Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 132.20K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 191

2021-11-24 08:02:57 [ ይቅናሽ ]

ከእኔ ጋ ስትሆኝ
ሰላም ካልተሰማሽ
ሰላምሽ እርቆ
ሐዘን ከከበበሽ
ያውልሽ መንገዱ
ደና ሁኚ ይቅናሽ
በእኔ ደስ ካላለሽ
እኔም ደስ አይለኝም
ቁንጅናሽ ውበትሽ
ምኑም አይጥመኝም
ትረጉም አይሰጠኝም
በእኔ ከተከፋሽ
ባንች ደስ አይለኝም።

ጥቅምት 25/2014 ዓ/ም

ብርሃኑ ዘላለም


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.7K viewsAbela, 05:02
Open / Comment
2021-11-23 19:59:59
1.7K viewsAbela, 16:59
Open / Comment
2021-11-23 19:33:56 ጊዜ

ሎተሪ ነው ጊዜ ባለእድል ባለ እጣ
ከዘረሰብ ደጃፍ ገብቶ የሚወጣ
ጊዜ ክፉ ፊደል ጊዜ ክፉ መምህር
ብራና ዘርግቶ ሁሉን የሚያስተምር
ሻረ ሲሉት መግል ወይ ሲመግል ሽረት
በነተበ አለላ አዲስ እንደመስራት።
የጊዜ ማሲንቆ ሲቃ እየተቃኘ
ሰውነት ረክሶ ባፈር እየናኘ
እንደ ተራ ነገር እንደሆነ ኦና
ስንት የበላ ጎጆ በስንቱ የፀና
ምንም እንዳልሆነ እግር ይሄዳል ትቶ
ኋላን እየረሳ ፊቱን ተመልክቶ
ዳሩ ምን ያደርጋል
ልብ መች ይርቃል
በደከሙ አይኖቹ እንባ ይወርባል
በቅዥት አለሙ ህልም ያመረግዳል።
ጊዜ ክፉ ሎሌ ጊዜ ክፉ ጌታ
የመነኩሴ ግዝት የወልይ እሪታ
የጀንበር አርምሞ የጨረቃ ዋይታ
ጊዜ ሴት ወይዘሮ ጊዜ ጋለሞታ።
ወዲህ ግልብ ቅኔ ወዲያ ባለ ምስጢር
ካልዋሉበት ማሳ እህል እሚሰፍር!!


11/02/2014
ሳሮናዊት እንድሪስ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.1K viewsAbela, 16:33
Open / Comment
2021-11-23 12:04:10 #ትመጣለህ
አትመጣም.........
እረሳህ ይሆን?
ደግሜስ ሌላ መውደድ እችል ይሆን?
.....................................
አዛኝቱ ልቤን አበርቺዉ ላንተ ግን ወዬ እንባዬ አለብህና

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.6K viewsBewketu, edited  09:04
Open / Comment
2021-11-22 20:50:40 ግራጫዬ
''''''''''''''''''

ዥንጉርጉር አሻራህ ያለየልህ ውሉ
ነጭ ነህ አንዳንዴ ባይገባኝም ቅሉ
ሲያሻህ ደስ ሲልህ
ጭር ላለው ቤቴ ድምቀት ትሆናለህ
ሰው ለራበው ልቤ ጥጋብ ትቸራለህ
ላላማረ መልኬ ውበት ታበጃለህ
ሁሉን ታቃናለህ ማሳመር ታውቃለህ
ደግሞ አንዳንድ ጊዜ
ጥቁር ነህ ለገፄ
የህመሜ ምንጩ የእንባዬ ቋጠሮ
የውስጠቴ ሃዘን የልቤ ሮሮ
መውደድ ምወድብህ 'እህ'ም ምታስብለኝ
መኖር ምጠላብህ መኖር ምታስመኘኝ
ጥቁርም ነጭም መልክ መሳል ምታውቅበት
ግራጫ ነው ፍቅርህ
ከብዙ ሃሴት ጋር እልፍ ህመም ያለበት

Nuniyat

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.9K viewsAbela, edited  17:50
Open / Comment
2021-11-22 17:53:52 ነፍስ ይማር

ስለ'ኔ ስላንቺ
ካህናት በወረብ ፣ ሼሆች በመንዙማ
ባርምሞም በጩኸት፤
ይቀኛሉ ቅኔ ፣ ይዜማሉ ዜማ
ቅዱስ ለፍቅራችን
ቅዱስ ለጠባችን
ቅዱስ ለፍጻሜው
በ'ንባሽ ታንቆ ፍቅር ፣ ላለቀበት እድሜው
ስብሃት ሶስቴ ላንቺ ፣ ስብሃት ደግሞ ለ'ኔ
ለደከመው አካል ፣ ለደቀቀው ጎኔ
ፍትሃት ለዛ ፍቅር ፣ ፍትሃት ለዛ ተስፋ
በኩርፊያሽ ተዳፍኖ ፣ በእምባሽ ለጠፋ
ወዩ ለትግስትሽ ፣ ሞቷል መጠበቄ
ነፍስ ይማር ለሳቅሽ ፣ ነፍስ ይማር ለሳቄ

