🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 135.71K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 167

2022-01-09 20:56:32
የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
1.1K viewsMerry G, 17:56
Open / Comment
2022-01-09 18:58:15 "አንተን ይንሳኝ"
ልማል ደሞ ልማል፣
ስምህን ጠርቼ፣
ፊደላት አጥርቼ፣
አንተን ይንሳኝ ብየ ልማል ልገዘተው፣
እንደማልዋሽ ያውቃል ስምህን የሚያውቀው፣
ዛሬም አንተን ይንሳኝ ነገም አንተን ይንሳኝ፣
ስምህ አንደበቴን አስሬ ይዳብሰኝ፣
አንተን ይንሳኝ ሆዴ መማያ ታቦቴ፣
የማትመለክው አድባር ነህ ጣወቴ፣
ልማል ደሞ ልማል አንተን ይንሳኝ ብየ፣
ስምል እንዳይነሳኝ ሰቀቀን አዝየ፣
ለረገፈው ቅጠል ለተቃናው እንጨት፣
አንተን ይንሳኝ እያልኩ መንፈሴ ይደሰት፣
ቀሎብኝ አይደለም ማነሳህ ዘወትር፣
እንዲያምኑኝ ብየ ነው ንግግሬ እንዲያምር፣
ሠው ኪዳኑን ሚያስር በሚወደው አይደል፣
እኔም አንተን ጠራሁ አንተን ይንሳኝ ብየ መሀላየን ልምል።
ትዕይንት

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.1K viewsAbela, 15:58
Open / Comment
2022-01-09 16:48:53 ስሜትሽን አሽሽ......ፍቅሬን እንድነጥቅሽ


አቦ ግራ ገብኝ
እንዴት ነው ምረዳሽ፤
ያንቺ ነገር ለኔ
እየደፉ ማፈስ።
.
.
.
የምሰጠው የለኝ
አንቺም ምትመልሽው፤
ከኔ ተቀብለሽ
ለሰው ምታደርሽው፤
ውቀሽው




ይህ ልቤን እንደሆን ይበለው ግድ የለም፤
ፍቅሩ ሲበዛ ነው ያጣ አንዴውን አለም።
.
.
.
ግን እንዲህም ሁኖ አስብልሻለው፤
የሰጠሁሽ አንሶሽ
እንዴሆነስ ብዬ ውስጤን እሰድባለው።
.
.
.
ምናልባት አይሆንም
ሌላ ነው ሽሽትሽ ትዕግስት ይፈትናል፤
የወደደ አይርቅም በሚል ትምክህት ፈሊጥ አሰበሽ ይሆናል፤
ምናልባት አደለ.....
ደሞ በምናልባት ሀሳቤን ከእውነት በድምር ሰረዤ፤
ለራሴ እፈራለሁ
ጊዜን እንዳልሸኘው በዋዛ ፈዝዤ።
.
.
.
እኔም ሀቅ ሳላውቅ
አንቺም ኩራትሽን በትዕግሥት ዋጅተሽ
ከምትከረስሽ፤
በምትችይው አቅም ለገድልሽ ስትይ
ስሜትሽን አሽሽ፤
እኔም ለምፈራው ፍቅሬን እንድነጥቅሽ።


ሚኪ
@mikiendialem

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.8K viewsAbela, 13:48
Open / Comment
2022-01-09 13:08:51 ቺርስ

የሞላለት ማነው ፥ የተደላደለ
በልቡ ጀርባ ላይ ፥ ሀዘን ያላዘለ
ማነው ያላነባ ፥ ተደብቆ ቤቱ
ህመሙ ሲሰማው ፥ ሀሳብ ትኩሳቱ

እኔ ግን ብልህ ነኝ ፥ አይመቸኝም ማንባት
የህይወቴን ክፍተት ፥ የልቤን ባዶ ቤት
በቢራዬ ጠርሙስ ፥ በጃንቦ ሞላውት
.
.
.ከምናለቅስ
.እንጠጣ ቺርስ

አቤል ታደለ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.1K viewsAbela, 10:08
Open / Comment
2022-01-09 10:00:04 [ #እልቂቱ_ገና_ነው ]
#ገጣሚ_ሄኖክ_ፀጋዬ

ከከፍታ በላይ ኢትዮጵያን ለማድረስ፣
በጠበኞች መሀል #የተከፈተው ተኩስ፣
ገና ነው ጅማሬው አልበላም #ብዙ ነብስ።

ምን ይሉት #ምህረት ነው ዛሬ የተሰማ፣
ጣምና የሌለው ልብን የሚያደማ፣
የኢትዮጵያን ወኔ #ስሜቷን አደማ።

#እልቂቱ_ገና_ነው

ዙሪያውን ስቃኘው #የኢትዮጵያን ሁኔታ፣
ትናንትና አሉ የወጋት ተፈታ፣
ሽብርተኛ ተብሎ ድባቅ የተመታ፣
ምስኪኑን ወታደር #ያረደው በደስታ።

ክህደት ይሁን ምህረት ልቤ ባይገባውም፣
ይሄንን ነገር! በምንም ባስበው መቼም #አልስማማም፣
ምክንያቱም ደግሞ ትክክል አይደለም፣
#ሽብርተኛ መቼም ከእስር አይፈታም።

#እልቂቱ_ገና_ነው

አንተ የሀገሬ ሰው እስቲ ልብህን #አብራ፣
እንዴት በዚህ ትውልድ የኢትዮጵያ መከራ፣
በደስታ ይተካል በቅሎ #የዘር ካራ፣
#የጨለምተኝነት ጥግ ሞትን የሚዘራ።

