Get Mystery Box with random crypto!

AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር A
Logo of telegram channel ashabuleyamine — AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር
Channel address: @ashabuleyamine
Categories: Uncategorized
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 7.32K
Description from channel

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q
Telegram _Join
http://t.me/AshaBuleyamine
Twitter
https://twitter.com/AshabuleYamlne?s=09
Facebook page
https://www.facebook.com/Ashabuleyamine/
Website
http://ashabulyemin70.blogspot.com

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


The latest Messages 12

2022-01-26 20:37:35 ሁለት ሠዎች ተመሳሳይ ሥራን ይሰራሉ፣ ነገር ግን ምንዳቸው እጅጉን የተበላለጠ ነው። ይህም በውስጣቸው ባሰቡት "ኒያህ" እና "በኢኽላሳቸው" ምክንያት ነው፦
ሱነን-ነሠኢይ ሐዲስ ቁጥር 2528
ከአቢ ሁረይራህ "ረ.ዐ." እንደተወራው ፣ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፣ "አንድ" ዲርሃም(የብር ሳንቲም) "መቶ ሺህ" ዲርሃምን በለጠ፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል? ተባሉ፣ እርሳቸውም፦ አንድ ግለሰብ "ሁለት" ደራሂም(የብር ሳንቲሞች) ብቻ ነበሩት፣ *አንዷን* ዲርሃም አንስቶ ለገሰ(መፀወተ) ፣ ሌላኛው ግለሰብ ከአካበተው "መቶ ሺህ" ሃብት አንስቶ መፀወተ፡፡ "አሉ"፡፡
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " سَبَقَ دِرْهَمٌ مِائَةَ أَلْفٍ ". قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَكَيْفَ ؟ قَالَ : " رَجُلٌ لَهُ دِرْهَمَانِ ؛ فَأَخَذَ أَحَدَهُمَا فَتَصَدَّقَ بِهِ، وَرَجُلٌ لَهُ مَالٌ كَثِيرٌ، فَأَخَذَ مِنْ عُرْضِ مَالِهِ مِائَةَ أَلْفٍ، فَتَصَدَّقَ بِهَا ". الحديث:حسن

አላህ ዘንድ ተፈላጊነቱ "የሥራ ብዛት" ሳይሆን "የሥራ ጥራት" ነው፡፡ አላህ ለሚሻው ሠው አንዷን መልካም ሥራ ከ700 "እጥፍ" በላይ ያነባብራታል፡፡ ሁለቱም መፀወቱ ግን በምንዳ ተበላለጡ ፣ ያበላለጣቸው "ኒያቸው እና "ኢኽላሳቸው" እንጂ ሌላ አይደለም"፡፡

“ኒያህ” نِيَّة የሚለው ቃል “ነዋ” نَوَى ማለትም “ወጠነ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ውጥን”intention” ማለት ነው። ኒያህ በልብ ውስጥ የሚቀመጥ እና አላህ ብቻ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፦
15፥51 *”አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል*፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي قُلُوبِكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَلِيمًا

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 47
ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ ብለዋል፦ *”ሥራ የሚለካው በውጥን ነው፥ ማንኛውም ሰው የወጠነውን ያገኛል። عَنْ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الأَعْمَالُ بِالنِّيَّةِ، وَلِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى،

በመጨረሻም አላህ እንዲህ ይላል፦
ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا
18:110 የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ "መልካም ሥራን ይሥራ"፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡

በጥሩ ሁኔታ ጌታውን መገናኘት የፈለገ "ብዙ ሥራ ይሥራ" ሳይሆን "መልካም ሥራ ይሥራ" በማለት "የኢሕሣንና" "የኢኽላስን" "የኒያን" *ወሳኝነት* እና አስፈላጊነት ይገልፃል፡፡

*የእድሜ* መብዛት የሥራ መብዛትን ሊያስገኝ ይችላል፤ የሥራ መብዛት ግን *የምንዳን* መብዛት "ላያስገኝ" ይችላልና አላህ ሆይ! እስልምናቸው አምሮ ሥራን በጥሩ "ኒያህ፣ "በኢኽላስ፣ "በኢሕሣን፣ ሠርተው አንተን ከሚገናኙት አድርገን! አሚን፡፡

በወንድም መህዲ
http://t.me/AshaBuleyamine
618 views17:37
Open / Comment
2022-01-26 20:37:35 "የሰለምቴነት ማማር"

