🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 135.71K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 19

2023-04-12 21:46:28 የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........


(ሜሪ ፈለቀ)

ክፍል 17

የምጣደፈው ጎንጥን ሽሽት ይሆን ኪዳንጋ ለመድረስ ተቻኩዬ ወይም በሁለቱም ምክንያት የታክሲው ሹፌር ትዕግስቱን እስኪያንጠፈጥፍ ድረስ አቻኩለው ጀመር። <ምን ያህል ቀረን?> ፤ <ትንሽ ፈጠን ማለት አትችልም?> ፤ < ሌላ ያልተዘጋጋ አማራጭ መንገድ አይኖርም?> ፤ < አሁንም ብዙ ይቀረናል?> አንድ አይነት ጥያቄ በየሁለት ደቂቃው እየደጋገምኩ ፤ ግማሽ ጎኔ ወደፊት ግማሽ ጎኔ ወደኋላ በሆነ አቀማመጥ ፤ በአንድ ዓይኔ ወደኪዳን (ወደፊት) በአንድ ዓይኔ ወደጎንጥ (ወደኋላ) ሳማትር

«ሴትዮ ካልሆነ ውረጂ እና ሌላ ታክሲ ተሳፈሪ! አይታይሽም እንዴ በማይነዳበት እየነዳሁልሽ? ሆ! ዛሬ ምኗን ነው የጣለብኝ ባካችሁ?» አለ ያለመታከት ሲመልስልኝ ቆይቶ ከትዕግስቱ በላይ ስሆንበት

«ይቅርታ በጣም ስለቸኮልኩ ነው። ይቅርታ በቃ እንደሚመችህ አድርገህ ንዳ!!» አልኩኝ። ታክሲው ውስጥ በቦርሳ የያዝኩትን የቱታ ሱሪ ከቀሚሴ ስር ለብሼ ሳበቃ ቀሚሴን አውልቄ ወደቦርሳው ከተትኩ።

እያደረግኩት ያለሁት ድፍረት ይሁን ድድብና መመዘን የምችልበት መረጋጋት ላይ አልነበርኩም። ምናልባት አለማወቅ ደፋር ያደርግ ይሆናል ወይም ደደብ!! ጎንጥ ሰዎቹን ስለሚያውቃቸው ይሆናል የሚጠነቀቀው እና የሚፈራልኝ። የማላውቀውን ሰው ወይም ልገምት የማልችለውን የሚገጥመኝን ነገር በምነኛው መጠን ልፈራ እችላለሁ? እስከገባኝ ድረስ ቢያንስ አለማወቄ ጎንጥን እስከአለመከተል ድረስ ደፋር ወይም አላዋቂ አድርጎኛል።

የተባለው ቦታ ስደርስ ለቀጠሯችን 20 ደቂቃ ይቀረኛል። ከታክሲው ከወረድኩ በኋላ እንደማንኛውም በአካባቢው እንዳለ ተንቀሳቃሽ ግለሰብ የአዘቦት ክንውን እየከወንኩ ለመምሰል ጣርኩ እንጂ እንደሌባ ዓይኖቼም አካሌም እየተቅበጠበጠ ነበር። እስከዚህ ደቂቃ ያልተሰማኝ ፍርሃት አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ይገለባበጥ ጀመር። መቆምም መራመድም መቀመጥም ሰው ይቸግረዋል? ወደላይ ትንሽ ራመድ እልና ደግሞ በተቃራኒው አቅጣጫ እመለሳለሁ። በመሃል እንደማቅለሽለሽም ያደርገኝና መሃል የእግረኛ መንገድ ላይ ቁጢጥ እላለሁ። ከመንበጭበጬ ብዛት ሽንቴን እላዬ ላይ የምለቀው መሰለኝ። ሰዓቴን በ60 ሰከንድ ውስጥ 120 ጊዜ አያለሁ። ደቂቃው ሰዓቴ መስራቱን ያቆመ ይመስል ፈቅ አይልም። ለአፍታ የጎንጥ እጅ ናፈቀኝ። ወላ ተከትሎ ደርሶብኝ በሆነና የፈራሁ ሲመስለው ሁሌም እንደሚያደርገው በዛ ሰፊ መዳፉ እጄን አፈፍ አድርጎ እጁ ውስጥ ቢደብቀው። «……. እኔ የት ሄጄ? …… ማን አባቱንስ እና ነው? » ቢለኝ። ሜላት ምንድነው ያደረግሽው?

የምጠብቀው እንዲህ ነበር። የሆነ ቀን እንዳየሁት የሆነ ፊልም። ጥቁር መኪና መጥቶ አጠገቤ ገጭ ብሎ ይቆምና ! በሩ ብርግድግድ ብሎ በተጠና ስልት ሲከፋፈት ፊታቸው የማይታዩ መሳሪያ የታጠቁ ግባብዳ ሰዎች ከመኪናው ዱብ ዱብ ብለው ያስቀመጡትን የሆነ ሻንጣ ብድግ እንደማድረግ ብድግ አድርገውኝ እየጮህኩ እግሬ አየር ላይ ተንጠልጥሎ ስፈራገጥ ምንም ሳይመስላቸው ወደመኪናው ይወረውሩኝና ልክ እንደቅድሙ በተጠና መንገድ በሩን ድው ድው አድርገው ዘጋግተው ይዘውኝ ይሄዳሉ።

የሆነው እንዲህ ነው። እግሬን ብርክ ይዞት ጉልበቴን ደገፍ ብዬ ባጎነበስኩበት አንዲት ቆንጅዬ ጅንስ ሱሪ በቲሸርት ለብሳ አጭር ጥቁር ጃኬት የደረበች ወጣት ሴት ከጀርባዬ ጠራችኝ። «ሜላት!» ለሰላምታ እጇን ዘረጋችልኝ። እነሱማ ሰላም ሊሉኝ አይችሉም ብዬ እያሰብኩ እጄን ዘረጋሁ!!

«ዝግጁ ነሽ?» ስትለኝ ማሰቢያዬ ተዛባ! ለምኑ ነው የምዘጋጀው? ለመታገት ዝግጅት? <አዎ! እጄን ለካቴና በቅባት አሸት አሸት አድርጌ አዘጋጅቸዋለሁ። ድንገት እጃችሁ ካረፈብኝ ዱላ መቻያ ደንደን እንዲል ቆዳዬን ወጠርጠር አድርጌ አለማምጄላችኋለሁ….. > እንድላት ነው ተዘጋጀሽ የምትለኝ? እሷ ቀጠል አድርጋ ከፊቴ ወደቆመ ዘናጭ ነጭ መኪና እየጠቆመችኝ ፈገግታዋ የሆነ የተንኮል ዓይነት እየሆነ « …. ግርግር አንፈልግም አይደል?» ብላ አጭሩን ጃኬቷን ከፈት አድርጋ ሽጉጧን አሳየችኝ። ለስሙማ እኔምኮ ሽጉጤን ጎኔ ላይ ሽጬዋለሁ። ምን ላደርግበት እንደሆነ ያሰብኩት ባይኖርም ለዝህች በቆንጆ ፊቷ ለሸወደችኝ ልጅ ግን ሽጉጥ ሳይሆን የመዘዝኩት እጄን ነው ለሰላምታ የዘረጋሁት።

ወዳሳየችኝ መኪና ሄድኩ። እያገተችኝ ሳይሆን የሆነ በክብር እንግድነት የተጠራሁበት ቦታ ልታደርሰኝ ነው የሚመስለው። የኋላውን በር ከፍታ ያንን ተንኮለኛ ፈገግታዋን እያሳየችኝ እንድገባ ጋበዘችኝ። በአጠገባችን የሚያልፉ ሰዎችን <ኸረ በትኩረት ለአፍታ እዩኝ እየወሰዱኝ ነው!> ብል ደስ ባለኝ። ማንም ለአፍታ እንኳን ገልመጥ አድርጎ ያየኝ የለም። በየእለት ተእለት ውሏችን ልብ ያላልናቸው ስንቶች ይሆኑ ከአይናችን ስር ብዙ የሆኑት?

