Get Mystery Box with random crypto!

ወንጌል ይለዉጣል📖

Logo of telegram channel kalu_hayal_new — ወንጌል ይለዉጣል📖
Logo of telegram channel kalu_hayal_new — ወንጌል ይለዉጣል📖
Channel address: @kalu_hayal_new
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 155
Description from channel

ወንጌል ይለዉጣል
ትምህርቶች
የእግዚአብሔር ቃል
የዝማሬ ግብዣ
እና ሌሎችም እራሳችንን እንድናይ የሚያደርጉ ፅሁፎች የሚቀርቡበት gospel channel contact us
@kalu_hayal_new
@enchanted_nuha

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 2

2021-08-13 14:40:50 Micah Tyler lyric >>different

I don't wanna hear anymore,
Teach me to listen
I don't wanna see anymore,
Give me a vision
That you could move this heart
To be set apart
I don't need to recognize,
The man and the mirror
And I don't wanna trade your plan,
For something familiar
I can't waste a day
I can't stay the same

I wanna be different
I wanna be changed
'Til all of me is gone
And all that remains
Is a fire so bright
The whole world can see
That there's something different
So came and be different
In me

And I don't wanna spend my life,
Stuck in a pattern
And I don't wanna gain this world
But lose what matters
So I am giving up,
Everything because...

I wanna be different
I wanna be changed
'Til all of me is gone
And all that remains
Is a fire so bright
The whole world can see
That there's something different
So came and be different,
Oh

I know that I am far, from perfect
Through you, the cross still says
I'm worth it

So take this beating in my heart and
Come and finish what you started
When they see me, let them see you
'Couse I just wanna be different,yeah

I wanna be different
I wanna be changed
'Til all of me is gone
And all that remains

Oh is fire so bright
The whole world can see
That there's something different
So came and be different

I just wanna be different
So could you be different
In Me

join us

@kalu_hayal_new
@kalu_hayal_new
74 views11:40
Open / Comment
2021-08-11 11:19:10
የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ከክፍል ሰባት የቀጠለ........
ስለ ፍቅር ሲነሳ ብዙ ነገሮችን መዳሰስ ይቻላል ነገር ግን ከዚህ ትምህርት አንፃር የመጨረሻውን ሀሳቤን እንካዋቹ ልበልና ሀሳቤን በመልካም ላሳርገው፦፦፦፦፦፦፦
በክርስትናው አለም ውስጥ በትራኩ ላይ ስለሮጥን ብቻ ተሸላሚዎች እንሆናለን ማለት አይደለም።ሩጫው በፍቅር መሮጥን ይጠይቃል።ብዙዎቻችን መሮጣችን ላይ እንጂ በፍቅር መሮጣችን ላይ ብዙ ጊዜ ትኩረት ስናደርግ አንታይም።
ፍቅር የህግ ሁሉ አራት ነጥብ እንደሆነ ቅዱስ ቃሉ በተለመደው ትህትናዊ ቃላቱ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ አስፍሮልን ይገኛል።ለምሳሌ(ማቴ 22:36-40)
ሐዋሪያው ጳውሎስ የፍቅርን ትርጉም በ1ጢሞ 1:5 ላይ የገለፀበት መንገድ በቀላሉ ለመረዳት የሚቀል ሆኖ አጊኝቼዋለው፦፦፦፦፦
ፍቅር በዋናነት ሶስት ነገሮችን በውስጡ እንዳቀፈ ክፍሉ ያሳብቀናል፦፦፦፦፦፦
1)ንፁህ ልብ፦ይሄ ማለት
ከክፋት ያልተዳቀለ ልብ
በሌሎች ስኬት የማይቀና ልብ
የክርስቶስን መስቀል
የሚተነፍስ ልብ ወዘተ..
2)በጎ ህሊና፦በጎ ህሊና ማለት በክፉ መረብ ያጠመደንን ሰው ከወጥመዱ ካመለጥን ማግስት መልሰን ገንዘባችን ለማድረግ የምንወስደው አዎንታዊ እርምጃ ማለት ነው።
3)ግብዝነት የሌለበት እምነት፦፦
ግብዝነት ማለት በማስመሰል ማንነት የተከፈነ ትወናዊ ህይወት ማለት ነው ግብዝነት የሌለበት እምነት ሲል ትወናዊ ያልሆነና በእውነተኛ ማንነት የተገለጠ እምነት ለማለት ፈልጎ ነው
በአጠቃላይ ከዚህ ክፍል አንፃር ፍቅር ማለት
ንፁህ ልብ
በጎ ህሊናና ግብዝነት የሌለበት እምነት
ማለት ነው።
ተወዳጆቼ ሆይ ቀሪውን ዘመናችንን በፍቅር በመሮጥ ለታላቁ ሽልማት በክብር እንድረስ እላለው።
እወዳችኋለው
by biruk mohammed
69 views08:19
Open / Comment
2021-08-05 22:53:46
የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

