2022-02-13 17:08:37
ሠለምቴው አብዲሳ ክፍል ሁለት.........።
ቢስሚላህ አልሀምዱሊላህ
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ። የአስሐቡል የሚን ቤተሰቦች ።
ዛሬ ኢንሻ አሏህ ከባለፈው የቀጠለ እነዴት ሰለምኩኝ የሚለውን ታሪኬን ልቀጥል እወዳለው በባለፈው ክፍል ወርቃማ ብዬ መግለፅ የማልችለው ስጦታ ከአሏሀ ተበረከተልኝ ብዬ ካቆምኩበት ኢንሻ አሏህ በአሏህ ውዴታ ልቀጥል እሻለው(ፈልጋለው) ሸሀዳ ከያዝኩ በኃላ በድብቅ(ቤተሰቦቼ ሳይሰሙ) ለሶላት ሚያስፈልገኝን
ጠሃር,ፋቲሃ,አተሂያቱ,አጫጭር የቁርአን አነቀፆችን,እንዴት እንደ ሚሰገድ ብቻ ምን አለፋችሁ ለሶላት የሚያስፈልገኝን ሁሉንም ካሟላው በኃላ በድብቅ(ቤተሰቦቼ ሳይሰሙ) ሶላቴን እየሰገድኩ ቀናቶች ባለፉ ቁጥር መስለሜን የሠሙ ሙስሊም ወንድሞቼ አንዳነዶቹ ማሻ አሏህ ሌሎቹ ደሞ አይዞህ በርታ እያሉኝ የተከበረው ወር ረመዷን መጣ! እድሜዬ 16 ለቤተሰቤ የመጀመሪያ ቤተሰቦቼን የምፈራ እነሱም በጣም የሚወዱኝ መሆናቸው ረመዷንን ለመፆም ድፍረት አሳጣኝ..........
አንድ ረመዷን ብቻ አይደለም ሌላ ሁለት ተጨማሪ ረመዷኖች መፆም አልቻልኩም። ግን የአሏህ እዝነት አያልቅምና 2013እ.ኢ.አ ሸዐባን ወር ውስጥ ጁሙአ ልሰግድ መስጂድ ስገባ እናቴ አይታኝ አባቴን ደውላ ጠርታው ከመስጂድ ኹጥባ እስኪያልቅ ድረስ ጠብቀው ከሶላት በኃላ ከመስጂድ ስወጣ እናቴ እና አባቴ በሩቁ ከፊትለፊቴ ሲመጡብኝ ተመለከትኩ ሳያዩኝ ቶሎ ብዬ ወደሆነ ቤት ስር እጥፍ ብዬ ተደበኩኝ ከዛ አጎንብሼ ያአሏህ ነስረኝ ብዬ ረህማኑን ለመንኩት ከዛ ቀና ስል እናቴ ፊትለፊቴ ቆማ እያለቀሰች "እኔን ላንተ ብዬ ያረጀውትን እናትክን ትሸጣለክ" አለቺኝ
አሏሁ አክበር መሬት ተቀዳ ብትውጠኝ ምኞቴ ነበር ከዛ እናቴ "ና አሁን ዝም በልና ከፊቴ ቀድመህ ሂድ አለቺኝ" እኔ ምንም እንዳልገባኝ ሆኜ ምነ ሆነሽ ነው እማ አልኳት አሷም ዝም በልና ና ወደቤት ሂድ አለቺኝ እኔም እምቢ አልኳት ከዛ እሷ ጥላኝ ሄደች ኡፍ ብዬ እነደተነፈስኩ በጣም ምፈራው አባቴ በሌላ መንገድ ዞሮ ሊይዘኝ ከፊትለፊቴ ከች ብሎ ናቅደም ሲለኝ ወላሂ አቅም አነሰኝ በድንጋይ አንዴ ተረከዜን ድብን አርጎ መታኝ ከዛ በጭንቅላቴ ውስጥ በቃ አሁን በአሏህ ልከፍር ነው ብዬ በድንጋጤ አያሰላሰልኩ ከፊቱ ቀድሜ ወደ ቤታችን አመራው ከመስጂድ አብረውኝ የወጡ ጓደኞቼ ግማሾቹ ከኃላ እየተከተሉ ግማሾቹ የአባቴን እጅ እንዳይመታኝ እየያዙ ሊያስጥሉኝ ቢሞክሩም አልቻሉም።
