Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 129.18K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 127

2022-05-21 12:35:55 #እንደ_ምግባር

ማወቅ 'ፈልጋለሁ
እንዴት እንደነበር
እንዴት እንደሚቀር
ይሄ ሁሉ ነገር!

ጥያቄዋን ገና አልኖርኩት
አልመልሰው ይከብደኛል
የት ይገኛል?
(መልሱ)
አሁን እኔም ኖርኩኝ ይባል?
(ጥያቄዋ)
ልርዳት ብዬ መንገድ ጠፋኝ
ምን አለፋኝ?
እህል አጣች?
እራፊ ጨርቅ?
ውበት አንሷት
ከኔ አትሰርቅ!
«..አይ እድሏ».
ሁሉን ሰጥቷት ሰልችቷታል
‘‘ችግር’’ ማየት ‘‘ቸግሯታል’’!

ናታን ኤርሚያስ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.4K viewsAbela, 09:35
Open / Comment
2022-05-21 01:11:44
ለ Pp የሚሆን ጥቅስ አጥተው ያውቃሉ?
ወይስ ለፍቅርኛዎ የሚልኩት የፍቅር መልዕክት ይፈለጋሉ? ተቀላቀሉን
534 viewsENFALOTE‌‌ ° , 22:11
Open / Comment
2022-05-21 00:56:16
• አስደሳች ዜና • !

•ማንኛውም አይነት አዲስ የአማሪኛ ዘፈኖችን የሚገኝበት ምርጥ ቻናል ነው
ከ 140,000 በላይ ተከታዮች የሉት ን ቻናል ይቀላቀሉ

https://t.me/joinchat/7b8Hl8TeX1xiMGQ0
https://t.me/joinchat/7b8Hl8TeX1xiMGQ0
365 viewsENFALOTE‌‌ ° , 21:56
Open / Comment
2022-05-20 18:50:14 #ነበር
:
:
ሁልጊዜ መደሰት፣
ሁል ጊዜ መሽቀርቀር፣
ቢሆን መልካም ነበር።
ግን እውነቱ ...
እስክንወርድ ወዳፈሩ፣
ባ‘ለም ቁና መሰፈሩ፣
አንዴ ልቅሶ አንዴ ሳቁም፣
ይኖራሉ አያበቁም።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.4K viewsAbela, 15:50
Open / Comment
2022-05-20 16:51:00 ጥያቄ(ዕርሱ ነው)

ዘመን ዕድሜው ሳይዘንፍ
ግብር ወዙ ሳይነጥፍ

ሰውነት ከዝክር
ዳኝነት ከምክር

ከአድባር ከቀያችን እየተፈተተ
የአያት የቅድመ አያት ያ' ብርቱ ክንዳቸው ዛሬ እየዘመተ

ደርባባ እንዳልነበርን
አምበሳ እንዳልነበርን....

ተራራ ደርምሰን ጥሻ እንዳላራቆትን
ከሸለቆ ዶለን መንጋ እንዳላጋደምን

ያ'ም እየተነሳ "ነብር ልሁን" ሲለን
ምነው እኛ ዛሬ "በግነትን" መረጥን!


ታደሰ ደምሴ

#ሼርርር

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.7K viewsAbela, 13:51
Open / Comment
2022-05-20 13:32:52 ብለሽኝ አልነበር?

ብለሽኝ አልነበር?
ዝምታህ ነፍሴ ነው ፀጥታህ ያምረኛል
በዘጋ አንደበትህ ልብህ ይሰማኛል
ዝምታህ ነፍሴ ነው
ፀጥ በል ስላልሽኝ ይሄው ዝም አልኩልሽ
ሳስመስል የግዴን
ማውራት እያሰኘኝ አፌን ዘጋሁልሽ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ብለሽኝ አልነበር?
ሳቅህ ገነቴ ነው ፈገግታህ ገዝቶኛል
ሳቅልኝ በሞቴ እኔን ደስ ይለኛል
ሳቅህ ገነቴ ነው ፍካልኝ ስላልሽኝ
ሳስመስል የግዴን
የውሸቴን ሳገጥ ሳሽካካ አስመሸሽኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ብለሽኝ አልነበር?
ድምፅህ ግዛቴ ነው ምቾት ይሰማኛል
'እወድሻለሁ' በለኝ ይሄ ቃል አምሮኛል
ድምፅህ ግዛቴ ነው ደጋግመው ስላልሽኝ
ሳስመስል የግዴን
'እወድሻለሁ' ብል በስምሽ አስማልሽኝ
("ሙች በል እስኪ" እያልሽኝ)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ብለሽኝ አልነበር?
ሀዘንህ ጌጤ ነው ያፍነከንከኛል
አንዴ አንብተህ ልይህ ይሄ ቀን ናፍቆኛል
ሀዘንህ ጌጤ ነው ተሰበር ስላልሽኝ
ሳስመስል የግዴን
ላንባ ብል እንቢ አለ እዚ ላይ ከበድሽኝ

(የምን ማስመሰል ነው የምንድን የግዴን?
ከአንቺ ያገጣጠመኝ
ቀኔን እያስታወስኩ ላንባልሽ የምሬን )
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ብለሽኝ አልነበር?


በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.3K viewsAbela, 10:32
Open / Comment
2022-05-20 07:42:10
ተወዳጁ ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በትላንት ዕለት ግንቦት 11, 2014 በተወለደ በ57 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ዶክሌ ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት በኮሜዲው ዘርፍ አዝናኝ፣ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል የኮሜዲ ስራዎችን ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። ዶክሌ ሀገራችን ካፈራቻቸው ብርቅዬና ግንባር ቀደም ኮሜዲያኖች ውስጥ አንዱ ሲሆን ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።

የኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ የቀብር ስነስርአት የሚፈጸመው በትውልድ ሀገሩ ኢትዩጵያ ስለሆነ ለዚህም ማስፈጸሚያ የሚሆን እና ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይህ የጎፈንድሚ አካውንት ተከፍቷል።
5.0K viewsAbela, 04:42
Open / Comment
2022-05-20 07:12:05
• አስደሳች ዜና • !

•ማንኛውም አይነት አዲስ የአማሪኛ ዘፈኖችን የሚገኝበት ምርጥ ቻናል ነው
ከ 140,000 በላይ ተከታዮች የሉት ን ቻናል ይቀላቀሉ

https://t.me/joinchat/7b8Hl8TeX1xiMGQ0
https://t.me/joinchat/7b8Hl8TeX1xiMGQ0
20 viewsENFALOTE‌‌ ° , 04:12
Open / Comment
2022-05-19 19:23:44 ቀድሼ :ላግባሽ.. 2....


የጸሎተ:ሐሙስ:የክርስቶስ:ራት
በረከት:የቀመሽ:በፈለግሽው:ሰዓት
ልሳንሽ:ወለላ:ፊደላትሽ;ስኳር
እንደ:ዮሐንስ:አፈ:ወርቅ:አፈ;ማር:አፈ:ማር !
:
በዻውሎስ:መፅሐፍ:እንደተነገረው
የስጋሽን:መንፈስ;ስሜት:ሳያረክሰው
በመንፈስ ቅዱስ :ኃይል:የከበረውን:ቤት
በወጣትነትሽ:የጠበቅሽ:ክቡር:ሴት

የዘመኑ :ልማድ:የዘመን:ፍካሬ
ያላስገረሰሰው:የህግሽን :ፍሬ
መዐዛው:ያራቀሽ:የክብር:ከልበኔ
ምስጢሩ:የገባሽ:የወንጌሉ:ቅኔ
በግዕዝ:በዕዝል:ስርአት:መልሼ
እባክሽን:ላግባሽ:ራሴው:ቀድሼ!!
ምዕመን:ይጠንቀቅ:ዘንድ:ከዝሙት:ፈተና
አንድ:ሰው:ካንድ:ሰው:ወንጌል;ፈቅዷልና
።።ቃል:ለሰማይ :ብለሽ:እኔም:ቃል ;ለምድር
የአብርሃምን:ህይወት:እባክሽ:እንጀምር!
በጌታ:ተአምር:በስልጣኑ:ቀመር
ፀንቻለሁና:ከእስጢፋኖስ:ማህበር
ነጠላ:ሳትጥዪ:ቀለም:ሳትቀቢ
አይንሽን:ሳይጋርድ:እኩይ:እንደረቢ
ጸዋጋን:ሳይሰልቡን:ጠብቀው:አሳቻ
ጥበብ:እንድስይሸሸን:የእግዚአሔር:ፍራቻ
ላንቾም:ጸጋ:ጽናት:ለኔም:ህይወት:ብርታት
እንዲወረብልን:ትዌድሶ:መርዓት...*...
:
በእዝል:በግእዝ:ስርአት:መልሼ
እባክሽን:ላግባሽ:ራሴው:ቀድሼ!!

Poet :Dawit tumey

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.6K viewsAbela, 16:23
Open / Comment
2022-05-19 18:01:43 የባስሊቆስ ዕንባ

ብዙ ያልተዘመረለት ፣ ማህበራዊ ሚድያው ያልጮለኸለት መጽሐፍ ነው። ውድ ነገር በርካሽ ፍራንካ ያገኘሁ ያህል ነው የተሰማኝ። መፅሐፉ በጣም ሚያስገርም መጽሐፍ ነው። በጣም የሚያምር የቋንቋ ለዛ ያለው ፣ አተራረኩ ማይጎረብጥ የጻህፊዋን የላቀ ስነፅሁፍ ችሎታ ሚያሳብቀ ድንቅ መፅሐፍ ነው። ደራሲዋ ትዕግስት ታፈረ ሞላ ትባላለች። ሴት ደራሲዎቻችን ወደፊት ሲወጡና በዚህ ልክ አቅማቸውን ሲያሳዩ ህይወትን እንደ ገብስ ግርዱን ከገላባው ለይተው ያስመለክቱናል ያሰኛል። በእያንዳንዱ ገጽ በሀሳቦቿና በመልዕክቷ አድናቆቴ ቀርቶላታል። ስለ ዕንባችን ፣ ስለ ህመማችን ፣ ሳቃችን ፣ ስለ ሀገራችን ፣ ስለ ፍቅር ሀያልነት ፣ ስለኑሮ ስቃይ በማራኪ መንገድ ከትባልናለች። ሀሳቧ ያምራል ፣ ገለጻዋ ያምራል።

በጣም ያስደሰተኝ ደግሞ መፅሐፏ ወደ ፊልም ተቀይሯል። በ Dstv '' አቦል ቲቪ '' ላይ በተከታታይ ክፍል እየታየ ነው። ያነበቡትን መፅሐፍ በፊልም ሲመለከቱት የእውነት አለም ነው።

እንድታነቡት ተጋብዛችኋል።

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.9K viewsAbela, 15:01
Open / Comment