🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 135.71K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 20

2023-04-11 19:17:21 «ህም መች ሰው ባሰበበት ይውላል?» አለ ከንፈሩን ብቻ ሸሸት አድርጎ። እኔ አንድ ሀገር አውርቼ ከአምስት ቃል ያልዘለለ ነው የሚመልስልኝ። ያለማቋረጥ መለፍለፌ ለራሴ እንኳን እንግዳ አይነት ስሜት ሰጥቶኛል። መልሼ ይሄንንም ያንንም ሳወራ ራሴን አገኘዋለሁ እንጂ። ምናልባት ከእናቴ ጋር የነበረኝ ጊዜ፣ ወይ ደግሞ ያስታወስኩት የትውስታዬ ሽራፊ፣ ወይም ትውስታዬ የመመለስ ተስፋ እንዳለው ማወቄ፣ አልያም አጎቴ ያወራልኝ የህይወቴ ክፍል …… አላውቅም! አንዳቸው ወይም ሁሉም ተደምረው ግን የሆነ ስሄድ ከነበረው ቅልል ያለ ስሜት ስመለስ እንዲኖረኝ አድርገውኛል።

«ከመመታቴ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያደረግኩት ምን ይሆን? ለመጨረሻ ያገኘሁት ሰው ማን ይሆን? ያስቀየምኩት ወይስ በጥሩ የሚያስታውሰኝ ሰው ይሆን?» ያልኩት እንዲመልስልኝ አልነበረም።

«የዚያን እለት ከቤት ወጥተሽ ብዙም ሳትቆዪ ነው የሆነው ነገር የሆነው። በመንገድሽ የገጠመሽ ካልነበረ ለመጨረሻ ያወራሽው እኔን ነው የሚሆን!» አለ ስሜቱን ለማንበብ በሚከብድ ፊት። ያልጠበቅኩት መልስ ሆኖ መሰለኝ ተስተካክዬ ተቀመጥኩ።

«ምንድነው ያወራሁህ? መጥፎ ነገር ነው? ጥሩ?»
«ያለፈውን ከኋላችን እንተወው ተባብለንም የለ?» መመለስ የማይፈልገው ነገር ሲሆን የሚያመልጥበት ዘዴው ነው።
«በናትህ? ለምንድነው ግን ያለፈውን ስጠይቅህ የምትሸሸው? ልቤ የሚነግረኝ ከነገርከኝ በላይ ብዙ የምታውቀውን ነገር እንደደበቅከኝ ነው ግን ዝም ብዬ እያመንኩህ ነው።» ….. ብዬ ጥርጣሬዬን ላስከትል ስንደረደር የሚቀጥለውን ለማስቆም በሚመስል

«ፀያፍ ነገር ነው!! እኔ አሁን የማልደግመውን ፀያፍ ነገር ብለሽኝ ነው የወጣሽ! እንደእውነቱስ አፍሽን ከፈትሽ ነው የሚባል።» አለ እንዲመልስልኝ ስላደረግኩት እየተናደደብኝ።

«እሺ በሙሉ ልቤ እንዳምንህ አስረዳኝ! እንደዛ ፀያፍ ነገር የምናገርህ ሴት ሆኜ እቤቴ ምን አቆየህ? ስራዬ ፣ እንጀራዬ ምናምን ብለህ ልትሸነግለኝ አትሞክር! እኔ የምከፍልህን ደመወዝ ብዙ እጥፍ ከፍሎ የሚያሰራህ ሰው አታጣም ባንተ ብዙ ችሎታ! ሲጀመር የአንድ ቤት ዘበኛ፣ መኪና መንዳት የሚችል፣ ሽጉጥ የታጠቀ ፣ ክብር ሀቅ እውነት እሴቶቹ የሆነ ሰው …… አፏን የምትከፍትበት ሴት ደጅ ምን ያደርጋል?»

«ውል የሌለው አድርገሽ አትቆጣጥሪውማ! ሹፍርና እሰራ እንደነበርኮ አውግቼሽ ነበር። ወታደር ቤት ስለነበርኩ መሳሪያውም አዲሴ አይደለም። ሽጉጡንም ያስታጠቅሽኝ አንቺው ነበርሽ! ይከው ነው!!» አለ

«አሁን ያልከው በሙሉ ለምን እኔጋ እንደቆየህ አያብራራም! እሺ ንገረኝ እስኪ የት ነው የተገናኘነው? ማለቴ ስራውን እንዴት አገኘኸው? ወይም እኔ እንዴት ቀጠርኩህ?»

ለማውራት አፉን ከመክፈቱ በፊት በረጅሙ ተነፈሰ። ግንባሩ ላይ ያሉት መስመሮች ብዛታቸው ጨመረ። ዞር ብሎ ሳያየኝ

«ሰው ነው ያገናኘን! አንቺ ጠባቂ እንደምትፈልጊ እኔ ስራ እንደሚያስፈልገኝ የሚያቅ ሰው!» አለ በድፍኑ። አጀማመሩ እስከነገ የማያልቅ ታሪክ ሊያወራኝ ነበርኮ የሚመስለው።

«በቃ!? ሰው?» ድምፄን ጨመርኩ።
«ቆይ እኔ የምጎዳሽ አለመሆኔን እንድታምኚ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?»
«እያወራን ካለነው ጋር ይሄ የሚያገናኘው ነገር የለም! ትጎዳኛለህ ብዬ ባስብማ አብሬህ አልገኝም!! አንተ መናገር ያልፈለግከው ወይም እየደበቅከኝ ያለ ነገር እንዳለ እየተሰማኝ ግን ምንም ሳትጠይቂ በጭፍኑ እመኚኝ ማለት አይዋጥልኝም።» አልመለሰልኝም። አሁንም በረዥሙ ተንፍሶ ዝም አለ። በዝምታችን ውስጥ ከራሴ ሳወራ ለካንስ ምንም ነገር ለእኔ የማስረዳት ግዴታም የለበትም። <የራስሽ ጉዳይ> ብሎ ጥሎኝ ቢሄድስ መብቱ አይደል? ያኔም ለምን አብሮኝ እንደቆየ አሁን ለምን አብሮኝ እንዳለ ምክንያቱን ማወቅ አልችልም። ስለእርሱ የማወቅ መብት እንዳለኝ እንዲሰማኝ ያደረገኝ ራሱ አይደል ግን?

ሀሳብ ሳዛቁል ስልኬ ጠራ። የማላውቀው ቁጥር ነው። ለምን እንደማደርገው ባላውቅም የማላውቀው ስልክ ሲደወል ጎንጥ አጠገቤ ካለ ድምፁን ስፒከር ላይ አደርገዋለሁ። ምናልባት የመጀመሪያ ቀን ስልኬ ሲከፈት ድንብርብሬ ወጥቶ ስንተባተብ እሱ ስልኩን ተቀብሎኝ ስላወራ እንደልምድ ወስጄው ይሆናል። አነስቼ ሀሎ አልኩ።

«እሺ ሜላት!! ሁልጊዜ ጀግና አይኮንም! አንድ ቀን አገኝሻለሁ ብዬሽ አልነበር?» ወፍራም ድርብ የወንድ ድምፅ ነው።
«ማን ልበል?»
«ማን እንደሆንኩማ አሳምረሽ ታውቂዋለሽ!! ዛሬውኑ እስከማታ ድረስ የምልሽን ታደርጊያለሽ!! ህም እመኚኝ ይሄ እንደሌላ ጊዜው ማስፈራሪያ አይደለም። ምንም አይነት ወጥመድ ከጀርባዬ ሸርባለሁ ብትዪ ወንድምሽን 12 ትንንሽ አድርጌ በየተራ እልክልሻለሁ። ……. » ጎንጥ መኪናዋን ሲጢጥ አድርጎ አቆማት። እየሆነ ያለው ነገር በቅጡ ሳይገባኝ ሰውየው ማውራቱን ቀጠለ « …… ልታናግሪው ከፈለግሽ አጠገቤ ነው። ቪዲዮ ላድርግልሽ ከፈለግሽ?» (እያላገጠብኝ ነው የሚያወራው) ይሄኔ ጎንጥ ከመኪናው ፊትለፊት ያለ ወረቀት አንስቶ ከኪሱ እስኪሪብቶ አውጥቶ የፃፈውን አሳየኝ። <ምንድነው የምትፈልገው? በይው።> ሰውየው ይሄን ሲሰማ እንደመደሰት አደረገው።