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ لِيَجْزِيَ الَّذِينَ أَسَاءُوا بِمَا عَمِلُوا وَيَجْزِيَ الَّذِينَ أَحْسَنُوا بِالْحُسْنَى
53:31 በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን "ያሳመሩትንም" በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ።

"ያሳመሩትን" ለሚለው የገባው ቃል "አሕሠኑ" أَحْسَنُوا ሲሆን "ኢሕሣን” إِحْسَٰن የሚለው ቃል “አሕሠነ” أَحْسَنَ ማለትም “አስዋበ” “አሳመረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስዋብ” “ማሳመር” ማለት ነው። ለምሳሌ “ሐሠን” حَسَن ማለት “ውብ” “ያማረ” “መልካም” “ጥሩ” “በጎ” ማለት ሲሆን “ሑሥን” حُسْن ማለት ደግሞ “ውበት” “መልካምነት” “ጥሩነት” “በጎነት” ማለት ነው። ኢሕሣን የዲን ማሳመሪያና ማስዋቢያ ነው። ይህን ከተረዳን፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ-2 ሐዲስ ቁ-41
"አባ-ሰዒዲኒል-ኹድሪይ "ረ.ዐ." እንዳስተላለፈው፣ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቼያአለሁ፦ "አንድ የአላህ ባሪያ ከሰለም(እስልምናን ከተቀበለ) እና እስልምናው "ካማረ" "ከተዋበ" *ሙስሊም ከመሆኑ በፊት የሰራውን "ኃጢአት" ሁሉ አላህ ያብስለታል።* ከዚያም(ከአበሰለት) ቡኃላ ቂሷስ(ማመሳሰል) ይሆናል፣ ማመሳሰሉም፦ "በአንድ" መልካም ሥራው *ከአሥር እስከ ሰባት መቶ* እጥፍ ድረስ "ይባዛለታል"። "በአንድ" ኃጢአቱ ደግሞ *መሰሏን* ይመነዳል፣ አላህ ይቅር ብሎ ካላለፈው በስተቀር (ያቺኑ ይመነዳል)።
أَنَّ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ : أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ : " إِذَا أَسْلَمَ الْعَبْدُ فَحَسُنَ إِسْلَامُهُ، يُكَفِّرُ اللَّهُ عَنْهُ كُلَّ سَيِّئَةٍ كَانَ زَلَفَهَا ، وَكَانَ بَعْدَ ذَلِكَ الْقِصَاصُ : الْحَسَنَةُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا إِلَى سَبْعِمِائَةِ ضِعْفٍ، وَالسَّيِّئَةُ بِمِثْلِهَا إِلَّا أَنْ يَتَجَاوَزَ اللَّهُ عَنْهَا ".

በሐዲሱ መሰረት ማንኛውም ሙስሊም ያልሆነ ሠው "ሁለት" መስፈርቶችን ካሟላ ኃጢኣአቶቹ ሁሉ *እንደሚታበሱለት* ተገልጿል። አንደኛው "ሙሥሊም" መሆን ሲሆን ሁለተኛው "ሙሕሲን" መሆን ነው።

ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ” አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” “መገዛት” “ማምለክ” ማለት ነው
ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል ሠለመ” سَلَّمَ “ማለትም “ታዘዘ” “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ታዛዥ” “አምላኪ” ማለት ነው፦
21፥108 ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *“አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን*? በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ስለዚህ የመጀመሪያ መስፈርት ለአንድ አምላክ ፍፁም መታዘዝን እርሱን በብቸኝነት መገዛት ሲሆን ይህ ደግሞ ከኢሕሳን ጋር የተያያዘ ነው።

“ኢሕሣን” ማለት ደግሞ “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ” "መገዛት" ማለት ነው፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 47 , ሐዲስ 6
…ዑመር ኢብኑ ኸጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው ወደ ነብያችንﷺ በመምጣት እንዲህ በማለት ጠየቃቸው፦ እስኪ ስለ "ኢሕሳን" ንገረኝ፣ እርሳቸውም፦“ኢሕሳን" ማለት አላህን ልክ እንደምታየው አድርገህ ማምለክ፥ አንተ እንኳን ባታየው እርሱ ያይሃልና” አሉ።عن عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ
قَالَ : فَأَخْبِرْنِي عَنِ الْإِحْسَانِ. قَالَ : " أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ "
ስለዚህ አንድ ሠው ለእስልምናው ማማር ዋነኛው ነገር ለአላህ ብሎ ሥራን አጥርቶና አሳምሮ "በኢኽላስ" መስራቱ ነው።

