Get Mystery Box with random crypto!

AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር A
Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር
Channel address: @ashabuleyamine
Categories: Uncategorized
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 7.32K
Description from channel

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q
Telegram _Join
http://t.me/AshaBuleyamine
Twitter
https://twitter.com/AshabuleYamlne?s=09
Facebook page
https://www.facebook.com/Ashabuleyamine/
Website
http://ashabulyemin70.blogspot.com

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


The latest Messages 18

2021-10-06 16:33:58 አርፍጄ ከነቃሁ በሁዋላ ጉራጌው ጉዋደኛዬን እስቲ ዛሬ መስጂድ ውሰደኝ ብዬ ጠየኩት፡፡ ሳየው በጣምደስተኛ ይመስል ነበር፤እኔ ግን ሌላ ምንም አስቤ አልነበረም…በቃ ሁኔታውን ማየት ስለፈለኩ ነበር፡፡

መደወር ገዝቶልኝ ወደ መስጂድ ስንገባ ሰው ሞቶ ነበር፡፡ ወደ ውስጥ ስገባ ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኝ
ነበር፡፡ ጥቂት ቁረአን የሚቀሩ ሰዎችንም ተመልክቼ ነበር፡፡ ታዲያ ውስጥ ኢማሙ አንድ ነገር ተናገረ፡፡

‹አንዱ ወንድማችንን ሲወስድብን አንዱን ወንድማችን ተካልን›ነበር የኢማሙ ንግግር፡፡ ይህን ያለበት
ምክንያት አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ እሱም እኔ ነኝ፡፡

በጉራጌው ጉዋደኛዬ አመካይነት ሳላምንበት ሸሀዳ
ይዤ ነበር፡፡ ሸሀዳ ለመያዝ አስቤ ስላሌድኩ አያያዜ በእምነት ላይ የተመሰረተ አልነበረም፡፡ ውስጤ
ምርምር ለማድረግ ይዳዳው ነበር፡፡ ግን በአንድ አጋጣሚ ደንገት ወደ መስጂድ ብመጣ ሙስሊም ሆኜ
ተገኘሁ፡፡

እስልምናን ተረዳሁት…. ከሰለምኩ ከሁለት ቀን በሁዋላ ረመዳን ገባና መጾም ጀመርኩ፡፡ ለኔ መጾም ከባድ ነገር
አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ ከልክ ያለፉ ጾምችን አስተናግድ ስለነበረ፡፡

በኔ የእስልምና ህይወት ውስጥ ወርቃማው ጊዜ ይሄ የመጀመሪያዬ የሆነው ረመዳን ነበር፡፡ ብዙ ዳአዋዎችን
የሰማሁበት፤የሙስሊሞችን የእምነት ጥንካሬ ያየሁበት ነበር፡፡ ለጥቆ ቀጥታ ወደ ቂራት ነበር የገባሁት፡፡

አሊፍ፣ባ፣ታ…ማለት ስጀምር ሁሉም ነገር ተቀየረ፡፡ አስቀድም እስልምናን በቤተሰቡ የተቀበለ ሰው ስለተውሂድ እና ስለአቂዳ ሲወራ ብዙ ግድ ላይሰጠው ይችላል፡፡ ለኔ ግን ልዩ ስሜት ይፈጥርልኝ ነበር፡፡

በእውነት ከአላህ ውጭ በቅንነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) የአላህ
መልዕክተኛ የመሆናቸውን እውነት በሂደት መላ የማቀው ሀቅ ላይ ተንሰራፋ፡፡ ሀቅን ከሀሰት መለየት ጀምሬ ነበር፡፡
ይሄም የሆነው በእስልምና ልዩ ባህሪ ነበር፡፡ እስልምና
እንደማር ነው፤ሲያዩት የሚያስጠላሲቀምሱት የሚጣፍጥ!!!


