2022-06-10 17:17:41
ፕሮፌሰሩ ኢማም
በአሜሪካ የሚገኘው የኢስላሚክ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ናቸው። በሜኖሶታ ሜናፖሊስ የዳረል ፋሩቅ መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም የአሜሪካ የፉቀሃዎች ስብስብ የፈትዋ ኮሚቴ አባል ናቸው። የተወለዱት በታላቋ አሌክሳንድሪያ ከተማ 1386 ሂጅራ ነው። የእውቀትን መንገድ ገና በ 12 አመታቸው አሊፍ ብለው የጀመሩ ሲሆን በ 14 አመታቸው አባታቸው ላይ ቁርአንን ሙሉ ሃፍዘው መጨረስና ሙሉውን በአንዴ ማሰማት ችለው ነበር። በመቀጠልም የእውቀቱን መንገድ በግብፅ ከሚገኙ ታላላቅ ሼኾች ጋር በመቀመጥ ማግኘት ችለዋል።እነ ሼኽ በርማዊ፣ሼኽ ሰይድ ኢብን ሰዕድዲን እና ሌሎችም ጋር ከአስር አመታት በላይ በመቀመጥ እውቀትን ከምንጩ መጎነንጨት ችለዋል።
ወደ ሳውዲ አረቢያ ሪያድ በመጓዝም በሸሪዓ አስተማሪነት ከስምንት አመታት በላይ አገልግለዋል። ከነ ኢማም ኢብን ባዝና የሳውዲ ታላላቅ ዑለማኦች አባል ከሆኑት ሼኽ አብድረዛቅ አልአፊፊ፣ሼክ አብደላህ ኢብን ቁዑድ፣ኢማም ኢብን ጂብሪን፣ሷሊህ አልፈውዛን፣ሷሊህ አልሼኽና ዓላማህ ሙሃመድ አልሃሰን አድ-ደደው የኢስላማዊ እውቀትን ተምረዋል።
በ14ቱም የቁርአን አቀራር ጥናት ደግሞ
ከነ ሼኽ አልሙቅሪእ ሙሃመድ አልኢስኪንድሪ፣
ሼኽ ሳሚር አድ-ዲመሽቂና ሼኽ ዓላማህ ደደውና ከሌሎችም ሼኾች በአስሩም የቁርዓን አቀራር ሰንሰለታቸውን ኢጃዛ መውሰድ ችለዋል። እሳቸውም በአሜሪካ በሪያድና በካይሮ ለብዙ ተማሪዎቻቸው ይሄን ሰንሰለት ያስተላለፉ ሲሆን የእውቀት ሰንሰለታቸውን የሰበሰቡበት ከ 40 በላይ ሼኾች ሲኖሯቸው።ይህንንም በኢንማዕ..ቢኢሳኒድ ወሊድ አልሚኒሲ በሚል ጥራዝ ሰብስበውታል።
ከሸሪዓ እውቀታቸው በተጨማሪ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እውቀታቸውን የተመለከቱ የሳውዲ ዑለሞች፣ በ 1418 ከሪያድ ወደ አሜሪካ ሊልኳቸው ችለዋል። በዛም እስካሁኑ ሰአት ድረስ በኢማምና ኽጢብ፣በማስቀራትና ፈታዋ በመስጠት፣ አሜሪካንን ከኢስላም ብርሀን ጋር በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።
ለሳቸው የእውቀት ደረጃ ምስክርነት ከሰጡ ታላላቅ ሼኾች መካከል የቀድሞ የሳውዲ የፈትዋ ኮሚቴ አባል አብድረዛቅ አልአፊፊ ይገኙበታል..
እኚህ ታላቅ ሸኽ ብዙ ኪታቦችን ፅፈው ያሳተሙ ሲሆን..
ሚስክ አልኺታም ፊ ሸርህ ዑምደቱል አህካም
ሙዘኪራ ፊ ሙስጠለህ አልሃዲስ
ሙኽተሰር ኢቅቲዳእ ሲራጠል ሙስጠቂም
አሰር ፊል ቂራአት አልዓሸራ የሚጠቀሱ ሲሆን በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን አለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር በዳኝነት ሊመሩ ሀገራችን ላይ ተሰይመዋል።
1.3K views14:17