Get Mystery Box with random crypto!

AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር A
Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር
Channel address: @ashabuleyamine
Categories: Uncategorized
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 7.32K
Description from channel

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q
Telegram _Join
http://t.me/AshaBuleyamine
Twitter
https://twitter.com/AshabuleYamlne?s=09
Facebook page
https://www.facebook.com/Ashabuleyamine/
Website
http://ashabulyemin70.blogspot.com

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


The latest Messages 15

2021-11-30 17:48:43
አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ ።

እንደሚታወቀው አስሓቡል የሚን ዘርፈ ብዙ ቅርንጫፎች አሉት ። ሆኖም ግን የእኛ አድራሻ ያልሆኑ እና እኛ የማናውቃቸው እኛ ያልከፈትናቸው በእኛ ሥም የተከፈቱ ቻናሎች እና መልእክት መቀበያ እና መስጫ ቦቶች በቅርቡ ተከፍተዋል ። ለእናንተ ለማለት የወደድነው እስሓቡል የሚን እንደሚታወቀው ዲናችንን አገልጋይ እና ዑማውን ጠቃሚ በእሥልምና አስተምሮ እና አደቦች ውስጥ ያለ የኸይር ስራ አስኪያጅ ነው ። የእኛ ባልሆኑ አድራሻዎች ከኢሥላም አስተምሮ እና አደቦች ያፈነገጠ ነገር ከተሰራ እና ከታየ እኛ እንዳልሆንን ለማሳወቅ እንወዳለን ።

የእኛ ትክክለኛ አድራሻችን ከታች የተጠቀሱት ብቻ እና ብቻ ናቸው ።

አስሓቡል የሚን የፌስ-ቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Ashabuleyamine

አስሓቡል የሚን ዩቱብ
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

አስሓቡል የሚን ቻናል
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

Twitter
https://twitter.com/AshabuleYamlne?s=09

Website
http://ashabulyemin70.blogspot.com

የሠለምቴዎች እንግዳ መቀበያ
https://t.me/Selmeta

አስተያየት መስጫ ቦት
http://t.me//Ashabulyeminbot

አስሓቡል የሚን አህለል ኸይር እንግዳ መቀበያ
https://t.me/joinchat/Th93dNNUa7fV1c79

ኦላይን የሱመያዎች መድረክ እንግዳ መቀበያ
https://t.me/+uOXoIXLrLCcxOTA0

ይወዳጁን
789 viewsedited  14:48
Open / Comment
2021-11-29 14:25:39 «ከሰዎች ይደበቃሉ፡፡ ከአላህ ግን መደበቅ አይቻላቸውም፡፡»
.
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
.
አማኞች በምንም ምክንያት ለእኩያን ወግነው ሊሟገቱላቸው እንደማይገባ አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣን በግልፅ ተናግሯል። ለፖለቲካ አሰላለፍ፥ለብሄር ወገንተኝነት፥ ለጥቅማቸው ወይም ሌላ ምክንያት በዚህ ዓለም ሳሉ ለእኩያን ቢከራከሩላቸውና ጥብቅና ቢቆሙላቸው እነኝህ ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ቅንጣት በማይፈይዱበት በእለተ ትንሳኤስ አላህ ፊት ማን ይሟገትላቸዋል? ሁላችንም በጥሞና ቀጣዩን የቁርአን አንቀጽ እንመልከት።አላህ እንዲህ ይላል፦

“ለነዚያ ነፍቦቻቸውን ለሚያታልሉት (ጥብቅና በመቆም) አትሟገት፡፡ አላህ አጭበርባሪና ኃጢአተኛ (የሆነን ሰው) አይወድምና፡፡ ከሰዎች ይደበቃሉ፡፡ ከአላህ ግን መደበቅ አይቻላቸውም፡፡ በሌሊት እርሱ የማይወደውን ቃል በሚነጋገሩበት ወቅት አብሯቸው ነበር፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ያካበበ÷ (ሁሉንም ዓዋቂና ተቆጣጣሪ) ነው፡፡ እነሆ ከዚህች ዓለም ላይ እናንተ ተከራከራችሁላቸው፡፡ በዕለተ ትንሳኤ ከአላህ ዘንድ ማን ይሟገትላቸዋል ማንስ ጠበቃ ይሆናቸዋል?” (ቁርኣን፥4÷107-109)