#እኮ? ይሄ ትውልድ ለሀገር ይጠቅማል?፣
ከብርና ከጫት #ከራሱ ዘር ውጪ ለኢትዮጵያ ያስባል!፣
ለአንድ ሀገር ወድቆ ትንሳኤ ያበስራል?፣
እውነቱን #ልንገርህ ይሄ ትውልድ ወድቋል።

#እልቁቱ_ገና_ነው

ይሄ የሀገር ወጣት #በዘሩ ያመነ፣
መቃብር ካልገባ ነብሱ ካልተነነ፣
ሀገር #አትነሳም ሽንፈት ካላመነ፣
በአንድነት አምኖ ፍቅር ካልዘገነ።

#ሐበሻ ጠንካራው የኢትዮጵያ ካስማ፣
ዙሪያህን ተመልከት ማንንም አትስማ፣
#ጥረገው ዘረኛን አንተን ሳያደማ፣
ይሄን የሰው ሰይጣን #ሰውነቱ
የገማ።

#እልቂቱ_ገና_ነው

ሞት ደጋሹ በዝቷል #ጀርባህን ሚወጋ፣
የሰው እባብ መቷል ቤትህን ሊያናጋ፣
ስለዚህ #ነቃ በል ፈልግ ያንተን መንጋ፣
ሀገር #ወዳጅ መርጠህ ይሄን አፍራሽ ውጋ።

እኒህ ክፉ ኃይሎች በአንድ አብረዋል፣
ኢትዮጵያን ለመሸጥ #አፍራሽ ሰብስበዋል፣
#ሴቶችን ለመድፈር ሀገርን ሊዘርፉ ቆርጠው ተነስተዋል፣
ታዲያ እንዲህ ስልህ ያዝናሉ አትበል፣
እነዚህ አጥፊዎች የሰው #ደም ጠጪዎች በዘር ታውረዋል።

#እልቂቱ_ገና_ነው

አንተ ኢትዮጵያዊ #በአንድነት ልብህ በፍቅር ያመነ፣
ለሀገርህ ብቻ ልብህ የታመነ፣
የኢትዮጵያን #ትንሣኤ ምትናፍቅ ከሆነ።

ወገኔ ሆይ ስማኝ ግጥሜን #አስተውል፣
ይሄ ጦርነት የሰዎች እልቂት በእውነት የሚያበቃው፣
ዘረኞች ሲሞቱ ሆዳዎች ሲያልቁ ሞት ደጋሽ ሲጠፋ #ሲወገድ ብቻ ነው፣
#እግዚአብሔር ምህረትን ለኢትዮጵያ ሚልከው፣
የኢትዮጵያ ትንሣኤም ችቦው የሚበራው#

#ገጣሚ_ሄኖክ_ፀጋዬ
[@Henilogy ]
ሼር ሼር ሼር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.5K viewsAbela, 07:00
Open / Comment
2022-01-08 20:00:26 መዋተት በሲቃ !

በኢዮአብ ደብዳቤ
በዳዊት ብድራት
የኦሪዮን ውበት
ለጣኦት ስብራት።
ያቆብን ጠጉር 
ለደስታችን  መሻት፣
በሰሎሞን ጥፋት
መጫር የእግር እሳት ።
በጲላጦስ እጥበት
በተቸረ  ቅናት
  መታጠብ  በጥላት።
በሰረፀ ብቅል
ባይናችን ሽፍታ
ራስን መሰዋት
በእንግዳ ገፅታ ።
በጥቁር ነፃነት
በዝብርቅርቅ  ቅኝት
በረገበ  ስሜት
በተሳለ ቅዠት
ባገር ልጅ አዙሪት
መዋተት በሲቃ !
ታዲያ . . .
ሳያውቁ መሃላ የይሁዳ መሳም
መቅበዝበዝ መዳከር መኳረፍ  ከሰላም
ባለመሸናነፍ  ሴራ  ዝንጣፊ
እናት እንዳጠፋ  ሁሉኑም ታቃፊ
ህብር  እንዳይከስም በጊዜ ሽራፊ !!!

ዘመነ ፀጋ ነኝ
ምናልባት የናንተን ጥሩ የግጥም ቻናል ደስ ስለሚለኝ በጥቂቱም ቢሆን ለናንተ ያለኝን ደስታ ለመግለፅ ያህል . . .

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.6K viewsAbela, 17:00
Open / Comment
2022-01-08 18:44:08 ያንን ቁማርተኛ ከዙፋኑ ያለው
"ነፍጠኛ ነህ" ብሎ ዘሬን ለነጠቀው
"እንደምነው ምህረት?" ብየ ልጠይቀው

ከፍቶኝ ከፍቶኝ ዝም አልሁ
"ለምን?" ትሉኝ እንደሁ...
ይሔውነው ተረቱ፣
"ሰማይ አይታረስ"
"ንጉስ አይከሰስ"

#ሼርርርር

ታደሰ ደምሴ
(@Maryam21161)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.2K viewsAbela, edited  15:44
Open / Comment
2022-01-08 15:13:41
1.5K viewsMerry G, 12:13
Open / Comment
2022-01-08 13:39:49 የ ኪያ ቁጥር 2 ፊልም አዲሱ ማጀቢያ ሙዚቃ ዳውንሎድ ማድረግ ሳይጠበቅባቹ ከስር 'Play' ሚለው በመንካት ያዳምጡ

ኤሊያስ ተሾመ - ኪያዬ ቁ.2
Play ▷ ◉─────── 04:55
243 viewsMerry G, 10:39
Open / Comment
2022-01-08 13:27:35
እስቲ ይሄ የፍቅር ሳይኮሎጂ ነው የእናንተን ወይም የፍቅረኛዎትን #የመጀመሪያ ፊደል ይምረጡና ፈታ ይበሉ
414 viewsMerry G, 10:27
Open / Comment