« የሰውን ስስ ጎን ማግኘት ደስ ሲል።አየሽ የምትሳሺለት ነገር ሲያዝብሽ እንዲህ ነው የሚያንገበግበው። ከገባሽ! አንደኛ ወለም ዘለም ሳትዪ የቪዲዮን ያሉሽን ቅጂዎች በሙሉ ካስቀመጥሽበት ሰብስበሽ ነይ የምልሽ ቦታ ይዘሽ ትመጫለሽ። ሁለተኛ አንቺን ማመን ስለማይቻል ማስተማመኛ እንዲሆነኝ እዚህ ከመጣሽ በኋላ በይ የምልሽን እያልሽ እንቀርፅሻለን። ይቅርታ እንግዲህ ባላምንሽ … ያለመታመን ልምድሽ አቻ ባይኖረው ነው።» እኔ እሱ የተናገረው ምኑም አልገባኝ እሱ ይገለፍጣል። ጎንጥ ፅፎ ያሳየኛል።

«እኮ ምንድነው እንድቀርፅልህ የምትፈልገው?»
«ቆቅ አልነበርሽ? ይህቺ ትጠፋሻለች? በማስፈራራት ያለፍሻቸውን እዚህም እዛም የሰራሻቸው ህገወጥ ነገሮች ሲሰበሰቡ እድሜ ልክ ዘብጥያ የምትበሰብሺበት ሆኖ አጊንቼዋለሁ። ብዙም እንዳትቸገሪ መረጃዎቹንም ሰብስቤልሻለሁ። አንቺ የሚጠበቅብሽ የሰራሻቸውን ወንጀሎች በመረጃ አስደግፈሽ አምነሽ ቃል መስጠት ነው። ከምታምኛቸው ውስጥ ፌክ የምስል ቅንብር እና መረጃ ሰርተሽ እኔን በማስፈራራት የግል ጥቅም ለማግኘት ያለመታከት መልፋትሽ ይካተትበታል። ያው እዝህችጋ ምንም ያህል የረቀ ሴራ ብትሰሪ እኔ ወደር የሌለኝ ለሀገሬ ታማኝ አገልጋይ መሆኔን አክለሽ ብትጠቅሽም አይከፋኝም። ሃሃሃሃሃ» እኔ ምኑም እየገባኝ ካለመሆኔ እየተነጋገሩ ያሉት ሰውየውና ጎንጥ ናቸው የሚመስሉት

«ኪዳንን አገናኘኝ? ማስረጃ እፈልጋለሁ።» ብሎ ጎንጥ የፃፈልኝን አነበብኩለት

«ምን ችግር። ቆዪማ ቪዲዮ ላድርገው?» ሲለኝ ጎንጥ ስልኩን ዘጋው እና እኔ ላይ አፈጠጠ።

«ወንድምሽን ስታዪው የተደናገጠ ሰው እንዳትመስዪ ፣ ድሮ የሚያውቋትን ሜላት መሆንሽን አሳምኛቸው። ምንም እንደማያውቅ ሰው አትምሰዪ ….. የማታውቂውን ነገር አትጠይቂ!! ምንም ቢፈጠር እንደማታስታውሺ እንዳትናገሪ ….. የምልሽን ብቻ አድርጊ!!» ብሎ በቁጣ እያስጠነቀቀኝ ስልኬን ተቀብሎኝ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ሰው ጣቱን ካመላለሰ በኋላ ከመጡለት ዝርዝሮች የሆነች ቀይ ምልክት ነገር ተጭኖ እየመለሰልኝ ስልኩ ጠራ። ድንብርብሬ ሲወጣ በሁለቱም እጆቹ ትከሻዬን በሁለቱም በኩል አጥብቆ እየያዘ « ታምኚኛለሽ?» ያለኝ ስለምን እንደሆነ ሳይገባንኝ ጭንቅላቴን ወደ ላይ ወደታች ናጥኩ!! «ተረጋጊና ያልኩሽን አድርጊ!!»
3.5K viewsAbela, 16:17
Open / Comment
2023-04-11 19:17:21 የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........


(ሜሪ ፈለቀ)

ክፍል 14


«ከዛ ሰውዬ ጋር አብሬው ተኛሁ? ምንድነው ያደረግኩት?» መልሱን ማናቸውም እንደማያውቁት እያወቅኩ ደጋግሜ እጠይቃቸዋለሁ። እነርሱም መልሱን ጠብቄ እንዳልጠየቅኳቸው ስለልገባቸው አይመልሱልኝም። ከዚህ ቀዬ ከወጣሁ በኋላ የተፈጠረውን ነገር ካወቀ ሊያውቅ የሚችለው ኪዳን ብቻ ነው።

እናቴን ካገኘሁ በኋላ ያለፈውን ራሴን የመፈለግ ውጥረቴ ትቶኝ ነበር። አጎቴ ታሪኬን ነግሮኝ ሲያበቃ እንደአዲስ ያቅበጠብጠኝ ጀመር። ምንድነው ያደረግኩት? ምን ዓይነት አቅል መሳት ላይ ደርሼ ነው ያን ሰውዬ ያገባሁት?

«እናቴ? ስለኪዳን የነገርኩሽን የምታስታውሺውን ሁሉ እስኪ ንገሪኝ! ከተመታሁኮ ሁለት ወር አለፈ። እንዴት አይፈልገኝም? እንዴት አይደውልልኝም?»

«እኔ እንጃ ልጄ! ብዙውን ያወራሽኝ ስለመውደድሽ ፤ ጎበዝ ተማሪ ሆኖ በማዕረግ ስለመመረቁ ፣ ፈረንጅ ፍቅረኛ እንዳለችው እና ሰርጉ ሀገሩ እንዲሆን ፈልጎ አንቺ እንቢ ማለትሽን …… እንዲህ እንዲህ ያለ ነገር ነው የነገርሽኝ እንጂ የምትገናኙበትን መንገድ አላውቅም ልጄ። ከመሞቴ በፊት ባየው ብዬሽ <በህይወት መኖርሽን አያውቅም። እንዴት እንደምነግረው እንጃ ግን እነግረዋለሁ> አልሽኝ።» እያለችኝ ሌላ የምታስታውሰው ነገር መኖሩን የጭንቅላቷን ጓዳ ትበረብራለች

«ለምን እንቢ አልኩት? ማለቴ ሰርጉን?»

«አንቺን ማጥቃት የፈለገ ሰው ሊያጠቃሽ የሚችልበት ብቸኛ መንገድ እሱ በመሆኑ አንድ ነገር እንደሚያደርጉብሽ ነው የነገርሽኝ። ሁኔታውን ልትነግሪኝ አልወደድሽም እንጂ ከዚህ በፊት በእሱ እንዳገኙሽ ነግረሽኛል።»

ድፍንፍን ያለ ነገር ሆነብኝ። ወደቤቴ መመለስ ፈለግኩ። ፍለጋዬን የት እንደምጀምር ባላውቅም እዛ የሆነ ፍንጭ አላጣም መሰለኝ። ያቺ መልእክት አስቀምጣ የነበረችው እመቤትስ? ያ የደወልንለት ሰውዬ ቃሊቲ እስር ቤት ናት ያላት እመቤት! ማን ያውቃል ለእሷ የሆነ ነገር ነግሬያት ይሆናል። ግን እስር ቤቱጋ ሄጄ በደፈናው እመቤትን ነው የምለው? ምናልባት አንድ ሀገር እመቤት የሚባል ሴት ይኖራል። አላውቅም ብቻ እዚህ ተቀምጬ ሀሳብ ከማመነዥክ መሞከሩ አይከፋም!

