Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 129.63K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 130

2022-05-15 22:40:19 በቀልና ፍንጥርጣሪው
ክፍል 41
የመጨረሻ ክፍል
ፀሃፊ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ
.
.
.
ሚኪ መኩሪያውን ሲያየው አየር ላይ ተንሳፎ ተስፈነጠረና አነቀው....
"አንተንማ አልገልህም ካጋሮችህ ጋር እሥር ቤት ፍርፋሪ እንድትበላ ነው የማረግህ" አለና በአንድ እጁ እንደያዘው ስልኩን አወጣ.....
"ተረጋጋ ጩጬው የምታደርገው ነገር ይቆጭሃል" መኩሪያው በሙሉ መኩራራት ነበር የሚናገረው....
"አሁንኮ አልቆልሃል...የምታምንባቸው ሠዎች ሁሉ ወህኒ ወርደዋል....ቤተሠቤን ላደረከው ነገር እድሜ ልክህን ትከፍላለህ"
"ጩጬው በህይወት እሥካለህ ድረስ አለቀ የሚባል ነገር የለም...እንዲያውም ካልክ ፊልማችን ገና ጀመረ....ስማ ወጣቱ እናትህ እኔ ጋር ናት" አለው መኩሪያው
ሚኪ ሠውነቱ ፍም መሰለ....ጡንቻዎቹ ተወጣጠሩ....የንዴቱ ልክ ጥርሱን እስከማንገጫገጭ ደረሰ
"አንተ ውሻ.....ምናባህ ነው ያልከው....? እናቴ የት ነች..? ሚኪ ከግድግዳ ጋር ገፍትሮ አጋጨው..
መኩሪያው በርሊን ሆኖ ሳለ ነው እየተካሄደ ያለውን ነገር ጆሮ ጠቢው ደውሎ የነገረው......ባለስልጣኖቹ እንደታሰሩና የሆቴሎቹ ስሞች አባተ በሚል መጠሪያ እንደተቀየሩ ሲሰማ ነው የድሮው ትዝታው ብልጭ ያለበት......የሚኪን ማንነት ከተገነዘበ በሁዋላ ወዲያው ከጀርመን ተመለሰና ከህግ አካላት እራሱን እየሸሸገ ወደ ጅማ አመራ....ከዛም እናቱን ጠልፎ በሚኪ ደካማ ጎን መጣበት...
"አንተ ልጅ ተረጋጋ እንጂ....እኔን ብትገለኝ ወይም ለፓሊስ ብታሥረክበኝ የእናትህን እሥትንፋስ ለማቋረጥ ሠከንዶችን የማይጠብቅ ታማኝ ሠው አለኝ" አለው መኩሪያው እየሳቀና ከወደቀበት እየተነሳ....
ሚኪ እራሱን አረጋጋ... መኩሪያው ፊት ላይ ለማረፍ የተወጣጠሩት ጡንቻዎቹም ረገብ አሉ.....ቆሞ ግንባሩን ማሸት ጀመረ...
"ሥንት የለፋሁለትን ሀብት በቀላሉ ሠጥቼህ እዛው የምቀር መስሎህ ነበር....ካካካ" መኩሪያው በድጋሜ ሳቀበት
"አንተ ቆሻሻ ሽማግሌ ንብረቱ የአባቴ ነው..." አለው ሚኪ
"ነበር ግን አሁን የኔ ነው....ይልቅ እናትህን ለማትረፍ የምልህን አድርግ.......ሙሉ ሀብቱን ትመልስልኛለህ........ ቦታውን ቴክስት አደርግልሃለሁ..ከአንድ ሰአት በሁዋላ ብቻህን መጥተህ እናትህን አድናት እሷ ብቻ ናት የቀረችህ ቤተሰብ" ብሎት ፊቱን መልሶ ሸፋፈነና ጎምለል ጎምለል እያለ ቢሮውን ለቆለት ወጣ...