የመጨረሻው ክፍል ሰባት

እጅግ በጣም የምወዳችሁ የአባቴ ብሩካኖች በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳቹ እያልኩኝ በመቀጠል ደግሞ የመጨረሻውን ክፍል ወደ ማካፈሉ መንደር እዘልቃለው።
"በፍቅር አለመሮጥ
አያሸልምም"
ስለ ፍቅር ጉዳይ ሲነሳ አለማችን ብዙ ዓይነት መረዳቶችን አንግታ እንደምትንቀሳቀስ ይታወቃል።ከሁሉም በላይ ግን መፅሀፍ ቅዱሳችን ፍቅርን በተመለከተ የሚሰጠን መረጃ በትልቁ ውሀ የሚያነሳ ነው።

ፍቅርን ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር ከማየታችን በፊት በግሪኩ በስንት እንደሚከፈል እንመልከት፦፦፦፦፦
ፍቅር በግሪኩ በ8 ይከፈላል
1)ፊልያ፦የወንድማማች ፍቅር
2)ኢሮስ፦የእጮኝነት ፍቅር
3)ስቶርጅ፦የቤተሰብ ፍቅር
4)ሉዳስ፦ለአካለ መጠን ባልደረሱ ወንድና ሴት መሀል የሚፈጠር ፍቅር
5)ፕራግማ፦በባልና በሚስት መሀል ብቻ ያለ ፍቅር
6)ፊላሺያ፦ራስን መውደድ(አዎንታዊና አሉታዊ ገፅታ ያለው ነው
7)ፓትሮቲዝም፦የሀገር ፍቅር
8)አጋፔ፦የእግዚሀብሔር ፍቅር
ከእነዚህ የፍቅር አይነቶች መካከል እኛ አማኞች እንዲሁ የተካፈልነው የእግዚሀብሔርን ፍቅር ነው
የተካፈልነው የእግዚሀብሔር ፍቅር ቢያንስ ቢያንስ ሶስት ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው፦፦፦፦፦፦፦
A)በጥልቅ መስዕዋትነት ላይ
B)እንካ በእንካ ባልሆነ መሠረት ላይ እና
C)ከፍርድ ይልቅ ወደ ምህረት በኩል ባዘነበለ መሠረት ላይ የተመሰረተ ፍቅር ነው።
ይቀጥላል.............................
አደራ በትዕግስት ጠብቁኝ
እወዳችኋለው
by biruk mohammed
68 views19:53
Open / Comment
2021-07-30 19:55:54
የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ክፍል ስድስት