የዚህ አንቀፅ መልዕክት ለሕዝቡ ሁሉ ቢሆንም አንቀጹ በምክንያትነት ሊወቅስ የወረደው መልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) አስመልክቶ ነበር፡፡ ታሪኩን ቲርሚዚ÷ ኢብኑ ጀሪር÷ ኢብኑ አቢሃቲም÷ አቡሻይ እና ሓኪም ቀታዳ ኢብኑ ኑዕማንን አጣቅሰው ዘግበዋል፡፡

ታሪኩ እንዲህ ነበር። የበኑ ኡበይረቅ ጐሣ አባላት የሆኑ ቢሽር÷ቢሽር እና ሙበሽር የተሰኙ እኩያን ግለሰቦች ነበሩ፡፡ “ቢሽር” ግን ሙናፊቅ ነበር፡፡ ግጥም በመግጠም ሰሀቦችን ያጥላላ ነበር፡፡ በዚሁም በሰዎች ዘንድ ታወቀ፡፡ የርሱን ግጥሞች የሰሙት ሰሀቦች “ይህንን ግጥም ይህ እኩይ ግለሰብ እንጂ ማንም አይገጥመውም” ይሉ ነበር፡፡ ይህንንም የሰሀቦችን ንግግር ቢሽር ሲሰማ ስንኝ በመቋጠር “አንድ ግጥም በሰሙ ቁጥር ሳያጣሩ ጆሮአቸውን ደፍነው እርሱ ነው” ይላሉን? የሚል ይዘት ያለው መልዕክት አሰራጨ፡፡

ይህ በእንዲህም እያለ እነኚሁ የበኒ ኡበይሪቅ ሰዎች በሌሊት የቀታዳ ኢብኑ ኑዕማን አጐት የሆነውን የሪፋአን ሠይፍ÷ ጋሻ ፣ ጦር፣ ምግብና ሌሎች ንብረቶችን ቤት ሰብረው ወሰዱ፡፡ ይህን ጊዜም ሪፋአና ቀታዳ ጋር ሆነው ሌባውን ለማፈላለግ ተንቀሳቀሱ፡፡ በኒ ኡበይሪቆች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ የሚያመለክት መረጃ አገኙ፡፡ ሄደውም ጠየቋቸው እነርሱም “እኛ አልሠረቅንም፡፡ የሰረቀውም ሊበድ ኢብኑ ሰህለ ይመስለናል “ሲሉ መለሱ፡፡ ይህ ግለሰብ ግን ምጡቅ ስብእና የነበረውና በዚህ በፍፁም ሊጠረጠር የማይችል ነው፡፡ በርሱ ያላከኩት ጥርጣሬን ከራሳቸው ለማስወገድ ነበር፡፡ በስርቆት የታማው ሊበድ ኢብኑ ሰህል ሰይፉን መዞ ወደ በኒ ኡበይሪቅ ሰዎች ዘንድ ሄደ፡፡ “እኔ ሌባ ነኝን? በአላህ እምላለሁ ይህንን ሰይፍ አንገታችሁ ላይ ሳላሳርፍ የሰረቀውን ግልፅ አድርጉ፡፡” አላቸው። እነርሱም “ከኛ ዞር በልልን! የሰረቅከው አንተ አይደለህም፡፡” አሉት፡፡ እርሱም ተዋቸው፡፡