ምናልባት ደግሞ ያ ስልባቦት የመሰለ ዳዊት የሚሉት ፍቅረኛዬ! ለእርሱስ ምንም ልነግረው አልችልም ኸረ! ማን ያውቃል ግን? ግን እንዴት ባለ ዘዴ ነው ትውስታዬን ማጣቴን ሳልነግረው ስለኪዳን የሚያውቀው ነገር መኖሩን የማወጣጣው?

እናቴ የቀሯትን ቀናት እዛው መሆን መፈለጓን እኔ እንዳይከፋኝ በማባበል በማስፈቀድ ለዛ ስትጠይቀኝ ግራ ገባኝ። በሽታዋ የማህፀን ካንሰር ነው። ምንም ማድረግ እስከማይችሉበት ሰዓት ድረስ ሀኪሞች ብዙ ትሪትመንት ሞክረውላታል። ያገኘኋት ጊዜ ሀኪም ቤት ካልወሰድኩሽ ብዬ ስነዘንዛት

«ልጄ አንቺው እኮ ነሽ ስታሳክሚኝ የቆየሽው! ከሀገር ውጪ ወጥተሽ ካልታከምሽ ብለሽኝኮ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ሀኪሞቹ ነግረውሽ ነው የተውሽው። አምላክ በታምሩ ይሄን ደስታ ቀምሰሽ ሙቺ ሲለኝ እንጂ እንዲህም መች ትቆያለች ተባልኩ?» ብላኝ ነበር። ሀኪሞቹ ከገመቱት ቀን በላይ መቆየቷ ተዓምር እንደሆነ ሁሉ ብትታከም ድጋሚ ተዓምር ሊፈጠር ይችል ይሆናል ብዬ ላሳምናት ብሞክርም <ደከመኝ> አለችኝ። ማረፍ ብቻ ነው የፈለገችው። መሞትን ሳትፈራው ቀርታ ይሁን ወይስ እንዳይታወቅባት ውጣው ለመሞት የተዘጋጀች ነው የምትመስለው። በመጣ ቀን <እንኳን ደህና መጣህ! ስጠብቅህ ነበር> ብላ የምትቀበለው።

«እሺ!» አልኳት እና ወደጎንጥ ዞሬ «አንተ ነገውኑ ባሻህ ሰዓት ተመለስ! እኔ እዚህ ከእናቴ ጋር እሆናለሁ! » አልኩት

«ማይደረገውን!! እኔ እዚህ መሆኔ ካልከበዳችሁ በቀር ወደየትም የመሄድ መሻት የለኝም!!» (አለ ወደአጎቴ እያየ)

«ኸረ ምን ከብደኸኝ? ባደረገውና እዚሁ በባጀህ! እኔማ የሚያነጋግረኝ አገኘሁ!» አለ አጎቴ።

ከመጣን ጀምሮ ጎንጥ ከዚህ በፊት የሚያውቀው ቤት እና ቤተሰብ ውስጥ የተቀላቀለ ነበር የሚመስለው። እጅጌውን ሰብሰብ አድርጎ እንጨት ለመፍለጥ ሰዓታት አልፈጀም። ሊወድቅ ያዘመመውን የከብቶቹን ቤት ያጋደለውን እንጨት እያስተካከለ ሲተክል በእንግድነት ውሎ አላደረም ነበር። ሱሪውን ሰብስቦ እንደቁምጣ አሳጥሮ የአጎቴን የጓሮ ማሳ ሲያርም …… የኖረበት …. የሚያውቀው እንደሆነ ያሳብቅበት ነበር። አጎቴ በእርሱ መገኘት ደስ መሰኘቱን ለማወቅ ብዙ ሂሳብ አያሰራም።

«እኔ እዚህ ምን እሆናለሁ? እዚህ ጠላት የለኝም ሲገባኝ። ዝምብዬ ነው የምፈራው እንጂ ምናልባትም ማንም እያደባብኝ አይደለም። የሚያስፈልግ ነገር ሲኖር ባይሆን ትመጣለህ።» አልኩት እናቴን ላገኛት የሄድኩ ቀን እንደዛ ተንበጭብጬ ምንም ያለመፈጠሩን እያሰብኩ።

«ህም!! ክፋት የከጀለ ልብ አይደለም እዝህች ሲኦል ከመውረድ የሚያግደው የለም!» አባባሉ ስለእርሱ ያለኝን ጥርጣሬ ቀሰቀሰብኝ። የሆነ ያልነገረኝ የሚያውቀው ነገርማ አለ።

«አይሆንም አንቺም እዚህ አትከርሚም!» አለች እናቴ ጠልቃ ገብታ « ….. በአካል ባልዳብሰው እንኳን የኪዳንን ድምፅ ሰምቼ አንዴ አውርቼው ባልፍ …… ይሄ ባይሆን እንኳን ለወንድምሽ ታስፈልጊዋለሽ። አግኝው!» አለችኝ አሁንም በልምምጧ። ልቤ መሃል ላይ ዋለለብኝ። እሺ የት ብዬ ነው የምፈልገው? እሱን ለማግኘት እኔ ስዳክር እናቴ ብታመልጠኝስ? ምን ያህል እንደሆነ የማላውቀውን የቀረንን ቀን ትቻት እንዴት ነው የምሄደው?

«የእኔ አበባ ? አትከፊብኝ! እዚህ አብረሽኝ ብትሆኝም ሞትን አታስመልጪኝም! ለእኔ አምላክ በእድሜዬ ማታ አንቺን መልሶልኝ ሀሴት ሰጥቶኛል። ወንድምሽን ባላገኘው እንኳን ደህና መሆኑን ማወቄ እረፍት ነው!! ስንት ቀኖች እና ስንት ለሊቶች <ልጆቼን ለየትኛው ጅብ ዳርጌያቸው ይሆን? ምን ዓይነት ህይወት እየኖሩ ይሆን? ትቻቸው ባልሄድ የተሻለ ህይወት ይሆንላቸው ነበር?> እያልኩ በፀፀት ነድጃለሁ መሰለሽ? ያንቺ እናት ስለሆንኩ እኔ እድለኛ ነኝ። ብቻ አንድ ነገር ቃል ጊቢልኝ! ያለፍሽውን ብታስታውሺም ባታስታውሺም ወደቀደመው ህይወትሽ ላትመለሺ ቃል ጊቢልኝ!! ልብሽን ያየ አምላክ ሁለተኛ እድል ሰጥቶሻል። ያለፈውን ለመድገም ሌላ አዲስ ህይወት ባላስፈለገሽ ነበር። አዲስ ህይወትን ገንቢ የእኔ አበባ! ……. » የስንብት የሚመስል ብዙ አለችኝ። ያለእርሷ የኖርኩትን ህይወት እንዴት እንደኖርኩት ባላውቅም አሁን ያለእርሱ የምኖራቸውን ቀናት ሳስብ በረደኝ።

ግማሽ ልቤን እናቴጋ ትቼ፤ ፈጣሪ ትንሽ ቀን ቢጨምርላት፣ ኪዳንን ባገኝላት እና ብትሰማው ወይ ብታየው እየለመንኩ በተከፋች ግማሽ ልቤ ከጎንጥ ጋር ወደቤት መንገዱን ተያያዝነው።

«ይገርማል! የዛን ቀን ሞቼ ቢሆን ኖሮምኮ መሞቴን እናቴም አጎቴም አይሰሙም። በዚህ አይነት ኪዳንም አይሰማም ነበር። ሊቀብረኝ ራሱ የሚመጣ ሰው ይኖር ይሆን?» አልኩኝ

« ህም የሌላውን እንጃ። እኔ የት ሄጄ ነው የማልኖር?»

