያዝያ ግንቦት

ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ

ጷጉሜ
686 views19:32
Open / Comment
2021-11-27 21:07:22 1*°°°መናፍቃንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸውን የሚያሳዩ 60 ነጥቦች◦

1. መናፍቃን፡- የጻድቃን መታሰቢያ በዓል መከበር የለበትም።

2. መናፍቃን፡- ቅዱሳን አማላጅና አስታራቂ አይደሉም፡፡

3. መናፍቃን፡- ኢየሱስ ዛሬም አማላጅ ነው።

4. መናፍቃን፡- ሥራ አያጸድቅም፡፡

5. መናፍቃን፡- ጾም አያስፈልግምተ

6. መናፍቃን፡- መጽሐፍ ቅዱስ 66ቱ ብቻ ነው፡፡

7. መናፍቃን፡- ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ አትባልም፡፡

8. መናፍቃን፡- ሐይማኖት አያስፈልግም፡፡

9. መናፍቃን፡- ጥምቀት ለድህነት አይጠቅምም፡፡

10.መናፍቃን፡- የጌታ ስጋና ደም (ቁርባን) ምሳሌ ብቻ ነው።

11. መናፍቃን፡- ታቦት በአዲስ ኪዳን ተሽሯል፡፡

12. መናፍቃን፡- ቤተ መቅደስ በአዲስ ኪዳን አያስፈልግም።

13. መናፍቃን፡- መስቀል መያዝ/
መጠቀም አይገባም፡፡

14. መናፍቃን፡- ማህተብ በአንገት ማሰር አያስፈልግም፡፡

15. መናፍቃን፡- ሕፃናት መጠመቅ የለባቸውም፡፡

16. መናፍቃን፡- ለሞተ ሰው መጸለይ አይገባም፡

17. መናፍቃን፡- በቅዱሳን ስም መዘከር/ምጽዋት መስጠት
አያስፈልግም፡፡

18. መናፍቃን፡- በቅዱሳን ስም ቤተ ክርስቲያንን መሰየም ትክክል አይደለም፡፡

19. መናፍቃን፡- ቅዱሳት ስዕላት አያስፈልጉም፡፡

20. መናፍቃን፡- ቅዱሳን መላእክት አማላጅ አይደሉም፡፡

21. መናፍቃን፡- የጌታ እናት አልተነሣችም፡፡

22. መናፍቃን፡- የጌታ እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት /ጥንተ አብሶ/ አለባት።

23. መናፍቃን፡- ኃጢአትን ለካህን መናገር/መናዘዝ አይገባም፡፡

24. መናፍቃን፡- ስግደት አያስፈልግም፡

25.መናፍቃን፡- ሴት ፀጉሯን ሳትሸፍን መጸለይ ትችላለች፡፡

ለነዚህ ሁሉ መልሶች በድንቅ መምህሮቻችን

1)መምህር ምህረት አብ አሰፋ
2)መምህር ዘበነ ለማ
3)መምህር ሮዳስ ታደሰ
4)መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
ድንቅ ድንቅ መልሶች ተሰተዋል።አሁኑኑ ቻናሉ ላይ ገብተው ይመልከቱ
155 views18:07
Open / Comment
2021-11-27 20:24:40 ከመቀመጥ በላይ
የመቆም ረፍቱ
ከመምጣት ይልቃል
የመሄድ ጥልቀቱ
መቅረት ለትዝታ
ለደግሞ መናፈቅ
በማጣት ተላወሶ
ማግኘትን መመኘት
መመኘት
መመኘት
መባከን
መብከንከን
የነበረን ሁሉ
የተኖረን ሁሉ
እንደነበር መርሳት
መቃጠል በምኞት
ባለማግኘት እሳት
.
ማግኘት በረዶ ነው
ቁርጡ ይታወቃል
ማጣትን የሚያህል
ፀሀይን ያጠልቃል
የህይወት ጥፍጥና
የመኖር ስሪቱ
ጠብቆ ጠብቆ
በምኞት መቅረቱ


...ሄለን ፋንታሁን

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.3K viewsAbela, 17:24
Open / Comment