2022-02-19 21:40:03
በአንድ ወቅት አንድ ቀልጣፋ እንጨት ቆራጭ በአንድ የስራ መስክ በጥሩ ደሞዝ ተቀጠረ።ስለዚህም እንጨት ቆራጩ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ እና ጥሩ ስራ ለመስራት ይወስናል።
በመጀመሪያው ቀን ሃላፊው መፍለጫ ሰጠውና የሚሰራበትን ቦታ አሳየው። መቁረጥ የሚችላቸው ዛፎች እነዚህ እንደሆኑ አስረድቶት ሄደ።በርግጥም እንጨት ቆራጩ በመጀመሪያው ቀን 15 ዛፎችን ቆርጦ ማስተካከል ቻለ።
በሁለተኛው ቀን የበለጠ ለመስራት ወስኖ ቢሞክርም ከ10ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም ነበር።
በሶስተኛው ቀን ከሁለቱ ቀናት የበለጠ ቢተጋም ከ7 ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም።
ቀናቶች ባለፋ ቁርጥ የሚቆርጣቸው ዛፎች መጠን እያነስ እያነስ መሄድ ጀመረ። በስተመጨረሻም አንዲትን ዛፍ መቁረጥ ከበደው። ሞከረ ሞከረ ሊሳካለት አልቻለም።
ይሄኔ ሃይሉን እንዳጣ ተሰማው። ጉልበቴም ከዳኝ ብሎ በማሰብ ላይ ሳለ የሆነ ሌላ ሰው ሲያልፍ ይህንን ሰው አንዲትን ዛፍ ያለጥቅም ሲደበድብ ይመለከተዋል።
"ሰውየው ወደ እንጨት ቆራጩ ጠጋ አለና አንድ ምክር ልምከርህ ትፈቅድልኛለህ?" አለው።
እንጨት ቆራጩም "አሁን ስራ ላይ ስለሆንኩ ምንም መስማት አልፈልግም" ይለዋል።
ሰውየውም እንዲህ አለው" እየፈለጥክበት ያለከው መፍለጫ ስለት የለውም ዶምድሟል። ከጥቅም ውጭም ሆኗል። ይህን አውቀህ እረፍት በማድረግ የምትሰራበትን ፋስ ልታስለው ይገባል" አለው።
ይሄኔ ይህ እንጨት ቆራጭ ቆም ብሎ አሰበ። እንዲህም አለ"እውነትም ፋሴን አልሞረድኩትም። ዛፎችን በመቁረጥ ቢዚ ስለነበርኩ" ብሎ ፋሱን በእርጋታ ሞረደና ከድሮ በተሻለ መልኩ ስራውን በአግባቡ ማከናወን ቀጠለ።
በህይወትህ ውስጥ መለወጥ ያለብህን ነገር ለመለወጥ ግዜ አትስጥ። ሁሉንም ነገር በጊዜ ለማከናወን ሞክር።ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.1K viewsAbela, 18:40