Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ በሱዳን.... የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ለሁለት ቀን የስ | ገራዶ ሚዲያ

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ በሱዳን....

የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ወደ ሱዳን አቅንተዋል። በፕሬዝዳንቱ በሚመራው ልዑክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ እንደሚገኙ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገ/መስቀል በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስና ልኡካቸው በካርቱም በሚኖራቸው ቆይታ በሁለትዮሽ፤ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

t.me/geradomedia