Get Mystery Box with random crypto!

AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር A
Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር
Channel address: @ashabuleyamine
Categories: Uncategorized
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 7.32K
Description from channel

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q
Telegram _Join
http://t.me/AshaBuleyamine
Twitter
https://twitter.com/AshabuleYamlne?s=09
Facebook page
https://www.facebook.com/Ashabuleyamine/
Website
http://ashabulyemin70.blogspot.com

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


The latest Messages 17

2021-10-13 00:52:39 (በአንዲት ጀምበር ሦስቴ አንዋሽም)

መንግስት ከአንድ ሚሊየን ወታደር በላይ አለኝ እያለ እየሸለለ ባለበት ወቅት በየአቅጣጫው እያለቀ ያለው፣ እየፈረሱ ያሉ ሐሪማዎችና እስከ ወዲያኛው ከስለው እየጠፉ ያሉ ኪታቦችን፣ እንዲኹም የሚገደለውን ደረሳ ስታይ፣ ይህም አልበቃ ብሎ ገበሬው ፊት አውራሪ ኾነህ ራስህን አድን ሲባልና ካለምንም በቂ መሳሪያ ከገዳዩ ፊት እንዲቆም ሲገደድ ስታይ፣ ጨዋታው በጨረቃ ፍም ስንዴ ቆሎ ቆልቼ አስቆረጥምኻለውና ምሽት ላይ ከሜዳው ጠበቀኝ ዓይነት እንደኾነ ትረዳለህ፡፡
በአስራ አምስት ቀን ከትግራይ ምድር ዘገደው ብሎ የዘለቀው መከላከያ ስለምነው ከወለጋ መስመር በየሰርኩ እያለቀ ያለውን ምስኪን ገበሬ መታደግ ያልቻለው? ብለህ ጠይቅ፡፡ ከአፋር ምድር ጨርሶ ለቋል የተባለው ኣካል ከሰሞኑን መድፍ ተኩሶ አውራ ወረዳ ላይ የሰፈረውን ምስኪን አርብቶ አደር አነደደ የሚል ዜና ብትስማ፣ ለመኾኑ ከቆቦ መድፍ ተኩሶ ነው የኣፋሩን ነዋሪ የጎማመደው ወይስ ከዚያው ከአፋር ምድር ላይ መሽጎ? ብለህ ጠይቅ፡፡ ወዳጄ መቼም መድፍ እንደ ሮኬት ኪሎ ሜትሮችን አይመዘገዘግምና ጭንቅላትህ አሰራው፡፡
ወዳጄ በየአቅጣጫው ስለ ቤቱ፣ሚስቱና ንብረቱ ክብር እየረገፈ ያለው ምስኪኑ ገበሬና አርብቶ አደር ብቻ እንደኾነና እየኾነ ላለው ኹሉ መንግስት በነጭ መዝገብ ላይ ጥቁር ታሪክ እየጻፈ እንደኾነ ልብ ይሏል፡፡ መቼም መቼም ቢኾን ይህ ግፍ በፈሰሰው ደም ጎርፍ አይታጠብም፡፡ይልቁንም ያፈሰሱትና እንዲፈስም ገፊ ምክንያት የኾኑ ኣካላት እለት እለት እየሞቱ ስጋ ቢለብሱና ነፍሳታቸው ዳግም ከስጋቸው እየተቀላቀለች ቢቀጡ እንኳ በዝንተ-ዓለም የዚህ ግፍ ገፈት እየተቀመሰ ኣያልቅም፡፡


t.me/religionandphylosophy
1.3K views21:52
Open / Comment
2021-10-12 17:44:55 ሸሪዓ ምንድነው?

ታሊባን አፍጋኒስታንን መቆጣጠሩን ተከትሎ የዓለም ሚዲያ ትኩረት የሸሪዓ ህጎች ላይ ሆኗል። እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ስለእስልምና የጠለሸ ምስል ላለባቸው እንዲሁም ለሌሎች፥ ብዥታው ይገፈፍ ዘንድ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ትክክለኛውን የጠራ ምስል ማሳየት ከኛ ከሙስሊሞች ይጠበቃል ብዬ አምናለሁ። እንዳለመታደል ሆኖ ግን እኛ ሙስሊሞች ለዳዕዋ አጋጣሚዎችን የመጠቀም ልምዳችን በጣም ደካማ ነው። እኛ ማድረግ የሚገባንን ሌሎች እያደረጉልን ነው። መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገው ታዋቂው ጋዜጣ ዘ ኢኮኖሚስት በድህረገፁ "ሸሪዓ ምንድነው?" በሚል ርዕስ ይህንን ፅሁፍ አስነብቧል። ከመጠነኛ ማስተካከያ ጋር በቀጥታ ነው የተረጎምኩት።

ሸሪዓ ምንድነው?

ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ፣ ከወንጀል እስከ ንግድ ስርዓት ሁሉንም ዓይነት ህጎች የሚያቅፍ ከዓለማዊ ህጎች ይበልጥ ሁለንተናዊ የሆነ ስርዓት ነው ሸሪዓ።

ታሊባን አፍጋኒስታንን በሸሪዓ መሠረት ለማስተዳደር አቅዷል። ታጣቂ ቡድኑ ቀደም ሲል በሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ኢስላማዊ የሕግ የበላይነትን በጥብቅ በመተርጎም ፣ ሙዚቃን በመከልከል እና ሴቶች በአደባባይ ሙሉ ሒጃብ እንዲለብሱ በማድረግ ይታወቅ ነበር። ነገር ግን ከአፍጋኒስታን በተጨማሪ ብዙ ሀገሮች - ሳዑዲ ዓረቢያ ፣ ኢራን፣ የኢንዶኔዥያ እና የናይጄሪያ ክፍሎች - ሸሪዓን ያለ እንደዚህ ያለ ጥብቅነት ሸሪዓን ይጠቀማሉ።

ሸሪዓ ምንድን ነው ፣ እንዴትስ ይተገበራል?

ሸሪዓ ማለት በአረብኛ “መንገድ” ማለት ሲሆን ፈጣሪን የሚያስደስት ምግባርን ያመለክታል። የወንጀል፣ የንግድ እና የቤተሰብ ሕግን ይሸፍናል። ከዓለማዊ የሕግ ሥርዓቶች የበለጠ ሁለንተናዊ ነው። ሙስሊሞች ለመኖር እና ለማምለክ ዓላማ ማድረግ ያለባቸውን የሥነ ምግባር ደንቦችንም ያወጣል። (ሕጋዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጉዳዮችን የሚቆጣጠር ተመሳሳይ ኮድ በአይሁድ እምነት ውስጥም አለ)። ሸሪዓ በእስልምና የሚተገበረው ቅዱስ መጽሐፍ በቁርአን ፣ በሐዲስ ወይም የነብዩ ሙሐመድ ንግግሮች እና የእስልምና የሕግ ምሁራን ቀጣይ ሥራ መሰረት ነው።

ለተጠረጠሩ ወንጀሎች (ሁዱድ በመባል የሚታወቁ) አንዳንድ በጣም ከባድ ቅጣቶች አሉ። በድንጋይ መውገር፣ ለአመንዝሮች 100 ግርፋት። ነገር ግን የጥፋተኝነት ማረጋገጫ ደረጃ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። እነዚህ ቅጣቶች እምብዛም አይደሉም። በዝሙት ጉዳይ አራት ምስክሮች መመስከር አለባቸው። እንደ ግድያ ባሉ በሰዎች ላይ ለሚፈጸሙ ከባድ ወንጀሎች ቅጣትም እንዲሁ ከባድ ሊሆን ይችላል ፣ ይህም በቂሳስ መርህ ወይም “ዐይን በዓይን” ላይ የተመሠረተ ነው። ነገር ግን እስልምና ተጎጂዎች መሐሪ እንዲሆኑ እና በምትኩ ካሣ እንዲከፍሉ ያበረታታል።

