Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 132.20K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 132

2022-05-10 21:17:18 ፀሎት አድራሽ ፈለኩ፣
ሰንፌ አይደለም፣
እመኚኝ ግድ የለም፣

ምልጃዬን ተረኩት፣
አጀብ ተባለልኝ፣
መንደርቴ ሲሰማ በቁሜ ለየልኝ!

ይቺ ናት ፀሎቴ፣
አድራሽ የምትሻ፣
ማትከብድ ለትከሻ!
የነገርኩት ሰማ ይቺን ፀሎት ብሎ፣

"መጨረሻዋን አስጀምርልኝ"

የወፈፌ፞፞፞ ፅንፉ ንገሪኝ ምን ይሆን?
እኔ ግን አላብድም፣
አላብድም ሰው ልሆን!
የሆንኩት እንዲህ ነው፣
ያልሆንኩትን እንጃ፣
ሰምተሽ ትሰጫለሽ “አብዷል” የሚል ፍርጃ!
.
.
«..ሲያለቅሱ ሳኩ እንጂ ሲስቁ አልሳኩም፣
«..ሱሪ ባንገት እንጂ በ'ግር አልሞከርኩም፣
«...ውሀ ፈራሁ እንጂ ምግብ አልፈለኩም፣
«..እርቃኔን ሄድኩ እንጂ ሽፋን አለበስኩም፣
«..አንቺ'ኳ ተረጂኝ እኔኮ አላበድኩም!

ናታን ኤርሚያስ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
8.3K viewsAbela, 18:17
Open / Comment
2022-05-09 18:29:01 እናት የኛ ጀግና!
አመት ሚፈነጨው : ክብርሽን ሚያጎድል
ደርሶ ዛሬ አክባሪ : እናቴ እናቴ ቢል ፤
እሱንም ችለሻል : ይህ አኮ ነሽ አንቺ
ማን ብቁ ነኝ ይላል : ሊነጻጸር ከአንቺ !
ብጨነቅ ብጠበብ : ብብሰለሰል ከቶ
ስላንቺ ለመጻፍ : ቃላትስ መች በቅቶ!
አንቺ አትደረሺም : ጥልቅ ነሽ ከውቅያኖስ
ስምሽም በቂ ነው : ውስጥን ልብን ሚደርስ!
እናትዬ ስልሽ : የሚሰማኝ ሰላም
ወዬ ልጂ ስትዪ : በድምጽሽ ስታከም ፤
ትበልጫለሽ ከሁሉ : ሀኪምም ነሽ ጠጋኝ
አንደበትሽ ጠል ነው : ክንድሽ አስተማማኝ።
ሁሉን ተሸካሚ : ቻይ አርጎ ፈጥሮሻል
እማ አንድ ቀን ሳይሆን : ሁሉም ይገባሻል።
ጉድለቶችሽ ሞልተው : ያሰብሽው እየቀና
ደስ እያለሽ ኑሪ : እናት የኛ ጀግና!!
በሀሴት ዮሐንስ
30/08/2014
ፍቅራችን ለዛሬ ብቻ አይሁን!
የእናትን ክፉ አያሰማን!

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
9.7K viewsAbela, 15:29
Open / Comment
2022-05-09 15:28:01 #"እማ''
እማ ወደር የለሽ
አለዋዳድርሽ!
የህይወት ድምቀት ሻማ ብረሀንነሽ
እኔ ሠዉ እንድሆንእራስሽን ሠጠሽ
#እማ አትዘኝብኝ እኔን ይከፍኛል
አንቺ ስትደሠች ብርሀን ይታይኛል
ከድምዬ ቀንሶእንድሜሽንያርዝመዉ
#እማ አትራቂኝ ህይወቴ ባዶ ነዉ
#አንቺ ካላገኘ ልቤ አይረጋጋም
ደሥታ አላገኝም ይርቀኛል ሠላም
እድሜሽን በሙሉ ለግሰሻል ለኔ
ህይወቴን ብሠጠሽያንስብሻል ከኔ