ይቀጥላል
በድምጽ ለማድመጥ




የተለያዩ ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ የሰለምቴዎችን ታሪክ ያገኙበታል ፦

የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-




AS_HABULE YAMlNE TUBE

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

የሠለምቴዎች መዝናኛ እና መማሪያ ግሩፕ
834 views13:33
Open / Comment
2021-10-06 16:33:58 መልካሙ አበራ ወይም ዲያቁን ዮሀንስ እባላለው፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ፡፡

በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኬን ላካፍላችሁ ወደድኩኝ ።

እርሱም ወደ ተፈጠርኩበት እምነት እንድመለስ ያደረገኝ አጋጣሚ ቢኖር ። እንዴት ሰለምኩኝ?

‹‹ ብርቱ የሆነ የስላሴ አመለካከት ያለበት ኦርቶዶክስ፡፡ እናት እና አባቴም እንደኔው ኦርቶዶክስ ናቸው፡፡
ኦርቶዶክስ ሲባል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማለቴ ነው፡፡ ሀይማኖቴን ከቤተሰቤ ነው የወረስኩት፡፡
ሀቂቃ ቤተሰቦቼ እንደ ሀቅ በተቀበሉበት እምነት ላይ ጠንካራ አቁዋም ነበራቸው፡፡ ገና በልጅነት ነበር የስለት ልጅ
መባል የጀመርኩት፡፡ የስለት ልጅ መባል የዛን ያህል ቀላል ነገር እንዳይመስላቹ ፡፡

አንድ ልጅ ቤተሰቡን በህመም ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ያስቸግር ከነበረ በሚያምኑበት ታቦት ሁሉ እየተሳሉ ልጁ ሲድን ያዳነው ያ ታቦት እንደሆነ እና ታቦቱን በየደብሩ በአደራ እየተሰጠ እንዲያገለግል ይደረጋል፡፡ እኔም ላይ ተመሳሳይ ነገር ነበር የሆነው፤ገና በልጅነቴ የስለት ልጅነቴን መቀበል እና ታቦት እያገለገልኩ ደብር ከደብር እየዞርኩ
እንደተለመዱት የቅኔ ተማሪዎች ሰው በልቶ የተረፈውን ነገር መብላት ግዴታዬ ነበር፡፡

የተወለድኩት መንዝ ሲሆን ልጅነቴን በሙሉ በቆሎ ትምህርት ቤት ነው ያሳለፍኩት፡፡ ወሎ እስጣይፍ እስጢፋኖስ ገዳም ውስጥ ነው ብዙ ጊዜዬን ያሳለፍኩት፡፡ አባ ገብረ መድህን ለሚባሉ እዛው ገዳም ውስጥ ሞኖክሴ ሆነው ለሚኖሩ ሰው ነበር በቤተሰቦቼ አማካኝነት በአደራ የተሰጠሁት፡፡ ከዚህ ውጭም የተለያዩ ገዳሞች እየዞርኩ የቆሎ ተማሪ ደረጃውን እስኪያገኝ የሚማረውን ትምህርት ሁሉ ወስጃለው፡፡

ግዕዝ አራራይ ዜማዎችን በተለያዩ ደብሮች እየተዙዋዙዋርኩ ተምሬያለው፡፡ ቅኔ አቁዋቁዋም
ለማወቅ ብዙ ለፍቻለው፡፡

ታዲያ በዚህ ሁኔታ አለበቃም፡፡ በተማርኩበት ነገር በተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች በቅዳሴ መምህርነት አገልግያለው፡፡ በአገልግሎት ደረጃ ከሀገር ቤቶች አንስቶ እስከድሬዳዋ ፤ከአሁኑዋ ሲዳማ ክልል አንስቶ እስከ ጂማ፤ከጂማ እስከ ጋምቤላ፡፡ መቼም በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት እየኖረ ነው
ልትሉ ትችላላችሁ፡፡
የቆሎ ተማሪ ምግቡን ለምኖ ነው የሚያገኘው፡፡ ቤቱ ደግሞ መቃብር ቤት ነው፡፡ የተሳሳቱ አመለካከቶች እንደጽድቅ ይቆጠራሉ፡፡ እራስን ዝቅ አድርጎ መኖር ፈጣሪ የሚወደው ነገር ቢሆንም ግን ይሉኝታን ሽጦ መኖር ለኔ ገንዘብ ከማጣት የበለጠ መከራ ነበር፡፡….

