Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 132.20K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 192

2021-11-21 12:43:31 *እስክትድኝ ልበድ**

አበርችኝ የኔ አለም አጽኒኝ የኔ አለኝታ
በገተሩሽ ሸንጎ ስለ ሀቅሽ ልርታ
ልጩህ በተራራ በሜዳበአደባባይ
ጉድሽን ልተርክ ይመስክረኝ ሰማይ።
እሷ ሰው በላ ናት እያልኩኝ ልናገር
ሲቃ ምርኩዟ ነው እያልኩኝ ልናገር
አበደች ይበሉኝ ከጠበል ልነከር።
ቄሱ ይድገሙልኝ የእብደቱን ማርከሻ
ጠንቋይ ይንተባተብ ድግምቱን ማደሻ
እንዳልሆነ ይሁን በርትተሽ አበርቺኝ
ጤንነት ምኔ ነው? አንቺ ታመሽብኝ!!
ይልቁንስ ልጩህ ሰው አርጊኝ እናቴ
ድክመትና ጉልበት ህመም መድሐኒቴ
ልንገራቸው ዛሬም የአርቡን ለታ ሸንጎ
ጌታ መሰቀሉን የእሾህ አክሊል አርጎ
የመሳሙን ቀመር የይሁዳን ደባ
የመስቀሉን ስቃይ የወላዷን እንባ
አበርቺኝ ልናገር ጩኸቴ ያድክመኝ
ቀዬው ይንሾካሾክ አበደች ይበለኝ
ወትሮስ እየነኩሽ ምን ጤንነት አለኝ??
ወለምታ ማያጣሽ አንቺ ልማደኛ
የልጆሽ ደም ነው የመምሽ መዳኛ።
ከጽዋሽ አጠጪኝ ባንቺነትሽ ልስከር
በጠጅሽ ሰምጬ በጠላሽ ልንዘርዘር
ያናግረኝ ሞቅታ እንዲህ ነው ትርጉሙ
ስካርና እብደት ነው የነጻነት ስሙ!
ደግሞ ልበድልሽ ካድባር ልንተፋተፍ
ጌታን ተደገፊ እኔ አንቺን ልደገፍ።
ፍጥረቱ ይዛባ ቀየሽ ይተራመስ
ቅኔ ትስገድልሽ ይጀብሽ መወድስ
ደግሞ ላቀማጥልሽ በንኩ ብዕሬ
ደግሞ ልገዝትሽ በጠና ስካሬ
በታሰረ ምላስ በወልጋዳ አካሄድ
በቡትቶ ጨርቄ እስክትድኝ ልበድ
ጤነኛ አልሆነሽም እብድ ነው ያንቺ ገድ!
ደግሞ ልቀዣብር ደግሞ ልቀባጥር
እንባሽ ነው መጠጤ በጠራራ ልስከር
እንባሽ ነው ጥንስሱ አረቄ የሆነኝ
ጨጓራዬን ልጦ ራሴን ሚፈልጠኝ
እንባሽ ነው እንባዬ እንባሽ ነው ህመሜ
ከአንድ እንስራ ገብቷል ደምሽና ደሜ።
ተውኝ ልበድበት
ተውኝ ልስከርበት ጤናን አልመኝም
ስንትዜ ነው ህይወት ስንትዜ ነው አለም?
ሀገሬ እየደማች እኔ እንዴት ልታከም?
ተውኝ ልበድላት መድሀኒት አልሻ
ስካር ሚያፋታኝ እብደቴን ማርከሻ።
አብጄም ሰክሬም እሷን ብቻ ልስበክ
ነፍስና ስጋዬ ለስሟ ይብረክረክ።
እኔ መታመሜ እሷን ከፈወሳት
አንድ ጊዜ ቀርቶ እልፍ ልበድላት!
ያኔ ነው የምድን ያኔ ነው ሚሻለኝ
ህመሟን ወርሼ ጤና ስትሆንልኝ
ያኔ ነው ሚገራ ይህ ከርዳዳ ድምጼ
ሀገሬ ስትድን ነው የሚወርደው ለምጼ!!
እሷው በሽታዬ እሷው ናት የኔ ሐኪም
እሷው ናት ድክመቴ እሷው ናት የኔ አቅም
እብደት ጤንነትን፣ህይወትና ሞትን ከርሷ ውጭ አላቅም!!!