መኪና ውስጥ ከኋላ ታግቼ ባይሆን « ምን ሆኖ ነው እንዲህ የቆነጀው?» የምለው የሚመስለኝ ፈርጣማ ወንድ ተቀምጧል። እንደገባሁ ቀለበኝ ማለት ይቀላል። ፓንቴ ስር መግባት እስኪቀረው እንያንቀረቀበ ሲፈትሸኝ ልጅቷ ከፊት ወንበር ሆና ሽጉጧን አስተካክላ ትጠብቀቃለች። የምራቸውን ነው? እዝህች የክብሪት ቀፎ የምታክል መኪናቸው ውስጥ ከነሹፌሩ ለሶስት ከበውኝ ታጠቃናለች ብለው ነው ሽጉጡ? ሽጉጤን ከፊት ለተቀመጠችው ሴት እንደመወርወር አድርጎ አቀብሏት በምትኩ የሆነ ጨርቅ ስትወረውርለት ነገረ እቅዴ ሁሉ ጎንጥ እንዳለው የጅል መሆኑ ገባኝ። የሰውየው መዋከብ ቶሎ የመጨረስ ውድድር ያለበት ነው የሚመስለው። በጨርቁ ዓይኔን ሲሸፍነው መኪናው መንቀሳቀስ ጀመረ። በዚያው ፍጥነት እጄ ላይ ካቴና አሰረ።

ለምን ያህል ደቂቃ እንደተጓዝን አላውቅም!! ወይ ከላይ ወይ ከታች እንዳያመልጠኝ ከሰውነቴ ጋር ግብ ግብ ላይ ነበርኩ። የእነርሱ ዝምታ ደግሞ ጭራሽ ያለሁት መኪና ውስጥ ሳይሆን ከሞት በኋላ የሰይጣን ፍርድ ዙፋን ስር ቀርቤ አስፈሪ ፍርድ ለምሳሌ እንደ < ለእሷ እሳቱ አስር እጥፍ ይጨመር!! ይሄማ ለሷ ሻወር መውሰጃዋ ነው!! ይንተክተክላት ውሃው እንጂ! > የሚል ፍርድ እየተጠባበቅኩ መሰለኝ። ከመኪናው ወርደን የበረበረኝ ሰውዬ ይመስለኛል ብብቴ ስር ገብቶ ጨምቆ ይዞኝ እየነዳኝ በእግር የሆነ ያህል እንደተጓዝን አይኔን የሸፈነኝ ጨርቅ ሲነሳ የተንጣለለ በውብ እቃዎች የተሞላ ሳሎን ራሴን አገኘሁት። ያሰረልኝ ሰውዬ ከእጄ ላይ ካቴናውን አወለቀው።

እንግድነት የሄድኩ ይመስል እንድቀመጥ ታዘዝኩ። ያ ሰውዬ በቪዲዮ ያወራሁት ሰውዬ እና አንዲት መሬቱን የነካ ጌጠኛ ቀይ ቀሚስ የለበሰች ሴት ተቀምጠዋል። ከእነርሱ በተጨማሪ ይዞኝ የገባው ሰውዬ እና ትንሽ ቁመቱ አጠር ያለ መሳሪያ የታጠቀ ሰውዬ ብቻ ናቸው ክፍሉ ውስጥ ያሉት። ሴትየዋ የጠቆመችኝ ከፊታቸው ያለ ሶፋ ላይ ለመቀመጥ ቂጤን ሳሾል «ከመጨዋወታችን በፊት እንዳው ለመተማመኑ …..
1.3K viewsAbela, 18:46
Open / Comment
2023-04-12 20:00:51 «በህይወት አለሽ? በህይወት እያለሽ ነው ልታዪኝ ያልፈለግሽው? ምን ሆነሽ እንደሆነ ብቻ ንገሪኝ? ደህና ሆነሽ ነው?» እያለች ማልቀስ ጀመረች። በጥይት መመታቴን ነገርኳት። መርሳቴን ግን ዘለልኩት። ደግሞ ወቀሳዋን ትታ ለእኔ ማዘን ጀመረች። ዞር ብላ ጎንጥን በ<ማንነው ?> አይነት ምልክት ሰጠችኝ። አጠያየቋ እንደምነግራት እርግጠኛ የሆነ ነው። የቀረቤታዋ ልክ ብዙ ነገር የምናወራ ሰዎች እንደነበርን ያስታውቃል።

«ጎንጥ ዘበኛዬ ነበር።» አልኳት። ለምን <ነበር> እንዳልኳት አላውቅም!
«ጎንጥ ጎንጤ? ጎንጤ ጥጋቡ? » ብላ ጮኸች። ስለጎንጥ የምታውቀው ምን እንደሆነ ባላውቅም የግርምት አጯጯኋ ስለዘበኝነቱ ብቻ እንዳልነገርኳት ያስታውቃል። ለአንድ አፍታ ሁሉንም ዝርግፍ አድርጌ ነግሬያት የምታውቀውን ብትነግረኝ ተመኘሁ።

«ኪዳንን ይዘውታል! ቪዲዮዎቹን ካልሰጠኋቸው እንደሚገድሉት ነግረውኛል።» አልኳት የማወራው ነገር አዲሷ እንደማይሆን እርግጠኛ ሆኜ።

«ኪዳን ምን ሊሰራ መጥቶ አገኙት? ሺት!! እርግጠኛ ነሽ? እኚህ አጋሰሶች!! የፈራሽው አልቀረም!! » ብላ በድንጋጤ እና በንዴት መሃል ዝም አለች።
«አዎ በቪዲዮ አይቼዋለሁ። አውርቼዋለሁም። ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ?» አልኳት ሌላ ፍንጭ ከሰጠችኝ ብዬ
«መቼም አትሰጫቸውማ? ሌላ መላ መቼም አይጠፋሽምኣ? »
«በኪዳን ነፍስ ቁማር መጫወትም አልችልም!»
«እየቀለድኩ ነው በይኝ!! ጥይቱ የዋህ አድርጎሻል ልበል? ወይስ ሚሞርሽንም ነው ያጠበልሽ?» ያለችው ለአባባል ነበር እኔ ግን አዎ ብያት ሁሉንም ብትነግረኝ ፈለግኩ። የጎንጥን ማስጠንቀቂያ ችላ ማለትም ከበደኝ። እራሱን ሳላምነው ቃሉን ለምን እንደማምን ምክንያት የለኝም። ግን መጠንቀቅ አይከፋም። እሷ ቀጠል አድርጋ