ሰላምና ሂዊ ማራማዊትን በመኪና እያንሸራሸሯት ነው..... አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፉም ነው.....ህጻን ማራማዊት አይታ የማታውቀውን አለም አንድ ባንድ በግርምትና በመደነቅ ታያለች....በጣም እንደተደሠተች በየደቂቃው የምትሥቀው ሳቋ ይናገራል።.......
የሂዊ ስልክ በድንገት ጮኸ.......በቶሎ አነሳችው...
"ሄሎ ሚኪ"
"ሂዊ መኩሪያው እናቴን አግቷታል.....ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም...አሁን እንድመጣ በነገረኝ መሠረት ወደ ቦታው እየሄድኩ ነው።..."
"ምን ..? ቦታው የት ነው.....?" ሂዊ አመዷ ቡን አለ...
"ወደ አዳማ የሚሄደውን መሥመር ይዘህ ሥትመጣ በጅምር ላይ የሚገኝ ፋብሪካ አለ....እዛ እንድገኝ ነው የነገረኝ....ቻው በቃ መፍጠን አለብኝ" ሚኪ ስልኩን ጆሯዋ ላይ ዘጋባት...
"ምንድነው ሂዊ.....ምን ተፈጥሮ ነው......?" ሠላም ጠየቀቻት
"አባትሽ የሚኪን እናት ይዟታል...እናም ሚኪ ወደ ቦታው እየሄደ ነው"
ሠላም በድንጋጤ መኪናውን ሲጢጥ አድርጋ አቆመችው
"ምን ጉድ ነው ሂዊ...መኩሪያውኮ መመለሻው ቀን አልደረሠም..." አለች ሠላም
"አዎ እኔም ምንም አልገባኝም" ሂዊ ተናገረች
"የት ነው ቦታው....?"
"ወደ አዳማ መውጫው ነው ያለኝ"
ሠላም ወደዛው መኪናዋን በፍጥነት ነዳችው.....
ሂዊ ለሮቤል ደውላ አሳወቀችው.....
"በሰአትህ መጣህ ጩጬው....እያት እናትህን" አለና የተሸፈነውን ፊቷን ገለጠው. ..
"ልጄ.......እዮቤ" አለች እናቱ ወ/ሮ የሺወርቅ እየተንሰፈሰፈች...
"መኩሪያው ይበቃሃል እናቴን ልቀቃት....ይብቃህ" አለው ጮኽ ብሎ
"ባለህበት ተረጋግተህ ቁም ጩጬው...አጉል ጀግና ለመሆን አትሞክር አለበለዚያ የእናትህን አናቷን ነው የማፈራርሠው" አለው ሽጉጡን ወ/ሮ የሽወርቅ ጭንቅላት ላይ እየደገነ
"ተው እንዳታደርገው መኩሪያው" አለው ሚኪ
"ሂድና ፈትሽው..." መኩሪያው አብሮት ላለው ሠው ትእዛዝ ቢጤ ሠጠው...
ሠውዬው አብጠርጥሮ ፈተሸው "አለቃ ምንም አልያዘም" በማለት አሣወቀው....
"እሺ ልጅ እዮብ ያልኩህን ይዘህ መጥተሃል....?"
"ይሄው ግን እናቴን ሳትለቃት አታገኛትም"
ሚኪ የያዘውን ወረቀት ከጃኬቱ ውስጥ አወጣና ወደ ላይ ከፍ አርጎ አሳየው......
"ምንም አማራጭ የለህም....ለሰውዬው ስጠው የያዝከውን" አለ መኩሪያው....
ምንም ማድረግ ያልቻለው ሚኪ ፋይሉን ለሠውዬው አሥረከበ....
"የፈለከውን አግኝተሀል....እሺ አሁን ልቀቃት".....
መኩሪያው ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ልክ መሆኑን ካጤነ በሁዋላ ሚኪ ላይ ሽጉጡን አነጣጠረበት...
"እባክህ ተው መኩሪያው ልጄን አትግደለው....ያለኝ እሡ ብቻ ነው.." ወ/ሮ የሺወርቅ እያለቀሠች ለመነችው...
"አይሆንም ይሄ ቤተሠብ እሥካለ ድረሥ ሠላሜን አላገኝም......እንደጀመርኩት እጨርሰዋለሁ....ልጅ እዮብ ገና ድሮ ነበር አንተን መግደል የነበረብኝ" አለና የሽጉጡን መጠበቂያ እንደከፈተው....
"መኩሪያው ተው እንዳታደርገው" ሠላም እየለፈለፈችና እየጮኸች ሚኪን በሠውነቷ ከልላ ጥልቅ አለች....