ግጥም
እርስትአብ (ፍፄ)
ማሥታወሻነቱ ለእናቴይሁንልኝ፡፡

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
8.5K viewsAbela, 12:28
Open / Comment
2022-05-09 14:28:01
" #መልካም_የእናቶች_ቀን !!!"
.
.
ሲርበኝ አጉራሼ ስታረዝ አልባሼ፣
ለቀን አቅም ባጣ ብታመም ፈዋሼ።
ብጠማ እርካታዬ፣
የንጋት ፈገግታ ፍካት አበባዬ።
ሞታ የምታኖረኝ፤
ሳጠፋ ምትምረኝ፤
የሽሽግ መውደዴ 'ማትነጥፍ ውበቴ፣
እልፍ ዘመን እንጂ፤
አንድ ቀን 'ማይበቃት እኝኋት እናቴ፡፡
.
.


ረጅም እድሜና ጤና ለእናቶቻችን !!!


ዓቢይ ( @abiye12 )

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
7.7K viewsAbela, 11:28
Open / Comment
2022-05-09 12:25:52 ከሰማይ ላይ ተስለሻል
ደመናውም ይመስልሻል
ፀሐይ ካንቺ ተስተካክላ
ሕይወት አንቺን አስመስላ
ጥርስሽ ፀዳል እየረጨ
ፊትሽ ጮራን አመነጨ
የሄድሽበት ሳር ቅጠሉ
ማማር ሆኗል እጣ እድሉ
የረገጥሽው መሬት ምድር
መፍካት ማበብ መድመቅ ክምር
ከጎዳናው የወጣሽ ለት
ካደባባይ የታየሽ ለት
ወንዱ አቅሉን እየሳተ
ሴቱ ገላ እየጎተተ
አበቦቹ እየፈኩ
እንስሳት እየረኩ
ሰማይ ምድር እያውካኩ
ሕይወት ከሞት ሲነካኩ
ሰይጣን ግብሩን ሲዘነጋ
የውበትሽ ሀያል መንፈስ እሱን እንኳን እያላጋ
መላእክታት ሲገረሙ
በአድናቆት ሲያረምሙ
አውሎ ንፋስ ሲነሰነስ
ሰማይ ምድር ሲቅለሰለስ
አይቻለሁ ሀያል መንፈስ
የውበት መናፍስት የቁንጅና ጌታ
ከአንድ ከትመው ባንቺ ወገን ተርታ
ወንዱ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮም ተረታ
ከሰማይ ላይ ተስለሻል
ደመናውም ይመስልሻል
ሰማይ ምድር አፍቅሮሻል
ይሄ ሁሉ ያንስብሻል።