መንደርደሪያ…. ‹‹ አንድ አንድን ነገር ከልክ በላይ የጠላ እንደሆን ሀቅ እና አምላክ የወደደለት ነገር ከሆነ
ወደጠላው ነገር መሳቡ አይቀርም፡፡ ለእስልምና ትልቅ የሆነ ጥላቻ ነበረኝ፡፡
ስለ እስልምና አስቀድሞ የነበረኝ አመለካከት የተዛባ እና ከእውነት የራቀ ነበር ፡፡ ታዲያ ልቤ በጊዜ ሂደት እየተረበሸ መጣ፡፡ የኔ የኦርቶዶክስ እምነት አዲስ ሰፈር ገብርኤል ሲደርስ በጃሂሎች አስተሳሰቦች እየተበከለ መምጣት ጀመረ፡፡

ከቤተክርስቲያን ውስጥ የዘር ትርክት እየገባ ሲመጣ እምወደው ጉዋደኛዬ እንኩዋ ምላሱ እየጨነቀኝ
መጣ ፡፡ እኔ ጠንካራ የእምነቱ ተከታይ ስለነበርኩ ይህ ነገር በአንዴ አልነበረም የተፈጠረው፡፡ ግን ሀቅ ውስጥ እንዳልነበርኩ ልቤ ሁሌ ይነግረኛል፡፡

ለረዥም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚደረጉት ነገሮች
ውስጤን ይረብሹት እና ጥያቄ ይፈጥሩበት ነበር፡፡ ግን ሁሉም ነገር አንገሽግሾኝ የማገልገያ ፍቃድ ወረቀቴን ቀድጄ እስክወጣ ድረስ ለኔ ከባድ ነበር፡፡ ታዲያ ከዚህ በሁዋላ ያለፍኩበትን መንገድ መጨረሻሳስበው ከንቱነት ተሰማኝ፡፡ ከዛ በሁዋላ ግን….

ታሪካዊ አመጣጥ….ከቤተክርስቲያን አለም ከወጣሁ በሁዋላ አለማዊውን ህይወት ለመቁዋቁዋም ስደት ነበር
የነበረኝ አመራጭ፡፡ ወደ ሱዳን ከተሰደድኩ በሁዋላ ለተወሰነ ጊዜ ስራ ለማግኘት ከባድ የነበር ቢሆንም በሁዋላ ላይ ከቻይናዎች ጋር የተያያዘ የመንገድ ስራ ውስጥ ገባው፡፡
ሲኒ ሀይድሮ ፕሮጀክት የሚል መጠሪያ ያለው የአስፓልት ስራ ውስጥ ከአንድ ጉራጌ ጋር ተዋወኩ፡፡ ጃሂል እንዴት መጣራት ይችላል?

ለራሱ ያላወቀበት ሰው እንዴት ሰውን ወደ ሀቅ ያመጣዋል የአምላክ ስራ ነው፡፡ የተዋወኩት ጉራጌ ሙስሊም ነበር፡፡ እና ከሱ ጋር ብዙ ጊዜ የሚያደርገውን እያደረኩ አሳልፍ ነው፡፡ ለእስልምና የነበረው አቁዋም የሚገርም ነበር፡፡ ግን ስለ እስልምና ጥልቅ እውቀት ስለነበረው ወይም ደግሞ ዲኑ በህይወቱ ውስጥ ልውጥ ስላመጣለት አልነበረም፤ግን እንዲሁ ለእስልምና ዘብ መሆን ምርጫው ነበር፡፡ ለእምነቱ
ለዘብተኛ ነገር ነው፡፡ አልኮል መጠጦችን ይጠጣል፡፡ እኔም የዛ ሰአት የመጠጣት ችግር አልነበረኝም፤ምክንያቱም ቄሶች እንኩዋ በመጠጥ ሰክረው በሚያገለግሉበት ቦታ ነው ረዥም እድሜዬን ያሳለፍኩት፡፡