https://t.me/Zelebet
1.4K views14:44
Open / Comment
2021-10-12 17:44:54
1.1K views14:44
Open / Comment
2021-10-12 13:42:57 አልሃምዱሊሏህ ዛሬ አንድ ሠለምቴ እህቴ ከብዙ ፈተናና እንግልት ስቃይ በኃሏ ነስርን አግኝታለች ።እንደ ዛሬ ደስ ብሎኝ አያውቅም ፈተናዋ አስጨንቆን ነበርም ። በህፃንነት ከሁለት ዓመት ልጅ ሳለች ከሃገሯ ወጣች የምትኖርባቸው ቤተሰቦቿ አይሁዳውያን ነበሩ ።እርሷም አሏህ አስመልክቷት በ19 አመቷ እሥልምናን ተቀበለች ።ታዲያ ይህንን ያወቁት ቤተሰቦች በሰው ሃገር ላይ በውጥተው የትም ጣሏት ለተወሰኑ ቀናት በበረንዳ ላይ አደረች ተንገላታች ያላሰበቻቸው ችግሮች ተደራረቡባት ። ያለችበትን በመፈለግ ህይወቷን እንድትጠላት አድርገው ስቃይ ላይ ጣሏት ። በዚያ ላይ መታወቂያ የላት ፓስፖርት የላት ። የለበሰችውን ልብስ ብቻ ነበር ለብሳ የወጣችው ። ግን ኃያሉ አሏህ ጥበበኛ አሸናፊም ነውና ዛሬ በእርሱ እና በደጋግ ባሪያዎቹ እርዳታ ወደ እናት ሃገሯ ኢትዮጵያ እግሯ ረገጠልን ። በእርግጥ ለዲናችን መጽዋትን ስንከፍል ጣፋጭ መዓዛው እና ጣእሙ እየገባን ይመጣል ። ክብር ይመስገን..! ይህንን ኢማን ለወፈቃት አሏህ።
በዚህ እድሜዋ ከገጠማት ፈተና ግዝፈት አንፃር ጥንካሬዋ እና ፅናቷ የሚገርም እና የሚደነቅ ነው ። አሁንም በዱዓችሁ አስቧት ..! ለመስለሟ ሰበብ የሆናት እና እሥልምናን እንድትመረምር ያደረጋት ።የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን(ረ.ዐ) (የጆንያው ባለቤት ) የህይወት ታሪክ በቅፅበት በሰማችበት ጊዜ ነበር ። የእርሷም ታሪክ ከእርሱ ታሪክ ጋር እየተመሳሰለብኝ ነው ወሏህ ሁሉ ነገሯን ለዲኗ አሳልፋ ሰጠች ። ታሪኳን በሰፊው እንመለስበታለን ኢንሻሏህ ።

ምንጭ ከ እህት ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ

የተለያዩ ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ የሰለምቴዎችን ታሪክ ያገኙበታል ፦
የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-

AS_HABULE YAMlNE TUBE
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A
2.4K views10:42
Open / Comment
2021-10-10 21:42:26 ☞#የዑመር ኢብኑል #ኸጧብ (ረዐ)
20 #ምርጥ___አባባሎች፤
1 ‹የምትጠላውን ሰው ተጠንቀቅ፤›
2 ‹ብልጥ ሰው የእለት ስራዎቹን ከራሱ ጋር
ይተሳሰባል፡፡›
3 ‹የዛሬን ስራ ለነገ አታሳድር፡፡›
4 ‹ከሰዎች ጥያቄ ተነስተህ አስተሳሰባቸውን
መለካት ይቻላል፡፡›
5 ‹ለሌሎች ዳዕዋ በምታደርግበት ወቅት
እራስህን አትርሳ፡፡›
6 ‹ከዱንያ ትንሽን ብቻ ስትፈልግ ይበልጥ
ነፃነትን እያገኘህ ትሄዳለህ፡፡›
7 ‹ወንጀል አለመስራት ከፀፀት ይሻላል፡፡›
8. ‹ታጋሽ ሁን፤ ትዕግስት የእምነት ምሶሶ
ነችና፡፡›
9. ‹ፈጣሪህን ፈሪ መሆን እድለኛነት ነው፤
ከዚህ ውጭ ያለው እድለቢስ መሆን ነው፤›
10. ‹ወደ አኺራ የሄዱ ሰዎችን ንግግር
ጠብቁ፤ እነርሱ የተናገሩት ፈጣሪ እንዲናገሩ
ያገራላቸውን ብቻ ነውና፡፡›
`` `` ``
11. ‹ፈጣሪህን ፍራ፤ እርሱ ሁሌም ህያው፤
ከርሱ ውጭ ያሉ ሁሉ ጠፊ እና አላቂ
ናቸውና፡፡›
12. ‹ጥፋቴን በነገረኝ ሰው ላይ የአሏህ
እዝነት ይውረድ፡፡›
13. ‹እውቀትን ገብያት፤ ከዚያም ለሰዎች
አስተምር፡፡›
14. ‹የተከበርክ፣ ታማኝ እና እውነተኛ ሁን፡፡›
15. ‹ትምክህተኛ ምሁር አትሁን፤
ትምክህተኛነት እና እውቀት አንድ ላይ
አይሄዱምና፡፡
16. ‹ለዚህች አለም ፍቅር ያለው አዋቂ
ባየህ ግዜ እውቀቱ አጠራጣሪ መሆኑን
ተረዳ፡፡›
17. ‹ትንሽ አውርቶ ብዙ በሚሰራ ሰው ላይ
የፈጣሪ እዝነት ይውረድ፡፡›
18. ‹ታማኝነት ማለት በምትሰራው፣
በተናገርከው እና በምታስበው ነገሮች ልዩነት
አለመኖር ማለት ነው፡፡›
19. ‹የሰው ልጅ ምንም እንኳ እንደ ቀስት
ቀጥ ያለ ስራ ቢሰራ ተቃውሞ አያጣውም፡፡›
20. ‹አዕምሮህ እንዲሰፋ ከፈለግክ፤ ከፈሪሀ
አሏሆች ጋር ተቀመጥ፤