"ሠላሜ እዚህ ምን ትሠሪያለሽ...ዘወር በይ አሁን ይሄ ባለጌ አምኜ ቤቴ ባስገባውና አንድ ማድ ባቀርበው እጄን ነከሰኝ..ሙሉ ሀብቴን በራሡ ሥም አዞረው" አላት መኩሪያው ሽጉጡን ሳያወርድ.....
"መኩሪያው የሠራሃውን ሁሉ ሀጢያት አውቂያለሁ...አንተ በሰው አምሳል የተሠራህ ዲያቢሎስ ነህ.....ትንሽ እንኳን እንጥፍጣፊ እዝነት የሌለህ አውሬ ነህ....አሁን አንተ ለሠራኸው ሁሉ ክፋት የምትከፍልበት ጊዜ ነው እንጂ ሌላ ወንጀል የምትሠራበት አይደለም። ካንተ በመፈጠሬ እኔም እርኩስ እንደሆንኩ ነው የሚሠማኝ" ሠላም ንዴቷ አየለ...
"ልጄ እኔ ምንም አልሠራሁም...ይሄ ውሻ ነው አይደል መጥፎ ሃሳብ አእምሮሽ ውስጥ የከተተብሽ ልጄ ዘወር በይልኝ...እደፋሃለሁ አንተ ጥላ ቢስ".....
"ልጄ አትበለኝ ልጅህን ገለህ ቀብረሃታል...እነሡን ከመግደልህ በፊት እኔን አሥቀድመኝ....በላ ይሄው ተኩስ" አላችው ሠላም እጇን እየዘረጋች....
"አንድ ቀን እንኳን በምታደርገው ነገር ጸጸት ተሰምቶህ አያውቅም....? አቶ መኩሪያው" የሂዊ ድምጽ ነበር የተሠማው ከነልጇ እነ ሠላምን እየተቀላቀለቻቸው....
መኩሪያው ኩምሽሽ አለ....በፊት መንገድ ላይ የጣላትን ሂዊን ሲያያት ተረበሸ።......የእሷ እዚህ መገኘት ግራ አጋባው.....
"አንቺ ደግሞ እዚህ እንዴት መጣሽ....እሥከዛሬሥ የት ነበርሽ.....?" አለ መኩሪያው በድንጋጤ ልጁ ሠላም እየሠማችው መሆኑን በመዘንጋት...
"ጥሩ የማስታወሥ ችሎታ አለህ.....ከነዚያ ሁሉ ሴቶች መሀል እኔን ማስታወስ በመቻልህ ተገርሚያለሁ.....አየሃት እቺ የአንተ ዘር ፍሬ ናት....የአንተ ደም ባትሆን ከኔ በላይ ደሥተኛ አይኖርም ነበር ግን ደግሞ እሷን በማግኘቴ እሥካሁን ልኖር ችያለሁ" አለችው ሂዊ በግራ እጇ የያዘቻትን ማራማዊትን ፈገግ ብላ እያየቻት....
መኩሪያው ትልቅ መአት ወረደበት.....የራስ ቅሉ የራሱ እንዳልሆነ ሁሉ ከበደው.....
አፍታም ሳይቆይ
1.0K viewsAbela, 19:40
Open / Comment
2022-05-15 22:30:39 ​​አሁን ስሜቴ ተደበላልቆብኛል ግን አንድ ነገር አውቃለሁ እናንተ ለኔም ሆነ ለሚ ስኪኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግኖቻችን ናችሁ። በሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ትኖራላችሁ እቺን ሀገር ሊያፈራርሷት ከተነሡ የቀን ጅቦች ታድጋችሁዋታል....
ኢትዮጵያችን ሀይልና ስልጣን ያላቸው ሠዎች ችግረኛውንና ሚስኪኑን ህዝብ እንደፈለጉ የሚገሉበት፤ የሚያሠቃዪበትና የሚዘውሩበት ሀገር መሆን የለባትም ......
ሁሉም ወንጀለ ኛ በፍትህ ሊዳኝ ይገባል.....አዎ መኩሪያው ምንም እንኳን አባቴ ቢሆንም እሥር ቤት እንዲበሠብሥ እፈልጋለሁ....ለእያንዳንዱ አረመኔያዊ ድርጊቱ ቅጣት እንዲያገኝ ከኔ በላይ የሚፈልግ የለም....
ሚኪ፤ሂዊና ሮቤል አይኔን ስለገለጻችሁልኝ ሳመሠግናችሁ እኖራለሁ..." ሠላም ንግግሯን ጨርሳ በረዥሙ ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ ብላ ተነፈሰች....
ሚኪ ሮቤልንና ሂዊን በየተራ አቀፋቸውና ተመልሶ ፍቅሩን ወገቧን ያዝ አደረጋና ባለበት ቆመ።....
ሂዊ እጅግ ደሥተኛ ከመሆኗ የተነሳ ስሜታዊ ሆናለች....ሮቤል ላይ ዘላ ተጠመጠመችበትና ጉንጩን ሳመችው....
ሚኪና ሠላም ሁኔታቸውን አዩና ተጠቃቅሠው ፈገግ አሉ።...