«ሬሳዬን የሚሸኝ ስለማይኖር ሰብአዊነት ተሰምቶህ እንጂ መቼም <ወየው እትይ!> እያልክ አትቀብረኝም ነበር።» ስለው አይኑን ለአፍታ ከመንገዱ ወደእኔ አዙሮ ፈገግ ብሎ ዝም አለ። በሱው የፈገግታ ለዛ ቀጥዬ «ሆስፒታል እንኳን መጥተህ እየኝ ብዬ ብልክብህ <የቀጠሩኝ ደጆን እንድጠብቅ ነው > ብለህ አልላክብኝም? ዛሬ ቤቱን ጥለህ ገጠር ለገጠር አብረኸኝ ልትንከራተት?»
3.2K viewsAbela, 16:17
Open / Comment
2023-04-11 14:44:08 #ወይናደጋ
:
:
እኔ ቆላ እኔ ደጋ
የሚሞቀኝ የሚበርደኝ፤
ስትቀርበኝ የምቦርቅ
ስትርቀኝ የሚነደኝ፤
ግልፅ ፊቴ ይነበባል
እንቆቅልሽ መች አውቅና፤
ባብሮነቷ ጮቤ ምረግጥ
ከሰው ሳያት የምቀና፤
ሆድ መቋጠር አልችልበት
የልቤን ቃል የምናገር፤
ስታኮርፈኝ የምሻክር
ጥርሷን ስትገልጥ የምሆን ገር።
:
:
እሷ እንደሆን ለዘብተኛ
ስቃ አትስቅ አትጨነቅ፤
ከፋም ደላት ፊቷ ደረቅ፤
ውጭም አልጋ ቤትም አልጋ፤
ለብ ያለች ሴት ወይናደጋ፤
ትውደድ ትጥላኝ ልወቅ በምን፤
ፀሀይ ናት ስል ደግሞ ድምን።

#ሄኖክ_ብርሃኑ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.9K viewsAbela, 11:44
Open / Comment
2023-04-11 13:07:32
መርጌታ ጥበቡየባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ። 0960516183
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። 0960516183
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት


ከምሰጣቸው በትንሹ ይህንይ
መስላል
ለጥያቄወ 0960516183
ይደውሉ።
መርጌታ ጥበቡ
ጥበብ ህይወት ናት
0960516183ሀሎ ይበሉን

@merigeta_Tibebu
@merigeta_Tibebu
@merigeta_Tibebu
3.9K viewsAbela, 10:07
Open / Comment
2023-04-11 07:37:08 አይገባኝም

የቃል እንጂ የተግባር አይደለሁ ክርስቲያን
ግማሽ ልቤ ያንተ ግማሽ ደግሞ የሰይጣን
በገዳመ ቆረንቶስ የተፈተንክበት
በአይሁዳኑ እጅ በሰላሳ ዲናር የተገዛህበት
ስለ ሰው ልጅ ፍቅር የተገረፍክበት
ከዙፋንህ ወርደህ መቃብር ያደርክበት
የስቃይህ ወራት በአለም ሲታሰብ
የእኔ ግን ስራ ይከብዳል ቢነበብ
ከዙፋን የወረድክ ለእኔ እንደሆነ
እያወኩ እየገባኝ
ሀጥያት የሌለብህን ሲሰድቡህ
ሲመቱህ ዝም አልኩ እያየሁኝ
ለእኔ ታዲያ አምላኬ ምህረት ይገባኛል
ካንተ ብመለስስ ልቤ ልብ ይገዛል
በፆመ ሁዳዴ በሀምሳ አምስቱ ቀናት
እኔ የተገኘሁት ጭፈራ መጠጥ ቤት
ከስጋው ታቅቤ የሰው ስጋ ሳኝክ
ከወተት ርቄ አረቄውን ስጋት
በሰሞነ ህማማት በህማምህ ጊዜ
መገኘት ሲኖርብኝ አዝኜ ተክዤ
ከቤቴ መቅደስህ ኪርያላይሶን እያልኩ
ወድቄ ሰግጄ ስቃይህን እያሰብኩ
ማዘን ሲኖርብኝ እያሰብኩ ስቅለትህን
ህግህን አፍርሼ ዘነጋሁ እረፍትህን
ህማሙ ለእኛ ነው አይሳቅም ሲባል
ሆዴን ይዤ ሳኩኝ
የሞተው ለሰው ነው ጨዋታ የለም ቢባል
ጨዋታ ጀመርኩኝ
የአስቆርቱ ይሁዳ አቅፎ
ስለሸጠው መተቃቀፍ የለም
እኔ ግን ዘንግቼ ያገኘሁት ላይ ጥምጥም
በዚህ ስራዬ እኮ ምህረት አይገባኝም
ካለህበት ልደርስ ፍቃድ አላገኝም
አንተ ግን አምላኬ መሀሪ ነህና
ትላንት በእኔ ሀጢያት ሞትን ሞተህልኝ
ዛሬም በተግባሬ ፊትህን አልነሳኸኝ
እንዳንተ ሆኖ እንጂ
እንደ እኔ ሀጢያት እንደፈፀምኩት በደል
ምህረት ሳይገባኝ እገኝ ነበር ሲኦል።

Selito


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.3K viewsAbela, 04:37
Open / Comment
2023-04-10 20:50:06 የጠገበ ልቤን የሚወጥር ሙገሳ ጆሮዬ ገባ። ኪዳን ከልጆች ጋር ተጣልቶ ሲያለቅስ የሰፈር ማቴ ለእኔ ሊያሳብቅ ሲሮጥ አንድ አልፎ ሂያጅ «አሁን አንተ የአባትህ ልጅ ነህ? ያ አባትህ ቢያይህ እንዴት ይክፉው? ወንድ አይደለህ እንዴ ምን ያነፋርቅሃል? ልጅማ ወልዷል የሴት ወንድ፣ የአባቷ ልጅስ እሷ ናት።» ያለውን ኪዳን ሲነግረኝ ጥጋቤ አናቴ ላይ ወጥቶ አጎቴን አሳር አሳየሁት። እየሰነባበተ የሆነ ቀን አንድ የኛ መንደር ልጅ እና የአባቴ ገዳዮች ወገን ልጅ ገበያ መሃል በተነሳ የግል ፀብ ሲያያዙ መሃል ጥልቅ ብዬ <እጇ ላይ መሞቱ ነው> ብሎ ሰው ጠልቃ እስኪገባ ድረስ በጥላቻዬ ልክ ቀጠቀጥኩት። ከአጎቴ ውጪ ማንም የከፋው አልነበረም። ይባሱኑ መንደርተኛው «ቁርጥ አባቷን፣ የአባቷ ቢጤ አመፀኛ ፣ ይህቺማ የመንደሩ መድሃኒት ናት ፣ ቱ በሉ የአባቷን ደም ትመልሳለች። » እያለ ልክ እንዳደረግኩ ዓይነት በየቡናው እና ጠላ ቤቱ በወሬ ሲቀባበለኝ ባሰብኝ።

«እንደአባቴ ጫካ ካልገባሁ አልሽ!» ብሎ ሳቀ አሁንም ይሄን ሲያስታውስ «አንድ ቀን እርሻ ውዬ ስመለስ አጅሪት ለካ ያንቺ ቢጤ ወጠጤ ጎረምሶች ሰብስበሽ ሄደን ጠላቶቻችንን ካልገጠምን ብለሽ ልባቸውን ዝቅ አድርገሽ ልከሻቸው፣ ይሄ ውሻ ቢያሯሩጠው ሱሪው ላይ የሚንበጫበጭ ማቲ ሁላ <መሸፈቴ ስለሆነ ስንቅ አዘጋጁልኝ> ብሎ እናቱን ሲያውክ የሰፈሩ እናቶች ተሰብስበው ጠበቁኝ። <ይህችን ልጅ አደብ አስይዝልን! የልጆቻችንን ልብ ወደ ጫካ እያሸፈተች ነው።> ቢሉኝ እንደው ሳቄን መቆጣጠር ተሳነኝ ስልሽ! (አሁንም ከት ብሎ እየሳቀ) በሽመል ጦርነት ልትገጥሚ መሆኑ ነውኮ!!» እንባው እስኪወርድ ሳቀ። አጎቴ ሲያወራው ልጅነቴን ከመራራነቱ ይልቅ የተዋዛ ጨፍጋጋ ያደርገዋል። እያንዳንዷን ክስተት በቅደም ተከተል ሳይስት ሲያወራኝ ያኔ ተሰምቶኝ የነረውን ነገር ባላውቅም ዛሬ ላይ ግን ስሰማት ሜላት ምሬት ብቻ አልነበረችም።

