Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም በድምፅ

Logo of telegram channel audio_poems — ግጥም በድምፅ
Logo of telegram channel audio_poems — ግጥም በድምፅ
Channel address: @audio_poems
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 10.47K
Description from channel

@Air_me1 ግጥሞን በዚ ይላኩ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages 7

2023-04-01 20:08:42 "እኔ አንተን ሳጠና"

...........እኔ አንተን ሳጠና
ሒሳብ አስተማሪ
Xን ለመፈለግ
እንደወጣ ቀረ
ሆነና መርማሪ
በጠመኔ ብርታት
በጀመረው ጉዞ
አማርኛ መምህር
ድንገት አገኘሁት
ከትምህርት ተወግዞ
ምዕራፍ አንድ ብሎ
ሳይንስ ለማስተማር
ሲቀጥል መምህሬ
ምዕራፍ ዘጠኝ ገባ
እኔ አንተን ሳጠና
ቆሜ ተገትሬ፡፡
..........ከደጀ ሰላሙ
ከቤተ መቅደሱ
ቆሜ ለመቀደስ
ያስለቅቀኝ ብዬ
ምን አልባት እጣኑ
"እትሁ በሰላም"
ብሎ ገላገለው
"አሀዱ አብ"
ብለው የተጀመረውን
የቄሱን ምስገና ጨርሶ ዲያቆኑ፡፡
................ ይኸውልህ ውዴ
እኔ አንተን ሳጠና
ከመንበሩ ወርዶ
ንጉስ ደጅ ጠና
የሰማዩ ፀሃይ
አፍቅሮ ጨረቃን
እሷኑ ሲከተል
እኛን እረሳና
ይኸው ብርሃን ነሳን፡፡
.............ይኸውል ፍቅሬ
እኔ አንተን ሳጠና
ጥቁረቱን ለቀቀ
ጠጉሬም ነጣና
ምርኩዝ ተደገፈ
እግሬም ዛለና
ብህሬም ደርቆ ቀረ
ቀለሜ አለቀና
እንደ ጨው ሞሞልህ
አይኔም ፈዘዘና
ድድ ብቻ ሆነ
ያምራል ምትለኝ
ጥርሴም ወለቀና፡፡
.........አድምጠኝ የኔ አለም
ካንተ እደርስ ብዬ
የሆንኩትን ሁላ
እንዲሁ ቀረውልህ
ከሜዳ ወድቄ
ሆኜልህ ተላላ
አጠናለው ብዬ
ስላንተ አፈጣጠር
ደብተሬን ብገልፀው
አጣው አንተነትክን
አይደለም ከጥራዝ
አለም ላይ ባስሰው፡፡
...........ካገኘውህ ብዬ
ከዚች ጠባብ ምድር
እኔ አንተን ሳጠና
አገኘውሁ ድንገት
ከአለም ከሚሰፋ
ከልቤ ደጃፍ ስር
ብርሃነኔ ሆንክና፡፡


https://t.me/MyMessagesss
284 viewsBarkot A, 17:08
Open / Comment
2023-03-31 06:38:08 ወደው አይስቁ

በሃዘን ዶፍ ዥረት
ማህበል ሲናጡ
ኑሮ ሁሉ ሲሆን
ከድጥ ወደማጡ
አይን ደርቆ ሲቀር
ማንባት እያቃጣው
አንደበት ዝም ሲል
ማውራት እያሰኘው
በውሸት አሉ ባልታ
ሲደነቁር ጆሮ
መኖር እየሻቱ
እጅግ ሲመር ኑሮ
ያገለሉት ቀርቶ
ያቀረቡት ሲሸሽ
ነገር ሁሉ ሲሆን
የተገላቢጦሽ
በነገሮች ግርምት
ካልተነቀነቁ
በዋዛ ፈዛዛ
ለካስ ወደው አይስቁ

https://t.me/MyMessagesss
187 viewsBarkot A, 03:38
Open / Comment
2023-03-30 22:21:16 https://vm.tiktok.com/ZMYVkYYtD