በአንድ ሳምንት ውስጥ ብዙ ነገር ተካሂዷል ወንጀለኞቹ ባለሥልጣኖች ካሉበት እየተለቀሙ በቁጥጥር ሥር ውለዋል....ሁለቱ የወንጀል መናሀሪያ የሆኑት ድርጅቶች በመንግሥት እገዳ ስር ሲሆኑ ከወንጀል ነጻ የሆኑትን ሆቴሎች ሚኪ በይፋ የራሱ አድርጓቸዋል በየክፍለ ሀገሩ ያሉትም የሆቴሎቹ ስሞች በአባቱ ስም እንዲሠየሙ አድርጓል ይሄን ስላችሁ ግን ሚኪ ራስ ወዳድ ሆኖ ድርጅቱን ለራሱ አደረገው እያልኳችሁ አይደለም...
የድርጅቱን የአክስዩን ድርሻ ለአራት ከፍሎታል 40%ቱን የአባቱን ድርሻ እራሱ ሲወስድ 30%ቱን ለሠላም እንዲሁም ቀሪውን 30% ደግሞ ለሂዊና ለሮቤል ሠጥቷቸዋል...
እለተ እሮብ ከጠዋቱ 3:30 ገደማ ሚኪ የቢሮ ስራውን እየከወነ ሳለ ካለምንም መንኳኳት ድንገት የቢሮው በራፍ ተከፈተ....
ሚኪ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ሲመለከት በስካርፕ፤ በመነጸርና በኮፍያ ተሸፋፍኖ ማንነቱ የማይለይ ሠው እየቀረበው ነው.....
ሚኪ ሁኔታው ስላላማረው ጥበቃዎች ለመጥራት እጁን ወደ ስልኩ ሲሰድ...
"እጅህን ብትሠበሥበው ይሻልሀል" አለው የተከናነበው ሠውዬ....
ወዲያውም ኮፍያውንና ስካርፑን በማወላለቅ ለእይታ ተጋለጠለት....
የሚኪ አይኖችና በፓሊስ እየተፈለገ ያለው የመኩሪያው አይኖች ፊት ለፊት ተጋጩ።