ኢትዬጲያዊነት
01/13/13
ሳሮናዊት እንድሪስ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
904 viewsAbela, 09:43
Open / Comment
2021-11-21 11:51:56 ደሞ ዳግሚያ

ደሞ ዳግሚያ አስፈለገኝ
አንተን አምጪ ብሎ ያዘኝ
ልቤ ልቤ ምን ነክቶት ነው
ያኛው ነገር ያስፈለገው
ባህል ወጉን እንዴ እረስቶ
ያባለገኝ ካንተ ገብቶ
ጋድሚያ ጋድሚየ የሚስብለው
ስንጋደም ምን ነበረው
ስሜሀለው ስመኸኛል?
እንጃ?ማስታወሱ ተስኖኛል
የማቀው ትዝ እሚለኝ
ሰውነቴን ሲሞቀኝ
ታዲያ ይሄን ምን ይሉታል
አንተን ማጣት ያሳብዳል

ማሳሰቢያ ይህ ግጥም ጠሀፊዋን አይወክልም ነብሴን ተቀበላት

ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
246 viewsAbela, 08:51
Open / Comment
2021-11-21 10:18:10 ህወሀት እና ጥበቡ
(በላይ በቀለ ወያ በበዕውቄ ስታይል)
.
.
መጀመሪያ ህወሐት ሳተ
ከቤተ መንግስት ተጐተተ፥
ህወሐት ከአራት ኪሎ ሲባረር
አነሆ በV8 ነበር
ትችት ስድብ ወረደበት
በሸበጥ የሚያውቁት ህዝቦች፣ በV8 ሲያዩት ሳቁበት።
ያኔ ህወሐት ተማረረ
ተማረረና ተመራመረ
ተመራምሮም አልቀረ
መብረቃዊ ርምጃ ጀመረ
ጅማሬውን እጅግ ወደደ
ተጀምሮ ሳይፈፀም ፣ መንከባለልን ለመደ
ያሳዝናል!
ማይጨርሰውን ጦርነት ፣ ጀምሮ ህዝቡን ማገደ።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
854 viewsAbela, 07:18
Open / Comment
2021-11-20 23:25:46
494 viewsAbela, 20:25
Open / Comment
2021-11-20 19:26:55 አስራ ኹለት ግጥም


ፀሀፊ ሰለሞን ሽፈራው

አንባቢ

ቅዱስ ዓርዮስ
የግማሽ አለም ጣኦት

።።።።።።።።። ።።።።።።።
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.3K viewsBewketu, 16:26
Open / Comment
2021-11-20 16:48:53 ከሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመን አይሽሬ ውብ
ግጥሞች መካከል አንዷን እንካችሁ !
"የፍቅር ቃጠሎ"
(ገብረክርስቶስ ደስታ)
**********
ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጠዋት ጨረር የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለሁ
እስረኛ ሆኛለሁ፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.8K viewsAbela, 13:48
Open / Comment
2021-11-20 11:59:21 እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ:: የበጎ ሰው ሀሳብ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር :: ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል…
475 viewsAbela, 08:59
Open / Comment
2021-11-19 20:51:11 ናፍቆት


ፀሀፊ ና አንባቢ

ቅዱስ ዓርዮስ
የግማሽ አለም ጣኦት

።።።።።።።።። ።።።።።።።
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.7K viewsBewketu, 17:51
Open / Comment
2021-11-19 19:57:51 እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ::

የበጎ ሰው ሀሳብ
ሲካድ እለት በእለት
ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር
በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ::

ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው ፥
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤

አዎ
ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል ::

ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም ::

( አዳምኤል )
Bewketu Seyoum

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.1K viewsAbela, 16:57
Open / Comment
2021-11-19 17:10:59
Adjustable Posture Corrector

Corrector Belt
Great for Men and Women!!

የአንገት፣የትከሻ እና የወገብ ህመምን የሚቀርፍ
Spinal-cord መደገፊያ አብሮ የተገጠመለት
አቅዋሞን በማስተካከል ቀጥ ያል እና ማራኪ ቁመና ለመላበስ የሚመርጡት።

#Size: Medium, Large, XL, 2XL & 3XL

ዋጋ፦ 1000ብር


አድራሻችን
አዲስ አበባ


0911468394
@abela1987
351 viewsAbela, 14:10
Open / Comment