17 ዓመት ሲሆነኝ ከአባቴ ሞት በኋላ ረጭ ብሎ የነበረው የሁለቱ ወገኖች ቁርሾ በሽመል የማይመከት የፀብ ጉርምርምታ ሆኖ ተጀመረ። ወጣቶቹ መሳሪያ ያለው በመሳሪያ የሌለው በጦር እና በጎራዴ እንዴት ጠላቶቻቸውን እንደሚመክቱ ሲመካከሩ አንደኛ የነገር ጠንሳሽ ሆኜ ተገኘው። ለካንስ ፀብ ፈጥሬ ቁምነገራቸውን ሳይቋጩ ስለምረብሻቸው ፈርተው ዝም አሉኝ እንጂ ከሴት ጋር በፀብ አውድማ መሰለፍን እንደውርደት ቆጥረውት ኖሮ ለአጎቴ መጥተው ነገሩት። ብመከር ብዘከር የ<አባቴን ገዳዮች፣ የእናቴን ደፋሪዎች የማገኝበት ብቸኛ አጋጣሚዬ ይሄ ነው። ቢከለክሉኝ ራሱ ተደብቄ እከተላቸዋለሁ።> ብዬ ፈረጠምኩ። የዛን ቀን በሩን ቆልፎብኝ የእህል ማዳበሪያ ሊቀበል ደርሶ እስኪመለስ የሳንቃውን በር ገንጥዬ ወንዶቹ የሚመካከሩበት ጫካ ሄጃለሁ። አጎቴ በጥቆማ ከቦታው ሲደርስ ከወንዶቹ መሃል ቆሜ <እኔ ነኝ ያለ ወንድ እጅ በእጅ አንድ ለአንድ ይግጠመኝ። አንዳችሁ ካሸነፋችሁኝ እቀራለሁ። አልበጠብጣችሁም። ሁላችሁንም ካሸነፍኩ ግን አብሬያችሁ እሄዳለሁ።> እያልኩ የሚጣላኝ ስጋብዝ ደረሰ። አጎቴ እንዳለኝ ከሴት ጋር ተደባድበው ቢሸነፉ ቅሌት እንደሆነ ስለገባቸው ሊደባደበኝ የደፈረ የለም። <መቼም አንቺም አንዱን ከጣልሽው በኋላ ወንድ ነኝ ያለ ደፍሮ ለመውደቅ አይመጣም ብለሽ እንጂ ያን ሁሉ ወጠምሻ እንደማትጥዪው ታውቂው ነበር።> አለኝ እንደመኩራት እያደረገው።

ከዛ በኋላ በምንም ሴትነቴ እንደማይመለስ ተስፋ ቆረጠ። እኔ እንዳላገኘው ደብቆ ያስቀመጠውን የአባቴን ሽጉጥ እና ታጣቂዎች በየቤቱ እየፈተሹ ነው ተብሎ ተቆፍሮ የተቀበረ ክላሽንኮቭ ጠመንጃውን አውጥቶ ሰጠኝ። ከመንደር አርቆ ወስዶ ኢላማ ያስለምደኝ ጀመር። አባቴ ከልጅነቴም መሰረታዊ ነገሮችን ከእናቴ ደብቆ ይዞኝ እየሄደ ያሳየኝ ስለነበር ብዙ አላስለፋሁትም። በመጨረሻም የአባቴን ገዳዮች የመጨረስ ሀሳብ ብቻውን ልቤን በሀሴት ሲሞላው ነው ሽማግሌ ልከው ፀቤ ላይ ውሃ የቸለሱበት።

ከእኔ ውጪ የቀረው ወጠምሻ መሳሪያውን ለታጣቂ አስረክቦ ጦርና ጎራዴውን ቀጥቅጦ የሽንኩርት መክተፊያ ቢላ አድርጎ ለሚስት እና ለእናቱ ሰጠ። ምንም እንዳልሆነ ሁሉ ሰላማዊ ህይወት መኖር ጀመረ። ጭራሽ ገበያ መሃል ሲገናኙ ሰላምታ መለዋወጥ ጀመሩ። ሚስቶች በመሃከላቸው ያለ የትዬለሌ ኪሎሜትር ርቀት ሳያግዳቸው ሽሮ መበዳደር ጀመሩ። እንደአጎቴ እምነት ከዚህ በኋላ ሴትነቴን ብቻ ሳይሆን ሰውነቴንም በከፊል ከዳሁ። የበቀል ጥሜን ያብርድልኝ እንጂ በመንገዴ የሚመጣ ማንም ሰው ቢሆን ከማስቀየም ወደኋላ የማልል አውሬ ሆንኩ። ቁጣዬን የምገልፅበት የማውቀው ብቸኛ መንገድ ፀብ ስለነበር <የምትጣዪው ብታጪ ከቆመ ግንድ ተጣልተሽ ትገቢ ነበር። የማደርገው ጭንቅ ጥብብ አለኝ።> ነበር ያለኝ አጎቴ። ሰላሙን የተቀበለ ሁሉ አጎቴንም ጨምሮ ጠላቴ ሆነ። መራር ሆንኩ። የቀን ተቀን የሆነ ቀን እንደምገድላቸው ነበር። አጎቴ በማያውቀው ምክንያት እንደዛ ሰፈርተኛውን እያሳቀቅኩ ግን ቆየሁ። አንድ ቀን ጭንቅህ ይብዛ ሲለው አንድ ወዳጁ ቲቪ ገዝቶ ሊያሳየን ተለማምኖ ይዞኝ እስከሄደ ቀን ድረስ። ቲቪ እንግዳ የሆነበት ብዙ መንደርተኛ ሰብሰብ ብሎ እስክሪኑ ላይ ባፈጠጠበት ያ ሰውዬ …… እናቴ ስትደፈር መጥቶ አይቶ ሱሪውን ሊፈታ ብሎ ሲጠራ የወጣው ሰውዬ አመዳም ካኪውን አውልቆ በውሃ ሰማያዊ ሱፍ ንግግር ያደርጋል። ሰውየው ሚንስትር ሆኖ ተሹሞ ብልግናውን ከአንድ ከተማ ወደ ሀገር አቀፍ የማዛመት እድል ከማግኘቱ በላይ የመንደሬው ማሽቋለጥ አንድዶኝ በጠበጥኩኝ።

«ሙሉሰውን አያችሁት? አሁንማ ጆሮው ቢቆረጥ የማይሰማ ባለስልጣን ሆነ።» እየተባባሉ ከዓመታት በፊት መንደራችንን አጋይቷት ፣ ሬሳ አስታቅፎን እየፎከረ እንደሄደ ረስተውት በኩራት ያወሩለታል። ብቻዬን የተበደልኩ አድርጌ የተሰበሰበውን ሰው ተሳድቤ ወጣሁ። በሚቀጥለው ቀን ኪዳንን አስከትዬ አጎቴ በሌለበት ቀዬውንም ለቅቄ ወጣሁ።

«ከዛስ?» አልኩኝ ተመስጬ ስሰማው ቆይቼ

«ከዛማ በእጄ ያሳደግኩሽ ልጄ ወሬሽን በእሩቅ የምሰማ ባዳዬ ሆንሽ። ብፈልግ ባስፈልግ እንዳትገኚ ስለፈለግሽ አጣሁሽ። አንቺም እንደእናትሽ ላትመለሺ መሄድሽን አምኜ ተስፋ በቆረጥኩ ሰዓት አንድ ቀን መንደርተኛው ጠላ ቤት ውስጥ ጉድ ጉድ እያለ ወሬ ሲፈጭ ደረስኩ። የምሽት የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ መታየትሽን <ልጅህ ዘንጣለች> ብለው ነገሩኝ። ምን ስታደርግ ታየች ብል <አታውቅም ኖሯል እንዴ የሚንስትሩ የሙሉሰው ሚስትም አይደለች? ከእርሱ ጎን ሆና ነው ባለፊልሙ የቀረፃት> ብለው መርዶዬን እንደምስራች ጋቱኝ።» ሲለኝ ጆሮዬም መሰለኝ።

«ሙሉ ሰው እናቴ……. » መጨረስ አንቆኝ ስንተባተብ

«ልትገያቸው ከመዘገብሻቸው ሰዎች መሃል ዋንኛውን ማግባትሽን ስሰማ የፍቅር እንዳልሆነ ጠርጥሬ ተከፋሁ። እንደባዳ ዜናሽን ከሰውም አይደል የምሰማው ? እንደፈራሁትም <ሚንስትሩ በገዛ ሚስታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።> የሚለው ዜና ሀገሪቷን ይንጣት ጀመር።» ብሎ ኩርምት ብሎ ተከዘ።

እቤት ካዝና ውስጥ ያገኘሁት የጋብቻ ሰርተፊኬት ትዝ አለኝ። ሙሉሰው!! ጠላቴን ነው ያገባሁት? ምን ምክንያት ይኖረኝስ ይሆን?