ይቀጥላል
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ
@bewketuseyoum19
1.3K viewsBewketu, 19:30
Open / Comment
2022-05-15 22:30:28 በቀልና ፍንጥርጣሪው
ክፍል 40
ፀሃፊ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ
.
.
.
ጀንበር ልትጠልቅ ብታዘቀዝቅም ሚኪ ከአልጋው አልወረደም።....
ብርድ ልብሱን ላመል ያህል ሠውነቱ ላይ ጣል አድርጎ ውስኪውን እየቀዳ ይጋታል.....እራሱን መጠጥ ውስጥ ሸሽጓል ከእውነታው ያመልጥ ይመስል....ለሱ ቀኑም ሌቱም አንድ ሁነውበታል።....ከአቅሙ በላይ ይጠጣል እዚያው እንቅልፍ ይደፋዋል።.....
ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ በሩ ተቆረቆረ.....
ሚኪ ድምጹን ቢሠማውም እንዳልሠማ ሆኖ መጠጣቱን ቀጠለ....
በር መቆርቆሩ ቀጥሏል ከውስጥ መልስ የሚያገኙበት ጊዜው ግን ራቀ....
"ሚኪ...ሚኪ እባክህ ክፈትልን....እኛ ነን" ሮቤል ድምጹን ከፍ አድርጎ ተናገረ...
ሚኪ ካላናገራቸው እንደማይሄዱና ነጻነት እንደማይሠጡት ስለገባው የውስኪ ጠርሙሱን በቀኝ እጁ ይዞ እየተንገዳገደ ከመኝታ ክፍሉ ወጣ......
በሩን ከፈተላቸውና "ለምድነው እናንተ ሠዎች የማትተውኝ...ብቻዬን ልሁንበት...በነጻነት ልጠጣበት እንጂ" አላቸው እየተኮላተፈና ሚዛኑን መጠበቅ አቅቶት ከግራ ወደ ቀኝ እየተወዛወዘ....
ሮቤልና ሂዊ ምንም ሳይሉት ወደ ጎን ገለል በማለት ቦታውን ክፍት አደረጉት......
በመጠጥ የደፈረሱት የሚኪ አይኖች ፈጠጡ....
የሞጨሞጩ አይኖቹን በግራ እጁ አሻቸው....
ፊት ለፊቱ ሰላም ድቅን አለችበት...ፈገግታዋ ደመና በሌለበትና ድቅድቅ ጨለማ በወረሰው ሠማይ ላይ እንደምትነግሥ እንደጨረቃ አንጸባረቀበት....
ሊያምን አልቻለም ምክንያቱም በየቀኑ ትመሰልበታለች....አብራው ትሆናለች ግን ሊነካት አይችልም ነበር...ዛሬም እንደዛው አእምሮው የሚፈጥረው ምስል መሠለው....
የአይን ቆቦቹን ከደነና መልሶ ገለጣቸው....አሁንም ከቦታዋ አልተንቀሳቀሰችም..ፈገግታዋም ከቅድሙ አልተዛነፈም..
"ሮቢ እኔ ሚታየኝ ይታያችሁዋል..?" አለ ሚኪ
"እእእ አንተ ሰካራም ምን ታየህ...?" አለችው ሂዊ እየሳቀች
"ሠላሜ ቁማለች ፊት ለፊቴ..."
ሃሃሃሃሃ...ክክክ ሁሉም አንድ ላይ ሳቁበት።....
ሠላም ከዚህ በላይ ልትጠብቅ አልቻለችም ሁለት እርምጃ ተራመደችና መጠጡን ከእጁ ላይ ተቀበለችው "አዎ የኔ ጌታ የእውነት መጥቼልሃለሁ...ይሄው ልትነካኝ ትችላለህ" ሠላም እጁን ፊቷ ላይ አንሸራሸረችው...
ሚኪ ከናፍርቶቹ ተፈለቀቁ...ነጫጭ ክራንቻ ጥርሶቹም ለእይታ ተጋለጡ።
"የኔ ጌታ እባክህ ይቅር በለኝ....በድዬሃለሁ ያለስምህ ስም ሰጥቼሃለሁ ይቅር በለኝ" ሠላም እጁን ይዛ እያለቀሠች ለመነችው..
ሚኪ ሳብ አደረገና ደረቱ ላይ ለጠፋት..
"ሠላሜ ምን አጥፍተሽ ይቅርታ ትጠይቂኛለሽ...ይልቅ እኔ ነኝ የገፋሁሽ ብዙ ዋሽቼሻለሁ ብዙ ነገር ደብቄሻለሁ" አላት እሡም በተራው እያለቀሰ....
"ሁሉንም ነገር አውቂያለሁ ሚኪዬ....የግድ መደበቅ ነበረብህ ምንም ጥፋተኝነት አይሠማህ"
"ሁሉም ነገር ሲገባሽ ወደ እኔ እንደምትመለሺ አውቅ ነበር....ያንን ቀን ስጠብቅ ነበር...እኔኮ ያላንቺ ምንም ነኝ" አላት ይበልጥ ጭምቅ አርጎ እያቀፋት....
ሂዊና ሮቤል ሁለቱን ፍቅረኛሞች እያዩ ውስጣቸው ተነክቷል።
"መተቃቀፉን ተቃቀፉ ግን የምን መላቀስ ነው....ዛሬ መልሰን አንድ ሆነናል....እዩ ሁላችንም አብረን ነን ስለዚህ ልንደሠት ነው የሚገባው" አላቸው ሮቤል....
ሂዊና ሚኪም ተላቀቁ....
"የኔ ጌታ ተጎሳቅለህብኛልኮ....ጸጉርህም ተንጨባሯል...አንተን ሳጸዳ መዋሌ ነው" ሰላም ሳቅ አለችና ደግፋው ሸዋር ቤት አስገባችው....