፨ወንድምን ጠልፎ መሮጥ
አያሸልምም
ተወዳጆቼ ከዚህ በፊት አምስቱን የማያሸልሙ የሩጫ ዓይነቶች ለመዳሰስ ሞክረናል ለማስታወስ ያህልም፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ግብን እያዩ አለመሮጥ
አያሸልምም
የሩጫውን መርህ ሳያከብሩ
መሮጥ አያሸልምም
ሩጫውን አቋርጦ መውጣት
አያሸልምም
በበቂ ዝግጅት ያልታገዘ ሩጫ
አያሸልምም
በልብ አለመሮጥ አያሸልምም
ዛሬ ደግሞ ስድስተኛውን የማያሸልም የሩጫ ዓይነት በጥቂቱ ለመዳሰስ እንሞክራለን
"""ወንድምን ጠልፎ መሮጥ
አያሸልምም""
፨የሚገርመው ወንድምን ጠልፎ በመጣል ቀዳሚ ሆኖ መገኘት አለብኝ የሚልን እኩይ ቢሂል አንግተው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች በተለይ በዚህ ዘመን እንደ አሸዋ ለመቁጠር እስኪያዳግት ድረስ በዝተዋል።
እነዚህ ሰዎች ከወንድማቸው መዘግየት ውስጥ
ፍጥነታቸውን ለማምረት የሚፈልጉ፥
ከወንድማቸው ሀዘን ውስጥ ደስታን ናፋቂዎች እና
በተጨማሪም ደግሞ፦፦፦፦፦፦፦፦
ከወንድማቸው ኪሳራ ውስጥ ትርፋቸውን ለመገብየት በማሰብ ዘምቢል ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ናቸው።
ተወዳጆቼ ሆይ እናስተውል ወንድማችንን ጠልፎ በመሮጥ የምናገኘው የትኛውም ሽልማት እንደ እግዚሀብሔር ቃል ከተመለከትነው ልክ እንደ መርዘኛው እንቦጭ ነው። ለዓይናችን ልምላሜ መስሎ እየታየን ቀስ በቀስ ግን ሁለንተናችንን እየገደለ የሚጓዝ በቀላሉ ተዛማች የሆነ ገዳይ መርዝ ነው።
(((((ፊል 2:3-4))))))
በዚህ ክፍል ላይ ከባልንጀሮቻችን ጋር በትህትና አቆጣጠር መሮጥ እንደሚገባን ይነግረናል
፨ሶስት ነገሮችን በትህትና እየቆጠርን አብረናቸው እንሩጥ ይለናል
1)ባልንጀራዬ ከእኔ እንደሚሻል
መቁጠር
2)ለባልንጀራዬ የሚጠቅመውን ነገር ሁሉ ልክ እንደ እኔ ማግኘት እንደሚገባው በአስተሳሰብ መቁጠርና
3)በከንቱ ውዳሴን ለማግኘት አስቦ አንዳች ነገር አለማድረግን በመቁጠር እንድንሮጥ ያበረታታናል።ከዚሁ ጋር አያይዘንም ትህትናን ከዚህ ክፍል ዐውድ አንፃር እንደዚህ መረዳት እንችላለን።
ተባብረን ተጋግዘን እንሩጥ
የመጨረሻውን ክፍል እባኮዎን በትዕግስት መስመር ላይ
ይጠብቁኝ
እወዳችዋለው
by biruk mohammed
65 views16:55
Open / Comment
2021-07-24 22:49:50
የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ከክፍል አምስት የቀጠለ.....
፨፨በሐጌ 1:5፤7)ላይ
"ልባችሁን በመንገዳቹ ላይ አድርጉ"የሚል ቃል አለ ይሄ ቃል ላነሳውት የክፍል አምስት ርዕስ ከፍተኛውን የማብራራት ሚና የመጫወት አቅም አለው
በሐጌ ዘመን የነበሩ ሰዎች የእግዚሀብሔርን ቤት መስራት ችላ ብለው የራሳቸውን ቤት በትጋት በመስራት ተጠምደው ነበር።
፨፨ጊዜው የእግዚሀብሔርን ሳይሆን የእኛን ስራ የምንሰራበት ነው በሚል እኩይ አስተሳሰብ ተቀንብረው ይነዋልሉ ነበር ከዚህ የተነሳ እግዚሀብሔር በነብዩ በሐጌ በኩል ህዝቤ ከመንገዱ ላይ ልቡን አንስቶ ትላንት በመልካም ያስጀመርኩትን ሠናይ ሩጫ እንደአጀማመሩ በልቡ መሮጥ ትቶ በእግሩ በመሮጥ ላይ ይገኛል እናም በዚሁ ከቀጠሉ መጨረሻቸው ስለማያምር አሁኑኑ ልባቸውን በመንገዳቸው ላይ እንዲያደርጉና በልባቸውም መሮጥ እንዲጀምሩ አሳስብልኝ በማለት አጣዳፊ መልዕክትን እንዲያስተላልፍ ይቀሰቅሰዋል