«ከዚህ በፊት ከእጃቸው ፈልቅቀሽ ወስደሽዋል። አሁንም ተረጋግተሽ አስቢ እና መላ አታጪም!!»
«ተረጋግቼ የማስብበት ጊዜ የለኝም!! የሰጡኝ ሰዓት ሊያልቅ ሶስት ሰዓት ነው የቀረው!» ስላት የሆነ ግራ ያጋባኋት አይነት በጥያቄ አስተዋለችኝ። አለባበሴን ጭምር በዓይኗ ለቀመች እና
«ምንድነው እሱ? ከመቼ ወዲህ ነው እንዲህ መልፈስፈስ ያወቅሽበት? የሆነማ ልክ ያልሆነ ነገር አለ። ደግሞ ልስጣቸውም ብትይ ሴትየዋን በ3 ሰዓታት ውስጥ አጊንተሽ አንደኛውን ኮፒ ልትቀበያት አትችዪም!! ነው ወይስ ኦልረዲ አጊንተሻታል?»

«ሴትየዋን?» ካልኩ በኋላ ሳላስበው « የአቅሜን እሞክራለኋ» አልኳት መልሼ!! መልስ የሰጠችኝ መሰለኝ። ለሰዎቹ የሰጡኝን የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ምክንያት!! የምጠይቃት ብዙ ቢኖርም!! በምን መንገድ እን,ደምጠይቃት ካለማወቄ የእሱን እንቢታ ጥሶ ሌላኛው ጠባቂ እመቤትን እንዲጠራልኝ ያስገደደው ልጅ እግር ጠባቂ ሰዓታችን ማለቁን ከግልምጫ ጋር ይነግረኛል። ለእመቤት መልሼ እንደምመጣ ነግሬያት። ወደከተማ መመለስ ጀመርን።

«ሴትየዋ ያለችሽ ማን ትሆን?» ሲለኝ ያወራነውን ሁሉ እንደለቀመ ገባኝ።
«አላውቅም! መርሳትሽን አትንገሪያት አላልክም? ማናት ብዬ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ? ሁሉን ነገር ታውቅ የለ? ይሄ እንዴት አመለጠህ?» ብዬ ጮህኩበት

«ታዲያ ምን የሚያስቆጣ ተናገርሁ? ቃሌን ያለማመንና ሴትዮይቱን ማመንምኮ ያንቺ ድርሻ ነበር።» አለ ተረጋግቶ።

«ለማንኛውም እቤት ንዳኝ!! ተረጋግቼ የማስብበት ሰዓት እፈልጋለሁ።» አልኩኝ። ከዛ ማውራት የእሱ ተራ ዝም ማለት የእኔ ተራ ሆነ።

« አሁን እኔና አንቺ አንባጓሮ የምንፈጥርበት ሰዓት አይደለም! በአንድነት መላ ብንዘይድ አይበጅም? ከሰውየው ጠባቂዎች አንዱ ወዳጄ ነው። ኪዳን ያለበትን አድራሻ ማግኘት ከቻልን መልዕክት አኑሬለታለሁ። እስታሁን የምትመጪበትን አድራሻ አልላኩም? መላክ ነበረባቸው!! ትክክለኛ አድራሻውን እንደማይልኩልሽ ግልጥ ነው። ከሆነ ቦታ ይቀጥሩሽና ነው በራሳቸው መኪና የሚወስዱሽ!! እርግጥ አድራሻውን ከደረስንበት እነርሱ የቀጠሩሽ ቦታ ሲመጡ እኛ ቀድመናቸው ቦታው እንደርስ ነበር ….. » እሱ እቅዱን ከጅምር እስከ ፍፃሜ ሲነግረኝ እኔ ደግሞ የራሴን እቅድ ከጅምር እስከ ፍፃሜ የሌለው አቅዳለሁ። እቤት እንደደረስን እዛ መሳቢያ ውስጥ ያለውን ሽጉጥ እወስዳለሁ። ምን እንደማደርግበት የማውቀው የለኝም። በሆነ መላ ከጎንጥ እሰወራለሁ። የቀጠሩኝ ቦታ ብቻዬን እሄዳለሁ። የሚወስዱኝ ቦታ ስደርስ (ኪዳን ይኖራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ) ሁሉንም ኮፒ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስላልነበረኝ ተጨማሪ አንድ ቀን እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ። የሚፈልጉት ቪዲዮ የዚን ያህል አንገብጋቢ ከሆነ አይገድሉኝም። የጠየቅኩትን ጊዜ ይሰጡኛል። በተቃራኒው ሊሆን እንደሚችል ሳስብ ልቤ ይደልቃል:: ትልቁ ፍላጎቴ ግን ለትንሽ ደቂቃ ከወንድሜ ጋር እንዲተውኝ ማድረግ ነው። ብቸኛ ላምነው የምችለው እና ሊያውቅ የሚችል ሰው እሱ ነው። ይሄ ጎንጥ እንዳለው የጅል እቅድ ሊሆን ይችላል። እጄን አጣጥፌ እየጠረጠርኩት ያለሁትን ጎንጥን ከመከተል ውጪ ሌላ የተሻለ እቅድ ግን የለም። ያን ደግሞ አላደርግም!!

እቤት እንደደረስን ተናኜ የማያቆም ጥያቄ እና ወሬ ታከታትላለች። እንደማልሰማት እንኳን የምታስተውልበት ፋታ አትወስድም። ጎንጥ ከገባ ጀምሮ በሩ ላይ እንደተገተረ ነው። ጮክ ብዬ ጎንጥ እንዲሰማ

« አንድ ላይ የምንበላው እራት አሰናጂ!! ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም! እራት አንድ ላይ እንቋደስ!» አልኩኝ ለእሷ ግራ እንደሚያጋባት ሳልረዳ

«ምነው እትይ የት ልትሄጅ ነው?»
«የትም አልሄድ! ያልኩሽን ዝም ብለሽ አድርጊ!» አልኳት። ቅር እያላት ገባች። ለመሄድ የሚያስፈልገኝን ነገር ካሰናዳሁ በኋላ ጥርጣሬውን ለመቀነስ ልብሴን አልቀየርኩትም። እራት ሶስታችንም ቀርበን እየበላን። አስተያየቱ እንዳላመነኝ፣ ነገረ ስራዬ እንዳላማረው ያስታውቃል።

«አድራሻውን ልከውልኛል።» አልኩት
«የት ነውስ?» አለ ቀና ብሎ ስልኬን እንድሰጠው መሰለኝ እጁን እየዘረጋ። ስልኬን የለበስኩት ሹራብ ኪስ ውስጥ የከተትኩት ለራሴ እቅድ እንዲመቸኝ በመሆኑ እጁን ችላ ብዬ

