🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 133.01K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 170

2022-01-05 20:03:47 መች በጀው

መች በጀው ለሱ
አዋቂነቱ ስለ ሳይንሱ

አውቃለሁ ብሎ በምሁር ስላቅ
መለያየትን ሰብኮ በገሀድ
እርስ በርሳቻን ከሆነ ምናልቅ
አንማር እና ዝንት አለም ይለቅ

ስለ ተማረ መስሎት ያወቀ
በትእቢት እሳት ልቡ ከሞቀ

በእውር ልቦና ሳያመዛዝን
በቃል በንባብ ከእወቀት መሬት
አብሮ ካጨደ አረሙን እወቀት

አርአያ ሆኖ በጥሩ ምግባር
ትውልድ ይቀርፃል ያንፃል ሲባል
ማፍረስ ከሆነ ስራው በተግባር
መች በጀው መማር

አቤል ታደለ
534 viewsAbela, 17:03
Open / Comment
2022-01-05 19:50:28 ፍቅር ብቻ ቻናል የበዓል ስጦታዎችን አዘጋጀ
Join በማለት በበዓል ሽልማቶች ይንበሽበሹ።
690 viewsMerry G, 16:50
Open / Comment
2022-01-05 19:30:43 ምን ይፈልጋሉ?
የፈለጉትን መርጠው JOIN

