2022-01-08 08:01:35
ባልወድሽ ነው እንጂ...
ባልወድሽ ነው እንጂ ባላስብሽ እንጂ ብወድሽ ኖሮማ፣
ቤት ሰራልሽ ነበር በሰማይ ከተማ፣
በታላቂቱ ሃገር በገብርኤሏ ራማ።
.
.
.
የሰማይ ፈጣሪ ብርሃን ይኹን ብሎ ብርሃን ባረገበት፣
አቆምሽ ነበረ ጸሐይ ባለችበት።
.
.
.
በጨረቃ ሸራ በነጩ ቀለም ላይ፣
እስልሽ ነበረ ዓለም ኹሉ እንዲያይ።
.
.
.
እልሻለሁ ግና እልሻለሁ ግና ብወድሽ ኑሮማ፣
ከመነኩሴ ሃገር ከገዳሙ ማማ፣
ትታይ ነበረ በሞገስ በግርማ።
.
.
.
እኔ ካፈቀርኩሽ ተራራው ይናዳል፣
ዳሽን ይፈርስና ቀይ ምንጣፍ ተነጥፎ መንገድ ይሆንሻል፣
ጣናም ይደርቅና ተረማመጂብኝ ብሎ ይጠራሻል፣
አክሱም ይወድቅና እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግልሻል፣
ዶፍ እንዳይወርድብሽ የጎንደሩ ፋሲል ዘብ ይቆምልሻል፣
ብወድሽ ኑሮማ እንኳን ሃገር ቀርቶ ዓለም ይበጅሻል፣
የምድሪቱ ሴቶች ቆንጆ ናት እያሉ ይተርኩልሻል፣
የሹማምንት ወንዶች የኔ ትሁን ሲሉ ደም ይቃቡልሻል፣
ታላላቅ ነገስታት ወደ ትቢያ ወድቀው ጫማ ያስሩልሻል ።
.
.
.
እንዲያው ተንሳፈፊ በሃሳብም ሒጂ፣
ብወድሽ መልካም ነው አልወድሽም እንጂ።
ተጻፈ በበረከት ለማ
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
848 viewsAbela, edited 05:01