«እንዳልከው ነው። ቀበና የሚባል ሰፈር የሆነ ካፌ ፊትለፊት ነው። ስልኬ መኝታ ቤት ነው አሳይሃለሁ። ከዛ ነው ከእነርሱ ጋር ሊወስዱኝ ያሰቡት! ምንድነው የምናደርገው? ወዳጅህ እስከአሁን አልመለሰልህም?።» አልኩት። ይመነኝ አይመነኝ ባላውቅም በእርሱ እቅድ እየተመራሁ እንደሆነ እንዲመስል ጣርኩ። አስተያየቱ ያመነኝ አይመስልም። ከጎሮሮዬ አልወርድ ያለውን እህል እንደምንም ካጋመስኩ በኋላ

« …… በልተሽ ስትጨርሺ እዚህ ላይ አንድ ስኒ ቡና ብታጠጪኝ ደግሞ?» አልኳት ተናኜን። ልትነሳ ሲዳዳት ተረጋግታ እንድትጨርስ ነግሪያት ወደጓዳ እጄን እንደሚታጠብ ሰው ገባሁ። እጅ መታጠቢያውን ውሃ ክፍት አድርጌ አስቀድሜ ክፍቱን በተውኳቸው በሮች የምፈልገውን ይዤ በጓዳ ወጣሁ። መጣ አልመጣ አድብቼ እየተርበተበትኩ የአጥሩን በር ከፍቼ ስወጣ ከኋላዬ የሚያባርረኝ ያለ ነበር የሚመስለው አሯሯጤ። የቤቴ በር ከአይኔ እስኪሰወር እሮጥኩ። ያገኘሁትን ታክሲ አስቁሜ ወደተላከልኝ አድራሻ እየሄድኩ።

«ማን ስለሆነ ነው ቆይ እንዲህ የምደበቀው? ያውም በገዛ ቤቴ?» እላለሁ በልቤ!!

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.1K viewsAbela, 17:00
Open / Comment
2023-04-12 20:00:51 የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........


(ሜሪ ፈለቀ)

ክፍል 16

«ብዙውን አላውቅም። እየሆነ ስላለው ነገር ምንም እውቀት እንደሌለሽ ያወቁ ሰዓት ግን እንደሚገድሉሽ በአስር ጣቴ ፈርማለሁ። ስራ አቀለልሽላቸው!! አንቺም ከእነርሱ እኩል የሚፈልጉትን ማስረጃ የት እንዳለ የማታውቂ ፣ ገና እያፈላለግሽ እንደሆነ ልቦናቸው ካወቀ ምን ትሰሪላቸዋለሽ?»

«እኮ ያ ማለት ጠላታቸው አይደለሁም እኔን የሚያሳድዱበት ወንድሜንም የሚያፍኑበት ምክንያት የላቸውም!»

«አንችዬ ጅልም ነሽሳ? ያስታወስሽ ማግስት እንደገና ራስምታታቸው እንደምትሆኚ እያወቁ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልሽ! ብለው እንዲሸኙሽ ነው የምታስቢ?»

«አንተስ የሆነ ቀን ማን እንደሆንክ እንደማስታውስ ግን በሀሳብህ ሽው ብሎ ያውቃል??»

«አይከፋኝም ዓለሜ!! ያኔ ከምታውቂኝ በላይ አሁን ነውስ ምታውቂኝ !!» አለ ዘወር ብሎ አይቶኝ መልሶ «ያለፈውን ብነግርሽ ታምኚኝ ይመስልሻል?»

«ስላልነገርከኝም እያመንኩህ አይደለም። ቢያንስ አውቄው ራሴ ልወስን!! ካልሆነ ግን እንድች ብዬ እግሬን ካንተጋ የትም አላነሳም!»

«አራት አስርት ዓመት እዝህች ምድር ባጀሁኮ!! ምኑን አውግቼሽ ምኑን ትቼው እዘልቀዋለሁ? የትየለሌ ነው!!» አለ በንግግሩ ብዙዙዙ እያስመሰለው።

«እኔ የ40 ዓመት ታሪክህ ምን ያደርግልኛል? እኔ ደጅ ያደረሰህን ታሪክ ነው የምፈልገው። አንድ ዓመት ያከረመህንም!!» በረዥሙ ተነፈሰ። ሁል ጊዜ እንደሚያደርገው። ሊነግረኝ ነው ብዬ ስጠብቅ አጀማመሩን አርዝሞ የቆመ ጆሮዬን ኩም እንደሚያደርገው

«አንዱ ከሌላው ይተሳሰራል። ሁሉን ካልነገርኩሽ ቁንፅል ነው የሚሆን። እንደው በጥቅሉ ደጅሽ ያመጣኝ እንዳልኩት ሰው ነው። ደጅሽ ያቆየኝ አንድ እለት የዋልሽልኝ ውለታ ነው!» ብሎ የማንነቱን እንቆቅልሽ ሁሉ የፈታልኝ ይመስል ጭጭ አለ። ተናደድኩ።

«ኸረ? ውለታ? እያዋረድኩህ እንኳን ደጄ የነበርከው ለአንድ እለት ውለታ ነው? ትንሽ እንኳን የሚመስል ነገር ብታወራ ምን አለበት? ማስታወስ እንጂ ያቃተኝ ጡጦ የሚጠባ ህፃን እኮ አይደለሁም!!»

«ምንአለበት? የሰው ልጅ ለአንዲት ቀን በደል እድሜውን ሙሉ ቂም ይዞ ይኖር የለ? ለአንዲት ቀን በደል ለዓመታት በቀል ሲጎነጎን ይከርም የለ? ምናለበት ለአንዲት ቀን ደግነት ብዙ ዓመት ደግ ቢሆን?» ዋናውን ርዕስ እየሸሸ መሆኑ ገብቶኛል። ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ።

«ምሽት 2 ሰዓት ላይ ፒክ የሚያደርጉሽ ሰዎች በዚህ አድራሻ ይጠብቁሻል። ሰው አይደለም የሰው ጥላ ቢከተልሽ ያልኩሽን አትርሺ!! የምልክልሽን ስጦታ!!» ይላል። ምን እንደሆነ እንድነግረው ዘወር ብሎ እያየ ይጠብቃል።

«እናቴ ናት!! በአጎቴ ስልክ ደህና መግባታችንን ለማወቅ ነው መልእክት የላከችው።» አልኩት።

ለመጀመሪያ ጊዜ ዋሸሁት! ለመጀመሪያ ጊዜ ደበቅኩት። ግን ልክ ያደረግኩ መሰለኝ አልከፋኝም!! አዲስ አበባ ገብተን ለምናልባቱ የተሻለ ፍንጭ ካገኘን ቃሊቲ እየሄድን ነው። በልቤ ወስኜ ጨርሻለሁ። ከቃሊቲ መልስ ፣ መልስ ባገኝም ባላገኝም ጎንጥን የሆነ ቦታ አመልጠዋለሁ። ለሽንቴ እንኳን ስወርድ ልጠፋበት እንደምችል ጠርጥሮ መሰለኝ በቆቅ አይኖቹ ይከተለኛል። እንዴት እንደማመልጠው አላውቅም። ግን ከእርሱ ጋር የሚቀጥለውን እርምጃ አልራመድም። አሁን ላይ ማንን እና ምን እንደማምን ግራ ገባኝ። ለምኜዋለሁኮ ስላለፈው ህይወቴ የሚያውቀውን እንዲነግረኝ። ምንም እንደማያውቅ ሲነግረኝ አምኜው ምንም ሳልደብቀው በእሱ ላይ ዘጭ ብዬ እምነቴን ስጥልበት ትንሽ እንኳን አይከብደውም? የምሸሸው ምን እንደሆነ እንኳን ሳላውቅ በፍርሃት ነፍሴ ሲርድ እና ስፈራ አላሳዝነውም? እርሱን ከምንም በላይ አምኜኮ ለሳምንታት እጁን ይዤ እንቅልፌን ተኝቻለሁ። ምን ይሆን ያስብ የነበረው? በልቡ <አይ ሞኞ> ብሎኝ ይሆን?