ንብረቱ የተሰረቀበት ሪፋአ ያሰባሰበው መረጃ ሁሉ ጥርጣሬውን ወደበኑ ኡበይረቅ ሰዎች አነጣጠሩ፡፡ በዚህን ጊዜም ሪፋ እና ቃታዳ ተነጋግረው ጉዳዩን ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ አቀረቡ፡፡ የበኑ ኡባይሪቅ ጐሣ አባላት የሆኑትን ግለሰቦች ከሰሱ፡፡ ንብረቱን የሰረቁት የበኑ ኡበይሪቅ ሰዎችም በተራቸው «ስማችንን በስርቆት አጠፋ» በማለት ሪፋአንና ቀታዳን መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ “ያለምንም ማስረጃና ምስክርም ሰማችንን አጠፉ” ሲሉም ከሰሱ፡፡ ጉዳዩንም መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ተመለከቱ፡፡

እነሪፋእና ቀታዳ የተጨበጠ ማስረጃና ምስክር እንዲያቀርቡ ተጠየቁ፡፡ እነርሱ ያላቸው ማስረጃ ቀጥተኛ ሳይሆን የአከባቢ ማስረጃ ነበር፡፡ መልዕክተኛውም (ሰ.ዐ.ወ) ለበኒ ኡበይሪቆች በመወሰን እነቀታዳን ወቀሱ፡፡ ምስክርና ቀጥተኛ ምስክር ሳይይዙ የግለሰቦችን ስም ማጥፋታቸው በመጥቀስ ተከራከሯቸው፡፡ በድርጊታቸውም ወቀሷቸው፡፡ እነ ቢሽር ጨለማን ተገን አድርገው መስረቃቸው ሳያንስ የተሰረቀባቸውን ሰዎች በስም ማጥፋት ከሰው አስወቀሱ፡፡ እነ ሪፋእና ቀታዳ ግን ንብረታቸውም ተሰርቆም ዳግም ስም በማጥፋትም ተወቀሱ፡፡

ይህን ሁሉ ነገር ይመለከት የነበረው አላህ (ሱወ) የእኩያንና መናፍቃኑን ጥፋተኝነት አረጋገጠ፡፡ መልዕክተኛውም ምስክርና ግልፅ ማስረጃ ባለመኖሩ ለእኩያኑ በመከራከራቸው ተወቀሱ፡፡ እንዲህም አለ፡-

“እኛ ሰዎችን አላህ ባመላከተህ (ፍትህ) ትዳኝ ዘንድ መጽሐፉን በአንተ ላይ በእውነት አወረድን፡፡ (ስለሆነም) ለከዳተኞች ተሟጋች (ጠበቃ) አትሁን፡፡ አላህን ምህረት ጠይቅ፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ ለነዚያ ነፍሶቻቸውን ለሚያታልሉት (ጥብቅና በመቆም) አትሟገት፡፡ አላህ አጭበርባሪና ሃጢአተኛ (የሆነን ሰው) አይወድምና፡፡ ከሰዎች ይደበቃሉ፡፡ ከአላህ ግን መደበቅ አይቻላቸውም፡፡ በሌሊት እርሱ የማይወደውን ቃል በሚነጋገሩበት ወቅት አብሯቸው ነበር፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ያካበበ÷ (ሁሉንም ዐዋቂና ተቆጣጣሪ) ነው፡፡ እነሆ ከዚህች ዓለም ላይ እናንተ ተከራከራችሁላቸው፡፡ በዕለተ ትንሳኤ ከአላህ ዘንድ ማን ይሟገትላቸዋል? ማንስ ጠበቃ ይሆናቸዋል?” (ቁርኣን።4÷105-109)

ይህ የቁርኣን አንቀፅ ለመናፍቃን መሟገትን አስመልክቶ ጠንከር ያለችን መልዕክትን ያዘለ ነው፡፡ አንቀፁ የወረደበት ምክንያት ደግሞ መናፍቃኑን ይታገሉ በነበሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ ጥብቅ ያደርገዋል፡፡ በስርቆቱ ጉዳይ ምስክርና ቀጥተኛ ማስረጃ በሌለበት ነገር ግን ግለሰቦቹ ቀደም ብለው በእኩይነታቸው የታወቁ ነበር፡፡ ቢሽር ደግሞ ሙናፊቅ ከመሆኑም በተጨማሪ የሰሀቦችን ስም ያጠፋ የነበረ ግለሰብ ነው፡፡ በመሆኑም ምስክርና ቀጥተኛ ማስረጃ ቢጠፋም መልዕክተኛው ለእኩያኑ ወግነው በመከራከራቸው ተወቀሱ፡፡