የለበሰውን ልብስ አወላልቃ መለ መላውን አሥቀረችውና በአናቱ ውሃውን ለቀቀችበት.......ሿ ሿ እያለ የሚወርደው ውሃ እሥኪለምደው ሚኪን አንቀጠቀጠው ....እጅና እግሩን አጣጥፎ እንደ ህጻን ልጅ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ....
ሠላም ሳቋ መጣባት "የኔ ሠካራም ቀዘቀዘህ..?" አለችው ቁልቁል እያየችው...
"አዎ ሠላሜ" አላት ጥርሱን እያፋጨ
"ትለምደዋለህ..ቅዝቃዜው ሥካርህን ያባራዋል" አለችውና ሳሙና አነሳች.....ከጸጉሩ ጀምራ እሥከ እግር ጥፍሩ ድረስ በአረፋው አዳረሰችው.....
እጇ ላይ ባለው ሣሙና ሠውነቱን ደጋግማ ከፈተገችው በሁዋላ ንጹህ መሆኑን ስታረጋግጥ መልሳ ቀለል ባለ ውሃ አለቀለቀችው.....
ጸጉሩን አስተካክላ አበጠረችና ሠውነቱን አደራርቃ በፎጣ ጠቀለለችው....
ደግፋው ሻወሩን ለቃ ስትወጣ ሮቤል ሶፋው ላይ ተቀምጦ ቲቪ እያየ ነው....ካለምንም ተቀናቃኝ ሪሞቱን በእጁ ይዞ ያሻውን እየቀያየረ ያያል.....ሂዊ ደግሞ የተመሰቃቀለውን ቤት ለማስተካከል ደፋ ቀና ትላለች..
ሠላም ሚኪን መኝታ ክፍሉ ወስዳው አስተኛችው.."የኔ ፍቅር አይንህን ጨፍነህ ለማረፍ ሞክር...እኔ ሂዊን በሥራ ላግዛት" አለችውና ልትወጣ ስትል እጇን ያዛት" ሰላሜ አትሂጅብኝ...አብረሽኝ ሁኚ" አላት እዛው ብርድ ልብሱን እንደለበሠ
"የትም አልሄድብህምኮ ስካሩ ሙሉ በሙሉ እንዲለቅህ ቢያንሥ ለግማሽ ሠአት መተኛት ስላለብህ ነው" ሠላም ግንባሩን ሳመችውና ወደ ሳሎን ተመለሰች....
ቤት ማጸዳዳቱ ላይ ለመሳተፍ ብትሞክርም ሂዊ አልቀመስ አለቻት....."እኔ እበቃለሁ" በማለት እንዳትሠራ ከለከለቻት...
ሠላምም ኪችን በመግባት ለአራት ሰው የሚበቃ ምግብ አዘጋጀች።..
ከአንድ ሰአት በሁዋላ ቤቱ ወደ ቀድሞው ተመልሶ ምግቡም ጠረጴዛው ላይ ተሰናድቶ ሚኪን ቀሠቀሡት......
እንቅልፍ ያልጠገቡ አይኖቹን እያጨናቦሰ ማእዱ ላይ ከሠላም ጎን ቀረበ።.....
ተመግበው ካጠናቀቁ በሁዋላ የተፈላውን ቡና እየጠጡ "ሠዎች ትልቅ ሠርፕራይዝ አለኝ" አላቸው ሮቤል....
ሁሉም ሮቤልን በአይናቸው የመውጋት ያህል ተመለከቱት..
"እረ እንደዚህ አታፍጡብኝ" ሮቤል ከተቀመጠበት ተነሳና ደረቅ ወንበሩ ላይ ያስቀመጣትን ትንሽዬ ቦርሳውን ከፈተ.....ሁለት ፋይሎችን መዞ አወጣና ቅድሚያ አንደኛውን ሠጣቸው....
"እዩት የመኩሪያው ሁለቱ ድርጅቶች በህገወጥ መንገድ ጊዜ ያለፈበት መድሀኒቶችንና ምግቦችን ከሚያስገቡለት ህገ ወጥ ነጋዴዎች ጋር የተፈራረመበት ነው........"
"omg አደረከው ሮቤል....አገኘኸው....?" ሚኪ አንዴ ፋይሉን አንዴ ሮቤልን ይመለከታል...
"ይሄ ደግሞ ትልቁ ሠርፕራይዛችንና የልፋታችን የመጨረሻ ውጤት ነው" አላቸው ሮቤል በቀይ ልባስ የተሸፈነውን ፋይል ከፍ አድርጎ እያሳያቸው....
"ልጠይቅህ ያሰብኩትን ብቻ እንዳይሆን" አለችው ሂዊ....
"እንኩ እዩት እዚህ ፋይል ውስጥ ያለው ድርጅቱ ውስጥ የአክስዮን ድርሻ ያላቸው ባለስልጣኖች ስም ዝርዝር ነው....ስማቸው፤ አሻራቸው ፎቷቸው በአጠቃላይ ሙሉ መረጃ ነው.....ሚኪ ስንፈልገው የነበረው ኮማንደርም ሠፍሯል..ኮማንደር መኮንን የሚባል ነው።..."አላቸው ሮቤል
"omg ይሄ ተአምር ነው...በአንዴ ሁሉም ነገር ሠመረ" አለ ሚኪ የደሥታ ጫፍ ላይ ደርሶ
ሮቤል ንግግሩን ቀጠለ" ይሄን መረጃ ሳንውል ሳናድር ለፓሊስ ኮሚሽነሩ ማድረስ አለብን....ፓሊሶች እነዚህን ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር ያውላሉ ከዛ መኩሪያው ሠምቶ በዚያው እንዳይቀር ሀገር ውስጥ እሥኪገባ ጠብቀን መረጃውን ለታማኝ ሚዲያዎች እናሠራጭና ለሌሎች ትምህርት ይሆን ዘንድ ነገሩን በይፋ እናወጣዋለን።"
ሠላም የሠዎቹን ሥም ዝርዝር ሥታይ በጣም ተገረመች" እንዴ በጠቅላላኮ ከላይ ያሉት ባለስልጣን ናቸው....ጎበዝ እቺ አገር ወዴት እያመራች ነው......?
1.6K viewsAbela, 19:30
Open / Comment
2022-05-15 19:04:16 እግዜር ላንቺ እድል

