Get Mystery Box with random crypto!

ሸኔ ማን ነው?? በርካቶች 'ሸኔ' እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ | ገራዶ ሚዲያ

ሸኔ ማን ነው??

በርካቶች 'ሸኔ' እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይደመጣሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ የፌዴራል ጠ/አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ለመሆኑ 'ሸኔ' ማነው? 

"በተለምዶ 'ሸኔ' የሚባለው እራሱን ደግሞ 'የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት' ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው። እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን።

ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ ህወሓት ተመዝግቦ፣ ህጋዊ እውቅና፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም፤ ስለዚህ ስያሜው እሱ እራሱን በአንድ ስያሜ ይሰይማል አንዳንዶች በሌላ ስም ይጠሩታል በተለምዶ 'ኦነግ ሸኔ' ይባል ነበር ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራበት 'ኦነግ ሸኔ' ወይም 'ሸኔ' ከሚባለው 'ሸኔ' የሚለውን መርጠናል።

እዚህ ጋር ግልፅ መሆን ያለበት በአዋጁ አንቀፅ 23 መሰረት ስያሜውን ብትለዋውጥ ያው ቡድን ያው ስብስብ እስከሆነ ድረስ በውሳኔ ሀሳቡ የተገለፀው ስብስብ እስከሆነ ድረስ ስያሜ መለዋወጥ የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ውሳኔ ሀሳቡ ተፈፃሚ ይሆንበታል።

አይ እኔ እራሴን የምጠራው እንዲህ ብዬ ነው፤ እንዲያ ብዬ ነው የሚለው ማምለጫ ሊሆን አይችልም።

በተለምዶ በሁለት መንገድ ይጠራ ነበር፤ 'ኦነግ ሸኔ' ይባል ነበር፥ በአጭሩ 'ሸኔ'ም ይባላል፤ 'ኦነግ ሸኔ' የሚባለውን አጠራር 'ኦነግ' የሚባል በምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት አለ ስለዚህ ከሱ ጋር ማምታት ሊፈጥር ይችላል ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራባቸው ስያሜዎች 'ሸኔ' የሚለው ብዙ ሰው ስለሚያውቀው በዛ እንዲሰየም ተመርጧል" ብለዋል። #Tikvah

t.me/geradomedia