አክሊሉ ተስፋዬ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
7.3K viewsAbela, 09:25
Open / Comment
2022-05-08 22:40:53 ​​ልጅቷ ስታያቸው ተረብሻ ነበር....የመኩሪያው ሠዎች መሥለዋት እጅግ ፈራች ነገር ግን እናቷ እየረዷቸው እንደሆነ አ ሳምነዋት ተረጋጋች።....
እነ ሚኪ ትንሽ ከተጨዋወቱ በሁዋላ የ20000 ብር ቼክ አበርክተውላቸውና ችግር ከተፈጠረ ሥልክ እንዲደውሉላቸው ሥልካቸውን አሥቀምጠውላቸው ወደ ቤታቸው አመሩ።.....
ወደ ቤት እንደገቡ ሚኪ ሊያስቀምጣቸው እንኳን አልቻለም "መኩሪያውን በቁሙ ቀበርኩት" እያለ ወረቀቱን ሰጣቸው......
"omg ላንተ ደስ ብሎኛል" ሂዊ ጉንጩን ሳመችው
"አደርገዋለሁ ካልክ እንደምታደርገው አውቅ ነበር ኮርቼብሃለሁ ጓደኛዬ" ርቤል ጠበቅ አድርጎ አቀፈው.....
"አመሠግናለሁ ጓደኞቼ...እሺ አሁን ምን እናድርግ....ፈጣን እርምጃ እንውሠድ ወይሥ.....?" አለ ሚኪ
"እንደኔ ብንረጋጋ ይሻላል ባይ ነኝ....በእርግጥ አሁን ያለን መረጃ መኩሪያውን ያስፈርድበታል ችግሩ ግን ድርጅቱ ውስጥ ያሉበት ባለስልጣንስ ነው...? መኩሪያው ቢታሰር ሌላኛው ይተካል መኩሪያውን ከእሥር ለማውጣት አንድ ዘዴም አያጡም.."
"እና ምን ይሻላል..?" አለች ሂዊ
"የሚሻለውማ ችግሩን ከላይ ሳይሆን ከስር እንንቀለው....ጭራሽኑ እናጥፋው ነው እያልኳችሁ ያለሁት.. ወንጀሉን ለማሥቆም መኩሪያው ጋር ሲሰሩ የነበሩትን እያንዳንዱን ባለስልጣን ቅጣታቸውን እንሥጣቸው ነው"...
"ግን እንዴት....መረጃው የት እንደገባኮ አናውቅም ደብዛውን አጥፍተውታል....ኮማንደሩን እንኳን መለየት አልቻልንምኮ" አለ ሚኪ ሁሉም ነገር ተዘጋግቶበት..
"እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ...ሀሳቤ እርግጥ ከሆነ" አለ ሮቤል ጺሙን እያሻሸ
"ሮቢ ተሳስተህ አታውቅምኮ ንገረንና እንሞክረው" አለችው ሂዊ ፈገግ ብላ
ሮቤል በሂዊ አፍ መሞገሱ እያስደሰተው ንግግሩን ቀጠለ "የመኩሪያውን ቤት መፈተሽ አለብን!" ሮቤል መፍትሄውን አሥቀመጠ
"የትኛውን...ሴቶችን የሚያባልግበትን ነው.....?" ሚኪ ጠየቀ
"አትሳሳት ሚኪ ወንጀለኞች ድብቅ ነገራቸውን ሁሉም ሰው የሚያየውና የሚያውቀው ቦታ ነው የሚያስቀምጡት ምክንያቱም ሰው የለመደውን ቦታ ማንም አካል ትኩረት እንደማያደርግበት ጠንቅቀው ያውቃሉ.....ስለዚህ ትልቁ መኖሪያ ቪላው ውስጥ ነው ሊደብቀው የሚችለው....እድል ከቀናን ቢሮው ውስጥ ወይም ልክ እንደኔ የሚስጥር ክፍል ይኖረዋል"
"የሚገርም ሀሳብ....እኔ በማንኛውም ሰአት ዝግጁ ነኝ...መች እናድርገው" አለች ሂዊ...
"በደንብ አቅደንበት እናደርገዋለን" ሮቤል መለሰላት....
ሁሉም ትልቁ መኖሪያ ቤት ያለውን ቢሮውን ለመበርበር ተ ስማምተው ተለያዩ።

ሚኪ ቤቱ ደርሶ ብቻውን ማሰብና አረፍ ለማለት ስለፈለገ ሂዊን መንገድ ላይ አውርዷት ወደ ቤቱ ገሰገሰ......ቤቱ ደርሶ በራፉን ለመክፈት ሲሞክር ግን በራፉ አልተቆለፈም በሰውነቱ ሲታከከው በራፉ ተከፈተ...
ሚኪ የባለፈውን ስህተት ላለመድገም ሽጉጡን አወጣና ቀስሮ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ ወደ ውስጥ ገባ ነገር ግን ፊት ለፊቱ በፍጹም ያልጠበቀውን ነገር ተመለከተ
ሰላም ቀኝ እግሮቿን አነባብራ ሶፋው ላይ ተቀምጣለች....የጭንቀቱን እጁ ላይ ያለውን ሽጉጥ ለመደበቅ ተውተፈተፈ........
"ለመደበቅ አትሞክር" አለችው
"እእእ ሰላሜ" ብሎ ሲጠጋት ቅድም በድንጋጤ ያላየው የአባቱ ፎቶ በሰላም እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ተመለከተው።
ከአይኖቿም እምባ እየፈሰሰ ነው..

