Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ጋር ተወያዩ! ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና | ገራዶ ሚዲያ

አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ጋር ተወያዩ!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ሲሪ ራማፎዛ ጋር ፕሪቶሪያ ተገናኝተው በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በኢትዮጵያ ያሉትን ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል። የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሶስትዮሽ ወገን ድርድር እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ያላትን ፅኑ አቋም አስረድተዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ወደ ኒጀር ያቀኑ ሲሆን ለኒጀር ፕሬዘዳንት መሀመድ ባዙም ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ መሪዎቹ ባደረጉት ውይይት የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነት አስረድተዋል። #AMN

t.me/geradomedia