እናቴ ከኃላችን እየተከተለች አባቴ እኔን እየገፈተረኝ ወደ ቤት አቀናን! እቤት እንደደረስን አባቴ ግቢአችን ውስጥ የበቀለ ሸንበቆ ከነ ስሩ ነቅሎ እቤት አስገብቶኝ ይገርፈኝ ጀመር ሸንበቆውን እኔ ላይ ስብርብር ሲያደረግ አክስቴ (የእናቴ እህት) ቤት ውስጥ ነበረች መሀላችን ገብታ ትገላግል ጀመረች መግቢያ የጠፋኝ እኔ ደሞ አሁን ሰልሚአለው ካልኳቸው ሲህር (ድግምት) አድርገውብኝ ያከፈሩኛል ብዬ ስለፈራው መሸምጠጥ(መካድ) ጀመርኩ አባቴ ሸንበቆው እጁን ቆርጦ ስላደማው ደሙን ሊጠርግ ወጣ ሲል እናቴ ከውጪ እያለቀሰች ገባች ከዛ እሷ"ምነው ፈጣሪዬ ምን በድዬህ ነው ለጄን ምታሰልመው" ብላ ስታለቅስ እኔ ደሞ ማደርገው ስለጠፋኝ ኧረ አልሰለምኩም ብዬ እሟገታት ጀመር እሷም "ከመስጂድ ስትወጣ አይቼሃለው" እኔም "እኔ አይደለሁም" አልኳት ይሄን ሲሰማ ደሙን ሊጠርግ የወጣው አባቴ በንዴት "ዝም አትልም አሁን አፍህን ያዝ" እያለ እኛ አካባቢ (ሐረርጌ) ሜንጫ የሚባል የስለት መሣሪያ አለ አሱን አምጥቶ ሊመታኝ መኝታ ቤት ሲገባ
እኔ ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሜ ሁለት ጫማዬን በእጄ ይዤ ፈረጠጥኩ ከዛ የሰፈራችን አንድ ሙስሊም ባለሀብት ቤት ገባው ቤተሰቦቼም ተከትለውኝ መጡ ከዛ በድንገት የት እንደገባው አጡኝ።
ከዛ በኃላ እዛው ቤት እያለው ሙደወር ለበስኩ ኢማማ ጭንቅላቴ ላይ ጣል አድርጌ ባጃጅ መጥቶ በር ላይ ቆመ ገባው ከዛ ሰፈር ወጥቼ ሊገምቱት የማይችሉት ሰፈር ሄድኩ አንድ ወንድማችን ቤት አረፍኩ።
ቤተሰቦቼ ደሞ ሰፈሩን ቀውጢ አደረጉት። ወዲህ ነው ነገሩ አባቴ ያለውን እውቅናና ገንዘብ ተጠቅሞ ሴራ ይሸርብ ጀመር በዛን ወቅት ወሎ ላይ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር
የኔን መስለም ከወሎው ጉዳይ ጋር አያይዞ ሴራ ጠነሰሰ የምን ሴራ አትሉኝም "
ክርስቲያኑን ልጄን መስጂድ ወስደው ገድለውብኝ አንድ ክርስቲያን መስጂዱ ውስጥ ተገደለ ብለው ሙስሊም እና ክርስቲያኑን ሊያጋጩት ነው" ብሎ ለመንግስት አካል አሳውቆ ሰፈሩን በፖሊስ በሚሊሻ በልዩ ሀይል አጨናነቀው ከዛ ጓደኞቼን ልጄ የት እንዳለ ካል ነገራቹኝ አሳስረቹዋለው ብሎ ያስፈራራቸው ጀመር ከዛ ጓደኞቼ ደውለው ነገሩን አሳወቁኝ እኔም ነገሩ ስሰማ ወላሂ ምገባበት ነው የጠፋኝ ግን ከአሏህ ወዴትም አየሸሽም እና አሏህ ሆይ አደራ አታክፍረኝ ብዬ አልቅሼ ምንም የማይሳነውን ከአርሽ በላይ ያለውን ራህማኑን ለመንኩት ከዛ በሰው ስልክ ለአባቴ ደውዬ እኔ በእራሴ ፍላጎት ወድጄ እና ፈቅጄ እንደሰለምኩ ።