አሊፍ ትዳገደምም ሆነ ትቃና የማያውቅ ጃሂል ነው ለኔ የመጀመሪያው ለውጥ ሰበብ

የሆነኝ…
የጉራጌው እና የኔ ጥል…. ‹‹ ከ2005 አምስት ጀምሮ ነበር ከጉራጌው ሙስሊም ጉዋደኛዬ ጋር ምተዋወቀው፡፡ ታዲያ
በመጨረሻ ወደ ኢትዮጲያ ስንመለስ ሁለታችንም ተዘርፈን ነበር የተመለስነው፡፡ ጥሩ ጉዋደኝነት የፈጠርን እና የተዋደድን ስለነበር ኢትዮጲያ ከመጣን በሁዋላ ተደዋውለን ተገናኘን፡፡ ጉራጌው ጉዋደኛዬ ጋምቤላ ይኖር ስለነበር፤ለኔም ኑሮ ከባድ ስለነበር ወደሱ ለመሄድ ተገደድኩ፡፡ በጣም ይወደኝ ስለነበር ካፊር ነህ
ብሎ ሳይገፋኝም ሚስት እያለሁ አብሬው እንድኖር ፈቅዶልኝ ከሱ ጋር ነበር ቲማቲም ምናምን በረንዳ ተከራይቼ እኖር የነበረው፡፡ ታዲያ አጋጣሚ በቤተክርስቲያን አከባቢ ስናልፍ እኔ ለመሳለም ዝቅ ስል ‹ይሄ

የውሸት እምነት› እኔን ማብሸቁ የተለመደ ነገር ነው፡፡ እኔ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ለቅቄ ብወጣም ለኦርቶዶክስ እምነት የነበረኝ አቁዋም እንደዛው ነበር፡፡
የውሸት እምነት ነው ስል እንዴት እንዲህ ትላለህ
በማለት ከገዛ ጉዋዳኛዬ ጋር እጣላ እና እኩዋረፍ ነበር፡፡ ግን ስላኮረፍኩት እሱ ሀቅን ለኔ ለማሳየት አልሰነፈም፡፡

ስለእስልምና በደንብ ሳይረዳ እኔን ለማስረዳት የሚሞክርበት ሁኔታ የሰነፍ መሆኑን ሲረዳ፤ስለእስልምና የሚያብራሩ ሲዲዎችን፤የአህመድ ዲዳት ዳአዋዎችን አዲስ አበባ ድረስ እየሄደ ያመጣልኝ ነበር፡፡
ግን ለኔ ሀሳቡ የማይገባኝ ነገር ስለነበር ውስጤ ሰርጾ የገባውን የኦርቶዶክስ እምነት ሊፍቅልኝ አልቻለም፡፡ እሱ ለራሱ የወደደውን ለኔ ቢወድልኝም፤መልዕክንትን የመንገር እንጂ በልብ ውስጥ እምነት የመፍጠር አቅም የለውም፡፡…
እምነት የሌለው ጅማሬ…

‹‹ ከአንድ አመት በሁዋላ 2007 ላይ ሌሊት አከባቢ ስለነበር የተኛሁት እንቅልፍ እስከ ረፋድ ቆየሁ፡፡ ጉራጌው ጉዋደኛዬ ስለመስጂድ የነገረኝ ነገር ውስጤ ጥቂት የሆነን ግድ የለሽነትን ፈጠረብኝ፡፡

መስጂድ ውስጥ ምንም የአምልኮ ስርአትን የሚያሳዩ ምስሎች እንደሌሉ እና ከምንጣፍ እና ከግድግዳ
በቀር ሰው ካልሆነ የተለየ ነገር እንደማላይ ነበር የነገረኝ፡፡ ከነገረኝ ቆየት ብሎአል፡፡ ስለክርስትና ጥልቅ እውቀት የሌለው ክርስቲያን መስጂድ ውስጥ መግባትም ሆነ በመስጂድ በኩል ማለፍን እንደሀጥያት
ይቆጥረው ይሆናል፡፡