ይቀጥላል
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ
@bewketuseyoum19
7.5K viewsBewketu, 19:40
Open / Comment
2022-05-08 22:40:49 በቀልና ፍንጥርጣሪው
ክፍል 37
ፀሃፊ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ
.
.
.
እንደነጋለት ሚኪ ቢሮ ገብቶ ከጥቂት ቀን በፊት ያዘጋጃቸውን ሰነዶች ማስተካከል ያዘ። ልቡ ግን ልትረጋለት አልቻለችም መኩሪያው ያቺን አንድ ፍሬ ልጅ የደፈረበት ሁኔታ ከእናቱ አደፋፈር ጋር ተመሳሳይ ነው ልክ እንደ እናቱ ሁሉ እቺም ልጅ እጆቿ ታስረዋል.. እግሮቿ ወዲያና ወዲህ ተበርግደው ተጠፍንገዋል።... ሚኪ ልጅቷን እያሰበ ውስጡን በረደው።...
"መኩሪያው አብቅቶልሃል...እጅግ በሚያምኑት ሠው መከዳት ምን ያህል እንደሚያም ዛሬ ይገባሀል" አለና ለሮቤል ስልክ ደወለለት...
"ሄሎ ሮቤል....ልጅቷን አገኛችሁዋት.... ?" አለው ሚኪ ስለ ደህንነቷ ለማረጋገጥ
"አዎ ሚኪ ግን እሥካሁን አልቀረብናትም....የመኩሪያው ሠዎች አምጥተው ጉሊት ወርውረዋታል...እናቷ ልጇን ታቅፋ እያለቀሠች ነው። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ስላሉ ፓሊስ ጉዳዩ ላይ ከገባ ብለን ነው እሥካሁን ምንም ያላደረግነው...
"ልጅቷ ተጎድታለች እንዴ...?"
"አዎ በጣም የተጎዳች ትመስላለች ደክማለች"
"እና ሮቤል ምንድነው የምጠብቁት ይዛችሁዋት ሆስፒታል ግቡሃ.....ህይወቷ እያለፈ ሥለምን ፓሊስ ነው የምታወራው"
"እሺ እንዳልክ" አለው ሮቤል
"እባክህ ሮቢ ፍጠኑ..እኔ መኩሪያው ጋር ያለኝን ጉዳይ ጨርሼ እመጣለሁ" ሚኪ ስልኩን ዘጋውና በዝምታ ለጥቂት ጊዜ ለማሰብ ሞከረ።....
ልክ ከጠዋቱ 5 ሰአት ሲል ወረቀቶቹን ይዞ ወደ መኩሪያው ቢሮ አመራ.....ሚኪ አምስት ሠአትን የመረጠው የሁልጊዜ የመኩሪያው ከስራ የመውጫ ሰአት በመሆኑ ነው....ያሰበው ነገር ደግሞ ሊሆንለት የሚችለው መኩሪያው ለመውጣት እየተጣደፈ ባለበት ጊዜ ነው።.....
ሚኪ ቢሮውን አንኳኳ....
"ይግቡ" አለ መኩሪያው....
"ጋሼ ሠላም ነዎት ...እንዴት ነው ለበረራው ተዘጋጁ....?" አለ ሚኪ በቆመበት...
"አዎ ተዘጋጅቻለሁ...እንዲያውም ልወጣ ሥል ነው የመጣኸው..ቤት ሂጄ ትንሽ እረፍት ማድረግ አለብኝ" አለ መኩሪያው ወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ.....
ሚኪ እሥከዛሬ ሲያየው ከሚይናድደው እጥፍ ድርብ አሁን በጣም እየተቃጠለ ነው ነገር ግን ያስበውን ለማሳካት መተወን የውዴታ ግዴታው ነው ..
"ብዙ ጊዜ አልወሥድብዎትም ጋሼ እቺን ወረቀት እንዲፈርሙ ነው.."
"ምንድነው....?" አለ መኩሪያው መነጸሩን ከፍ ዝቅ እያደረገ
"አዲስ ምርቶችን ከሚያቀርብልን ድርጅት ጋር የተዋዋልነው ውል ነው.....እርስዎ ለአንድ ወር ስለሚቆዩ ስራው መጓተት የለበትም ብዬ ነው ሳይሄዱ በፊት ቀድሜ ላስፈርመዎት የመጣሁት"