ከዚህ ታሪክ እኩያን ራሳቸው በደል ፈጽመው ንጹሓንን መልሰው ሊከሱ እንደሚችሉ፥ ያለ ተጨባጭ ማስረጃ ሌሎችን መወንጀልና መፍረድ፥እንዲሁም ለእኩያን ጥብቅና ቆመን መሟገት እንደማይገባን እንረዳለን።

በመጨረሻም በጥላቻ፥ለፖለቲካ ትርፍና ሴራም ሆነ ሌላ በምክንያት መስጂዶቻችንና ንጹሓንን ላይ ጥቃት የፈጸመና የሚፈጽም፥ ራሱ ጥቃት ፈጽሞ በሌላው ያላከከና የሚያላክክ፥ እንዲሁም እውነቱን እያወቀ ለመሸፋፈን የሚተጋም ጭምር ማንም ይሁን ማን አላህ የክፉ ሥራውን ዋጋ ይስጠው።
471 views11:25
Open / Comment
2021-11-29 14:25:35
443 views11:25
Open / Comment
2021-11-27 17:18:03 ‹‹ከአላህ ባርያዎች ውስጥ ሰዎች አሉ፤ ነቢያትም ሰማእታትም ሳይሆኑ ግና የቂያማ ለት ነብያቱ እና ስማእታቱ በነዚህ ሰዎች የክብር ስፍራ ይቀኑባቸዋል።›› አሉ ነቢ ሰዐወ።

‹‹ያ ረሱለሏህ! እነማን ናቸው?›› ሲሉ ሰሓባዎች ጠየቁ።

‹‹እነሱ በአላህ ውዴታ የተዋደዱ ሲሆኑ በመካከላቸውም ዝምድናን ያላሳበቡ ናቸው። በውዴታቸው መካከልም ምንም አይነት የጥቅም ግንኙነት የለም ። ወላሂ! ፊቶቻቸው ብርሀን ነው፣ የተሰየሙበት ዙፋንም ብርሀን ነው፣ ቂያማ ለት ሰዉ ሲሸበር እነሡ አይሸበሩም፣ ሰዉ ሲያዝንም በዝያ ለት እነሱ አያዝኑም›› ሲሉ ነቢ ሰዐወ መለሱላቸው።

ከዚያም ረሱል ሰዐወ ይህንን የቁርአን አያ አነበቡ፦‹‹ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡

(እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው።ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡›› ሱረቱ ዩኑስ
#ለሌችም_ሼር_ያድርጉ
https://t.me/joinchat/RXYpviFTL70OQdu2
647 viewsedited  14:18
Open / Comment
2021-11-25 17:28:36
ጥያቄ ስጠይቃቸው ጥያቄ አትጠይቂን ይሉኝ ነበር የሃይማኖት አባቶች ። ሠለምቴዋ ትእግስት በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም በቁጥር 32





የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-





AS_HABULE YAMlNE TUBE
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A
1.1K viewsedited  14:28
Open / Comment
2021-11-23 18:34:34 ሁሉ ነገሩ ጥሎ ወደ ነቢያችን ﷺ የሄደው ታላቅ ሰው የጆንያው ባለቤት የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን

#የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን(ረ.ዐ) የህይወት ታሪክ
እስልምናን በመቀበሉ ብቻ የለበሰውን ልብስ እንኳን ሳይቀር በአጎቱ ሀብት ንብረቱን ተቀምቶ ጆንያ ለብሶ የናፈቃቸውን ነቢዩን ﷺ ለማግኘት ጉዞውን ወደ መዲና አደረገ ልክ መዲና ሲደርስ የነቢዩን ﷺ ቤት በር ላይ ቆሞ የእነርሱን ከቤት መውጣት በናፍቆት ይጠባበቅ ጀመር ነቢዩ ﷺ ከቤት ሲወጡ ባየ ጊዜ የደስታ እንባው ጉንጩ ላይ መፍሰስ ጀመረ የናፈቃቸውን ወዳጆቹን እና
ነቢዩ ሶላት አሰግደው እንደጨረሱ እንደ ልምዳቸው ቆሙ እና ማን ሰገደ ማን ቀረ እያሉ የባልደረቦቻቸውን ፊት ማስተዋል ጀመሩ፦

