Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 141.64K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 139

2022-02-24 19:20:52
ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት 10 ምልክቶች እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተሽ ተመልከቻ
267 viewsMerry G, 16:20
Open / Comment
2022-02-24 19:18:53
የተወለዱበትን ወር በመንካት ስለ ፍቅር ህይወቶ ይወቁ
100% እውነት ነው
TRUE
ፍቅር
276 viewsMerry G, 16:18
Open / Comment
2022-02-24 09:11:58
ባለ ዕፀ መሰውር

ዕፀ መሰውርን ፣ ከደብተራ አግኝቶ
ከሰው እንዲሰወር ፣ ገላውን ቀብቶ
እንደ እግዜር ሳይታይ
በሚታይ ጎዳና
ወደ ባንክ ሄደና ፣
በንቁ ዘበኛ በሚጠበቀው በር
አልፎ ገንዘብ ሲዘርፍ አይታይም ነበር።
በዚህ ተደስቶ
ከዘላለም ቀንበር ፣ ካ'ይን ነጻ ወጥቶ
ግና ፣ ግና ፣ ግና
ተመልካች ባይኖረው ሆድ ነበረውና
እህል ወዳለበት በፍጥነት አቀና
ምግብ ቤት ሲገባ ፣ ማንም አልታዘዘው ፣ አይታይምና።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.7K viewsAbela, 06:11
Open / Comment
2022-02-23 09:16:41
ሒደት...

ከአስራ አምስት ዓመት በኋላ..

... ባለመኪና ሆናለች ። ሠራተኞቿን ጠርታ ዕቃ ታስወርዳለች ። ካፌዋ በከተማው ሥሙ የተጠራ ዘመናዊ ሆኗል።

....ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት...

...አንድ የሻይ ፔርሙዝና አምስት ድንጋይ ብርጭቆዎች ብቻ ነበሯት ። የላስቲክ መጠለያዋን ቋጥራ ወለሏን ጠራርጋ ለመቀመጫ አምስት የመአዘን ድንጋዮች ደርድራ ገበያ ጥበቃ ጀመረች ።

"ሻይ ፣ ስኳር አትጨምሪ" አሉ የመጀመሪያ ደንበኛዋ።

"ለምን?" ጠየቀች

"ስኳር በሽታ ስላለብኝ"

አቀረበችላቸው ። ቀምሰው ተቆጡ

"ስኳር አትጨምሪ አላልኩም?"

"መች ጨመርኩ ዛዲያ ? ስኳር አልፈልግም ብትሉኝ ማር ጠብ አደረኩሎት ። እንዴት ያለ አመል ያላቸው ሰው ናቸው ?"

ሁለተኛው ደንበኛ ሌላ አመል ይዞ መጣ

"ግማሽ ሻይ"

አቀረበች ፤ ተቆጣ

"ግማሽ ነው ያልኩት ለምን ሞልተሽ አመጣሽ?"

"እኔ የሰው ዕድል አላጎድልም ። የቻሉትን ጠጡና ሲበቃዎ ይተውት"

ሌላው ከጓደኞቹ ጋር መጥቶ

"ቀጭን ሻይ"

"ከሻይ አቅም ቀጭን? ቡና መሰልዎ ጌታው? እኔ ሻይ ሳወፍር ሳቀጥን አልገኝም ። ይጠጡ እንደሆን ያለውን ይጠጡ አሆሆይ..."

ከከተሜ ረቂቅ ባህሪ ጋር ነገሩ ሁሉ አልገጥም ብሏት ስንት ተንገላታ እንደነበር ለመገመት እንኳን ያዳግታል። አንድ ቀን ደሞ ሌላ ተስተናጋጅ...

"ባዶ ሻይ"

"እንደው ሌጣውን?"

"አዎ"

"ከተጠጣልህ ምንገዶኝ"

ሰጠችው። ሊወጣ ሲል ሒሳብ ሰጣት።

"ለእግዚሀር ውኋ? ገና ለገና ሻይ ቅጠሊቱ ገባችበት ብዬ ዋጋ ልቀበል? አላደርገውም!"

