2022-02-01 20:51:04
በፊት የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነበርኩኝ ስሜም ምህረት ይባላል ። ምህረት በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ።
ኢሥልምናን እና የክርስትናን ምንነት ለማወቅ የቻልኩት በድንገት በማላውቀው ሰው ከንጽጽር ግሩፕ ላይ አድ በተደረኩበት ታይም ነው። ንጽጽር ግሩፑም የኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር ዒሳ ነበር ።
ውይይቶችን እያደመጥኩኝ እያደመጥኩኝ ሳለ
ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑን ሙሥሊሞች ሲያወሩ በጣም ተናደድኩኝ ። በውስጥ እየገባሁኝ ኡስታዝን እሳደባለው ልጆችን እሳደባለው። ለምን ብቻ ኢየሱስ አምላክ አይደለም አላችሁ ብዬ
እነርሱም የሆነ ጥቅስ ሰጡኝ ከባይብል ማርቆስ ፍእራፍ 12 29 በሰጡኝ ጥቅስ በጣም ተገረምኩኝ እና ማሰብ ጀመርኩ ። ባይብልንም ገልጬ አየሁኝ ጌታ አምላካችን ነው እንጅ ያለው ጌታ አምላካችሁ አላለም ።እዚህ ጋር ኢየሱስ የእኛም የእርሱም አንድ አምላክ እንዳለ በመጥቀስ እርሱም አምላክ እንዳልሆነ ያሳያል ።
ለሁለት ዓመት ያህል በሃይማኖት ንጽጽር ላይ ዘገየሁ። በመካከል ግን ስለ እምነት ያለኝ ትኩረት እና እሳቤዬ ቀጠለ ። ካቶሊክንም እሥልምናንም ማየት እና ማነጻጻር እና ማጣራት ጀመርኩ ።
እሥልምናን ቶሎ አልተቀበልኩም ነገር ግን ባለሁበት እምነት ላይ ሆኜ ብጸልይም ምንም ብል ውስጤ ደስተኛ ሆኖ እየተቀበለኝ አልነበረም ። ቀስ በቀስ ከካቶሊክ ርቄ ወደ እሥልምና ቀረብኩኝ ። ከባይብል ላይ ያሉትንም ጥቅሶች እያነበብኩኝ ማገናዘብ ያዝኩኝ ። ኢየሱስም ወደ ተራራ ወጥቶ እንደ ፀለየ እዚያው ባይብል ላይ ይናገራል።
ሉቃስ 6- 12 በእነዚያም ወራቶች ሊፀልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲፀልይ አደረ ይላል።
ይህንን ሳነብ አምላክ እንዴት ለሌላ አምላክ ይፀልያል ? የሚለው ጥያቄ ፈጠረብኝ ።እስከዛሬ የት ነኝ ብዬ እራሴን ጠየኩኝ።
ዩሐንስ 7- 16 ትምህርቴ ከላከኝ ነው እንጅ ከእኔ አይደለም ይላል ። የላከኝ ሲል ኢየሱስን የተላከ እና የላከው ደግሞ ሌላ አካል እንዳለ እየነገረን ነው ።ይህ የሚያሳየው ነቢይ መሆኑንም ነው ።
ዩሐንስ 14-24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም የምትሰሙት ቃል የላከኝ አብ ነው እንጅ የእኔ አይደለም ይላል ።
ቆም ብለን ማሰብ ያለብን ይህ ሁሉ ጥቅስ ባይብል ውስጥ ነው ያለው ።ኢየሱስ አምላክ እንዳለው እና ከአምላኩ ዘንድ የተላከ ነቢይ ፍጹም ሰው መሆኑንም እየነገረን ነው ። ታዲያ የእኛ የሙጢኝ ብለን አምላክ ነው የምንለው በምን መረጃ ነው ..!? መጽሐፍ ቅዱስ ቀጥታ የሚነግረንን እኛ ግን በፈለገን በግራም በቀኝም እያዞርን ነው የምንጓዘው ።
መምህሮቻችን እራሱ አይ ኢየሱስ እራሱን አምላክ ነኝ ብሎ መግለጽ ስለማይፈልግ ነው ብለው የሚነግሩን ጊዜም ነበር ። ግን ይገርማል አምላክ ከሆነ እንዴት በማንነቱ ያፍራል ? እንዴትስ የእኛም የእርሱም ፈጣሪ ሌላ አምላክ እንዳለ ይናገራል ? ቆም ብለን ማሰብ ያስፈልጋል ።
ሌላው ቅዱስ ቁርባን ነው። ቅዱስ ቁርባን የሚዘጋጀው ከስንዴ ነው ።ስንዴው ይፈጫል ይሞካል ይጋገራል ። ከተጋገረ በኋላ የራሱ የሆነ ቅርጽ ማውጫ አለው በዚያ ይቆረጣል ። ይህንን እኔም አዘጋጅ ነበር ።
ግን ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እና ሥጋ የሚባለው ከኸምር ከወይን ጠጅ ነው የሚዘጋጀው ።
የተዘጋጀው ስንዴ ሥጋው ነው ...!