የሚገርመው እነዚህ ተደራሲያን በልባቸው ባለመሮጣቸው ምክንያት የሚሰሩት ሁሉ በኪሳራ ምች ተመቶባቸው ነበር
ይበላሉ አይጠግቡም
ይጠጣሉ አይረኩም
ይለብሳሉ አይሞቃቸውም
ደሞዛቸውን ይቀበላሉ በቀዳዳ ኪስ ይጨምራሉ
ይዘራሉ ምድር አትተባበራቸውም ነበር የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ደግሞ በልባቸው ሳይሆን በእግራቸው በመሮጣቸው ነው
በልባችን በመሮጥ የእግዚሀብሔር ቤት እንስራ
፨፨ልባችንን በመንገዳችን ላይ እናድርግ
፨፨በእግራችን ሳይሆን በልባችን እንሩጥ እላለው
ክፍል 6 ይቀጥላል
እወዳችዋለው
by biruk mohammed
71 views19:49
Open / Comment
2021-07-22 19:55:39
የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ከክፍል አምስት የቀጠለ........
፨ምክንያቱም ከሰማይ
ለመጣላቸው ነፍሳችሁን አድኑ
ወደ ኋላ እንዳትዞሩ ለሚለው ጥሪ(ድምፅ) የሰጠችው መንቻካ ምላሽ የነበራትን የወረደ መረዳት ያሳብቅባት ስለነበረ ነው።
በወቅቱ እግዚሀብሔር በሰዶምና ገሞራ ሰዎች የስርዓት አልበኝነት ኑሮ በእጅጉን በመበሳጨቱ ምክንያት በምድሪቱ ላይ የእሳትን ዲን ለማዝነብ በዝግጅት ላይ ነበረ ግን ደግሞ ከላይ በዘረዘርኳቸው ሶስት ነጥቦች ምክንያት እግዚሀብሔር ለሀጢያተኛው የመጣው ዱላ ፃድቁንም እንዳያገኘው በማሰብ በፍጥነት ከከተማዋ ሎጥና ቤተሰቡ እንዲያመልጡ በመልዕክተኞቹ በኩል እቤቱ ድረስ በመሄድ ሹክ ለማለት ግድ ሆነበት
ሎጥም ለመጣለት የራስህን አድን ጥሪ በፍጥነት አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ጀመረ
፨ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው የሩጫው ትራክ ላይ በመገኘት ሩጫቸውን በመልካም ጀመሩ
የሚገርመው ደሞ ይሄኛው የሩጫ ዓይነት በእግር ሳይሆን በልብ የሚሮጥ ሩጫ ነበር የሎጥ ሚስት ግን የተወሰነ ርቀት ለዚህ መርህ ተገዢ ሆና መሮጥ ብትችልም ከተወሰነ ጉዞ በኋላ ግን ከሩጫው ለማፈንገጥ ስትንደረደር ተገኘች
፨፨እንዳሰበችውም ልቧን ለሰዶምና ገሞራ እግሯን ደሞ ለመጣላቸው ሰማያዊ ድምፅ ለማከራየት ሞከረች ሙከራዋም የአውልትነትን ዕጣ ፈንታ ወሰነላት
ሩጫውንም ሳትጨርስ ከሁለቱምም መሆን ሳትችል ምድረበዳ ላይ ቅጥር ያልተቀጠረለትና ጥበቃ የሌለው አውልት ሆና ቀረች
ሎጥና ልጆቹ ግን የተሰጣቸውን የራስህን አድን ጥሪ ይዘው ሩጫቸውን በእግራቸው ሳይሆን በልባቸው በመሮጥ በድል አጠናቀቁ
፨፨ውዶቼ በልብ የማይደረግ ሩጫ እንደማያሸልም ከሎጥ ሚስት እንማር
፨**የእግዚሀብሔርን ሩጫ በልባችን እንሩጥ እርሱም ኢየሱስ ነው** የዚህን ቀጣይ ክፍል ቀጥዬ አቀርባለው እባኮዎን መስመር ላይ ይጠብቁኝ ............
እወዳችዋለው
by biruk mohammed
65 views16:55
Open / Comment
2021-07-21 23:04:27
የማያሸልሙ 7 የሩጫ ዓይነቶች