ትላልቅ ዓይኖችሽ ኮብለል ኮብለል ስሉ
እኚያ ውብ ከንፈሮች ከፈት ከደን ሲሉ
ከጉንጭሽ ላይ ያሉት እኚያ ስርጉዶችሽ እንዲው ሲዋልሉ
የተመልካችን ልብ ብሎን ያላላሉ
ዘንካታው ፀጉርሽ ደርሶ ሲዘናፈል
እንደ ጦር የቆመው ጡትሽ ሲንከባለል
የቀጠነው ገላሽ በእይታ ላይ ሲውል
ያቃጭላል ከውስጥ የወንድነት ደውል
ከጀርባሽ ላይ ኮርቶ የተፈናጠጠው
ያላፊ አግዳሚውን አንገት የሚያሳጣው
ስሜትን ወጥሮ አካልን ሚያግለው
ስለ ውብ ቁመናሽ ዳሌሽ ምስክር ነው
ቁመናሽ ማማሩ መልክሽ መሽቀርቀሩ
ፀባይሽ የሰጠ ያየለ ቀመሩ
አንቺን እንዳየሁሽ ወደ አምላክ አንጋጠጥኩ
በተሰጠሽ ውበት እጅግ እየታወኩ
ይህን የመሰለ ውበት ባንቺ ፈላ
ከፍጥረታት ሁሉ እግዜር ላንቺ አይላ።