ከዛ ይሄንን ወጣት አዩት ከየት ነው የመጣህ አንተ ወጣት ብለው ጠየቁት እርሱም ከሙዘይና ጎሳ ነው ሸሽቼ የመጣሁት አሏቸው፦ ነብዩ ስምህ ማነው አሉት አብዱል_ኡዛ(የኡዛ_ባርያ) እባላለሁ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተገርመው አዩት እና ይሄ የለበስከው ጆንያ ምንድነው ልብስ የለህም ብለው ጠየቁት፦

እርሱም አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አጎቴ በእርሶ መስለሜን ባወቀ ጊዜ ያለኝን ንብረቴን ሁሉ ቀማኝ ከእነዚህ ጆንያዎች ውጪ ምንም አላገኘሁም አንተን ለመገናኘት ስል ላይ እና ታች አስሬ ወደ አንተ መጣሁ የአላህ መልእክተኛ አሏቸው፦

ነቢዩ ﷺ ይህንን አደረክ እንዴ አንተ ለአላህ እና መልእክተኛው ስትል ንብረትህን ጥለህ መጣህ ? አላህ በእነዚህ ሁለት ጆንያዎች ልብስ ይስጥህ ጀነት ውስጥ የፈለከውን እየበላህ የፈለከውን ለብሰህ ኑር በጀነት ውስጥ አንተ ከአሁን በኋላ #አብዱል_ኡዛ አይደለህም #ዙል_ቢጃደይን ነህ የጆንያዎች ባለቤት ነው ስምህ ።

ኡላሞች ይሄ ሰው የውመል ቂያማ መክሉቃታ በአላህ ፊት በቆመበት ፊት ይጠራል አንተ ዙል ቢጃደይን ውጣ ወደ አላህ ይባላል ።

ዙል ቢጃደይን ንብረቱን ሁሉ ነገሩን ትቶ ወደ ነቢዩ ﷺሸሸ እራቁቱን እሳቸው ጋር ተገናኘ አህለ ሶፋ የሚባሉ ነቢዩ ﷺሶሃባዎች ደሀዎች ከነብዩ ቤት ጀርባ የሚኖሩ ሰዎች አሉ ከነሱ ጋር መኖር ጀመረ ይሄ ሶሃባ ።

አብዱል ኡዛ የዛሬው አድሱ ስሙ አብደላህ ዙል ቢጃደይን ይባላል አብደላህ ከሰለመ በኋላ የአላህ ሱብሃናሁ ወተአላ ትልቅ ባርያ ሆነ ከኢባዳዎቹ ውስጥ በጣም ዱዓ እና ዚክር ያበዛ ነበር፦ ተመላሹ ተፀፃቹ ብለው ነበር ስሙን የሚጠሩት ሌላው ባህሪው ቁርአን መቅራት በጣም ያበዛ ነበር ።

ከችግር ጋር ምቾት አለ ። ከፈተናዎች በኃላ ኸይር ነገር ይመጣል ።

65፦7 አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል፡፡
94፦5 ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡

ኢብኑ አህመድ


https://t.me/joinchat/RXYpviFTL70OQdu2
1.1K views15:34
Open / Comment
2021-11-23 18:34:23
922 views15:34
Open / Comment
2021-11-11 18:31:25

1.0K views15:31
Open / Comment
2021-11-11 18:25:30 ለእኔ ለመስለሜ ሰበብ የሆነኝ የመሳጅድ አዛን ነው ። #ሰለምቴዋ #መዲና በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም #ቁ-32

በቅርብ ቀን ሙሉ ታሪክ ይለቀቃል።


2.8K viewsedited  15:25
Open / Comment