2022-05-19 12:01:14
ክርስቲያኖች ምን ይላሉ?
እናንተ ሙሥሊሞች የፈለጋችሁትን እየበላችሁ ጾምን ትላላችሁ ? የፈለጉትን ከበሉ ምኑን ጾሙ ? ይላሉ… ጥሩ ጥያቄ ነው.!
በመጀመሪያ ጾም ማለት ከምግብ እና ከመጠጥ ነገር መከልከል ማለት ነው።
እውነት ነው የፈለግነውን እንበላለን አልሃምዱሊላህ ግን ለ14 ሰዓታት ያህል ያለምንም ምግብም ሆነ መጠጥ ንክኪ ከጾምን በኋላ ነው የፈለግነውን የምንበላው ። የትም ትርጉሙም ይህ ነው።
ግን እስኪ እኛ እናንተን እንጠይቃችሁ… ?
እናንተ ምን አይነት ጾም ነው የምትጾሙት 24 ሰዓት ሙሉ እየበላችሁ ሥጋ እና የእንሰሳት ተዋፆ ስላልበላችሁ ብቻ አይደል እንዴ ጾምን ብላችሁ የምታስቡት..?
እስኪ አስቡት 24 ሰዓት ሙሉ እንጀራ ሽሮ አትክልት ፍራፍሬ ጥራጥሬ አሳ የአትክልት ቅቤ/ዘይት እየበሉ ሥጋ ስላልተበላ ብቻ ጾምን ማለት ይቻላል ?
አዎ ካላችሁ የሃገራችን ሕዝብ 75% የእድሜ ልክ ጾመኛ ነው ማለት ነዋ! ምክንያቱም ሥጋ የሚያገኘው በዓመት አንዴ ወይም ሁለቴ ቢበዛ ሦስቴ ነው ። ሥለዚህ እነዚህ ሰዎች ያለምንም ፋሲካ ስለጾሙ ገነት ይገባሉ ማለት ነው?
ደግሞ የሚገርመው እኮ 2ወር ያለ ሥጋ ጾመው ጾሙ ሲፈታ እንኳን በምስር ወጥ በዓላቸውን የሚያከብሩ ሰዎች በሚኖሩባት ሃገር ነው ሥጋ አለመብላት ብቻ ጾም ነው የተባለው ። እነዚህ ሰዎች ጾምም ባይሆን እኮ አይበሉም ግን ሰው ሲጾም አይተው ነው እንጂ የጾሙት
ጾም ማለት ዋና አላማው እራስን በመጉዳት ወደ ፈጣሪ ማሰብ ነው እራስን በማስራብ የተራቡትን ማሰብ ነው።
እና ሥጋ ብቻ ቀርቶ ሥጋን የሚተኩ ምግቦችን 24 ሰዓት እየበሉ እንዴት ነው እራስን ጎድቶ ወደ ፈጣሪ የሚታሰበው? ቀኑን ሙሉ ሌላ ምግብን ጠግበው እየዋሉ እንዴት ነው እራስን አስርቦ የተራቡትን የሚያስበው ?
በባይብል ሥለ ጾም ይህንን ብሉ ይህንን አትብሉ የሚል አስተምሮ የለውም ። ክርስትና ውስጥ ግን ጾም ማለት ምን ማለት እንደሆን እራሱ መልስ የለም። መለኮት በሚባለው ቦታ ውስጥ ሥር የሌለው ነገር ምንጭ አይኖረውም ።
እኛ ሙሥሊሞች የምንጾመው አምላካችን አሏህ ሥላዘዘን ነው። እሥልምናን ለመተቸት የሚመች እምነት አይደለምና ከጉድለቶች ሁሉ የጸዳውን አሏህን የምናመልክበት ከጉድለት የጸዳ እምነት ነው ያለን አልሃምዱሊላህ
https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg
371 viewsedited 09:01