ዐሹራን በመፆም የሚገኘውንም ታላቅ ምንዳ አውስተዋል። وقال النبي صلى الله عليه وسلم: «صيام يوم عاشوراء، إني أحتسب على الله أن يكفر السنة التي قبله» (رواه مسلم) " እለተ ዐሹራእን መፃም አላህ ዘንድ ያለፈውን አንድ ዓመት( ትናንሽ ) ወንጀሎች ያስምራል ብዬ አስባለሁ " በማለት ገልፀዋል። ታዲያ ይህን እለት አይሁዶችና ነሳራዎችም ክብር ይቸሩት ስለነበር የአላህ መልዕክተኛ በቀጣይ ከ10 ኛው ቀን በተጨማሪ 9ኛውንም ቀን ለመፆም እንዳሰቡ ተናግረዋል። فقال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «فإذا كان العام المقبل إن شاء الله صمنا اليوم التاسع»، قال: فلم يأتِ العام المقبل حتى توفي رسول الله صلى الله عليه وسلم. (رواه مسلم ) " የአላህ ፈቃድ ከሆነ በመጪው ዓመት ዘጠነኛውንም ቀን እንፆማለን " ይሁንና የቀጣዩ ዓመት ግዜ ሳይደርስ የአላህ መልዕክተኛ ወደ ኣኼራ ሄደዋል።