.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.6K viewsAbela, 17:50
Open / Comment
2023-04-09 18:10:08 በትክክልም ክፉ ሴት ነበርኩ ማለት ነው። የሚያዩኝ ሰዎች ዓይን ውስጥ ለሞላው ጥላቻ እና ፍርሃት ምክንያት ከክፉነቴ ውጪ ሌላ ሰበብ የለም። ባለፉት ቀናት ሁሉ የምሰማውን ድርጊቴን ምክንያት እያጋባሁ <እንዲህ ስለሆነ ሊሆን ይችላል ይሄን ያደረግኩት> እያልኩ ድርጊቴን በሰበብ እየደገፍኩ ራሴን ይቅር ለማለት ፣ ያለፍኩትን ጥፋት ለመካስ፣ በንሰሃ ተመልሼ የበደልኳቸውን በመልካም ስራ ልዋጅ ……… አውጠንጥኜ ነበር። የትኛውን ሀጢያቴን ከምን ጀምሬ ነው ይቅር የምለው? ማን ያውቃል ከዚህ የባሰም ፀያፍ ነገር ሰርቼ ይሆናል።

«ጎንጥ?» አልኩት ሰውየው ከወጣም በኋላ እዛው በቆመበት የነበረውን ጎንጥን

«አቤት እትይ?»

«ህገ-ወጥ አይደለም በሴቶች መነገድ? ያለው በሙሉ እውነቱን ይመስልሃል? መቼም ህግ መንግስት ባለበት ሃገር እንዲህ አይነት ነገር ስሰራ አንድ እንኳን ለህግ የሚያቀርበኝ ሰው ጠፍቶ ነው? ወይስ ህገ-ወጥ አይደለም?»

«አላውቅም እትይ! ስለነገርየውም ሰምቼ አላውቅ!»

«ነውረኛ ሴት ነበርኩ አይደል? አንተም አውቀህ እየደበቅከኝ እንጂ ብዙ የሰማኸው እና የምታውቀው ነውር አለኝ አይደል? ንገረኝ እስኪ ምን ዓይነት ሴት እንደነበርኩ እያወቅክ አሁንም ድረስ ለምን ትጠብቀኛለህ? ለአንተም ለተናኜም ቢሆን ክፉ ሴት እንደነበርኩ ግልፅ ነው። እንዴት ነው በደሌን ረስታችሁ ከጎኔ የቆማችሁት? እስኪ ንገረኝ አንተንስ ምን ቀምቼህ ይሆን? »

«እትይ ደክሞዎታል ትንሽ ይረፉ ግድ የለም!»

«አንቱ አትበለኝ ማለት አይሰማህም?» በማን እንደተናደድኩ አላውቅም ግን እየተቆጣሁ ነው።

«ይሁን! ይሰማኛል! አንቺ እሎታለሁ። ግን እንደው እትይ በማያስታውሱት ነገር መብሰክሰኩ ምንም ፋይዳ የለውኮ! …….»

«አንቱ አትበለኝ! አንቱ የሚባለው የሚከበር ሰው ነው። አንቱ የሚባለው ክብርን ለመግለፅ ነው። ለየትኛው ክብሬ ነው አንቱ የምትለኝ?» አሁንም እየተቆጣሁ እና እየጮህኩ ነው። እየተቆጣሁ ያለሁበት ምክንያትም እየተቆጣሁ ያለሁትም ሰው የቁጣዬ መንስኤ አለመሆናቸውን ባውቅም ልቆጣጠረው ግን አልቻልኩም። አልጋው ጫፍ ላይ በአንድ ጎኑ ተቀምጦ በግንባሩ እያየኝ እኔ ከምናገርበት ድምፅ በተቃራኒ በእርጋታ እና በለሆሳስ

«እትይ ማንም የነበሩ ቢሆን አለቃዬ ነበሩ! ኖትም! አለቃን አንቱ ማለት ያደግኩ የጎለመስኩበት ስርዓት ነው። ተው ካሉኝ ካስከፋዎት እተዋለሁ። ግን ከበሬታዬን የተውኩ እንዳይመስልብኝ!»

«አዎ ተው!» አልኩኝ ስናገር በነበረበት ቁጣ

«እሺ እተዋለሁ!» አባባሉ የተረጋጋ ነገር ....... የተከፋ ሳይሆን ለእኔ ያዘነ ዓይነት ነው። ለምን እሱ ላይ እየተናደድኩ እንዳለሁ አላውቅም። የሚያውቀውን ሁሉ አልነገረኝም ብዬ ስላመንኩ? ጭርሱኑ አብልጦ ሊጠላኝ ሲገባ አብልጦ ስለተንከባከበኝ? ወይስ የክፋቴን ልኬት በሱ ጥላቻ ልክ መመዘን ፈልጌ? ከሁሉ ከሁሉ ሚዛኔ እሱ እንዲሆን ለምን ፈለግኩስ? ለደቂቃ ዝም ማለቴን ተከትሎ እንደቅድሙ ጀርባዬን በቀስታ ወደላይ እና ወደታች ማሸት ጀመረ። ውስጤ እየጎፈላ የነበረ ንዴቴ እየበረደ በምትኩ ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ ተተካ። የፈለግኩት ማልቀስ ነበር።

« እንዴት አገኘሃቸው? ፖሊስ እንኳን ፈልጎ ያላገኛቸውን አንተ እንዴት አገኘሃቸው?» አልኩት ድንገት

«ፖሊስ አልፈለጋቸውም። ያልተፈለገ ወንጀለኛ እንዴት ይገኛል? መድሃንያለም ብቻ በሚያውቀው ምክንያት ፖሊሶቹ ይሄን ጉዳይ መንካት አልፈለጉም። እንደው እትይ ልቤ ሲነግረኝ የተኮሰቦትንም ሰው መፈለጉን እርም ብለው ትተውታል።»

«እነሱ እንዴት አላገኟቸውም አይደለም ያልኩህ አንተ እንዴት አገኘሃቸው ነው ያልኩት። ደግሞ አሁንም አንቱ ማለትህን ተው!» አልኩት በደከመው ለዛ

«መንገዱ ምን ያደርጋል እትይ? ዋናው መዳረሻውም አይደል? እንዴት እንዳገኘሁት ዝርዝሩ ምን ይፈይዳል? ዋናው መገኘቱም አይደል?»