"አንበሳኮ ነህ የኔ ልጅ...ምነው እንዳንተ አይነቱ ታታሪ ድርጅቴ ውስጥ ሶስት አራት ቢሆንልኝ...ስጠኝ ወረቀቱን ልጄ" አለው መኩሪያው በመደሰት...
ሚኪ ወረቀቱን አቀበለውና መኩሪያው ሳያነብ እንዲፈርም ለአምላኩ ጸሎት ማድረስ ጀመረ...
መኩሪያው ወረቀቶቹን እየገለጠ ያለምንም ጥርጣሬ ይፈርማል..ሚኪ ሳቁ ሊያመልጠው ምንም አልቀረውም......
መኩሪያው ሁሉም ወረቀቶች ላይ ፈርሞ አቀበለው....
"መልካም ጉዞ" አለው ሚኪ ለመውጣት በሩን እየከፈተ....
"አመሰግናለሁ . .ቆይ ልጄ አንዴ" አለው መኩሪያው
ሚኪ ፊቱን መለሰ "ልጄ የውክልና ወረቀት ስላስገባሁ እሥክመጣ ወክለኸኝ ድርጅቱን ትቆ ጣጠርልኛለህ.....ማንኛውንም ነገር ለማከናወን እኔ አላስፈልግህም በራስህ ማድረግ ትችላለህ" አለው መኩሪያው...
"አያስቡ ጋሼ እርሥዎ እንዳዘዙ" ሚኪ ቢሮውን ለቆ ወደ እራሱ ቢሮ ገባና ከውሥጥ ቆለፈው....
ተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተቀምጦ ዝም ብሎ ይስቅ ጀመር ካካካካ ብቻውንም ያወራል።
"አይ መኩሪያው ምን አይነቱ ጅል ነህ በፈጣሪ ድርጅትህን ካለምንም ችግር በቀላሉ በገዛ ጣቶችህ ፈርመህ ሰጥተኸኝ ውክልና ምናምን ሠጠሁህ ትላለህ ካካካካካ ሲጀመር ምን ድርጅት አለህና ወሠድኩብህኮ ካካካካ"
ሚኪ መልሶ ደግሞ ይናደዳል...ወደ ነብርነት ይቀየራል
" መኩሪያው እንዲያውም እንዳንተ ጨካኝ ባለመሆኔ አመስግነኝ...አንገትህን አላረድኩትም ወይም ቤተሠብህን አልጎዳሁትም" አለ ሚኪ ጠረጴዛውን በእጆቹ ተደግፎ እራሱን በመስታወቱ ትኩር ብሎ እያየ....
"እቺ ቀን ልጅነቴ ነች..እቺን ቀን ለማግኘት ልጅነቴን አጥቻለሁ....ዛሬ የመደሠቻዬ ቀን ነው ለምን አዝናለሁ።...አባዬ ንብረትህን አስመልሻለሁ አሁን ነፍስህ በሰላም ታርፋለች በልጅህም ትኮራበታህ። ጥቂት ቀን ብቻ ጠብቅ መኩሪያው በህዝብ ፊት ተዋርዶና ተንቆ ዘብጥያ ይወርዳል" አለ ሚኪ ድምጹን ዝቅ አድርጎ ከዋሌት ኪሱ ያወጣውን የአባቱን ጉርድ ፎቶ አዘቅዝቆ እያየ።
ሚኪ ቢሮውን ቆለፈና ተጠቂዋን ልጅ ለማየት እነ ሮቤል ያሉበት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሄደ።
እንደደረሰ ልጅቷ በቂ ህክምና እየተደረገላት ነበር... ሮቤል፤ሂዊ፤የልጅቷ እናት እንዲሁም የሠፈሩ ሰዎች የድንገተኛ ክፍሉን በራፍ ከበው ቆመዋል።
ሚኪ እነ ሮቤል ጋር በማምራት "ልጅቷ እንዴት ናት.....?" አላቸው የማንሾካሾክ ያህል
"ደህና ትሆናለች ብዬ አሥባለሁ" አለው ሮቤል...
"ምን ማለት ነው ይሄ ለህይወቷ ያሰጋታል እንዴ....?" ሚኪ በድጋሜ ጠየቀ...
"አናውቅም ዶክተሩ መጥቶ ምንም አላላንም" ሂዊ መለሰችለት
"ምንድነው የያዝከው ወረቀት" አለው ሮቤል...
"ሂዊ.. ሮቢ"...አደረኩት አላቸው ሚኪ ገለጥ አድርጎ እያሳያቸው...
"በቃ ቤት ስንደርስ በዝርዝር እናወራበታለን።" አለው ሮቤል..
በመሀል ዶክተሩ ከድንገተኛ ክፍሉ ወጣ....ወሬያቸውን ትተው ወደ ዶክተሩ አመሩ.....
እናቷ "ልጄ እንዴት ናት ዶክተር..?" አሉት እያለቀሱ...
"አይዞዎት ደህና ናት....ግን በወንድ ጥቃት ደርሶባታል.."