እኔ ግን ስለክርስትና ጥልቅ እውቀት ነበረኝ፡፡ ምክንያቱም እድሜዬን ሙሉ በሀይማኖታዊ አስተምህሮ ነው ያለፍኩት፡፡ ምንጣፍ እና ግድግዳ የሆነን ቤት ለመጎብኘት መሄድ ለኔ
ብርቅ አልነበረም፡፡ ምንም አይነት ሀይማኖታዊ ተጽእኖም አልነበረውም፡፡ቀኑ የጁመአ ቀን አርብ ነበር፡፡
873 views13:33
Open / Comment
2021-10-05 18:33:46 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤ እንደሚታወቀው በአስሓቡል የሚን ስር የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ከተጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል ። እርሱም የተለያዩ ከክርስትና ወደ እሥልምና የመጡ እህቶችና ወንድሞች የሒዳያ ሰበብ የሆነውን ታሪካቸውን ቀጥታ በድምጽ ወይም በጹሑፍ የሚገልጹበት ሲሆን ለዛሬ የኡስታዝ ካሊድ ክብሮም እንዴት ሰለምኩኝ ፦ ጥያቄ ቁጥር አንድ ይዘን ቀርበናል…
1.3K viewsedited  15:33
Open / Comment
2021-10-05 18:27:57
በፈረንሳይ የካቶሊክ ቄሶች ባለፉት 70 ዓመታት ውስጥ 216ሺ ሰዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት (አስገድዶ ደፈራ) ፈፅመዋል። ከተደፈሩት ውስጥ አብዛኃኞቹ ህፃናት ናቸው። ወሲባዊ ጥቃት የመፈፀም ወንጀል የኃይማኖቱ መሪዎች ዘንድ የዚህን ያህል ከተንሰራፋ ተራውን ምዕመን ደግሞ አስቡት?

እስልምና ይህን ዓይነት ወንጀል (ዚና) ለሚፈፅሙ ሰዎች አንድም ሰውዬው እራሱ ዳግም ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፅም የሚያስተምር፤ ሁለትም ተመሳሳይ ወንጀል ለመስራት ለሚያስቡ ሰዎች እንዳይሞክሩት መቀጣጫ የሚያደርግ ኮምጠጥ ያለ የቅጣት ህግ አለው። ወንጀሉን የፈፀመው ሰው ያላገባ ከሆነ 100 ግርፋት፤ ያገባ ከሆነ ደግሞ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል።

ይህ ህግ ፈረሳይ ውስጥ ተግባራዊ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ እና የመጀመሪያው ቄስ ደፈራ ሲፈፅም በዚህ ህግ መሰረት ተቀጥቶ ቢሆን ኖሮ፥ ደፈራው የዚህን ያህል ተባብሶ 216ሺ ሰዎች ለደፈራ ባልተጋለጡ ነበር። ጭካኔው መረን አልፎም ህፃናት ሁሉ የዚህ ጥቃት ሰለባ ባልሆኑም ነበር።

ምዕራባዊያን ይህንን ኢስላማዊ ህግ እንደጭካኔ ሲያዩት ያስገርመኛል። ጭካኔ የሚሆነው አንድን ወንጀለኛ መቀጣጫ አድርጎ ብዙ ንፁሃንን የወንጀል ተጠቂ ከመሆንና በወንጀለኞች ከሚደርስባቸው ጥቃት መጠበቅ ሳይሆን ወንጀለኛውን በግዴለሽነት አልፎ የብዙ ንፁሃን ሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ መጣል ነው። ለዚህም ነው ወንጀል እጅግ እየተበራከተ እየመጣ ያለው።

ዓለም ለገባችበት አዘቅት መፍትሔው ኢስላም ነው የምንለው ለዚህ ነው።

https://t.me/Zelebet
1.1K views15:27
Open / Comment
2021-10-04 20:09:51 ይችን ሙስሊም ሳትሆን እንደሙስሊም ለብሳ የፕሮቴስታንት ቲቪ ላይ እንደከፈረች አድርጋ ጥሩ ተውኔት የተጫወተችውን አጭበርባሪ ሳይ በሆነ ወቅት የገጠመኝ አጋጣሚ ትዝ አለኝና ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።

አጋጣሚው እንዲህ ነበር። ከዓመታት በፊት በእጅግ አጫጭር ቀሚሶች ለብሳ የማውቃት ልጅን ሒጃብ ለብሳ አገኘኋት። በደስታ ደነገጥኩኝ እሷ ናት ወይስ አይደለችም ብዬ ተጠራጠርኩኝ። ሰላም ስትለኝ ነው እሷ መሆኗን እርግጠኛ የሆንኩት። ሙሉ ለሙሉ አለባበሷ የሙስሊም ነው። አለባበሷ አጉል ሰለጠንን እንደሚሉ እንደ አንዳንድ ሙስሊም ሴቶች እንኳን ግማሽ ሒጃብ አልነበረም። ማሻአላህ አልኳት ሰልማ እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜ። እጅግ የሚያስደስተኝ ነገር ሰው ሰልሞ ማየት ነው።