[ቶማስ ትግስቱ]
1.5K viewsAbela, 14:53
Open / Comment
2021-11-22 08:23:56 ከመጽሐፍ ገጽ
ዝጎራ
አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

“እውነት አለህ የእኔ ልጅ ! ይሁንና ሞት ብትፈራውም ብትንቀውም የማይቀር ዕዳ ወይም መንገድ ነው፡፡ የዕድሜህ ማጠር ወይም መርዘም አያስጨንቅህ፤ የፈጣሪ ፈቃድ ነውና፡፡ ይልቁንም በተሰጠችህ እያንዳንዷ ቀን በመልካምና በደስታ ለመኖር ሥጋህን ተጠንቀቀው፤ ነፍስህን ቁጠራት፣ እምነትህን ጠንቅቀው”
“ኢትዮጵያዊነት በአምስት አምዶች የታነጸ መኖሪያ እልፍኝ ነው፡፡ ጥልቅና ሰፊ ዕውቀት፣ መዛል የሌለበት ትጋት፣ በትዕግስት የታሸ ጀግንነት፣ ርኩሰት የሌለበት ቅድስና፣ ግብዝነት የሌለበት ምስጢራዊ ሕይወት ነው!”

“የምሥጢር ሙዳይ ሁን እንጂ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን፡፡ ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር፣ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን፡፡ ለእውቀት ትጋ፡፡ በከፊል በተረዳ¤ው ነገር ራስህን እንደአዋቂ አትቁጠር፡፡ በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል፡፡ ሥራ ስትሰራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው፡፡ ትጋት ጥሩ ነው፡፡ ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፤ በችኮላ መሥራት እና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው፡፡ ርኩሰት የዕውቀትና የሥልጣኔ መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ፡፡”

“እናም በየዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን፡፡ ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ፤ ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር፤ ልክ እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና የመወለድ ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናወን የምትመርጠውን ዐይነት ሕይወት ለመኖር ሞክር ፡፡ እንዲህ ያለ ጥየቄ ብትጠየቅ መልስህ ምንድን ይሆን? አንደገና የመወለድ ምርጫ ቢኖርህ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ሆነህ ለመወለድ ትመርጣለህ? የያዝከውን ሙያ በድጋሚ ትመርጠዋለህን? ያገባሃትን ሚስትህን እነደገና ታገባታለህ ወይስ መነኩሴ ከሆንክ እንደገና ምንኩስና ሕይወትን ትደግመዋለህን? ……….….”

“…የምትፎካከሩባትን፣ ሲያሻችሁ የምትወዷትንና የምታወድሷትን ስትፈልጉ ደግሞ የምታዋርዷትን፣ በለስ ሲቀናችሁ ከላይ ሆናችሁ ስትረግጡ ሌላ ጊዜ በተራችሁ ከሥር ሆናችሁ ስትታሹ የምትኖሩባትን ሀገራችንን፣ የትጋትና የበረከት ምድር መሆኗ ይገለጽ ዘንድ፣ ለራሳች ላይ ያራቅነውን ጸጋ እንጎናጸፍ ዘንድ ፣ፈጣሪ ለተስፋው የሰነፈውን ልባችንን ያነሣሣው ዘንድ፣ የመከራችን ፍጻሜ ይቀርብ ዘንድ የሰጠንን እናስተውልበት ዘንድ ኅሊናችንን በብርሃኑ እንዲሞላው በዚህ ቦታ እንለምነዋለን፡፡ የተናቀውንና የተረሳውን ጥበባችንን የሚፈልገው ትውልድ እስኪመጣ ድረስ በእምነት አደራችንን በአርምሞ የምንጠብቅበት ስፍራ ነውና ከዚህ በላይ አትድፈረው……”

“የኔ ልጅ ይልቁንም፡ -
‹‹ፈጣሪ ለምን አይሰማንም ሳይሆን ለምን አንሰማውም፣ ፈጣሪ ለምን አይባርከንመ ሳይሆን ለምን በረከታችንን አናውቅም ማለትን ተማሩ፤ ለምን ተወን አይደለም ለምን ተውነው በሉ፤ ለምን የብልጽግና ቁልፍ ደበቀብን ሳሆን ለምን ችሎታችንን ስንፍና ጉድጓድ ውስጥ ቀበርን፣ አቅማችንን ለምን በልግመት ስልቻ ከተትነው›› በሉ!”
“ ሌላወን መስላችሁ ሳይሆን ራሳችሁን ሆናችሁ ለማደግ ሞክሩ……….”

