2022-07-25 14:44:05
ከእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም የተወሰደ የሠለምቴዋ ቃልኪዳን ታሪክ ።
የበፊቱ ስሜ ቃልኪዳን ይባላል አሁን ደግሞ እስልምናን ከተቀበልኩኝ በኋላ ስሜ መናር ይባላል ።
እሥልምና ላውቅ እና ወደ ኢሥላም ልገባ የቻልኩበት ምክንያት ማንበብ ነው ።
በአካባቢዬ ጭራሹን ሙሥሊም ማህበረሰብ የሌለበት ብሎም ስለ እስልምና በክፉ እና በአጸያፊ መልኩ ከሚሠበክበት ቤተ እምነት ነው የመጣሁት ።
ሃይማኖትን ማወቅ እና ወደ ማንበብ ማነጻጸር የመጣሁት በመጀመሪያ የእናት አባቴ አምነት የኦርቶዶክስ ክርስትና አምነት ሲሆን እኔም እሥልምናን እስካገኘሁበት ጊዜ ድረስ በዚያው እምነት የምኖር ነበርኩ ። በኦርቶዶክስ ውስጥ ።
ከጊዜአቶች በኋላ ግን በነበረኝ እምነት ላይ አንዳንድ ጥርጣሬዎች እና ጥያቄ ይፈጠሩብኝ ጀመር ከእነርሱም በጥቂቱ ለምን ለተቀረጹ ምስሎች ለፎቶዎች ለምን እንሠግዳለን ?
የሚል ነበር..!
አንዳንዴም የሃይማኖት አባቶችን ቄሶችን በምጠይቅበትም ጊዜ ። ከፊሎቹ ምነው ጥያቄ አበዛሽ ሙሥሊም ልትሆኚ ነው እንዴ እያሉ ሙድ ይይዙብኝ ነበር ሌሎቹም እኛ ቅዱሳንን ለማስታወስ ነው እንጂ ለእነርሱ አንሠግድም ይሉኛል ። ይህ መልስ ለእኔ አልሸሹም ዞር ነው ።አጥጋቢ እና አሳማኝ መልስ ስላልሆነ ።
ነገር ግን መጸሐፍ ቅዱስ በሰማይም በምድርም ከምድር በታችም ለእግዚአብሔር አምሳያን አታርግ ይላል እና እንደዚህ አይነት ማስረጃዎችን በማመጣበትም ጊዜ የሚመልሱልኝ ነገር ስለሌላቸው ሃይማኖትሽን ልትለቂ ነው ወይ የሚል ነበር ። ይህንን ብሎም ሌሎች ነገራቶችን ከክፍል ጉዋደኞቼ ጋር ውይይት እናደርግ ነበር እና ከዚያ ነው ደግሞ ከፕሮቴስታንት እምነት ጋር የተዋወኩት።
ኘሮቴስታንት እምነት የስእሉን ጥያቄ መለሠልኝ ምክንያቱም ቸርች ውስጥ ስእላ ስእሎች ስለሌሉ ማለት ነው ። በፕሮቴስታንት እምነት 3 አመት እንደቆየሁ አሁንም ደግሞ ጥያቄ ይፈጠርብኝ ጀመር ማለት ነው ። ብዙ ብዙ ከመለኮት ጋር የማይያያዙ ስብከቶች አሉ አስተውሎ ለተመለከታቸው ። ሆኖም ሥላሴ ላይ ጥያቄ አነሳሁኝ ።
ሥላሴ ምንድን ነው ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔርስ ኢየሱስ ነው ...!? እግዚአብሔር ማን ነው..?