ለአላህ ብሎ ተነይቶ መልካም ሥራዎችን መሥራት "ኢኽላስ" ይባላል፥ “ኢኽላስ” إِخْلَاص የሚለው ቃል “አኽለሰ” أَخْلَصَ‎ ማለትም “አጠራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከወቀሳና ሙገሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ የሚደረግ “ማጥራት” ማለት ነው፦
فَاعْبُدِ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ
39:2 አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ኾነህ ተገዛው፡፡

አንድ ሠው በሰለመ ጊዜ ኃጢአቱ ሁሉ ከእርሱ ይታበሳል፦
قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوا إِن يَنتَهُوا يُغْفَرْ لَهُم مَّا قَدْ سَلَفَ
8:38 ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ "ያለፈውን" (ሥራ) "ምሕረት" ይደረግላቸዋል፡፡

አንድ ሠው ከሰለመ ቡኃላ በኢኽላስ ጥርት ያለ ሥራ ከሰራ አንዷ መልካም ሥራው *ከአሥር እስከ ሰባት መቶ* "እጥፍ" አላህ ያባዛለታል፣ ይህም እንደ ሰውዬው *ኒያው* እና *ኢኽላሱ* ደረጃ ይለያያል፦
مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
6:160 በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ *ዐሥር* ብጤዎችዋ አሉት፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው *ብጤዋን* እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
مَّثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنبَتَتْ سَبْعَ سَنَابِلَ فِي كُلِّ سُنبُلَةٍ مِّائَةُ حَبَّةٍ ۗ وَاللَّهُ يُضَاعِفُ لِمَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ
2:261 የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች (ልግስና) ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ "መቶ" ቅንጣት ያለባቸውን "ሰባት" ዘለላዎች እንደ አበቀለች "አንዲት" ቅንጣት ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) "ያነባብራል"፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡

ይህን የቁርኣን አንቀጽ ከላይ ያሳለፍነው ሐዲስ ያብራራዋል፣ *አንዷ* ቅንጣት በላይዋ ላይ "ሰባት" ዘለላዎች ያበቀሉ ሲሆን እያንዳዱ ዘለላ ደግሞ "መቶ መቶ" ቅንጣቶችን ያበቀሉ ናቸው። 7×100=700 ይሆናል። ይህ ማለት የሚጣፋለት እስከ 700 ብቻ ነው ማለት አይደለም። "አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) *ያነባብራል*፡፡" ባለው መሰረት የሰው ልጅ "ኒያው" እና "ኢኽላሱ" ምንዳውን ያበላልጠዋል። መነሻው ግን 10 እጥፍ ነው።
590 views17:37
Open / Comment
2022-01-24 22:14:31 AS-HABULE YAMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር pinned «የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም የሰለምቴው Dawit Solomon ታሪክ ክፍል1 share አርጉት ሥሜ ሱለይማን በላይ ሲሆን ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሠዎች የሚያውቁኝ "ዳዊት ሠለሞን" ወይም "ዴቭ" በሚል ስም ነው። ሥሙን የምጠቀመውም አቡ-ዳውድ ስለሆንኩ ነው። በእድሜየም ከወጣትነት አልፌ ወደ ጎልማሳነት ተሸጋግ.ሬአለሁ ። እድገቴ ከቤተሰቦቼ የወረስኩትን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይዤ ነው።ያው…»
19:14
Open / Comment
2022-01-24 18:56:42
526 views15:56
Open / Comment
2022-01-24 18:56:34 ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A
529 views15:56
Open / Comment
2022-01-24 18:56:34 ክርስትና ሃይማኖት ላይ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ተሰርተው የተለያዩ ለአምልኮ የሚጠቀሙዋቸው ነገሮች እንዳሉ ተናግሪያለው ። እሥልምና ሃይማኖት ላይ ግን ይህንን አላየውም ። አምልኮ የሚገባው ለአላህ ብቻ እንደሆነ ነው የተረዳው ለምሳሌ ብንመለከት ሱረቱል ጂን ቁጥር 18 ላይ መስጂዶች የአላህ ብቻ ናቸው በመሆኑም ከአላህ ጋር (ዉጪ) ማንንም አታምልኩ ነው የሚለው አምልኮ የሚገባው ለአላህ ብቻ እንደሆነ ተረድቻለዉ ሰለዚህ ወደ እሥልምና ሃይማኖት እንድገባ አድርጎኛል ማለት ነው ። በመቀጠል ደግሞ እኔ የክርስትና እምነት እያለዉ እሥልምና ሃይማኖትን አድርጌ የማስበው አዲስ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ያመጣው እምነት ነው ብየ ነበር የማምነው ከክርስትና ሃይማኖት በኋላ የተቋቋመና አዲስ እምነት ነው ብየም አስብ ነበር ።