"ምን ማለትህን ዶክተር...እንደው ምና አድርጋቸው የኔን ሚስኪን ልጅ ይደበድቧታል" አሉት
"ማዘር አዝናለሁ ይሄን ስልዎት ግን ማወቅ አለበዎት ልጅዎት ተደፍራለች" አላቸው
"እግዚኦ...እግዚኦ ልጄን አንድ አይኔን ጉድ ሠሩኝ...ልጄን ቀሙኝ" እናቷ ሆስፒታሉን በጩኸትና በእዬዬ አደበላለቁት....
"ማዘር ይረጋጉ አሁን ላይ በህይወት አለች..
መድሀኒቶች ሠጥተናታል ከግማሽ ሠአት በሁዋላ ትነቃለች.....ስለዚህ እንዲህ አይሁኑ" አላቸው ዶክተሩ
ሚኪና ሂዊ እናትዬዋን ደግፈው እንዲረጋጉ ጥረት አደረጉ...
ሮቤል ግን ዶክተሩን ተከተለው...
"ዶክተር አንዴ ቆይ" አለው ሮቤል
"አቤት..."
"ልጅቷን እናቷ ይዘው ሲያለቅሱ አይተን እኛ ነን ከመንገድ ይዘናት የመጣነው..አሥፈላጊውን ወጪ እኛ እንሸፍናለን" አለው ሮቤል
"ተባረኩ ሠውን መርዳት የሚችሉት ጥሩ ልብ ያላቸው ብቻ ናቸው...." ብሎ መለሰለት ሽበት የወረረው ዶክተር
"ዶክተር ያው ቤተሠብ ስላልሆን ልጅቷን ማየት አይፈቀድም ይሆናል ግን ሁኔታዋን አይተን አሥፈላጊውን ነገር እንድናሟላላት ገብተን ብናያት ብዬ አሥባለሁ...ሥለዚህ ልትፈቅድልን ትችላለህ...?"
"ችግር የለውም እተባበራችሁዋለሁ...ከአንድ ሠአት በሁዋላ ልታዩዋት ትችላላችሁ..እንዲያውም እያሰብኩ ያለሁት ምን መሠለህ አካላዊ ቁሥሏ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይድናል ግን ሥነ ልቦናዋ ሊቃወሥ ይችላል ብዙ ጊዜ እንደሷ አይነት ተጠቂዎች እራሳቸውን በቶሎ ማግኘት አይችሉም ስለዚህ ከዚህ ስትወጣ የስነ ልቦና ሀኪም ጋር ብታሳዩዋት ጥሩ ነው.." ዶክተሩ የመፍትሄ ሀሳብ ያለውንም እግረ መንገዱን አክሎ ነገረው...
"እሺ ዶክተር እናመሰግናለን"...
ልጅቷ ከግማሽ ሠአት በሁዋላ ነቃች...እነ ሚኪም በተፈቀደላቸው መሠረት ከአንድ ሠአት በሁዋላ ሊያዩዋት ገቡ.......
5.9K viewsAbela, 19:40
Open / Comment
2022-05-08 22:36:39 ​​"ይሄ አረመኔ እዩዋት ትንሽ ልጅኮ ናት ምን ሊያደርጋት ነው" አለ ሚኪ ጅማቶቹ ግንባሩ ላይ መስመር ሠርተው....
"ስሚኝ አንቺ ልጅ የምትሠሪውን አቁሚና ሻወር ቤት ገብተሽ ገላሽን ታጠቢ" አላት መኩሪያው እያቅበጠበጠው...
"እሺ ጌታዬ የጀመርኩትን ልጨርስና እተጣጠባለሁ" አለች ልጅቷ
"ሂጂ ታጠቢ ካልኩ መታጠብ አለብሽ...እዚህ ቤት ውሥጥ እሥካለሽ ንግግሬን መስማት አለብሽ መደጋገም የለብኝም" መኩሪያው ጮኸባት...ልጅቷም በድንጋጤ እየሮጠች ሻወር ቤቱ ውስጥ ገባች....
ጥቂት ደቂቃ ወስዶባት ተለቃልቃ እንደወጣች...መኩሪያው እጇን እየጎተተ ወደ መኝታ ቤቱ ወሰዳት።
"እንዴ ምንድ ነው ነገሩ...?" አለች ግራ የተጋባችው ህጻን
"ሥራ ልትሠሪ ነው....አሁን ፎጣውን ከገላሽ ላይ አውልቂው" አላት
"እንዴ ለምን ይሄን ልሠራ አይደለም የተቀጠርኩት" በአቅሟ ለመወጣጠር ሞከረች
መኩሪያው ከደረት ኪሱ ብዛት ያላቸው የመቶ ብር ኖቶችን አውጥቶ ፊቷ ላይ በተነው....
"አየሽ ሳታስችገሪኝ እራስሽን ከሠጠሽኝ ይሄ ሁሉ ገንዘብ ያንቺ ነው...እምቢ ብትይም ምንም እንደማትፈጥሪ አውቀሽ በሠላም አብረን እንደሠት...ካንቺ በፊት የነበሩትም ሴቶች አልቀረላቸውም እጅ ሠጥተዋል" አላት