በዚሁ እምነት ላይ በምቆይበትም ጊዜ ስለ እሥልምና የሚሠበኩልን ነገራቶች ነበሩ እነርሱም ፦ እሥልምና አራጅ እንደሆነ፦ ሴቶችን የሚጨቁን ፣ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ የፈበረኩት እምነት ፣ በመስኪድ ውስጥ ዘንዶ እንዳለ እንደሆነ የመሳሰሉት የሃሰት ወሬዎችን ነበር የሚሰብኩን። ስለ እሥልምና እውነተኝነት እንዳናውቅ ቀድመው መጥፎ እሳቤ እንዲኖረን ያልሆነውን እሥልምና ውስጥ የሌለውን ሁሉ ይነግሩን ነበር ።
ሥለ ሥላሴ ቄሶችንም ፓስተሮችንም ጠይቄአለው ።ስጠይቅ ግን አእምሮ የማይቀበለው መልስ ነው የሰጡኝ ። ይህ ሚስጢር ነው ለአንች አይገባሽም ሥላሴ ትታመናለች እንጅ አትመረመርም እንዲህ እመረምራለው ካልሽ ታብጃለሽ እንጅ አይገባሽም ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ያስፈልግሻል በሚል ነው መልስ የሚጀምሩት ።
የፕሮቴስታንቶቹ ደግሞ ሥላሴን በሎጅክ ነው ለማስረዳት የሚፈልጉት እንቁላል ዛፍ ጽሐይን ሳይቀር ለምሳሌ ይጠቀሙታል።
ለምሳሌ ጽሐይ አንድ ናት ታበራለች ሙቀት አላት በሚል ሦስት ያደርጉትና ሥላሴን በዚህ ተረጂው ይሉኛል እኔ ግን በሚሰጡኝ መልስ ህሌናዬ አላረፈም ።
ሥላሴ የሚለው ሥም ራሱ ባይብል ላይ ፈጽሞ የለም ። ሌላው ነቢያቶችም አንዱን አምላክ ብቻ እና ብቻ እንደሰበኩ እውን ነው።
ባይብል እራሱ እስራኤል ሆይ ስማ ጌታ አምላክህ አንድ ጌታ ነው የሚለው እንጅ ጌታ አምላክህ ሶስት ናቸው አይልም ።
ሌላው ነገር ደግሞ በፕሮቴስታንት እምነት ውስጥ ቅባት የሚባል በብዙ ድራማ የታጀበ ለእኔም ሆነ ለማንም አእምሮ ለተሰጠው ለሠው ልጅ ትርጉም የማይሰጥ ነገር አለ ።
በሥተ-መጨረሻም ምንም ሃይማኖት ሳይኖረኝ ቀረሁ ። ለዓመታት ሃይማኖት አልባ ሆንኩኝ ማለት ነው። በቃ ምንም ሰላም ሊሰጡኝ አልቻሉምና።
ከዚያ በኋላ ነበር በራሴ መጽሐፍ ቅዱስን መርምሬ አንድ አምላክን ብቻ አመልካለሁ ወደሚል ደረጃ የመጣሁት በዚያ ነው ማንንም ሳልሰማ በራሴ ውሳኔ ወደ ማንበብ የገባሁት ።
ከዚያም ከሃገር የመውጣት እድል አግኝቼ
እዚህ ከመጣሁ በኋላ የተለያዩ የንጽጽር መጸሐፍቶችን የማንበብ ጀመርኩኝ ።
ከጊዜያቶች በኋላ አእምሮዬም አርፎ ህሌናዬም ተደስቶ የተፈጠርኩበትን እሥልምናዬን ያዝኩኝ ። እሥልምና ውስጥ መልስ አለ አልሃምዱሊሏህ ።
@
አስሓቡል የሚን የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም
እርሶ ሰለምቴ ኖት..!? እንግዲያውስ ታሪኮዎ ለሌሎች መማሪያ ይሆን ዘንድ ። ለአንዲት ነፍስ የሒዲያ ሰበብ ሊሆን ይችላልና ታሪኮዎን ያካፍሉን ።
አድራሻችን ፦
የሰለምቴዎች ግሩፕ
http://t.me/Selmeta
http://t.me//Ashabulyeminbot
ቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me/AshaBuleyamine
የፕሮግራሙ መገኛ ዩቱብ፦
ሠለምቴ የሆኑ ይምጡ ለመሥለም የሒዳያ ሠበበዎን ያካፋሉን! እኛም ለሌሎች አሥተማሪ በሆነ መልኩ እያዘጋጀን እናቀርባለን።
3.2K views11:44