ክፍል አምስት

፨"በልብ አለመሮጥ አያሸልምም"
፨ለዚህ ሀሳቤ መነሻ የሚሆኑኝ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ብዙ ቢሆኑም ነገር ግን ላነሳውት ሀሳብ ድጋፍ የሚሰጡልኝን ጥቂት ክፍሎች ብቻ ጠቆም ማድረግ እፈልጋለው
፨(ዘፍ 19)የሎጥ ሚስታ ታሪክ
፨(ከግብፅ የወጡ)እስራኤላውያን
፨ት/ሐጌ 1:5፤1:7)
በመፅሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከተካተቱ አሳዛኝ ታሪኮች አንዱ የሎጥ ሚስት ታሪክ ነው
፨የሎጥ ቤተሰብ በሰዶምና ገሞራ ላይ ከመጣው መለኮታዊ ጥፋት እንዲያመልጡ እድሉን ያገኙት በሶስት ምክንያቶች ነው እነርሱም
1)በአብርሀም ምልጃ
(((ዘፍ 18:23-33)))
2)በሎጥ የፅድቅ ህይወትና
(((2ጴጥ 2:7-8)))
3)በእግዚሀብሔር የምህረት ልብ
(((ሰቆ ኤር 3:22)))አማካኝነት ነው ይሄ ማለት ግን የአማኞች ምልጃና የፅድቅ ህይወት ከእግዚሀብሔር የምህረት ልብ ልክ ሰዎችን ከተለያዩ ጥፋቶች ውስጥ የመናጠቅና የመታደግ ሙሉ ብቃት አለው ለማለት ፈልጌ አይደለም
ለማለት የፈለኩት እግዚሀብሔር በመልካምነቱ ባህሪው በኩል ከመጣው የጥፋት ሰደድ ውስጥ ሰዎችን በአማኞች ምልጃና የፅድቅ ህይወት አማካኝነት እንደሚታደግ የገባውን የራሱን ቃል ተንተርሶ እንደሚሰራ ለማመላከት ነው
የሎጥ ሚስት ግን ይሄንን እውነታ የመረዳቷ ነገር አጠራጣሪ ይመስላል ምክንያቱም............................
እወዳችዋለው
by biruk mohammed
62 views20:04
Open / Comment
2021-07-19 23:48:33 #ሠርቼ_ሳይሆን_ተቆጥሮልኝ......


እኔ በራሴ ደካማ ነኝ! #አልችልም! በመልካም ማንነት በጥንቃቄ ብራመድም ለጥቂት ነው እንጂ ፤ ተመልሼ እወድቃለሁ ፤ እንዲሁም እነሳለሁ። እድሜዬን በሙሉ ጠንካራ ሁኜ ያለምንም ስህተት መኖር አልችልም! ህጉንም ሁሉ መጠበቅም አልችልም! ምክንያቱም ፍጹም አይደለሁም።



በዚህ ሁኔታም ፤ ህግን በመጠበቅ እና በመልካም ሥራ የሚጸድቅ ማንነት የለኝም!.... #ብቁ_አይደለሁም ፤ እራሴን አላምንም! ምክንያቱም እጅግ ደካማ ነኝ [በመንፈስም ደሃ ነኝ]። #በሥራዬ_ብጸድቅ ፤ ነገ ደግሞ ስደክም ጽድቄን አጣዋለሁ። በእኔ ኃይል እና በሥራዬ ቢሆን ዛሬ ላይ ባልደረስኩ ነበር። #እንደ_ሥራዬ ቢሆንማ አጠቃላይ ውጤቴ የከፋ ነበር። በሥራዬ ቢሆን ፤ እንኳን በእግዚአብሔር ፊት #ልጸድቅ ይቅርና ፤ በሰዎች ፊት እንኳን ጻድቅ አልባልም ነበር።



