2022-03-01 15:30:39
ወይ መምህር ሊያሳድረን ነው እንዴ?
ጨርሻለሁ ካለ ግማሽ ሰዓት አልፎታል
ምሳሌያዊ አነጋገር ምን ማለት ነው? ጥያቄው ለ'ኔ ነበር።
ኸ ምሳሊያዊ አነጋገር ያው በስነ-ምግባር የታነፀ ንግግር ማለት ነው ከማለቴ ጥግ ላይ 'ምትቀመጠው ፅዮን ከጓደኛዋ ጋ ከትከት ብለው ሳቁብኝ።
መምህር ተበሳጩ ምን ማለት ነው ምሳሌያዊ አነጋገር ላንቺ ፂዮን?
ም ሳ ሊ ያ ዊ አ ነ ጋ ገ ር ማ ለ ት ቲ ቸ ር ዬ
ምኗ ሞዛዛ ናት አሉ መምህሩ እንደውም ከክፍሌ ውጡልኝ ውልፍጥ።
ተማሪዎች ምሳሊያዊ አነጋገር ማለት በማህበረሰቡ ልማዳዊ ስምምነት መሰረት የሚፈጠር በቁጥብ'ና ምርጥ ቃላት ባ'ጭሩ የሚነገር የተጨመቀ ጥልቅ ሀሳብን የያዘ የስነ-ቃል አይነት ነው።
መሀል ሰፋሪው ማስረሻ ለመጠየቅ እጁን አነሳ እሺ ማስረሻ ጠይቀኝ።
መምህር ምሳሌያዊ አነጋገርን ለመግለፅ ምሳሌያዊ አነጋጋር አጥተው ነው እንዲህ ያረዘሙት?
እቺ ባቄላ ካደረች አሉ መምህር በየነ ....ኸረ እንደውም ውጣልኝ።
በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ከአስር ሰው በላይ ከክፍል አውጥተው የቀረነው ጥቂት ነን። ተማሪዎች የምሳሊያዊ አነጋገር ምሳሌዎች ፅፍላቹሀለው በማስታወሻ ደብተር ላይ ያዟቸው ይመጣሉ ፈተና ላይ ፃፉልን።
- ቀን የሰጠው ቅል ዲንጋይ ይሰብራል
- ከእብድ አጠገብ ዲንጋይ አይወረወርም
- ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል
- ተመካክረው የፈሱት ፈስ አይሸትም።
ሁላችንም እየፃፍን ነበር ጨርሻለሁ ሲሉን ግን አሁን 'ምናርፈውን ሳይሆን ከሰዓት ሚንገላጀጁብን ነገር ያስጨንቀኛል። ለነገሩስ በኔ አልተጀመረ ዛሬ ላይ ማግኘቱን ሳይሆን የነገን ማጣት ስንቱ አይደል እያሰበ ሚጨነቀው? መምህሩ አሁን መጨረሱ ሳይሆን ቡሀላ መጀመሩ ነው 'ሚያስጨንቀኝ።
ሁሉም ወደቤቱ እየገባ ነው እኔና ጓደኞቼ ግን የለመድናት ነገር ስላለች ወደየቤታችን አንገባም። የዛን ቀን ከቤት አንዳችን አንዳችን ቤት 'ንደምንሄድ እናስፈቅዳለን። ብር ፈላልገን ወደ ለመድንበት እንሄዳለን። በያይነታችን በልተን ፣ ለውዝ ጠጥተን ፣ ስኳር ድንች በልተን ወደ ከሰዓቱ ክፍለ ጊዜ እንመለሳለን። የከሰዓቱ ትምህርት ቶሎ ነው 'የሚጀምረው ጥግግብ ብለን ክፍል ገባን።
ተስብረው 'ንኳ በክራንች ይመጧታል እንጂ መምህር በየነ እንኳን ሊቀሩ ሽራፊ ሰከንድ አያረፍዱም።
ክፍል ገቡ ስነ-ግጥም ብለው በዝርዝር ከፃፉ ቡሀላ ማስረዳት ጀመሩ። መከታተል እየከበደኝ ነው። ሆዴ ላይ ደስ የማይል ስሜት እየተሰማኝ ረብሾኛል። ጓደኞቼንም እንደዛው። እኩል ታመናል አናስፈቅድ ነገር ለሶስታችንም እሺ አይሉም። ከጓደኞቼ ባህርይ ምወደው አስተዋይነታቸውን ነበር እናም አንድ የተቀደሰ ሀሳብ አመጡ ጠዋት ከተማርነው ጋርም ስለሚደጋገፍ ሙሉ በሙሉ ሀሳቡን ተቀበልነው። መፍትሔውም ሰራ መሰለኝ ህመማችን ለቀቅ አደረገን በአንፃሩ ግን መምህሩ ማስተማሩን ትተው እያነፈነፉ ነው።
ማነው የፈሳው? አሉ በሀይለ ቃል ለካ ምሳሌያቸው'ና የጓደኞቼ ምክር ጉድ ሰርቶን ኑሯል። እንዳይሸት ብለን ክፍል ውስጥ ተመካክረን ብንፈሳም ክፍሉን ፈንጂ ላይ ጣድነው።
ማን ነው ልክ?
ትምህርቱ?
ምሳሌው
እኛ
ፈሱ?
መልሱን ባላውቀውም።
ተመካክረን የፈሳነው ፈስ ከመሽተት አልታደገንም
ናታን ኤርሚያስ
@UniqueDy
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.9K viewsAbela, edited 12:30