#ሼር

ምርጥ ምርጥ አባባሎች
https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg
1.9K views18:42
Open / Comment
2021-10-07 20:20:30 ጠንካራ ምርጥ እንስቶች አሉ..! የምለው በምክንያት ነው ።ሰለምቴዋ ብርቱካን እሥልምናን ተቀብላ በዲኗ ጸንታ የአሏህን ፍራቻ እና ውዴታ ተጎናጽፋ ። በክርስትናው አለም ውስጥ የነበረውን ጓደኛዋን እርሷን ሳይሆን አሏህን እንዲያውቅ አድርጋ የእኔ ህይወት በቅጽበት ተቀይሯል ህይወትህን ቀይር ብላ እሥልምናን እንዲቀበል ሰበብ ሆናዋለች ። በአሏህ ህግጋት ተጋብተው ልጅ ወልደዋል ሙሉ ታሪክ በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም በቅርብ ቀን ይጠብቁ። ምርጥ አስገራሚ ታሪክ

የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-



AS_HABULE YAMlNE TUBE
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q
በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125
ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta
አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot
ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule
290 views17:20
Open / Comment
2021-10-07 19:07:04
ኢማሙና የዳቦ ጋጋሪው እስቲግፋር

የእስልምና ታዋቂ ሊቅ የነበሩት ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል በአንድ ወቅት ጉዞ ያደርጉና የሆነች ከተማ ይደርሳሉ። እዛች ከተማ ወደ ሚገኝ አንድ መስጂድ ይገቡና ሰላታቸውን ይሰግዳሉ። በጣም ትሁት የነበሩት ሸይኽ ዝናቸውን ተጠቅመው ሰው ማስቸገር ባለመፈለጋቸው ምክንያት እዛው መስጂድ ውስጥ ለማደር ይወስናሉ። ከስማቸው በስተቀር በአካል የማያውቃቸው የመስጂዱ ጠባቂ ታድያ መስጂድ ውስጥ እንዲያድሩ አልፈቀደላቸውም። ከመስጂዱ አባሮ አሶጣቸው።

ይህንን ሲታዘብ የነበረ አንድ ዳቦ ጋጋሪ ታድያ በድርጊቱ እጅግ አዝኖ ሸይኹን ከሱጋ እንዲያድሩ ይዟቸው ወደ ዳቦ ቤቱ ይወስዳቸዋል። ነገር ግን ማንነታቸውን አላወቀም ነበር። ዳቦ ጋጋሪው ዱቄት ሲያወጣም፣ ውኃ ሲጨምርም፣ ሲያቦካም፣ መጋገሪያው ውስጥ ሲከትም በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ውስጥ "አስተግፊሩላኽ፣ አስተግፍሩላህ፣ አስተግፍሩላህ" እያለ ኢስቲግፋር ያደርግ ነበር።

በዳቦ ጋጋሪው ኢስቲግፋር ማብዛት የተገረሙት ሸኽ ታድያ ኢስቲግፋር በማብዛቱ ምን እንደተጠቀመ ጠየቁት። እሱም "በአላህ ይሁንብኝ ጌታዬ ምንም ነገር ጠይቄው ከልክሎኝ አያውቅም፥ ከአንድ ነገር በስተቀር" በማለት ይመልስላቸዋል። ሸይኹም "ያቺ ጠይቀህ አላህ ያልሰጠህ አንድ ነገር ምንድናት?" በማለት ጥያቄ አስከተሉለት። ዳቦ ጋጋሪውም "ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበልን በአካል እንዲያገናኘኝ ጠይቄው ነበር፥ እስሁን ያልተመለሰው ዱዓዬ እሱ ብቻ ነው።" በማለት መለሰላቸው። ሸይኹም ዓይናቸው እምባ አቅርሮ ለዳቦ ጋጋሪው እንዲህ አሉት "እኔ ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል ነኝ።"

https://t.me/Zelebet
421 views16:07
Open / Comment
2021-10-06 17:22:26
የተለያዩ ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ የሰለምቴዎችን ታሪክ ያገኙበታል ፦
የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-

AS_HABULE YAMlNE TUBE
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A
3.6K viewsedited  14:22
Open / Comment
2021-10-06 16:34:13
888 views13:34
Open / Comment