‹‹ዝጎራ››


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
467 viewsAbela, 05:23
Open / Comment
2021-11-21 19:10:21
ዛቅ እፍስ  ከሰማይ ከከዋክብት መሃል
መዳፎቼን  ዝርግት እንደው 'ላመል ታህል

አንዲቷን  ለአፍሽ
ጥለት  ከመሰለው  ስስ  መስመሮች  መሃል
ብርሃን  ፈንጥቆ  ደምቄ  እንድስምሽ

መንታ  ለአይኖችሽ
ጸሊም  ፊቴ  ፈክቶ
አብርቼ  እንድታይሽ

አንዲቷን  'ላፍንጫሽ ለተንሰለከከው
'ብስብስ መዓዛዬን አርቅቆ ቢልከው

ቆንጥሬ ብሰጥሽ
ጥቂቱን   ለጭንሽ
የ'ርግማን  ምጥሽን
በዘመን  ያረጀ ወልድን  ሳትማልጂ 
ጣርሽ ቢሻርልሽ

አልቦ ተስፋው እኔ በቅዠት እጆቼ

ዛቅ እፍስ  ከሰማይ ከከዋክብት መሃል
መዳፎቼን  ዝርግት እንደው 'ላመል ታሀል።
አድርጌ  ልቸርሽ
ከልቤ  ባሻገር
ሙላተ  ዓለሙን  ላንቺ  እንደምለግስ
ትዝ  ትውስ ቢልሽ።

ብሩክ (ዝብርቅርቅ)

።።።።።።።።። ።።።።።።።
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.2K viewsAbela, 16:10
Open / Comment
2021-11-21 15:55:06
KIDS Tab ( Atouch) 32 GB storage

የልጆች መማሪያ ታብሌት

ዋጋ - 3500 Birr (fixed)

Wifi መጠቀም የሚያስችል
ልጆች አልባሌ ነገር እንዳያዩ የራሱ ማቆጣጠሪያ ያለው
የፊትና የኃላ ካሜራ ያለው
3 GB RAM
32 GB ROM ( Storage )
10 Point Multi Touch
ተጨማሪ ሚሞሪ እስከ 32ጂቢ የሚወስድ
7 ኢንች ስክሪን እንዲሁም የራሱ ፕሮቴክተር
አንድሮይድ 8.1 የተጫነበት (kids software)
ሙሉ በሙሉ ተች ስክሪን የሆነ
አስተማማኝ ባትሪ 3000 mAh
Processor Type - Quad Core

MORE Free Gift
ለልጁ የተሻለውን ለሚመርጥ ወላጅ የቀረበ
Free DELIVERY

Contact @abela1987
0911468394
1.1K viewsAbela, 12:55
Open / Comment
2021-11-21 15:27:19 የጎዳናዋ እናት


ወላጅ ቤት ባይኖረኝ፣ የሥሜ መጠረያ
እናት ግን አለችኝ፣ ዋርካ መጠለያ

ጎጅዋ የማትነፍግ፣ሠለቸኝ የማታቅ
ኪስ ጉስቆላን አይታ፣ተጸይፋ የማትንቅ
ፊቷ የማታጠቁር፣በክፉ የማታይ
ካላት የማትሠሥት፣የተቸራት ከለይ

አባት፣ዘመድስ፣ቤት ኧረ እኔ ለምኔ
እናቴ አለች ብዬ፣ይበቃል ማመኔ

ምድሯ መኝታዬ፣ዳገት ቁልቁለቱ
ለዛልኩኝም እለት፣ያደርገኛል ብርቱ

ሠንደቆ ካባ ነው፣በውርጭ አያስመታ
አመኖም ለተካበው፣ለልብ አያስረታ

አይርበኝ ምግብ ነው፣ስሟ ላንደበቴ
ይብቃኝ ለሧ ልኑር፣ምለው የለኝ ቤቴ

እጄ ስዘረጋ፣ባንድ አፍት ምትሞላ
ጸሀይ ስትበረታ፣ምቶነኝ ከለላ

ታዳ ቤት ለምኔ፣ድሎት ነው፣ይህ ኑሮ
ይበቃኛል ይቅር፣ቤቴ ኧረ አልበል ጓሮ

አይሠለችም ስሟ፣ላንደበ ኩራት ነዉ
በፍቅር ለጠራው፣ኢትዮጵያ የሚለው

ኢትዮጵያ ኩራት ናት
ኢትዮጵያ ምግብ ናት
ኢትዮጵያ አርኪ ናት
ኢትዮጵያ እራብ ናት
" "ጥማት ናት
ኢትዮጵያ(+2)እናት ናት
ኢትዮጵያ ፍቅር ናት
ኢትዮጵያ(+2)ሀገርም ናት
ኢትዮጵያ ቤትም ናት

ለተከፋ አንደበት፣መጽናኛ ሙዚቃ
ቢሰሙት ቢዘፍኑት፣ማይሠለች ማይበቃ
ጥንካሬዬ ናት፣የመንፈሴ ምግብ
በመንገዷ ብኖር፣የማይነካኝ እራብ

ወላጅ የለኝ ብዬ፣ከቶም አልከፋ
ዘላለም ምትበራ፣ሻማ ናት፣ማትጠፋ
አባት፣እናት፣ወንድም፣እህቴም እሧ ናት
አትንኳት ትለምልም፣የጎዳናዋ እናት

በቶኒ ይፋቱ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.2K viewsAbela, 12:27
Open / Comment