«እመቤት በአንድ ወቅት ከእነርሱ ወገን የነበረች ጋዜጠኛ መሆኗን ሰምቻለሁ። ወዳጃምነታችሁ እምንድረስ እንደነበር የማውቀው ባይኖረኝም ለጊዜው መዘንጋትሽን ግልፅልፅ አድርገሽ ባትነግሪያት እመክርሻለሁ።» አለኝ ልንቃረብ ገደማ። አስቤ የነበረው ሁሉንም ነግሪያት የምታውቀውን መጠየቅ ስለነበር ካልጠየቅኳት የመሄዴ ትርጉም ራሱ ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ። ቢሆንም ሄድን!!


በሩ ላይ ስንደርስ የሆነ ልጅ እግር ጠባቂ «ይሄ ባሻሽ ሰዓት እየመጣሽ እገሌን ጥሩልኝ የምትዪበት የጎረቤትሽ ቤት መሰለሽ እንዴ? እስረኛ መጠየቂያ ቀንና ሰዓት አለውኮ!!» ብሎ ፊቱን ወደ ውስጥ መለሰ
«እናውቃለን! እንደው የሞት ሽረት ጉዳይ ገጥሞን ነው! እንደው ለ2 ደቂቃ!» አለ ጎንጥ
«አትሰማኝም እንዴ ሰውየው? ስራዬን ልስራበት ከዚህ ራቁ!! እንደውም እዚህ አቅራቢያም መቆም አይቻልም ዞር በሉ ብያለሁ።» ብሎ አምባረቀ። ምንም ተስፋ እንደሌለው ሲገባኝ

«እሺ የእስረኛ መጠየቂያ ቀን መቼ ነው?» አልኩ። ይሄኔ ሌላኛው በእድሜ በሰል ያለ ጠባቂ «ምንድነው? » እያለ ብቅ አለ። ልጅ እግሩ ምንም የሚለንን የማንሰማ መሆናችንን እያብራራለት ሰውየው እኔን በትኩረት ካየ በኋላ

«አጅሪት? መቼም ካንቺ ውጪ እዚህ በር ላይ ሁከት የሚፈጥር የለም!! ስትጠፊኮ ሌላ ቦታ ሸቤ ገብታ ነው ወይም ከባርች ጋር ተጣልታ! ብለን አስይዘን ነበር። ኸረ ለውጥ ቁርጠቴ በቀሚስ?» አለኝ። አወራሩ የእስር ቤት ጠባቂ ሳይሆን የሆነ የወዳጅነት ነው። ልጅ እግሩ ጠባቂ ግራ ገብቶት ያየዋል። « ከባርች ጋር ተጣልታችሁ ነው መምጣት ያቆምሽው??» ካለኝ በኋላ ወደልጅ እግሩ ጠባቂ ዞሮ « …. ቁርጠቴ የሴቶቹ ካቦ ነበረች እዚህ እያለች።» ሲል ልጅ እግሩ የሆነ ነገር እንደማስታወስ ብሎ ከላይ እስከታች ካየኝ በኋላ « ቁርጠቴ ማለት እሷ ናት? የሰማሁትን አትመስልም!» አለ

« ምን እንታዘዝ ታዲያ? መጠየቂያ ቀን አለመሆኑን ታውቂያለሽ መቼም!!» አለ በሰል ያለው ጠባቂ ወደ እኔ እየተጠጋ
«ብያለሁ አልሰማ ብለውኝ ነው። እመቤት የምትባል ነው የሚሉት?» አለ ልጅ እግሩ እኔ ሰውየው የሚጠራቸው ቅፅል ስሞች የማን እንደሆኑ ሳላውቅ ያለቦታው ሰክቼ ስህተት እንዳልሰራ ስደነባበር። ንግግሩ ያለመፍቀድ ዓይነት አይደለም። የመፍቀድም አይነት አይደለም። ግራ የገባ ነገር አለው። ይሄኔ ጎንጥ ጠጋ ብሎ እየጨበጠው

«እግዜር ይስጥልን ጌታዬ!! የሞት ሽረት ጉዳይ ባይሆን ካለቀኑ መጥተን ባላስቸገርን!!» አለው። ሰውየው ሳቅ ብሎ የጨበጠበት እጁን ከልጅ እግሩ ጠባቂ ደበቅ አድርጎ ገለጠው። ገንዘብ ነው ያቀበለው። ገንዘብ መፈለጉ እንዴት ገባው? ቆይ እሱ የማያውቀው ነገር ምንድነው? ሰውየው ዞር ብሎ ለልጅ እግሩ እመቤት ያለችበትን ምድብ ይመስለኛል የሆነ ቁጥር ነግሮት እንዲጠራ አዘዘው። ልጁ እየተነጫነጨ የተባለውን አደረገ። ምን መጠየቅ እንዳለብኝ እና እንደሌለብኝ መወሰን አቃተኝ። እንደማላስታውሳትስ መንገር አለብኝ? እሷስ የእኔ ወዳጅ ናት ወይስ እንደጎንጥ ማንነቷን የደበቀችኝ ሴት? የስራውን ይስጠው እንኳን ጠርጥርትያት ብሎ ሹክ ብሎኝ እንዲሁም ጥላዬን የምጠራጠር ጠርጣራ አድርጎኛል:: ስትደርስ ለቅሶ እና ሳቅ የተደባለቀው ነገር ሆነች። በእኔ ተመሳሳይ እድሜ የምትገኝ ዓይነት ሴት ናት። ጎንጥ ጆሮውን ቢተክል የምናወራውን ሊሰማ በሚችልበት ርቀት ቆሟል።
2.0K viewsAbela, 17:00
Open / Comment
2023-04-12 14:20:08 እኛኮ...
ህልማችን እስከ ቀራንዮ ፣
አፋችን እስከ ጎልጎታ
ወኔያችን እስከ ዓርብ ንጋት፣
ጉዟችን እስከ አሙስ ማታ።

አብዮት አሃዱ ስንል፣
መጽናት ከሰማይ እርቆን
ዝንታለም ጎህን እንዳናይ፣
የመከራ አረም ያነቀን
ደግሞግን...
ላፍታ በሚፈስ ሃሞት ፣
ነጻነት የሚናፍቀን
የእሳት ልጅ፣
አመድ ትውልድ ነን!!!

