Get Mystery Box with random crypto!

የሰብዓዊ ድጋፍ ጥሪ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልል በርካታ ዜጎች ሰብ | ገራዶ ሚዲያ

የሰብዓዊ ድጋፍ ጥሪ

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልል በርካታ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። እስካሁን እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከእርዳታ ፈላጊው ቁጥር አንፃር ገና የሚቀረው በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሃላፊነቱን እንድወጣ ጥሪ እየቀረበ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርም እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በገንዘብ መደገፍ ለሚፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000000902008 ላይ ማስገባት እንደሚችሉ ምስህበሩ ገልጿል። በአይነት መደገፍ ለሚፈልጉ ደግሞ በማህበሩ ብሄራዊ ፅህፈት ቤት እና በሁሉም የቀይ መስቀል ቅርንጫፎች በመሄድ መለገስ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ስለ ቀይ መስቀል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ደግሞ 0946659969 / 0911411719 መደወል ይቻላል።

ሁላችንም በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን እንድረስላቸው!

t.me/geradomedia