አሁን ግን #የምጸድቀው_በሥራዬ_አይደለም! የምጸድቅበት አዲስ ተስፋ መጥቷል ፤ እርሱም #እምነት ይባላል። ያገኘሁትም #ጽድቅ የራሴ አይደለም! #ተቆጥሮልኝ እንጂ። በራሴ በየትኛውም ሥራ #የእግዚአብሔርን_ጽድቅ ላገኘው ስለማልችል ፤ #እንዲሁ_ተቆጠረልኝ ፤ ያውም የራሱ #የእግዚአብሔር _ጽድቅ። እኔ መሥራት ስላልቻልኩ #ልጁ ሥራዬን ሠራልኝ እና ለእኔ ለደካማው #ተቆጠረልኝ። ልጁ በሠራው እኔ እንዲሁ በእምነት ገባሁ ፤ ልጁ ህጉን በሙሉ መፈጸሙ ለእኔ #ተቆጠረልኝ ፤ ያለ ኃጢአት መመላለሱ ለእኔ #ተቆጠረልኝ።

ሮሜ 3÷28፤ [ #ሰው_ያለ_ሕግ_ሥራ_በእምነት_እንዲጸድቅ >>#እንቆጥራለንና<<። ]

ሮሜ 4 (Romans)
5፤ [ #ነገር_ግን_ለማይሠራ_ኃጢአተኛውንም_በሚያደድቅ_ለሚያምን_ሰው_እምነቱ_ጽድቅ_ሆኖ >>#ይቆጠርለታል<<።

6፤ [ እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር >>#ያለ_ሥራ<< ጽድቅን #ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል። ]
22፤ [ ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ >>#ተቆጠረለት<<።

23፤ ነገር ግን፦ >>#ተቈጠረለት<< የሚለው ቃል #ስለ_እርሱ_ብቻ_የተጻፈ_አይደለም፥ >>#ስለ_እኛም<< ነው እንጂ፤

24-25፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው >>#ለምናምን_ለእኛ >>#ይቈጠርልን_ዘንድ<< አለው። ]

ገላትያ 3 (Galatians)
8፤ [#መጽሐፍም እግዚአብሔር >>#አሕዛብን_በእምነት_እንዲያጸድቅ >>#አስቀድሞ_አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። ]



እግዚአብሔር #በልጁ_ስም በማመኔ ብቻ #የልጁን_ጽድቅ ለእኔ ለኃጢአተኛው እንዲሁ ከቆጠረልኝ ፤ ታዲያ ኃይማኖት የምን #ምቀኝነት ነው? ፤ ለምንድነው "#ለመጽደቅ_መሥራት_አለብህ" የምትለኝ? እህ!!!!!!...... ቆይ መቼም በሥራዬ ፈጽሞ መጽደቅ እንደማልችል ስለሚያውቅ መስሎኝ እግዚአብሔር እንዲሁ #በነጻ ፤ ማመኔን ጽድቅ አድርጎ #የቆጠረልኝ። ወይ ሃሳብህን አስተካክለው ፤ "#ስለጸደክ_መስራት_አለብህ" በለኝ። እንዲህ ስላልከኝም አይደለም ፣ መልካም መስራት የኔ አዲሱ ሰው ማንነት life system ነው።

ሮሜ 8 ÷ 33፤ [ #እግዚአብሔር_የመረጣቸውን_ማን_ይከሳቸዋል? >>#የሚያጸድቅ_እግዚአብሔር_ነው፥ #የሚኰንንስ_ማን_ነው? ]


ሮሜ 10 (Romans)
3፤ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።

እወድሃለሁ አንተ ወንድሜ! ይህ ጽድቅ ለእኔ ብቻ እኮ አይደለም #ላንተም ነው! እመን! #ይቆጠርልሃል! በሥራ ካልክ እውነቱን ልንገርህ መቼም አትጸድቅም! እግዚአብሔር የራሱን ጽድቅ ሊሰጥህ ይፈልጋል ፤ ታዲያ አንተ ለምን የእርሱን ትተህ #የራስህን_ጽድቅ ለማቆም ትጥራለህ? እርሱ እንዲሁ በነፃ ስለሰጠህ?...... የምትድነው እኮ #በራስህ_ጽድቅ ሳይሆን በራሱ #በእግዚአብሔር_ጽድቅ ነው።
@marsilchannel
@marsilchannel
@marsilchannel
71 views20:48
Open / Comment