ውልብታ በ አለማየሁ ገላጋይ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
893 viewsAbela, 06:16
Open / Comment
2022-02-22 21:44:57 የፍቅር ቻናል ይቀላቀሉ
835 viewsMerry G, 18:44
Open / Comment
2022-02-22 21:42:17
የሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ቆየት ያሉ እና
አዳዲስ ዝማሬዎችን በነፃ ለማግኘት

#የኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ልጆች
•➢ ተቀላቀሉ // JOIN
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
1.4K viewsMerry G, 18:42
Open / Comment
2022-02-22 21:40:03
​​​⩩⩩⩩ የተቃጠለ ልብ ⩩⩩⩩
እነሆ በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው
ልብ አንጠልጣይ አዲስ የፍቅር ታሪክ
ይዘንላቹ መተናል። የተቃጠለ ልብ
ሊያመልጦት አይገባም!!
ከመጀመሪያ ጀምሮ ለመከታተል
ከታች ክፍል ⓵ የሚለውን
ይጫኑት።
789 viewsMerry G, 18:40
Open / Comment
2022-02-22 16:20:18
#አልረሳህም
#እንዴት #ይረሳኛል
ውኃ ለመገደብ…በጥም የነደድከው
ሀገር ልታበራ… ራስህ የጨለምከው
#ባንተ_ነው_ያየሁት
በረሃ እያቀኑ … ከተማ ላይ መውደቅ
መሬት ላይ ተጥሎ…ሰው ልብ ላይ መፅደቅ
#ስመኘው #ነው #እንጂ
ከዬት አመጣለሁ…እንዳንተ አይነት ሀሞት
ልጆችህን ትተህ …… ለልጆቼ መሞት
ማያልፈውን ሕይወት…ለሚያልፈው ተራ ቀን
ርካሽ ፖለቲካ …… ውድ አንተን ነጠቀን
* * *
እንዴት ‘ረሳሀለሁ … ሀገር ሆኗል ስምህ
በልቤ ላይ በቅሏል … የጎፈረው ፂምህ
ትዝታና እውነትህ
ሀቅና አሟሟትህ … ሆዴን እንዲያባቡ
ዘወትር ፊቴ ላይ
ድቅን ትላለህ …… በሰበብ አስባቡ

ላልረሳህ ምያለሁ… ማስታወሴን ላልተው
ሞላ ሲሉኝ አንተ … በራ ሲሉም አንተው
===||===
ከሙሉቀን ሰ•


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.1K viewsAbela, edited  13:20
Open / Comment
2022-02-22 11:55:28
Navie Force Watches
2500 birr

Contact @abela1987
0911468394
469 viewsAbela, 08:55
Open / Comment
2022-02-22 10:42:06 የሀገሯ ~ ገመገም
ከጥርሶቿ ~ ግርግም፣
ሳቋ ~ ሲያፍገመግም
ሳልፍና ~ ሳገድም።


አማትሬ ~ ባየው:
ተሰትረው ~ ኑረው
የቅርብ ሩቅ ~ ሆነው።


ኩንስንስ አመሏ
ጵስጡቂስ ጠረኗ
ኑረት አኳኃኗ፣

ዘንጠፍጠፍ እያለ
ቀልብ እያዋለለ፣


የገዛ ጥላዋ
ብርቅርቅ ገላዋ፣


ውልብ ይልብኛል.....
የድምጿ ሲርሲርታ
ያቃጭልብኛል።


እናማ......

ምናብ ሀሳብ ሲምስ
ሲያወጣ ሲመልስ፣


ጣዕሙን ሊያጣጥም
ምላስ ሲፈረጥም፣


እፀበሉ ግርጌ
ነጠላ አደግድጌ፣

ስለቴን ላስገባ
በእግዜሩ ሙሀባ፣

መጣሁ ከአድባርሽ
እቤተስኪያን ቅጥርሽ፣


የኔ እንዲያ መዋተት
ደርሶ መንከራተት፣

የኔ እንዲያ መውተረተር
ካንቺ ለመሰተር።


እነሆ አካሏን ጎብኝቶ ጠረኗን በምናቡ ምጎ ካጣጣመ በኃላ በዕውኑ አለም ፍለጋውን ማነፍነፉን ቀጠለ።


አንቺ ሆዬ ወዴት አለሽ?


ቅዱስ አርዮስ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.0K viewsAbela, 07:42
Open / Comment