🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ተረተረት ......ከለታት አንድ ቀን በአንድ ሀገር ውስጥ የሚፈራ ንጉስ ነበር እና ይሄ ንጉስ አን | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ተረተረት ......ከለታት አንድ ቀን በአንድ ሀገር ውስጥ የሚፈራ ንጉስ ነበር እና ይሄ ንጉስ አንድቀን አሽከሮቹን ያስጠራና ሶስት እርግቦች እንዲያመጡለት ይነግራቸዋል እነሱም በተባሉት መሰረት ይዘውለት ይመጣሉ ንጉሱም ተቀብሎ ተራ በተራ አንድዋን እርግብ አንስቶ በመስኮት ወረወራት እርግቧም በረረች ሀለተኛዋንም አንደዛው ወረወራት እስዋም በረረች ሶስተኛዋንም አንስቶ ሲወረውራት ግን አልበር አለች ንጉሱ በጣም ይናደድና እንዴት የማትበር እርግብ ያመጡልኛል ብሎ ተቆጣ ከዛ በሀገሩ ያሉትን አዋቂዎች ጠቢባንን አስጠርቶ ይችን እርግብ ከናንተ መሀል ያስበረረ ብዙ የወርቅ ሳንቲም እሰጠዋለው አለ ከዛ አዋቂዎቹ እና ጠቢባኑ ያችን እርግብ ለማብረር ብዙ መከራ አዩ ነገር ግን ማንም እርግቧን ሊያበር አልቻለም የሆነ ቀን አንድ ገበሬ በዚያ ሲያልፍ እነዛን ሰዎች ያያቸዋል ወደ እነሱም ጠጋ ብሎ ምን እንደሆኑ ጠየቃቸው እነሱም ሁሉንም ነገር ነገሩት ገበሬውም እርግቧን ለኔ ስጡኝ አላቸዉ እነሱም እኛ አዋቂዎች እኛ ጠቢባኖች ያልቻልነውን አንተ ተራ ገበሬ እንዴት ትችላለህ አሉት እሱም ግድ የለም ለኔ ስጡኝ አላቸው እነሱም ሰጡት ገበሬውም እርግቧን ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ እርግቧንም እያበላ እያጠጣ ተንከባከባት አንድ ቀን ንጉሱ መስኮት አጠገብ ቁጭ ብለው ሳለ ያቺ አልበር ያለች እርግብ እየበረረች ያያሉ ከዛ በደስታ አዋቂዎቹን እና ጠቢባኑን አስጠርተው ማን ነው እርግቧን እንድትበር ያደረገው ብለው ሲጠይቁ እኛ አደለንም የሆነ ገበሬ ነው ብለው ይናገራሉ ንጉሱም ገበሬውን ይዛችውት ኑ ብሎ አሽከሮቹን ላከ ብዙም ሳይቆይ ገበሬውን ይዘውት መጡ ከዛ ንጉሱ ገበሬውን አንዴት አድርገህ ነው ያበረርካት እነዚህ ትላልቅ ሰዎች ያቃታቸውን ብሎ ጠየቀው ገበሬውም እኔ ምንም አላደረኩም አንድ ረዘም ያለ ዛፍ ላይ የዛፉ ቅርንጫፍ ላይ አስቀመጥኳት ትንሽ እንደቆየች የተቀመጠችበትን የዛፍ ቅርንጫፍ ሰበርኩባት ከዛ በረረች ብሎ ተናገረ ንጉሱም በጣም ተገርመው ቃል በገቡት መሰረት የወርቅ ሳንቲም ሰተውት አሰናበቱት ...............አየሽ ይሄ ታሪክ ሰው የተደገፈው ነገር ሲከዳው ወዶ ሳይሆን በግዱ ይበራል ያቺ እርግብ ንጉሱ ሊያበራት ቢሞክር እምቢ አለች ምክንያቱ በእጅ አንስቶ ወረወራት እንጂ እጅ ላይ አላስቀመጣትም ነበር ነገር ግን ገበሬው የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አድርጓት በስርአት እንደ ተቀመጠች ሲያይ የዛፉን ቅርንጫፍ ሰበረባት እርግቧም ሳታስበው ስለሆነ የሰበረባት ድንገት የተደገፈችው ነገር ከአጠገብዋ ሲለያት ምንም ማድረግ አትችልም በረረች ......ደግሞ ሁል ጊዜ ከትላልቅ ሰዎች መፍትሔ አንጠብቅ እነዛ አዋቂዎች ገበሬውን ንቀውት ነበር ግን አድርጎ አሳያቸው .........አንቺም ችግር ሲገጥምሽ ግዴታ ለትልልቅ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ካንቺ በታች ላሉትም ተናገሪ ከትልልቅ ሰው መፍትሔ የለም እያልኩ ግን አደለም ወረድ ብሎ ማሰብም ጥሩ ነው ።.......ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ ያብሱ