የምር

(ታደሰ ደምሴ)

#ሼርርር

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.2K viewsAbela, 11:20
Open / Comment
2023-04-12 12:20:06 በዚህ ዘመን ኖረው ካልጠጡ ካረሱ
በመቀመሱት ቁራሽ በድሎት ካልፈሱ
የሚገፋ አይደለም የዘመኑ ጋሪ
ተገትሮ ከርሟል እንደ ሀገሬ መሪ
እርሳቸው እና ኑሮ !
ዋጋቸው ውድ ነው ከቶ ማይነካ
በአካል አናውቃቸው ካልሆ 'ን በትረካ
ይተረክልናል!
ይሰበክልናል! የፈፀሙት ገድል
    ወትሮም ዕጣፋንታው
የምስኪን ልጅ ዕድል
ነው ሲሉት ነው ይላል ፆሙን ላለማደር
አሜን ሲሉት አሜን ምርጫ የለው ነገር

በ ኪሩቤል አሰፋ
@Cher7ub


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.9K viewsAbela, 09:20
Open / Comment
2023-04-12 11:04:03
Airpod Pro

5- 8 hrs Earphone Music
9-12 hrs Music with Charging Box
100% Original size/Quality
የድምፅ ጥራቱ አስገራሚ
IOS ላይ የሚሰራ
ጂም ቤት ሆኖ ሙዚቃ እያዳመጡ ስፖርት ለመስራት ተመራጭ
በ 15 ሜትር ርቀት ውስጥ የሚሰራ

2000 birr


Samsung air F9 pro+ Wireless Earbuds With Power Bank
በብሉቱዝ የሚሰራ ኤርፎን ጥራት ያለው ድምፅ ፓወር ባንክ ያለው
ከ AkG ቴክኖሎጂ ጋር
ስልክ ቻርጅ ማድረግ የሚችል(emergency power bank)
ውሀ ማያስገባ

ድምፅ መጨመር መቀነስ ዘፈን መቀየር ስልክ ማንሳት የሚያስችል(Fast reponsive touch assisted)

በ አንድ ፉል ቻርጅ 5 ቀን መጠቀም የሚያስችል

ዋጋ:1600 ብር


INPOD 12
Bluetooth Earphone

Bluetooth version: 5.0
Key: Touch control
Distance: 8-15m
Time of endurance: 3-4 hours
Charging time of box: an hour
colors: Pink, Yellow, Light Blue, Green
Price :- 800 birr with free delivery
contact :- 0911468394
3.2K viewsAbela, 08:04
Open / Comment
2023-04-12 09:32:28 አየሽው በአናቴ ለይ እያፏጨ ያለውን ነገር ጥይት ነው ወፍ አይደለም!!...እይው እዛ ማዶ የሚበራውን ደግሞ! ደመራ እንዳይመስልሽ የ አንዱ ባላገር ጎጆ ጋይቶበት ነው!! የገዛ ስንዴአችንን ሽጠን ነው መድፉን የገዛነው እኮ ...ትላንት ፈንድቃ ያየሻት አበባ ዛሬ ማታ በርታ ተመልከቻት መለኮት ወርዶባት አይደለም!ነዳ ነው!!....ከ ሁሉም ቦታ የሚነሳውን ጭስ እይው የ በአል ኩበት ጭስ እንዳይመስልሽ ከተዳፈነ ሰፈር የተነሳ ነው!!ቀጣዩዋን 2 ደቂቃ ሚሆነው ስለማይታወቅ እቀፊኝ .....

@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.3K viewsAbela, 06:32
Open / Comment
2023-04-11 21:53:48 «አትንካኝ አልኩኮ!! » ብዬ ከመጮሄ እኩል በምን ቅፅበት እንደሰነዘርኩት ያልተቆጣጠርኩት ለቡጢ የተጨበጠ እጄ ጉንጩ ላይ አርፏል። ያደረግኩትን ሳውቅ ደንግጬ የመታሁበትን እጄን እንደበዓድ እጅ አየሁት። ከመኪናው ኮፈን ድብደባ ይሆን ከእርሱ ጉንጭ እጄ በልዟል። ወደኋላ ዞሮ አፉ ውስጥ የሞላውን ደም ከተፋ በኋላ ወደ እኔ እየዞረ በሱ ብሶ ይጮህ ጀመር « ከበረደልሽ ድገሚኝ!! እ? በያ!» እያለ ለፀብ ይጋብዘኛል። ትቼው ወደመኪና ልገባ ስል እየተከተለ ሆነ ብሎ ይገፋፋኛል። «ይህችን ታህል ነው የተናደድሽብኝ? ለዝህችው ነው የጎፈላሽው?» ሲለኝ እንዴት ዥው ብዬ እንደዞርኩ አላውቀውም። እጄን ስሰነዝር በሚያስደነግጥ ፍጥነት በመዳፉ ቀለበው። ያልቆጠርኩትን ያህል ጊዜ ተከላክሎ አንዴ ነው አጓጉል ያገኘሁት። ዋጥ አደረጋት!! ቁጣዬ ረጭ ማለቱን ያወቅኩት ይሄኛው የድሮዋ ሜላት ማንነት መሆኑን መገንዘብ ስጀምር ነው።

«ደግ! አሁን ከሰከንሽ እየተጓዝን ስለኪዳን እናውጋ?» አለኝ የመታሁትን ጉንጭ እያሻሸ ወደመኪናው እየገባ
«ጉንጭህን አገላብጠህ ስለሰጠኸኝ እንዳምንህ ነው የምትጠብቀው?»
«እና ምን ይሁን ነው የምትይ? እዚሁ ቁመን ይምሽ? አንዱን አካሉን እዚሁ እንዲልኩልሽ ነው ያሰብሽ?» እየጮኸብኝኮ ነው። ከቃላት ሁላ በላይ ሆነብኝ እና አፌን ከፍቼ አፍጥጬ አየው ጀመር

«አንተ ግን የምርህን ነው? ካንተም ብሶ …….. » አልጨረስኩትም እየሮጥኩ መኪና ውስጥ ገባሁና ስልኬን አነሳሁ። አጎቴጋ ደወልኩ። ተከትሎኝ ገብቶ የማደርገውን በትኩረት ያያል።

«አጎቴ እናቴን አገናኘኝ እስቲ የሆነ ሳልጠይቃት የረሳሁት ነገር ትዝ አለኝ።» አልኩት

«እናቴ ? በቀደም <አምላክን በልመና አታድክሚ!!! የምትችውዪውን አድርጊና በተረፈው አመስግኚው!! ። ያመሰገንሽው አምላክ የጎደለውን ይሞላልሻል> ብለሽኝ ነበርኣ?»

«አዎ የእኔ አበባ ምነው?»

«አጎቴንም እንደዛው ስትዪው ሰምቻለሁኣ?»