የፍቅር ዘፈን.............. JOIN

የፍቅር ደብዳቤ ............ JOIN

የፍቅር ጥያቄ.............. JOIN

የፍቅር ግጥሞች........... JOIN

አጫጭር የፍቅር ታሪኮች.......... JOIN

የፍቅር ጥቅሶች.......... JOIN
816 viewsMerry G, 16:30
Open / Comment
2022-01-05 19:17:47
የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎች የሚቀርብበት ልዩ ቻናል እነሆ https://t.me/joinchat/aLHyVIpQPIBhYzQ0 ተቀላቀሉን።
843 viewsMerry G, 16:17
Open / Comment
2022-01-05 11:55:57 ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
43 viewsBewketu, edited  08:55
Open / Comment
2022-01-05 07:31:21 በተመን..
(በእውቀቱ ስዩም)
ከባለንጀሮቼ ጋራ ስናወራ “ እኔኮ ዲያስፖራ አይደለሁም፤ ተመላላሽ፥ ሲራራ ነኝ “ እላቸዋለሁ፤ እነሱ ግን” እሳት ካየው ምን ለየው “ብለው በግድ በዲያስፖራነት ይመድቡኛል፤ እሺ ለዛሬ በነሱ ሀሳብ ልስማማና ልቀጥል፥
ባለፈው መንግስት ዲያስፖራውን አትመጣልኝም ወይ” እያለ ሲጀነጅነው አልነበር ?! ብዙ ወዳጆቼ ልባቸው በጅንጀናው ቀልጦ ለገና በአል ትኬት ቆረጡ፤ እኔም ግፍ-ያው ትንሽ ቀለል ሲል ለመድረስ ብየ ለጥምቀት ቆረጥሁ፤ ይህ በእንዲህ እያለ “ ከውጭ አገር ለሚመጡ እንግዶች ያርሶ አደሩን ሰብል የሚሰበስቡበት እድል መመቻቸቱ ተገለጸ”! የሚል ዜና ለቀቁብን፥ እንዴት እንዴት ያለ ነገር ነው! ቀድማችሁ ብትነግሩን እኮ ደርዘን አይፎን ን ከገዛንበት ቀንሰን ዘመናዊ ማጨጃ እንሸምት ነበር፤ በበኩሌ አርሶ አደሩን ለማገዝ ሁሌም ዝግጁ ነኝ፤ ግን እድሜን ከግምት ያስገባ ስምሪት ቢደረግ አሪፍ ይመስለኛል ፥ ከአርባ አመት በላይ ያስመዘገብን ሰዎች ከሰብል መሰብሰብ ወጣ ያለ ስራ እንዲፈለግልን ጥሪየን በማቅረብ ምክንያቱን አስከትላለሁ ። ባለፈው ቀኑን ሙሉ የመዋእለ ሕጻናት ማቲዎች የሚነጫጩበትን አውቶብስ ስነዳ ዋልሁ፤ አመሻሽ ላይ ጫማ ለማስር ጎንበስ ብል ዲስኬ ተንሸራተተ ፤ እና አሁን በዚህ እድሜ ዲስኬን ልሰብስብ ወይስ ሰብል ልስብስብ? የሌላውን አላውቀም! በበኩሌ ከተፈቀደልኝ ሰብሉ ተሰብስቦ እስኪጠናቀቅ ደመናውን ቆልፎ የመያዝ አገልግሎት ልሰጥ እችላለሁ፥
ዲያስፖራው ሚሊዮን ሆኖ ይመጣል ሲባል ከህብረተሰቡ ዘንድ ቢሊዮን ምላሾችን እያየን ነው፤ ባለፈው አንዱ “ ወደ አገር ቤት የሚመጡ እንግዶችን በነጻ ከኤርፖርት ወደ ማረፊያ ቤት ለማመላለስ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ” በማለት ሲናገር ሰማሁት፥
ቀድሞ የገሰገሰ ወዳጄ ከቦሌ አየር ማረፍያ እንደ ወረደ ሰውየውን ደውሎለት ተሳፈረ፤ ሰውየው ዲያስፖራ እናቱ ቤት ካደረሰው በሁዋላ አይን እና እጁን እያፈራረቀ ይሾፈው ጀመር፥
“ በነጻ ነው አይደል?” አለ ወዳጄ!
“አዎ! ግን አገልግሎቴ ከተመቸህ ደስ ያለህን ክፈለኝ፥"
እኔ እምለው፤ አንዳንድ ነዋሪዎች በዲያስፖራው ላይ የሚያወርዱት ነቆራ ትንሽ ልኩን አላለፈም ? በቀን በሌት፥ ሶስት አራት ስራ እየሰራ ያገራችንን የኢኮኖሚ ዋልታ የሚደግፍ ግዞተኛና ስደተኛ የውለታው ምላሽ ይሄ ነው? እኔ አሜሪካን ከግር እስከ እምብርቱ አይቻለሁ፤ የ“ኩበት ሽታ ናፈቀኝ” እሚል ዲያስፖራ ገጥሞኝ አያውቅም፤ ኩበት እሚናፍቅ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ ድረስ መሄድ አይጠበቅትም፥ አሁን እዚህ አሜሪካ አምሽ እሚባል እልም ያለ ገጠሬ ማህበረሰብ ይገኛል፤ ዲያስፖራው ከፈለገ ወደ Amish ነድቶ፤ እበት በኪሎ ሸምቶ በማይክሮዌብ ሞቅ አድርጎ ማሽተት ይችላል፤ አንዳንዶች ደግሞ ዲያስፖራውን ጭንጫ ሰገጤ አድርጎ መሳል የሚሄዱበት ርቀት ያስመንናል፥ በበኩሌ በየዞርኩበት ከተማ ሁሉ ከብሩህ አእምሮ እስከ ምርጥ ምግባር አስተባብረው የያዙ ዲያስፖራዎች ገጥመውኛል፤ በርግጥ አለፎ አልፎ ከስንዴ መሀል ቦለቄ አይጠፋም፤ በቀደም ለምሳሌ አንዱ ሀበሻ ዩቲዩብ ላይ “ የጎሬላ ውጊያ” የሚል ርእስ አንብቦ ምናለኝ” ጎሬላ ካላማጣ ምን ያህል ትርቃለች?”
አስተውላችሁ ከሆነ የነቆራው ባለቤቶች በሴት ዲያስፖራዎች ላይ አይጨክኑም!
ከላይ ከላይ ሲታይ፥ በዲያስፖራና ባልደሰፖረ መካከል ይመስላል እንጂ ውስጥ ውስጡን በዲታ ወንድና በቺስታ ወንድ መካከል የነበረ እና የሚኖር ፉክክር ነው ፤ ዲያስፖራው ዶላር አለው፥ በሀያል አገር የመኖርያ ፈቃድ አለው፥ እኒህን አስማቶች ተጠቅሞ ሴቶቻችንን ያስኮበልልብናል እሚል ስጋት የወረራቸው ሰዎች አሉ፤ እኒህ ሰዎች ዲያስፖራውን ጭንጫ ሰገጤ አድርጎ በመሳል የመታጨት አቅሙን ለማውረድ ይታገላሉ፥
በዲያስፖራና በአገር- በቀል መሀል ያለውን ይህንን ስውር ውድድር ስመለከት አንድ ነገር ትዝ ይለኛል፤ ልጅ እያለን ደብረማርቆስ ውስጥ ትልቅ ደመወዝ ተከፋዮች የግብርና ድርጅት ሰራተኞች ነበሩ፤ እና ቅዳሜ ምሽት ወደ አንድ ዝነኛ ባር ጎራ ብለው ሌላውን እንቁልልጭ እያሉ በሰፊው ይዝናናሉ። አልፎ አልፎ ደግሞ ለቡና ቤት ወይዛዝርት ዳጎስ ያለ ክፍያ በማቅረብ ይጠቀማሉ። ጥቂት ቆይቶ የፊላንድ ተራድኦ ድርጀት ተከፈተ፥ ፊኒዳ ይባል ነበር፥ የፊኒዳ ሰራተኞች የደሞዙን ሪከርድ ሰበሩት፤ ለቡናቤት ወይዛዝርት የሚቀርበውን ክፍያ በእጥፍ አሻቀቡት፥ አንዳንድ የግብርና ሰራተኞች ወድድሩን ለማሸነፍ ኪሳቸውን ባዶ አድርገው እስከመግባት ደረሱ ፤
ይህንን ሁሉ ድራማ ጥግ ተቀምጦ ይህንን ይታዘብ የነበረው አየለ ጀንብ እግር የተባለው
የከተማው አውቆ አበድ እንዲህ አለ፤
"ፊኒዳ
በተመን …ዳ
አንተን አክል ብሎ ግብርና ፈነዳ፥"
ጃንሜዳ ላይ ያገናኘን!