ከክርስትና እምነት በኋላ የተቋቋመው ብየ ማስረጃ የማቀርብበት የሆነው አመተ ሂጅራ አቆጣጠርን መሰረት በማድረግ ነው ። አመተ ሂጅራ አቆጣጠር የሚጀምረው እሥልምና በተጀመረበት ዘመን ነው ብየ ነበር የማምነው ። እንዲህ ብየ የማምነው እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎቹ ክርስቲያኖች እሥልምና ሃይማኖት ከክርስትና ሃይማኖት በኋላ የተቋቋመ አዲስ እምነት ለመሆኑ እንደ ማስረጃ የሚጠቀሙት አመተሂጅራን ስለሆነ ነው ። ለማንሳት የፈለኩት ዳሩ ግን አመተ ሂጅራ አቆጣጠር መጀመር እና እሥልምና እምነት መጀመር በአንድ ላይ የተጀመሩ ነገሮች አለመሆናቸውን ተረድቻለው ።

አመቱ ሂጅራ አቆጣጠር የሚጀመረው ነቢያችን ሙሐመድ ﷺ በተላኩ ከ13 አመት በኋላ ነው ሂጅራ በራሱ ትርጉሜ ስደት ማለት ነው ። ከመካ ወደ መዲና ካደረጉት ስደት ከዛ ጊዜ ጀምሮ ነው አመተሂጅራ የሚጀምረው ። እሥልምና ሃይማኖት ግን የሚጀምረው ከአባታችን አደም አለይሂ ሰላም እና ማንኛውም ሰው የተፈጠረበት አላማ ነው ።

የሰው ልጆች የተፈጠሩበት አላማ አላህን በብቸኝነት ለመገዛት እንደሆነ አምላካችን አላህ ሱረቱል ዛሪያት ቁጥር 56 ላይ ይገልፅልናል አጋንትም ሰዎችም እንዲያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም ይላል ። ስለዚህ የመጀመሪያ ሰው አባታችን አደም አለይሂሰላም እስከሆነ ድረስ እሥልምና ሃይማኖት የሚጀምረው ከአባታችን አደም እንደሆነ ተረድቻለው ። ከአባታችን አደም ጀምሮ እስከ መጨረሻዉ ነቢይ ሙሐመድ ﷺ ድረስ የነበሩት ነቢያቶች ሁሉ እምነታቸው ኢሥላም እንደነበረና ጥሪያቸው ወደ እሥልምና እንደሆነ ተረድቻለው ።

የምሰራባቸው ሰዎች ሙሥሊሞች ናቸው ሁሌም ጠዋትና ማታ አያተል ቁርሲይን ይቀራሉ አይረሡትም ሁል ጊዜም ይቀሩታል ነገር ግን ለእኔ ተፅዕኖ አሳድሮብኝ ነበርና ትርጉሙን ማወቅ ፈለኩኝ አሳዩኝ እነርሱን ጠይቄያቸው ማለት ነው ።

ሱረቱል ኢኽላስ ላይ አላህ 1 እንደሆነ እና የሁሉም ነገር መጠጊያ እንደሆነ አልወለደም አልተወለደም ለእርሱም አምሳያ የለውም ነው የሚለው አያተል ኩርሲይ ላይ ስንመጣ ደግሞ ማብራሪያ ነው የሚሰጠን አምልኮ የሚገባው ለአላህ ብቻ እንደሆነ ከአላህ ዉጪ ሌላ አምላክ እንደሌለ ህያውና ራሱን ቻይ እንደሆነ ስለሚያብራራ ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ አይዘውም ይላል አምላካችን አላህ ሱብሃነወታአላ ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ አይዘውም ።