የተወሰነ አወራኋት፤ በወሬዋ ግን ጥርጣሬ ፈጠረብኝ። አዲስ ሰለምቴ ስለሆነች ይሆናል ወሰድ የሚያደርጋት(ወሬዋ ወደ ኩፍር የሚሄድባት) ብዬ አሰብኩኝ። ውስጤ ግን ይሞግተኝ ያዘ። ለማጣራት ስሞክር እውነታው አስደነገጠኝ አስገረመኝም።

ልጅቱ አልሰለመችም፤ አለባበሷ ብቻ ነው የሰለመው። የተራቆቱ አጫጭር ልብሶቿን ጥላ ሒጃብ ከለበሰች ሁለት ዓመት ገደማ ሆኗታል። ምናልባትም አለባበሷን አትወደው ይሆናል። እንዲያ የለበሰችው ግን በዓላማ ነው። ዓላማዋም ሙስሊም መምሰል ነው። ሙስሊም ሳትሆን ሙስሊም መምሰል ምን ይጠቅማታል ትሉ ይሆናል። በመምሰል ውስጥ አንድም ሙስሊሞችን በቀላሉ ቀርባ ወደ ምታገለግልበት ቸርች ለመጎተት ይጠቅማት ዘንድ ታጠምድበታለች። (በዚህ ወጥመዷ የተጠለፉ ጥቂት ሙስሊም ሴቶች እንዳሉ ሰምቻለሁ) ሁለትም የቸርቹ ፕሮግራም በቲቪ በሚተላለፍበት ጊዜ ካሜራ ፊት ሙስሊም መስላ ትታያለች ከፍ ሲልም ትተውናለት።

በዚህ ሁሉ የልጅቱ ማጭበርበር ውስጥ ግን ብቻዋን አይደለችም። የልጅቱ የስራ ድርሻዋ የተሰጣትን ስክሪፕት በብቃት መተወን ብቻ ነው። በገንዘብም ሆነ እቅድ ነድፎ በመስጠት ግን ከጀርባዋ ተኝተው የማያድሩት አክፍሮት ኃላት አሉ። ተመልከቱ እንግዲህ አክፍሮት ኃይላት ሙስሊሙን ለማጥመድ ምን ያህል ርቀው እንደተጓዙና ዓይነቱን እየቀያየሩ ወጥመድ እንደሚያጠምዱ? ምን ያህል ሴቶችን ሒጃብ እያስለበሱ በትነው ይሆን? ምን ያህል ሙስሊሞችስ በነዚህ ወጥመዶች ተጠልፈው ይሆን?

አላህ በሒክማው ከወጥመዳቸው ይጠብቀን!

https://t.me/Zelebet
1.4K views17:09
Open / Comment
2021-10-04 20:09:51
1.2K views17:09
Open / Comment
2021-10-03 20:36:31 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

እንደሚታወቀው በአስሓቡል የሚን ስር የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ከተጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል ።

እርሱም የተለያዩ ከክርስትና ወደ እሥልምና የመጡ እህቶችና ወንድሞች የሒዳያ ሰበብ የሆነውን ታሪካቸውን ቀጥታ በድምጽ ወይም በጹሑፍ የሚገልጹበት ሲሆን ለዛሬ የኡስታዝ ካሊድ ክብሮም እንዴት ሰለምኩኝ ፦
ጥያቄ ቁጥር አንድ ይዘን ቀርበናል ፦

ወደ እሥልምና ለመግባት ሰበብ የሆነህ ሰዎች ናቸው ወይስ እውቀት ...!?

