Get Mystery Box with random crypto!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵና በራሺያ ፌዴሬሽን መንግስታት መካከል ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓ | FACT

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵና በራሺያ ፌዴሬሽን መንግስታት መካከል ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓላማ ለማዋል የተደረገ የስምምነት የውሳኔ ሃሳብን አጸደቀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን አምስተኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵና በራሺያ ፌደረሽን መንግስታት መካከል ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓላማ ለማዋል የተደረገ ስምምነትን ለማጽደቅ በውጪ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አድምጧል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ስምምነቱ ለሀገሪቱ ከሚኖረው ጥቅም አንጻር ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች ተካሂደው ኮሚቴው አስፈላጊ መሆኑን አምኖበታል ብለዋል፡፡

ስምምነቱ የሀገራቱን የቆየ ግንኙነት የሚጠናክር፣ አዲስ የሀይል አማራጭን የሚፈጥርና በዘርፉ ልምድ ለማካፈል እንደሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ምክር ቤቱም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፌደራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበለት ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ላይ መክሯል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አቡ ብርኪ የፌደራልና የክልል መንግስታት የተናጠል ኃላፊነት ያላቸው ቢሆንም አዋጁ በጋራ ስራዎቻቸው ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት አዋጁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተመራው ከሶስት አመት በፊት ነበር ለምን ዘገየ፣ ከፌደራል ስርዓት ጋር አይጋጭም ወይ፣ ክልሎች ለመተግበር ያላቸው ቁርጠኝነት ምን ይመስላል የሚሉ ጥያቄወችን አንስተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አቡ ብርኪ አዋጁ የፌደራል ስርአቱ የሚያጠናክር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባዓ አቶ ታገሰ ጫፎ የፌደራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መፍጠርን ያግዛል፣ በአመራሮች በጎ ፈቃድ ላይ ብቻ የሚመሰረት ስርዓት እንዳይኖርም ያደርጋል ብለዋል፡፡

ከክልሎችና ከፌደሬሽን ምክር ቤት ጋር በቂ ውይይቶችም እነደተካሄዱ አንስተዋል፡፡ ምክር ቤቱም የውሳኔ ሃሳቡን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

Via #AMA