«ለእኔ ዝርዝሩ ይረባኛል! ማወቅ እፈልጋለሁ። አውቀህ ነው የምትጠመው?» አልኩት መልሼ እየተቆጣሁ።

«ካሉ መልካም ….. ይቅር ይበሉኝ ካልሽ ይሁን! የሰው ፊት አየሁ!» ብሎኝ ይቀጥላል ብዬ ስጠብቅ ልክ የጠየቅኩትን የመለሰ ይመስል ዝም አለ።

«ምን ማለት ነው?»
«እንዴት አገኘኻቸው? አይደልም ጥያቄ …. ዎ …ሽ ? <የሰው ፊት አይቼ!> ነው መልሱ! ከሰው ፊት ቆምኩ!» አለ መልሶ። ከሰው ፊት መቆም ወይም የሰው ፊት ማየት ሀሳቡ የደበደቡኝን ሰዎች ከማግኘት ጋር የሚያያዝበት ገመድ በግልፅ ባይገባኝም እሱ ሲለው ደስ የሚል ነገር እንዳልነበረ ለማወቅ አልተቸገርኩም። ቃላቶቹን እየረገጣቸው ባለመደሰት ነው ያወራው።

«የማንን ፊት ነው ያየኸው? ማን ፊት ነው የቆምከው?» እያልኩት በጭንቅላቴ ውስጥ ድንበር ላበጅለት የማልችለው ሀሳብ ይጓዛል። ጎንጥ ራሱ ማን ነው? ፊቱን አይቶት ወይም ፊቱ ቆሞ ከመኪና ታርጋቸው ውጪ ስለማንነታቸው ምንም ፍንጭ ያልነበራቸውን ደብዳቢዎቼን ያስገኘለት ማነው? ለሰከንድ ክፉ ሀሳብ ሽው አለ። ጎንጥ ራሱ ነኝ ያለኝን ሰው ባይሆንስ?


.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
510 viewsAbela, 15:10
Open / Comment
2023-04-09 18:10:08 የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........


(ሜሪ ፈለቀ)

ክፍል 9

ፍርሃት ልቤን ከደረቴ ጎትቶ ሊያስወጣት ታገለኝ። ሳይታወቀኝ ዓይኔን ከድኜ እግሬን ሰብስቤ ጉልበቴን አቅፌ ጥቅልል አልኩ። ጎንጥ በፊት ለፊቴ መጥቶ ጉልበቴን ያቀፍኩበትን እጄን አምባር ማሰሪያው ጋር ያዝ ሲያደርገኝ ዘለልኩ። ሰውነቴ በሙሉ እየተንቀጠቀጠ ነበር። በሌላኛው እጁ ጀርባዬን እንደልጅ አሸት አሸት አደረገኝ እና ወደጆሮዬ ጠጋ ብሎ

«እትይ ይቅርታ ሊጠይቆት ነው የመጣው! እኔ እዚህ ቆሜ ማን አባቱ ምን ያደርገኛል ብለው ነው የሚፈሩት?» ያለኝ መርበትበቴ አናቴ ላይ ወጥቶ የሰማሁት የቅዠት ድምፅ ይሁን ወይም ያለው ነገር ከነጭራሹ የገባኝ ይሁን እንጃ ብቻ የተናገረበት ድምፅ እና ጀርባዬን ከላይ ወደታች እያሸ የሚያባብለኝ እጁ አላውቅም በአፌ ልትወጣ ጉሮሮዬጋ እየደረሰች የምትመለስ ልቤን በቀስታ ወደቦታዋ መለሳት። በቀስታ ዓይኔን ገልጬ ሰውነቴን ዘና ለማድረግ እየሞከርኩ እየሆነ ያለውን ማጤን ጀመርኩ። እንግዳው ሰው በእኔ አልጋ እና በበሩ መሃል ያለ ቦታ ላይ ቆሞ አንዴ እኔን አንዴ ጎንጥን ያያል። ይሄኔ ነው ከደበደቡኝ ሰዎች መሃል አንዱ መሆኑ የገባኝ እንጂ የዛን እለት ምሽት ፊታቸውን በስርዓት የማይበት እድል ስላልነበረኝ ላውቀው አልችልም ነበር። አይቼው የነበረ ቢሆንም እንኳን በዛሬው ሁናቴው ላስታውሰው አልችልም ነበር። ፍርሃቴ ትንሽ ገለል ሲልልኝ ፊቱ ‘ንፋሱ ተንፍሶ ህፃናት እየተቀባበሉ የተጫወቱበት ኳስ’ መስሎ መጨረማመቱን አየሁ። ግንባሩ ላይ ሁለት ትንንሽዬ ፕላስተር ተለጥፎበታል። ጎንጥን አየሁት። በዓይኑ ሰውየውን ወደ እኔ እንዲጠጋ አሳየው። በዓይኑ ገፈተረው ብል ይቀለኛል። ወደ እኔ እየተራመደ ሲጠጋ እያነከሰ መሆንኑን አስተዋልኩ።

«ይቅርታ!» አለኝ አጠገቤ ደርሶ መሬት መሬቱን እያየ። ጎንጥ የሆነ መልእክት በማስተላለፍ አይነት ጉሮሮውን ጠረገ።

«ይቅርታ አድርጊልኝ! አንቺ ላይ እጃችንን ማንሳት አልነበረብንም! በእኔም በጓደኛዬም ስም ይቅርታ እንድታደርጊልን ልለምንሽ ነው የመጣሁት!» ብሎ እሱም የሆነ መልእክት እንደማስተላለፍ ጎንጥን አየው። ጎንጥ ጭንቅላቱን በአወንታ ነገር ነቀነቀ።

«እሺ» ከማለት ውጪ ግራ የገባው ጭንቅላቴ መልስ አላቀበለኝም። እንደአመጣጡ ፊቱን አዙሮ እግሩን እየጎተተ ሲወጣ ጭንቅላቴ ያልተዘጋጀበትን ጥያቄ አፌ ጠየቀ

«ለምን? ለምንድንነበር ግን እንደዛ ያደረጋችሁት?» አልኩኝ። መለስ ብሎ እኔን ሳይሆን ጎንጥን አየው። እኔም ወደእሱ ዞርኩ።

«የተጠየቅከውን መልስ!» አለው እንደትእዛዝ

«እህቴን …… ፍሪታን ስለቀማሽኝ። ተናድጄ ነበር። በፀባይ ላናግርሽ ስራሽ ቦታ ድረስ ብመጣም አላገጥሽብኝ። እኔ አቅሜ ጉልበቴ ብቻ ነው። አንቺ የገንዘብ አቅም አለሽ ፣ በአንድ ፉጨት ያልሽውን የሚፈጽሙልሽ ቁልፍ ሰዎች አሉሽ፣ ፖሊሶቹ በእጅሽ ናቸው፣ በዛ ላይ ጉልበትም መሳሪያም አለሽ! ........ በእህቴ ገላ አንቺ ገንዘብሽን ስታካብቺ አንጀቴ እየተቃጠለ ዝም ከማለት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር። ባለፈው ሳምንት አደጋ ደርሶብሽ ምንም እንደማታስታውሺ ስሰማ ደስ አለኝ። (ቀና ብሎ ጎንጥን አይቶ ቀጠለ) እየተከታተልኩሽ ነበር። » ብሎኝ ትከሻውን ሰበቀ። ምንም እንደማላስታውስ ካወቀ የነገረኝ ነገር እንደማይገባኝ እንዴት ጠፋው? ቀና ብዬ የአልጋውን ራስጌ ተደግፌ ተቀመጥኩ። ከምን ጀምሬ ምን እንደምጠይቀው ግራ ገባኝ። ከነአካቴው መጠየቁ ራሱ ልክ ይሆን አላውቅም! የተናገረው ነገር ውስጥ ምንም ለልክ የቀረበ ድርጊት መች አለ? አሰላስዬ ሳልወስን አፌ ቀደመኝ።

« እህትህን? ምን አድርጌ ነው የነጠቅኩህ? በእህቴ ገላ ያልከኝ እህትህ ምንድነው የምትሰራው? እንዴት ነው እኔ በእህትህ ….. (እሱ ያለውን መድገም ዘገነነኝ) እየተከታተልከኝ ከነበር ምንም እንደማላስታውስ የሰማኸው እውነት መሆኑን ማረጋገጥ አይከብድህም መቼም? » አልኩኝ ፍርሃቴ ድምጥማጡ ጠፍቶ። እሱ አሁንም በማስፈቀድ አይነት ጎንጥን አየው። በቁመት ከጎንጥ ጋር ተቀራራቢ ናቸው። ጎንጥም ግዙፍ ዓይነት ወንድ ቢሆንም ደብዳቢዬ ግን የበለጠ ጡንቻው የተወጣጠረ እና ደረቱ የተነፋፋ ነገር ነው። እጅ በእጅ ቢያያዙ ማንም ሰው የሚያሲዘው በደብዳቢዬ ጡንቻ ነው። ታዲያ ጎንጥ ምን ቢያደርገው ወይስ ምንስ ቢለው ነው ይሄን የሚያክል ሰውዬ እንዲህ የሚንበጨበጨው? የተነፈሰ ባሎኒ ኳስ ካስመሰለው በኋላ እንኳን እዚህ ድረስ መጥቶ ይቅርታ እንዲጠይቀኝ ያስደረገው ያልገባኝ ነገር ምን ተከውኖ ነው?