"አልፈልግም ለገንዘብህ ብዬ እራሴን አላረክስም.....በችግር ተቆራምዳ ያሣደገችኝን እናቴን አላዋርዳትም ልቀቀኝ ልሂድበት" አለችና ከአልጋው ላይ ወረደች..
"አይ እንግዲህ ሠይጣኔን አታምጭው...አበዛሽው" አለና አልጋው ላይ ገፍትሮ ጣላት..
ሥትንፈራገጥ በጥፊ መታትና ሽጉጥና ጩቤውን አውጥቶ አስፈራራት....
"አላርፍ ካልሽ አሥክሬንሽ ነው ከዚህ የሚወጣው"..
"እባክህ እሡን ነገር ወደዛ በለው...እባክህ እንዳትገለኝ" እያለቀሠች ለመነችው...
መኩሪያው ደጋግሞ በጥፊ መታት ልጅቷም ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት ተሸነፈች።....
"ሮቢ ምንድነው የምንጠብቀው ሊደፍራትኮ ነው ሄደን እናትርፋት እንጂ" አለ ሚኪ እንባው ኩልል እያለ...
"ቆይ ተረጋጋ ሚኪ" አለው ሮቤል
"እንዴት ነው የምረጋጋው ለቅሶዋና የምታሰማው ጣር አያማችሁም...? እናንተ ካልረዳችሁኝም ብቻዬን እሄዳለሁ" አለ ሚኪ ሽጉጡን አቀባብሎ በሽንጡ እየሻጠ...
ሮቤልና ሂዊ እንዳይሄድ ለሁለት ጥፍንግ አድርገው ያዙት...
"ልቀቁኝ ልሂድበት....ገናኮ አንድ ፍሬ ልጅ ናት"
"ሚኪ እረጋ በል ቦታው እሩቅ ነው..አሁን ብንሄድም ይረፍድብናል..እሥክንደርሥ መኩሪያው ሥራውን ይጨርሳል...ስለዚህ ለመሞት ካልሆነ መሄድ የለብንም" አለው ሮቤል..
"ሚኪ ለዚህች ልጅ አልደረሥንላትም ለሚቀጥሉትሥ ልትደርሥላቸው አትፈልግም...? መኩሪያውን እሥር ቤት እንዲበሰብስ የሚያደርግልንን መረጃ ይሄው ኮምፒውተሩ እየቀዳው ነው...መኩሪያው አልቆለታል...እቺ ልጅ ግፍ የተፈጸመባት የመጨረሻዋ ትሆናለች...ከሄድን ግን ሁሉንም ነገር ታበላሸዋለህ እዛ ግቢ ብንገባ ምን የሚፈጠር ይመሥለሀል ሁላችንንም ያስገድለናል....ቅጂውም ዋጋ ያጣል" አለችው ሂዊ የሮቤልን ሀሳብ በመደገፍ...
"ግንኮ...." አለ ሚኪ
"ምንም ግን የለም ተቀመጥ" አሉና ወንበር ላይ አሥቀመጡት
ሚኪም ትንሽ ተረጋጋ..ለመሄድ ያሰበውንም ተወው "እሺ ሀሳቤን ቀይሬያለሁ...እናንተ እንዳላችሁ" ሽጉጡን ለሮቤል አሥረከበው...
ግን ከዚህ በሁዋላ በኮምፒውተሩ ስክሪን ላይ የሚታየውን የመኩሪያውን እንስሳነትና የልጅቷን ስቃይ የሚከታተልበት አቅም ስላልነበረው "ውጪ ልሁን" ብሏቸው በሩን ከፍቶ ወጣ...
ሮቤል ሂዊን እንድትከተለው በምልክት ነገራት.....
ሮቤል የድምጽ መቅጃውም ሆነ ካሜራዎቹ በትክክል ስራቸውን እየሠሩ መሆኑን ካረጋገጠ በሁዋላ ከመቀመጫው ተነስቶ ሚኪና ሂዊን አያቸው......
ሁለቱም በረዳው ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው ፊት ለፊታቸውን እያዩ ፍዝዝ ብለዋል....ምንም አይነት ንግግር በመካከላቸው የለም ከአይናቸው ግን ንጹህ እንባ እየፈለቀ በጉንጫቸው ላይ ይፈሳል....አባይ ኢትዮጵያን አቋርጦ ግብጽና ሱዳንን እንደሚያካልልው የእነሡም እንባ ከገደብ አልፎ ደረታቸውን አበስብሶታል....
ሮቤል በሩን መለስ አደረገና ተቀላቀላቸው.......