በመጀመሪያ ሰበቡን ከመናገሬ በፊት አላህ የቀደረው ወይም አላህ ሽቶልኝ ነው ።አምላካችን አላህ ነው ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመራው ሰዎች ልቦቻቸውን ለቅን ጎዳን እስከከፈቱት ድረስ።

በነበርኩበት እምነት ላይ ጥሩ አምላኪና ጥሩ የእምነቱ ተከታይ ለመሆን ሙከራ አደርግ ነበር።

ሆኖም በትክክል መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጥረት ነበረኝ ከልቤም አነበው ነበር ።

ሳነበው ግን በእውነት መቀበል ብቻ ሳይሆን ጥያቄዎችን በመጠየቅ መጽሐፉንም በመመርመር ነበር የንባብ ቆይታዬ

በዙሪያዬም ሙሥሊሞች ነበሩ ስለ እሥልምና ባያብራሩልኝም ባይገልጹልኝም ነገር ግን የእሥልምናን ውበት የማይባቸው አንዳንድ ጓደኞች ነበሩኝ ።

አላህ የከፈተልኝ እውቀት መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና ሳይንስን በተወሰነ ደረጃ መረዳት ምክንያታዊ ሰው መሆን ከንባብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከፍተኛ የሆነ ተጽኖ አላቸው ወደ እሥልምና ለመምጣት ።

ያ ማለት ግን ሙሥሊም ወንድሞች ወደ ኢሥላም ለመምጣቴ አስተወጾ አላደረጉም ማለት አይደለም። የሁለቱም ውጤት ድምር ነው።

ነገር ግን መጽሐፍን ማንበብ እና ቆም ብሎ ማሰብ ወዴት አቅጣጫ እየሄድኩኝ ነው የያዝኩትም ነገር እውነት ነው ወይስ አይደለም ..!? የውርስ ሃይማኖት ነው ወይስ የተፈጥሮ ብሎ በመመርመር ትልቅ ቦታ ነበረው እና አላህ ሲመራኝ በዚህ እውቀት ላይ መሠረት አድርጎ ነው ወደ ቅኑ ጎዳና የመራኝ ።

ወደ እሥልምና ስገባም ሙሉ በሙሉ እሥልምናን አምኜ ክርስትናን የውርስ እምነት መሆኑን የተረዳሁት በሰው ሳይሆን በእውቀት መሠረት ወደ እሥልምና ስለገባሁ ይመስለኛል ።

ጥያቄ ቁጥር 2

ከቤተሰብህ እሥልምናን የተቀበለ ሌላ ሰው አለ.. ?ደግሞ በእምነቱ ዙሪያ ቤተሰቦችህ ምን አይነት አመለካከት አላቸው..!?

የኡስታዝ ካሊድ ክብሮም መልስ ይቀጥላል.....

ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ

የተለያዩ ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ የሰለምቴዎችን ታሪክ ያገኙበታል ፦

የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-




AS_HABULE YAMlNE TUBE

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

የሠለምቴዎች መዝናኛ እና መማሪያ ግሩፕ
1.7K viewsedited  17:36
Open / Comment
2021-10-03 20:36:22
1.3K views17:36
Open / Comment
2021-10-01 19:27:05 አስ-ሓቡል የሚን!

አስሓቡል የሚን ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ ሰፊ መርሓ-ግብር የያዘ ተቋም ነው። በአሁን ሰዓት በገጠሩ ክፍል ሚሽነሪዎች በጥቅማ ጥቅም የሚደልሉበትን ቦታ እግር በእግር እየተከታተል ሙሥሊሙን የሚደጉም፣ መድረሳ የሚያቋቋም፣ ቁርኣን የሚያስቀራ፣ ሠለምቴዎችን በመሰብሰብ ታሪካቸውን በማቅረብ ለሠለምቴዎች በእርዳታ የሚደግፍ ሰዎችን ወደ ዲኑል ኢሥላም የሚጣራ ተቋም ነው። ይህንን ተቋም በንዋይ(በገንዘብ)፣ በአሳብ እና በጉልበት መደገፍ የምትፈልጉ እንግዲያውስ ይህንን ሊንክ በማስፈንጠር ተጭነው ይግቡ፦

ቴሌግራም፦ https://t.me/joinchat/Th93dNNUa7fV1c79

ዋትስ-አፕ
https://chat.whatsapp.com/6O1nFgi4oKHLgB1fdY0Air
766 views16:27
Open / Comment