Get Mystery Box with random crypto!

#የበጎ_ሰው_ሽልማት ለሀገርና ለህዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ኢትዮጵያውያንን በ | ገራዶ ሚዲያ

#የበጎ_ሰው_ሽልማት

ለሀገርና ለህዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት፤ የዘንድሮ የእጩዎች ጥቆማ የካቲት አንድ 2013 እንደሚጀምር አዘጋጆቹ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ አሰታውቀዋል።

ለዘንድሮው ሽልማት አስር ዘርፎች የተመረጡ ሲሆን እነሱም፦ መምህረነት፣ ሳይንስ (ህክምና፣ ቴክኖሎጂ፣ ምሕንድስና፣ ኬሚስትሪ፣ አርክቴክቸር....)፣ ኪነ ጥበብ፣ በጎ አድራጎት፣ ቢዝነስና ፈጠራ፣ መንግስታዊ ተቋማት ሀላፊነት፣ ቅርስና ባህል፣ ማህበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነትና ለሀገሪቱ እድገት በጎ ስራ ያከናወኑ ዲያስፖራዎች ናቸው።

ለአንድ ወር በሚቆየው የእጩዎች ጥቆማ ለመስጠት በቫይበር፣ ቴሌግራም፣ ኋትስአፕ እንድሁም በስልክ ቁጥር 0977 23 23 23 መጠቀም የሚቻል ሲሆን በተጨማሪም በኢሚይል አድራሻ begosewprize@gmail.com ወይንም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 150035 ጥቆማ መስጠት አንደሚቻል አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት እስከአሁን ከ160 ሰዎችን የሸለመ ሲሆን ሽልማቱ ካባ በመሰልበስ የምስጋና ሰርተክፌት የሚሰጥበት አመታዊ ፕሮግራም ነው። #FBC

t.me/geradomedia