2023-04-10 18:13:43
ኪራላይሶን ማረን አባ አባታችን
ለተወጋዉ ጎንህ
ለበትረ መስቀልህ
ለፈሰሰዉ ደምህ
ቀራንዮ ሞትህ
ጎለጎታ ቤትህ
ኪራላይሶን ማረን ለዛ ህማማትህ።
አባ አባታችን
በጥፊ ስመታህ እጆቼን ይዘሀኝ ልማርህ ብለሀል
ዉሀ አልሠጥም ብዬ በከርቤ ኮምጣጤ ጉንጭህን ሞልተሀል
ጠማኝ አባቴ ስል ይሄ አይጠቅምም ብለህ
የዘላለም ዉሀ ለኔ አዘጋጅተሀል።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን..........
መፃጉ ሆኜ ሳለሁ መዳኔን ሽተሀል
አልጋህን ተሸከም ብለህ ምረሀኛል
ሰንበት አፈረሰ እያልኩ መክሰሴን
ጌታ አረሳሁትም ማራት ይህቺን ነፍሴን።
ጎንህን ወጋሁት በጦሩ ጎርጉሬ
አቤቱ ማዳንህ አይኖቼን አበራህ ትተህ መነወሬን።
የሀጥያቴ መብዛቱን አይተህ ሳትጠየፍ
ፈራሽ ሰዉነቴን አፈር ማንነቴን ተመልክተህ ሳታልፍ
እኔ የከንቱ ከንቱ ፊትህን ተጠይፊ
የማይፈርስ አካልህን ፍቅርህን ጠፍፌ
ማረዉ ብለህ ስትል ሰዉነቴ ቀፎት
ምራቅ ተፋዉብህ ለኔ መምጣትህን እኔነቴ ክዶት።
ኪራላይሶን ማረን
ስለናትህ ማረን................
ሸክማችሁን በኔ ጣሉት ብለህ ስትል
ችግሬን ጥዬብህ
እንቅልፍና እረፍትን ባንተ አገኘዉብህ
ችግሬ አንሶብኝ
መስቀል ማሸከሜን ጌታ አትይብኝ
ከኃላ እንድትፈጥን እየገፈተርኩ
ከፊት ቀስ እንድትል እየገፈተርኩ
መሬት ስትወድቅ እያንቀለቀልኩ
ስትነሳ ደግሞ እያወዛገብኩ
መቼ ይረሳኛል እንዳንከራተትኩህ።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን...............
መዳፍህ ይታየኛል
ጭቃ አበጃጅቶ እኔን የሰራልኝ
ዳብሶ የፈወሰኝ
እኔ የእፉኝት ልጅ
አዴራ አላዶር ሳዳርና ዳናት በሚባል ችንካሮች
መዳፍህን በሳዉ አለምን በያዙ በነዛ ድንቅ እጆች።
እግርህን ቸነከርኩ ምድርና ሰማይ ሊችሉት ያልቻለ
አልፋና ኦሜጋ በመስቀል ላይ ዋለ።
ኪ..ራ..ላ..ይ..ሶ..ን ማረን
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
178 viewsTIZITA21, 15:13