«ሁሌምኮ የምለው ነገርኮ ነው ልጄ?» አለች ግራ እየገባት።

«የተለየ ትርጉም ነገር አለው እንዴ?»
«ኸረ ምንም ቅኔ የለውም ልጄ! ምን ጉድ ነው?»
«እንዲሁ ነው የሆነ ሚስጥር የያዘ አረፍተነገር ይመስል ውስጤ ተመላለሰ። ድንገት ሌላ መልዕክት ካለው ብዬ ነው።»
«በፍፁም! ሁሌም ሰዎች እጅ እግራቸውን አጣጥፈው በቀላሉ መስራት በሚችሉት ነገር ሁሉ ሳይቀር ፈጣሪን በልመና ሲያደክሙ እንደዛ እላለሁ። »

«እሺ በቃ እናቴ» ስልኩን ዘግቼ አስባለሁ። ምንም ሳይለኝ መኪናውን መንዳት ቀጠለ።

«እኔን አይደል የሚፈልጉት? እኔ ሄድላቸዋለሁ! እኔን የሚያደርጉትን ያድርጉና ወንድሜን ይለቁታል።» አልኩኝ ለራሴ ያሰብኩትን ድምፄን አውጥቼ እየተናገርኩት

«ህእ! አንቺን ቢፈልጉ እስከዛሬ ላንቺ የሚሆን አንድ ጥይት ጠፍቷቸው ይመስልሻል? ካንቺ በላይ የያዝሽባቸውን መረጃ ይፈልጉታል።» አለ <ቂል ነሽ እንዴ?> በሚል ለዛ

«ሊገድሉኝ ሞክረው የለ?»
«እኔን ከጠየቅሽኝ በፍፁም እነሱ አይመስሉኝም!!»

«እሺ ያለውን ቪዲዮ የምናገኝበት ፍንጭ ታውቃለህ? መቼም የማታውቀው ነገር የለም!» አልኩት አፍንጫዬን እየነፋሁ።
«አላውቅም!!» አለኝ በመድከም አይነት።

«ስለዚህ እሄዳለሁ። አትከተለኝም። እውነቱን እነግራቸዋለሁ።» አልኩኝ ፍርጥም ብዬ
«የማይደረገውን!!» አለ ኮስተር ብሎ

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.3K viewsAbela, 18:53
Open / Comment
2023-04-11 21:53:48 የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........


(ሜሪ ፈለቀ)

ክፍል 15

በአትኩሮት ቢያየኝ እኮ በአፌ ልትወጣ የደረሰች ልቤ ስትደልቅ የለበስኩትን ሸሚዝ እያርገበገበችው ነው። በጀርባዬ የሚንቆረቆር ላቤ ለአፍታ ሌሎች ድምፆች ረጭ ቢሉ፤ ከማጅራቴ ወደ መቀመጫዬ ሲወርድ እንደ ዝናብ <ጠብ> ሲል ይሰማ ነበር። ስክሪኑ ላይ ያለውን የራሴን ምስል ሳየው ለመኮሳተር (የማላስታውሳትን የድሮዋን ሜላት ለመምሰል) በታገልኩ ቁጥር የዞረበት ፊት እያሳየሁ እንደሆነ ገባኝ። እጄን የያዘው የጎንጥ እጅ (ገባቶት ነው መሰለኝ) እንደመጭመቅ ሲያደርገኝ ትኩረቴን ከራሴ ፊት ላይ ወደ ኪዳን መለስኩ። መስሎኝ የነበረው ከወንበር ጋር ታስሮ እየተሰቃየ የማየው ወይም ያ ድምፁን የሰማሁት ሰውዬ ግንባሩ ላይ ሽጉጥ ደግኖበት አልያም ፊቱ በድብደባ ብዛት አባብጦ እና በደም ተለውሶ ነገር የማየው ነበር የመሰለኝ። የሆነው ግን ሌላ ነው። ኪዳንና ሰውየው እየተዝናኑ እንጂ አጋች እና ታጋች በማይመስል ሁኔታ አጠገብ ላጠገብ ተቀምጠዋል። ኪዳንን ለመለየት አልተቸገርኩም። የስልኬ ስክሪን ላይ ካለው መልኩ ምንም ለውጥ የለውም። አስቀድሞም በግራ መጋባት የጦዘውን ጭንቅላቴን ልክነት ያጠራጠረኝ የኪዳን መረጋጋት ነው። የሆነ ልክ ሰላም ልንባባል የተደዋወልን አስመስሎ

«ሜልዬ! ደህና ነሽልኝኣ?» አለ። ምንድነው እየሆነ ያለው? ኪዳን አይደለም ይሆን? ሰውየው ቅድም 12 ቦታ ቀነጣጥሼ እልክልሻለሁ ሲለኝ አልሰማም ማለት ነው? አሁንም የጎንጥ እጅ አነቃኝ።

«እኔ ደህና ነኝ! አንተስ?» ይባላል ቆይ? ከአጋቹ ጋር የተቀመጠ ሰው ደህና እንደማይሆን ግልፅ አይደል? እሱ ዝንቡ እንኳን እሽ እንዳልተባለ ሰው ዘና እያለ ታዲያ ምን ልበል? ምናልባት ለእኔ ብሎ ይሆን? እኔን ለማረጋጋት?

«አታስቢ ደህና ነኝ! ከልቤ ደህና ነኝ።» እያለ ምንም ያለመጎዳቱን ሊያሳየኝ ስልኩን እያራቀ ከተቀመጠበት ተነስቶ መላ አካላቱን አሳየኝ። እያባበለኝ ነገር መሰለኝ።

«እንዴት ነው የማላስበው? መዝናኛ ቦታ …… » እኔ ባልገባኝ ምክንያት ለእርሱ ግን ልክ በመሰለ እንድናገር አልፈለገም። ወዲያው አቋርጦኝ

«ሜል እንዲሁ ተጨነቂ ስልሽ ነው። እኔኮ ደህና ነኝ አልኩሽ። » ሲለኝ ጎንጥ ምን እንዳናደደው ሳይገባኝ ተበሳጭቶ ጥርሱን ነክሶ እኔን ባልያዘው እጁ አየሩን በቦክስ ጠለዘው። እየሆነ ያለው ነገር አፍና ጭራው የጠፋኝ እኔን ብቻ ነው? እኔ ሳይገባኝ እሱ የገባው አብረን ከሰማነው የደህና ነኝ መልእክት ውጪ ውስጠ ወይራ አለው? « በኋላ እንገናኝ የለ? እስከዛ ደህና ሁኚልኝ! ደግሞ አምላክን በልመና አታድክሚ!!! የምትችውዪውን አድርጊና በተረፈው አመስግኚው። ያመሰገንሽው አምላክ የጎደለውን ይሞላልሻል።» አለኝ ጭራሽ። የድሮዋ ሜላት ፀሎተኛ እንዳልነበረች ጠፍቶት ነው? ይሄንኑ ዓረፍተ ነገር ግን ከዚህ በፊት የሆነ ሰው ብሎት ሰምቻለሁ!! የት ነው የሰማሁት?