አክሊሉ ተስፋዬ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.4K viewsAbela, 16:04
Open / Comment
2022-05-15 07:29:48 ኢላማህ
............



ቅድሚያ ኢላማው ፡ውስጥ ሰዶ
ቀስቱን ለማስገባት፤
ሊሰድ የቆመው ሰው፡ አይምሮና እጁ፡
መስማማት አለበት።


ቢሰድ ቢወረውር ፡ኢላማውን ባይመታ ፡
የተወረወረው ቀስት፤
ሁለት ነገር አለ፡ ግቡን እንዳይጨብጥ ፡
የጋረጠው አለት።



አንድ

በድል አጠናቆ ፡ከልቡ ተነስቶ፡
ኢላማውን ለመምታት፤
የወርዋሪው አይን ፡ኢላማው ላይ ብቻ፡
ማተኮር አለበት።

ሁለት

ያየውን ራዕይ፡ እውን ሆኖ እንዲያይ ፡
ግቡን እንዲመታው፤
መስደድ ብቻም ሳይሆን ፡እስከመጨረሻው፡
ቀስቱን ይለጥጠው።




ታዲያ ዋ

ድል ማድረግ ስትፈልግ ፡መንሳፈፍ እንድትችል
ከሰፊው ደመና፤
ለግብህ ትይዩ ፡የሚገኝ ስፋራ ላይ፡
መገኘትህን አጥና።።

ከዚን

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.5K viewsAbela, 04:29
Open / Comment
2022-05-15 00:16:29
ለዋይፋይ ፓስወርድ ፈላጊዎች በሙሉ
እንኳን ደስ አላችሁ
password መለመን ቀረ
ያለ ፓስወርድ የምናገናኝበትን አፕልኬሽን ከስር አስቀምጫለው
#WIFI_UNLOCK የሚለውን ይጫኑ
331 viewsEzra ❷❶, 21:16
Open / Comment
2022-05-15 00:10:51
ለ Pp የሚሆን ጥቅስ አጥተው ያውቃሉ? ወይስ ለፍቅረኛዎ የሚልኩት የፍቅር መልዕክት ይፈልጋሉ? ተቀላቀሉን Ezra Profile pictures
339 viewsEzra ❷❶, 21:10
Open / Comment
2022-05-14 19:11:16 ማነው ገላ ሻጩ ?
__
እሷ
ሰማይ ተደፍቶባት
ከሰማዩ በታች
ምድር ከእግሯ ርቋት
መኖር አይሉት ኑሮ
ኑራ የምታኖር
ባዶ ባደረ ሆድ
ባዶ ላደረ ሆድ
አልቅሳ ምታጎርስ
በእንባዋ ጠብታ
እንባን የምታብስ

እሱ
እምነቱን ገዝቶ
ውስጡን አሸብቶ
በሰከንዶች ስሜት
በሰከንድ ተገዝቶ
በጭኗ ያረፈ
ማእበሉን በእንባዋ
ተሻግሮ ያለፈ
ከሱ ጋ ተዋግቶ
በሱ የተሸነፈ
ታድያ ማነው ገላ ሻጩ
እራሱን አጉድሎ ጎዶሎን የመላ
ወይስ
በራሱ ስር ወድቆ
በጭኗ ያሽላላ።

ፀጋየ ግርማ(ሜሎስ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.0K viewsAbela, 16:11
Open / Comment
2022-05-14 18:21:56
ቤቲንግ ለምትመድቡ ሁሉ ይህን ምርጥ ቻናል እናስተዋውቃቹ

ብዙ ዓመት ልምድ ባላቸው ቀማሪዎች የተከፈተ ብችኛ ታማኝ ቻናል ነው ከኛጋ በመሆን ከሳምንት እስከ ሳምንት አሸናፊ ለመሆን ቻናሉን JOIN ያድርጉ

https://t.me/+RU8rzd2SuDnHu0Id
2.2K viewsAbela, 15:21
Open / Comment
2022-05-14 15:37:40 #እባክሽ
:
:
ትናንት ባማን ደና በሚያስቀና ለዛ፣
ሆነን አቻ ላቻ ያበጀነው ታዛ፣
ቀን በገፋ ቁጥር የኋላ የኋላ፣
ዘመም እዳይልብን በዳዋ እንዳይበላ፣
ዘላለም እንዲከርም የልባችን ምግብ ሆኖ በአንድ ትሪ፣
ባክሽ የኔ ፍቅር ሰው መምሰሉን ትተሽ ሰው መሆን ጀምሪ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
722 viewsAbela, 12:37
Open / Comment