«እናንተ ቤት ስትሪፐር ናት! (እንደማፈርም እንደማዘንም የቀላቀለው ስሜት ድምጹን ወሮታል። ያለኝ ነገር እንዳልገባኝ ሲያውቅ አሁንም ጎንጥን ዞሮ አየው። ጎንጥ በአይኑ <ቀጥል> እንደማለት ነዳው።) አንድ እህቴ ናት ያውም ታናሼ! ልጠብቃት ይገባ ነበር። ማታ ማታ ሆቴል ውስጥ ሪሴፕሽንነት ስራ አገኘሁ ስትለኝ እንኳን <አይሆንም አንቺ አርፈሽ ተማሪ። እኔ አኖርሻለሁ> ብያት ነበር። እንቢ ብላ ስራውን መጀመሯን ነገረችኝ። የምትሰራበትን ቦታ ልትነግረኝ አለመፈለጓ ስለከነከነኝ የሆነ ቀን ተከተልኳት እና እናንተ ክለብ ደረስኩ። (ለሰከንዶች ዝም አለ። የሆነ የሚቀጥለውን ለመናገር ጉልበት እንደሚሰበስብ ያለ ዝምታ) በአይኔ እንኳን ጫን ብዬ ላያት የምሳሳላት እህቴ ስራዋ እቤታችሁ ለሚመጡ ነውረኛ ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች እርቃኗን እየደነሰች ማስደሰት መሆኑን አየሁ።» ብሎ ሆነ ብሎ ይመስለኛል ፊቴ ላይ አተኮረ። መደበቅ ያልቻልኩት ድንጋጤ እና መደናገር ፊቴ ላይ ተተረማመሰ። እሰራ የነበረው ስራ ፅድቅ ያለበት አለመሆኑን ምንም በማያስታውስ ወና ጭንቅላቴ እንኳን መገመት ከባድ አልነበረም። ሴትን ልጅ ራቁት እያስጨፈሩ ገንዘብ ማግኘት ግን ሌላ ደረጃ ብልግና መሰለኝ። ከዳዊት ጋር ቀን የሄድኩኝ እለት ያየሁት …… ቤቱ ውስጥ የነበሩት የተለያዩ ክፍሎች…….. ክፍሎቹ ውስጥ የነበሩት ሶፋው መሃል የተንጣለሉት አልጋ የመሰሉ መሃከላቸው ላይ የቆመ ብረት ያለባቸው ሰፊ ክብ መድረኮች ……. መድረክ ነገሩ ላይ አለመልበስ ለብሳ እንቅልፍ ወስዷት የነበረችው በጡት ማስያዣ እና በፓንት የነበረችው ቆንጅዬ ልጅ ……. አንድ በአንድ ከነገረኝ ጋር ላዛምድ ሞከርኩ። ልጅቷ ስታየኝ እየተደነባበረች «አሁኑኑ ተጣጥቤ ፏ እላለሁ! ይቅርታ» ብላኝ የነበረው ይሄን ልትሰራ ነበር? እሷው ልጅ ትሆን እንዴ እህቱ?

ጭንቅላቴ ውስጥ የሚተረማመሱትን ጥያቄዎች ሁሉ መጠየቅ ቢያምረኝም የሰውየው ሁኔታ ለመጠየቅ የሚጋብዝ አይደለም። ተገድዶ ቆመ እንጂ በጣም እንደሚጠላኝ ያስታውቃል።

«አሁን ላይ ሆኜ ……ምን አድርጌ እንደነበር ወይም ለምን እንዳደረግኩ የማውቀው ነገር የለም። ምንም ይሁን ብቻ እህትህንም አንተንም ስለበደልኳችሁ ነገር በጣም ይቅርታ! ባለፈው ህይወቴ በጣም ክፉ፣ እግዜአብሄርን የማልፈራ ጨካኝ ፣ ሀጢያትንም ወንጀልንም የምደፍር ሴት እንደነበርኩ ቀስ በቀስ እያወቅኩ ነው። የእኔ ዛሬ ሌላ ሴት መሆን ወይም ምንም አለማስታወስ የደረሰብህን በደል እንደማይሽረው አውቃለሁ። በቃ ግን በጣም ይቅርታ አድርግልኝ ከማለት ውጪ ማድረግ የምችለው የለም።» አልኩት ከልቤ። ምንም እንዳልተዋጠለት ያስታውቃል። <አሁንስ መሄድ እችላለሁ?> በሚል አስተያየት ጎንጥን አየው። የጎንጥን ፈቃድ በምልክት ሲያገኝ ወጥቶ ሄደ።
298 viewsAbela, 15:10
Open / Comment
2023-04-09 17:49:50 የፍቅረኛችሁን   ሰው   ስም   የመጀመርያ ፊደል   በመጫን   የምታገኙትን   የፍቅር ቻናል   ተጋበዙልኝ ︎


ዳይ ለሁላችሁም ነው እንዳያመልጥዎ!!
289 viewsPapa , 14:49
Open / Comment
2023-04-09 14:02:07
++++++++++++++++++++
ሆሣዕና....
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤
የታሰረች አህያ፥
ፈተው እንዲያመጡ፥ ላካቸው ክርስቶስ።
እነዚህ ለጌታ፥ ያስፈልጋሉና፤
የታሰረችውን፥ አምጡልኝ ፍቱና።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ላሳየሽ በጎነት ላሳየሽ ትህትና፤
እልል በይ ዘምሪ፥ እያልሽ ሆሣዕና።

አዳኝና ትሁት፥ ፃድቅ ንጉስሽ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ መቷል አዳኝሽ።
ዘንባባ አንጥፉ፥ ህፃናትም ውጡ፤
አሁን አድን በሉት፥ ምስጋናችሁን ስጡ።
ሆሣዕና....
ደግሞም በዚያችው ቀን፥ ከመቅደስ ገባና፤
የሻጮችን ዙፋን፥ ገለበጠውና።
የወንበዴዎች ዋሻ፥ ያረጉትን ቤቱን፤
ርግብ ሻጩን ሰዶ፥ አፀዳ መቅደሱን።
የገንዘብ ለዋጩን፥ ወንበር ገለበጠ፤
በመቅደሱ ዙፋን፥ ጌታ ተቀመጠ።

ከሚጠቡትም አፍ፥ ምስጋና አዘጋጀ፤
አምላክነቱንም፥ ለአለም አወጀ።
የምትቀድሙ የምትከተሉ፥ ሆሣዕና እያላችሁ፤
በአርያም ይሰማ፥ መዝሙር እልልታችሁ።

አቤቱ ጌታ ሆይ፥ አሁን አድን በሉት፤
ልብሳችሁን ዘርጉ፥ ዘምባባ አንጥፉለት።
አሁን አድን ብለን፥ ወተናል በመንፈስ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ አምላካችን ሲደርስ።
የዘካርያስ ትንቢት፥ አልቀረም ተፈቷል፤
በውርንጫ ጀርባ ፥ንጉሳችን መቷል።
+++++++++++++++++++++

ታዜና
" የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤"
(የማርቆስ ወንጌል 11:9)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.8K viewsAbela, edited  11:02
Open / Comment