እስካሁን ድምፁ ያልተሰማው ሰውዬ ስልኩን ተቀበለውና በአይኑ እንደመጥቀስ አድርጎኝ ዘጋው!! አፌን እንደከፈትኩ ስልኩ ላይ አፍጥጬ ቀረሁ።

«ይሄ የውሻ ልጅ አውቆታል!» አለ ጎንጥ። መኪና ውስጥ ሆነ እንጂ ሜዳ ላይ ቢሆን <ዘራፍ> የሚል ነው የሚመስለው።
«ምኑን?» አልኩኝ ከድንዛዜዬ ሳልወጣ

«እየቀረፅሽው እንደሆን !» ብሎ ስልኩን እንድሰጠው እጁን ዘረጋልኝ። ስሰጠው ስልኩ ስክሪኑ ቆልፎ ስለነበር እንድከፍትለት መልሶ ሰጠኝ። ያለኝን የምከውነው ምኑም ገብቶኝ አይደለም። ያለውም የገባኝ ነገር የለውም።

«ማን ነበርኩ? ከምን ጋር የተቆላለፈ ህይወት ነው የነበረኝ? የምን ቪዲዮ ነው የምወስድለት? ስልኬ ውስጥ ያለ ነገር ይሆን?»

«ህም! ስልክሽ ውስጥ ልታኖሪው አትችዪም!» ሲለኝ አፌን ከፍቼ ቀረሁ። ስለቪዲዮው ያውቃል!!

«ምን ይመስልሃል ቪዲዮው?»

«እሱን በምን አውቄው! ብቻ ቅሌቱን የተሸከመ ነገር ነው የሚሆን»

ድንዝዝ እንዳልኩ አይኔ ብቻ ሲንቀዋለል ስልኩ ላይ ቅድም የተጫናት ምልክት ስክሪኑን መቅጃ መሆኗን እና ሰውየው እንደመረጃ እንዳንይዝበት ኪዳንን ምንም የተለየ ምልክት እንዳይሰጥ አስጠንቅቆት እንደሆነ እርግጠኛ ሆኖ ከነገረኝ በኋላ እኔን ረስቶ የተቀዳውን ቪዲዮ እየደጋገመ ወደፊት ወደኋላ ቅርብ …. ራቅ እያደረገ ያያል። እኔ ደግሞ ዝም ብዬ እሱን አየዋለሁ።

«በስተመጨረሻ ልመና አታብዥ ያለው ነገር ያላስፈላጊ ቦታ የተዶለ አይመስልሽም? ላንቺ የሚያስታውስሽ ነገር አለ?» አለኝ አሁንም ከስክሪኑ አይኑን ሳይነቅል።

«የሆነ ሰው ሲለው የሰማው ይመስለኛል። አላውቅም!! ራሴም እለው የነበረ ነገር ይመስለኛል። ምንም መጨበጥ አልቻልኩም።» ስለው እንባዬ ዓይኔን ሞልቶታልኮ እሱ ግን አላየኝም። ቪዲዮውን ኪዳን ስለምስጋና ያነሳበት ጋር አቁሞ

«ተመልከች እዚህ!!» ብሎ ሰውየውን ጠቆመኝ « ልክ ኪዳን ሲናገር ፊቱ አንድ አፍታ ይቀየራል። ተመልከች! ያ ማለት ይህ መስመር እንዲናገር ከተፈቀደለት ውጪ ነው ማለት ነው! ሊገልጥልሽ የፈለገው አንድ መልእክት ቢኖረው ነው።»


«ጎንጥ?» አልኩት ፍስስ ባለ ድምፅ

«ወይ!» አለ አይኑን እዛው እንደሰነቀረ

«ማ ነ ህ? » አልኩት እንባዬ አብሮ ከቃላቱ ጋር ዱብ ዱብ እያለ። እዛ ነጥብ ላይ ጎንጥ ዘበኛዬ ብቻ እንዳልሆነ ገብቶኛል። የሚያስለቅሰኝ በትክክል ምን እንደሆነ እንጃ።

«ኸረ በመድሀንያለም?! » አለ ደንግጦ የሚያደርገው ጠፍቶት ። እጄን ሊይዘኝ እጁን ሲሰድ መንጭቄ ቀማሁት

«እንዳትነካኝ! ሁሉንም ነገር ታውቃለህ! ይሄን ሁሉ ጊዜ ስሰቃይ እያወቅክ ምንም እንደማያውቅ አብረህ ስታፋልገኝ ነበር። ሰውየው ያወራው ሁሉ ነገር ገብቶሃል። ንገረኝ አንተም የእነሱ ወገን ነህ? ምን ፈልገህ ነው?» እንባዬ ባይቆምልኝም ሰውነቴ ሲቆጣ ፣ ደሜ ሲሞቅ ይታወቀኛል።

«መድሀንያለም በሚያውቀው እንደሱ አይደለም!! አንች ያሰብሽውና የእኔ ድርጊት ለየቅል ነው!! ሀሳቤ ጠላትነት ከነበር ምን እጠብቅ ነበር? ከጠዋት እስከማታ እጀ ላይ አልነበርሽ?»

«አላውቅም! የሆነ የምትፈልገው ነገር ይኖራላ!!» ተነስቼ ከመኪናው ወረድኩ። ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ድረስ ንዴቴ ያጨሰኝ ጀመር። የመኪናውን ጎማ በሃይል መጠለዜን ያወቅኩት የእግሬን አውራ ጣት ሲያመኝ ነው። የሆነ ውስጤ ተኝቶ የነበረ አውሬ የነቃ ይመስል የምቦጫጭቀው ነገር ፣ ቁጣዬን የምወጣበት ነገር ፈለግኩ። እሪሪሪ ብዬ መጮህም ፈለግኩ። የመኪናውን ኮፈን በቡጢ እየነረትኩ ማቆም እፈልጋለሁ ግን እጄን የምሰነዝርበት ቁጥር በጨመረ ልክ ሰውነቴ እየረገበ ፣ ቁጣዬ እየበረደ ስለተሰማኝ አላቆምኩም። ከመኪናው ወርዶ መምጣቱን ያወቅኩት አጠገቤ መጥቶ ሁለቱን እጄን ለቀም አድርጎ ሲያስቆመኝ ነው።
3.7K viewsAbela, 18:53
Open / Comment
2023-04-11 19:17:21 «እኔኮ ኪዳንን እንኳን ላልለየው እችላለሁ?» አልኩ አፌ ውስጥ ምራቄ ደርቆብኝ ትን የሚለኝ እየመሰለኝ። ስልኩ ጠርቶ እንዳይዘጋ እየተቻኮለ ስልክ ያልያዝኩበትን እጄን ቀለብ አድርጎ ጨብጦ ከቅድሙ በተረጋጋ ድምፅ

«ትለይዋለሽ ግድ የለም!» አለኝ። የድምፁ መርገብ ይሁን የያዘኝ እጁ ያረጋጋኝ መርበትበቴን ገትቼ የያዘኝን እጄን አስለቅቄ ስልኩን ካነሳሁ በኋላ እንዲይዘው መልሼ ሰጠሁት።

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.7K viewsAbela, 16:17
Open / Comment