2021-12-09 16:15:17
‹‹አይነኬው የመድረኩ ፈርጥ››
ዛሬ እስኪ ስለ አንድ ጀግና ሰው በጥቂቱ እናውራ በንጽጽር መስክ ከዶ/ር ዛኪር ናይክ እስከ ዶ/ር ቢላል ፊሊፕስ.. ከዶ/ር ሻቢር አሊ እስከ እውቁ የንጽጽር ምሁርና ሰለምቴ አረብ ኢሥላም………
https://t.me/+RXYpviFTL70OQdu2
ሺዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ስለቻለው ታላቁ ሰው!!!! ሸህ
አህመድ ዲዳት!!!
ልጃቸው ዩሱፍ ኢስላም ‹‹የመድረኩ አንበሳ››/lion of the stage/ ይላቸዋል፡፡
ምናልባት በንጽጽር መስክ የንግግርና የጹሁፍ ክህሎትን ሁለቱንም በማጣመር የሚስተካከላቸው
አይኖርም፡፡
አብዛኛው ሰው ሸይኹን የሚያውቃቸው አፍ
በሚያዘጋ የክርክርና የመድረክ ንግግር ጥበባቸው ነው፡፡
ነገር ግን እኚህ ሸይኽ መጽሀፍት በመጻፍም ረገድ
የተዋጣላቸው ነበሩ፡፡ በመጽሀፍ ረገድ በሚልዮን ኮፒዎች መሸጥ የቻሉ ከ20 በላይ መጽሀፍትን አበርክተዋል፡፡
ብዙዎቹ መጽሀፍቶቻቸው ደግሞ በተለያዩ ቋንቋዎች
መተርጎም የቻሉ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ
.
- >Is the bible God’s word
- >What the bible says about Muhammad
- >Muhammad the greatest
- >Al-qura’n the miracles of miracles የተሰኙት
ይጠቀሱበታል፡፡
->
በዚህም ለእስልምና ላበረከቱት ታላቅ አስተዋጽኦ የንጉስ
ፋይሰል ሽልማትን/international prize for service to islam/ ለመቀዳጀት በቅተዋል፡፡
አንድ ናይጀሪያው የንጽጽር ሰው ስለሸይኹ በአጭሩ እንዲህ ያስቀምጠዋል፡፡
‹‹በሚሽነሪዎች ከመጣብን ወረራ የታደጉንና በምን መልኩ አፋቸውን ማዘጋት እንዳለብን አይናችንን የከፈቱልን መምህራችን ናቸው››
ስለሸይኽ አህመድ ዲዳት ለመግቢያ ይህን ካልን አስኪ ወደ ገጠማቸው እንለፍ::
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪ የነበሩት እውቁ የነጻነት
ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በ1994 ለጉብኝት ወደ ሳዑዲ አረብያ ሂደው በነበረበት ወቅት ያጋጠማቸውን ክስተት አስመልክቶ አልጀዚራ remembering the life of sheikh ahmed dedat በሚለው መጣጥፉ እንዲህ ማለታቸውን ይነግረናል፡፡
-
‹‹ሳዑዲ ውስጥ የተለያዩ ወጣት ምሁራንን ባገኘኋቸው
ቁጥር የሚጠይቁኝ ጥያቄ
‹‹ሚስተር ማንዴላ ሸይኽ አህመድ ዲዳት እንዴት ናቸው? የሚል ነበር፡፡
በጣም የሚገርመው ለቃለመጠይቅ
የሄድኩበት የቴሌቭዥን ጣቢያ የመጀመሪያ ጥያቄው
‹‹ሸይኽ አህመድ ዲዳት በደቡብ አፍሪካ እንዴት ናቸው?››
የሚል ነበር ሲሉ ሸይኽ አህመድ ዲዳት በሙስሊም ዓለም ዘንድ የነበራቸውን ጥልቅ ፍቅር ገልጸዋል፡፡
ከጉብኙቱ መልስም ቀጥታ ወደ ሸይኽ አህመድ ዲዳት በመደወል ሀገራቸውን ያስጠሩ ድንቅ ሰው በመሆናቸው ምስጋናቸውን ችረዋቸዋል፡፡
https://t.me/+RXYpviFTL70OQdu2
አላህ ይዘንላቸው!! ከሰፊው እዝነቱም ያስገባቸው!!
373 views13:15