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.3K viewsAbela, 04:31
Open / Comment
2022-01-04 18:24:21 መጭውን ጠበቅሁት
(በእውቀቱ ስዩም)
ከማዶ ሚመጣው፥ ዘመድ ነው እንግዳ
ከላይ የተለጋው፥ ኳስ ነው ወይስ ናዳ
ብየ መች ጠየቅሁኝ
መጭውን ጠበቅሁት
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብየ፤ ጸሀይ እየሞቅሁኝ፥
መከራም አላጣም፥ ተድላም አልጎደለኝ
ደንታ ነው የሌለኝ፥
ባካል በስሜትም፥ ታሞ ላገገመ
ወድቆ ለተነሳ ፥ እየደጋገመ
ከገዛ ጉድጓዱ ፥አጽሙን ለሚለቅም
ሞትም ብርቅ አይደለም፥ ትንሳኤም አይደንቅም ::


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.5K viewsAbela, 15:24
Open / Comment
2022-01-04 15:04:35 ደስታ ግን ምንድነው ያለውስ ወዴት ነው
ደስታን እሚሰጠው የሚያድልስ ማነው
ከራስ እሚመነጭ ነውስ እሚሰጥ ነው ?
ሀዘን አስረስቶ ሰላም እሚያወርሰው
አረ እሱ ግን ማነው ከወዴትስ ነው ያለው
ጨበጥቁት ሳልለው ቶሎ እሚበተነው
እረዥሙን ጊዜ አጭር እሚያደርገው
ደስታ ግን ምንድነው ምንጩስ ከወዴት ነው
ደስታን ተቀብሎ እሚወስድብኝ
ደሞ ሲያስፈልገኝ እንካ እሚለኝ
በራሴ ደስታ ላይ እሚወስንልኝ
ለካ ሌላ አይደለም ደስታን እሚሰጠኝ
የደስታዬ ምንጩ እኔ እራሴ ነኝ
ታድያ እንዲ ከሆነ ደስታን ማን ነጠቀኝ
ብዬ ራሴን እንዲ ስል ወቀስኩኝ
ስለሌለኝ ትንሽ ስለጎደለኝ
ሁል ጊዜ በህይወቴ እያማረርኩኝ
ባለኝ በሞላልኝ ደሞም በተሰጠኝ
እግዚአብሔርን ካላመሰገንኩኝ
ያለኝ በቃኝ ብዬ ካልተደሰትኩኝ
የደስታዬ መጥፋት ተጠያቂ ነኝ ።

ዩናስ ጌታሁን
@Yoniiiiiiii7

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.5K viewsAbela, edited  12:04
Open / Comment
2022-01-04 12:46:38
2.7K viewsAbela, edited  09:46
Open / Comment
2022-01-04 09:18:38 በእውቀቱ ስዩም እና ስነ-ፅሁፍ pinned a photo
06:18
Open / Comment