አስረዳሁት እሱ ግን ሊሰማኝ ፍቃደኛ አልነበረም እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ካልተመለስክ ማደርገውን አውቃለው እንደውም ከፖሊስ ጋር አውራ ብሎኝ ስልኩን ለፖሊሱ ሰጠው ፖሊሱም የውሸት ዲሞክራሲውን እየነዛ "የፈለከውን እምነት መከተል መብትክ ነው" ብሎ ይሸብበኝ ጀመር ግን በድንገት ስልኩ ተቋረጠ ካርድ ጨርሶ ከዛ ልክ ከምሽቱ 12:00 ሲሆን አባቴ የሰፈሩን ቤት በጠቅላላ በፖሊስ ያስፈትሽ ጀመር ግን ምንም ማግኘት አልቻሉም እኔ ከዛ ሰፈር ጊዜ ሳላባክን እንደወጣው አላወቁም ከዛ ሌሊቱን ሙሉ ሲፈትሹ አደሩ የከተማችን ከንቲባ እንኳን አለቀረም በተጨማሪም አባቴ ለምዕራብ ሐረርጌ ዞን የኦርቶዶክስ እምነት አባቶች ደውሎ ተፅዕኖ ለመፍጠር ዘዴ አወጣ ግን አሏህ ከነሱ የበለጠ ዘዴ አውጥቶ እንደገና ሴራቸውን አከሸፈው........
ታሪኩ ብዙ ነው አላርዝምባቹ ከዛ በሚቀጥለው ቀን ልጄን ወሰዱብኝ ብሎ ክስ ሊመሠርት ወደ ሐረርጌ ዞን ፍርድ እየሄደ ሳለ የሰፈራችን ሰዎች እኔ አመጣዋለው ክስ ብትመሠርትም ምንም ማድረግ አትችልም ብለውት አረጋግተውት እኔ ያለሁበት አንድ ታማኝ ሰው ተላከ ከዛ ወደ ቀበሌ ፅ/ቤት ወሰዱኝ ከዛ እናቴ አባቴ አጎቴ የአክስቴ ልጅ ተሰብስበው መጡ እናቴ እና አባቴ ፊትለፊቴ ተቀመጡ እንዴት እንደሰለምኩ አስረዳዋቸው ይሄን ሲሰማ አባቴ የተናገረው ነገር ቢኖር እኔ ከዚህ በኃላ ልጄ አይደለህም ከኔ ምንም አትጠብቅ ወይም ደሞ ከእምነትህ ተመለስ አለኝ የኔ ምላሽ ግን እሱ እንደጠበቀው ቀላል አልሆነለትም የሰሃቦችን ልብ የሚነካ ታሪክ ሰምቼ ስለነበር እኔም እነዲህ አልኩት ከእምነቴ ከምመለስ የአንተ አባትነት ይቅርብኝ ከአንተ ምንም አልፈልግም ብዬ ፈረምኩለት እሱም አንተ የደረስክበት አልደርስም ብሎ ፈረመ ነገሩ እዚህ ላይ አበቃ አሏህ በእዝነቱ ነሰረኝ ከዛ ቤተሰቦቼ ያለሁበት ድረስ ሽማግሌ ልከው ወደ ቤት ተመለሼ የዘንድሮውን የመጀመሪያ ፆሜን 2013(1442) ረመዷን እቤተሰቦቼ ቤት ፆምኩኝ አል-ሀመዱ-ሊላህ! ታሪኬ እዚህ ላይ አበቃ..........
.በቅርብ ቀን በአስሐቡል የሚን ፕሮግራም ላይ በድምጽ የምቀርብ ይሆናል ። በዱአ አስታውሱኝ ወሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ።
የሠለምቴዎችን ታሪክ ለመከታተል ይወዳጁን
AS_HABULE YAMlNE TUBE
541 views14:08