ከኸምር ከወይን ጠጅ የሚዘጋጀው ደግሞ ደሙ ነው ይባላል ።
እንዴት ነው ይሄስ ነገር .? በእምነቴ አለም ውስጥ እያለሁኝ ምንም አይመስለኝም ነበር ግን ጥናት እና ምርምር ስጀምር እንዴት ነው የአምላክ ደም እና ሥጋ ሊሆንስ የሚችለው ብዬ ውስጤን በጥያቄ ማጨናነቅ ጀመርኩኝ ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በኤፌሶን 5- 18 ላይ መንፈስ ይሙላባችሁ እንጅ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና ይላል ። እዚህ ጋር በወይን ጠጅ አትስከሩ እያለ እነርሱ ደግሞ በግልባጭ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው ብለው ኸምርን እየነከሩ ይሰጡናል ።
እሥልምናን ከተቀበልኩኝ በኃላ አንድ ቄስ ጋር በመደወል አባ ኤፎሶን 5- 18 ላይ እንዲህ ይላል ብዬ ነገርኳቸው ። እንዴትስ መጽሐፉ ይህንን እያለ እናንተ ግን ቁርባንን የምታስፈጽሙን በዚህ ነው ብዬ አልኳቸው ። እነርሱም አትስከሩ ነው እንጅ ያለው መጠጣቱ ይቻላል ብለው መልስ ስጡኝ ሱብሃነሏህ። በጣም ነው የገረመኝ ። ስለታቦትም ጠየኳቸው በጎግል ሰርች አድርገሽ እይውና አንብቢ ይህንን ለመመስ ጊዜ የለኝም አሉኝ ።
ይሄስ እንዴት ነው ? ቆም ብለን እናስብ !
እኔ ግን ኢትዮ ውስጥ አምልኮ ስለሚሰጡት 44 ታቦቶች መልስ ፈልጌ ነበር ።
አልሃምዱሊሏህ የእሥልምናን መምህሮች ሳላደንቃቸው አላልፍም ። አንድን ነገር ስንጠይቅ ወዲያውኑ መልስ ይሰጡናል ።
እኔ እውነትን አግችኜ አምላኬ መርቶኝ ትክክለኛውን መንገድ አግኝቻለው። አለማወቅ ኃጢኣት አይደለም ነገር ግን እያወቅንም ሆነ ላለማወቅ ችላ ማለታችን ዋጋ ያስከፍላል ።እምነት ማለት የማንኛውም ሰው የግሉ የህይወት ጎዳና ነውና አንብቡ እወቁ ያላችሁበትንም እምነት መርምሩ እላለሁኝ። ምህረት ሠለምቴዋ ጸሐፊ ሳራ ሰለምቴዋ ።
የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-
AS_HABULE YAMlNE TUBE
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q
በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125
ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta
አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot
ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A
1.2K viewsedited 17:51