ይቀጥላል
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ
@bewketuseyoum19
5.4K viewsBewketu, 19:36
Open / Comment
2022-03-02 13:07:33
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.3K viewsAbela, edited  10:07
Open / Comment
2022-03-02 11:10:06
~~~~~~~ //~~~~~~~~~~~~~

"ሰው"ነት
.
.
የቱርኩ ሶላቶ፤
ክብሬን ተመኝቶ፤
ሊበላኝ ጎምጅቶ ሊገዛኝ ሲቃጣው፤
አርፎ የተኛውን፤
የአንበሳ መንጋ ነብሩን አስቆጣው፡፡

ያ ነጩ ወንድሜ፤
ዘረኝነት አንቆት "ሰው"ነት ሲያማታው፣
ሰው መሆን የገባው፤
"እምዬ"ያሉት "ሰው"
ዋጀኝ እንደገና እግረ ሙቄን ፈታው።
"አሉላ" ያሉት "ሰው"
ያ "ባልቻ" ያሉት "ሰው"
በጦር በጎራዴ እያንገረገበ መገፋቴን 'ረታው፡፡

ክብር ሀገር ላቆዩልን ሁሉ ይሁን !!!
.............. .................

ዐብይ ( @abiye12 )

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
508 viewsAbela, 08:10
Open / Comment