እነሆ ትረካ ለሚመቻችሁ ወዳጆች !
332 viewsEyob Z Mariam, 19:21
Open / Comment
2023-03-29 19:52:24
https://t.me/MyMessagesss
386 viewsBarkot A, 16:52
Open / Comment
2023-03-28 22:19:04 @Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
220 viewsTIZITA21, 19:19
Open / Comment
2023-03-28 18:31:35 "ለካስ ያን ዕለታ"

አለም በቃኝ ብዬ
ስኤድ ወደ አንድዬ
ደረቱ ሲደለቅ
ሁሉም ተሰብስቦ
እሪታውን ሲለቅ
ቅኔው ሲቀኝልኝ
ሞሾዎውም ሲወረድ
መሬቱ ሲመታ
እናት በአዘን ስትነድ
ወዳጅ ጎረቤቱ
ለኔ ልቡ ሲርድ
እግዜር ያፅናቹ
ሲል ሁሉም ተሰብስቦ
አስክሬኔ ሲሸኝ
በዘመድ ታጅቦ
የቤቴ ይቅርና
እንኳን የመንደሬ
የውል ስሜ ቀርቶ
ሲኬድ ለቀብሬ
እማዬ እምዬ
አባት አባት አለም
እህት የናት ምትክ
ወንድም የኔ ጋሻ
ዘመድ አዝማዶቼም
የጭንቄ መሸሻ
የለካስ ያንህለታ
ሞት አሸንፎት
ገላዬ ሲረታ
ክፋት ደግነቴን
ሊዘረዝልኝ ሁሉም ሲበረታ
ለካ ያን ለታ
ሁሉም ይረሳና
ስሜ ይቀየርና
እሬሳ እባላለሁ
በድን ሰው ነኝና


https://t.me/MyMessagesss



https://t.me/MyMessagesss




https://t.me/MyMessagesss
448 viewsBarkot A, 15:31
Open / Comment
2023-03-17 19:54:43 እኔን ለማግኘት @Yohannn
361 viewsվohaŋŋes Lawgaw, 16:54
Open / Comment
2023-03-16 14:44:47
ይህን ግጥም ሙሉውን እስከ ዛሬ አልሰማሁትም እንዳትለኝ ብቻ

ሰምቼዋለው አልሰማሁትም

https://t.me/MyMessagesss
357 viewsBarkot A, 11:44
Open / Comment
2023-03-14 17:32:58
__
ቅናት ያደት ልብ
እንኳንስ በልብሽ
የምታስቢያቸው
ነገሮች በሙሉ ፣ እኔ በሆንኩልሽ
ብላ ትቀናለች
የናፍቆት አምላኳ ፣ መሲህ ልታደርግሽ

ፍቅር የሰጣት ነፍስ
ነፍስነቴ ቀርቶ
ስጋዋ በሆንኩት ፣ በተደረብኩላት
የሳቅ የለቅሶዋን ፣ የስሜቷን ምልአት
በጀርባዬ መርከብ ፣ ልኑር ተሸክሜ
የምናፍቃትን
ገነቴን ልቀፋት ፣ ሲቃሽን ደክሜ
ብላ ትጣራለች..!
:
በየሄድሽበቱ
ኮቴሽ ለሙዚቃ ፣ ዜማ እየቀረበ
ዝምታሽ በገና
የምስጠት ማይ ውሃ ፣ ሆኖ እየዘነበ...
ዛሬም ሳስተውልሽ
ዝምታ እየራቀኝ
ቃል እየረቀቀኝ...

አንድ እውነት ተነፈስኩ !
ቀድሞ ስላሰበሽ....
ሞዛርትም ነሽጦት
እያንጎራጎረ.....
ይኼን ዘመረ!
<<"ምልኡ በኩልኼ
ውበት ሁለንተናሽ
የትዝታን ክራር ፣ እየደረደረ
ወደ ትንቢት ሰማይ
መጥቆ እየበረረ...
ሙዚቃ ህይወቴን
እስትንፋስ ባይሰጠው ፣ ምን ይሆን ነበረ!?
ምን እሆን ነበረ!?
____

https://t.me/MyMessagesss
374 viewsBarkot A, 14:32
Open / Comment
2023-03-13 11:09:49

193 viewsEyob Z Mariam, 08:09
Open / Comment