ወደ ክርስትና እምነት መመሪያ ስንመጣ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 4:38 ላይ እርሱም በስተኋላ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር አንቅተዉም መምህር ሆይ ስንሰምጥ አይገድህምንዴ አሉት ይለናል አምላካችን የሚሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ተኝቶ ነበር ማለት ነው ። አምላካችን አላህ ሱብሃነህወታአላ ግን ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ አይዘውም ። ስለዚ ማመን የነበረብን ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ የማይዘውን አንድና ብቸኛ ፈጣሪ የሆነውን አላህን ብቻ ስለሆነ ወደ እሥልምና ሃይሜኖት ገብቻለው ።

እሥልምና የተቀበልኩኝ ለት በጣም ነው ደስ ያለኝ ከምናገረው በላይ የተፈጠርኩበትን አላማ አዉቄ ተቀብየ ተግባር ላይ ለማዋል ሀ ብየ የጀመርኩበት ቀን እስከ መቼም ድረስ ሁሌም የማረሳው ቀን ነው ቀኑ ጁምአ ቀን ነበር እንዳጋጣሚ ሆኖ ደግሞ አማኞች ለማየት የሚመኙትን መከተል ሙከረማ በአካል ተገኝቼ ያየሁበት ቀን ስለነበረ ሁሌም የማይረሳ ልዩ ቀን ነው ለእኔ።

ከእሥልምና ጸጋዎች እኔን ይበልጥ የማረከኝና የሳበኝ አንድ አምላክነቱ ሁለተኛ ሶስተኛ የሌለው አንድና ብቸኛ የሆነውን አምላካችን አላህ መገዛት ነው ። በመቀጠል እሥልምና ሚዛናዊና ፍትሀዊ የሆነ እምነት ነው።

ሂወት በእሥልምና አልሃምዱሊላህ በጣም ነዉ ደስ የሚለው እሥልምና የሚያዘው ለተፈጠርንበት አላማ እንድንንኖር ነው እናም ይሄ ትልቅ ኒዕማ ነው ። አልሃምዱሊለህ ። የበፊቱ ሂወቴና አሁን ያለሁበት ሂወቴ በጣም ልዩነት አለው ከጨለማ ወጥቼ ወደ ብርሃን እንደመጣው ያክል ተሰምቶኛል። ፈጣሪያችን አላህ ሁሉን ነገር ሲፈጥር የራሱ የሆነ ምክንያት አለው እኛን የሰው ልጆችን ደግሞ ሲፈጥር በብቼኝነት እንድንገዛ ነው ።
እና አሁን እኔ ባለሁበት ሂወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ አልሃምዱሊላህ ።

በመጨረሻም ለማስተላለፍ የምፈልገዉ መልዕክት ከእሥልምና እምነት ዉጪ ያሉ የክርስትና እምነትም ሆነ የሌላ እምነት ተከታዮች ሁሉም የራሳቸው የሆነ መመሪያ አላቸዉ መመሪያችንን በደምብ ካነበብነዉና ፅንሰ ሀሳቡን ከተረዳነዉ እምነታችን መመሪያ መለኮታዊ ነዉ ወይስ ተሳሰቻለዉ የሚለዉን መለየት እንችላለን ከዚያ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራናል። በመቀጠል ደግሞ እምነታችንን ሰዎች እንዲመርጡልን መፍቀድ የለብንም እምነታችን የተፈጠርንበት አላማ አስከሆነ ድረስ መምረጥ ያለብን እኛዉ ነን ብናምን የምንጠቀም እኛው ነን ብንክድም የምንጎዳው እኛው ነን።

እና ደግሞ አንዳዶቹ እሥልምና እምነት ትክክለኛ እምነት መሆኑን ያውቃሉ ግን ደፍረው ለመግባት ፈርተው ዳር ላይ ቆመው የሚመለከቱ አሉ እነዚያ ያስፈራቸው ነገር ቤተሰብ ወይም ዘመድ ይርቀናል በሚል ነው ። ቤተሰብ ሆነ ወዳጅ ዘመድ ሊርቁን ይችላሉ ግን ለእነርሱ መልካም እንድንሆን አላህም ያዘናል መልካምነታችን ግን ገደብ አለው ።

ለምሳሌ ሱረቱል አንከተቡት ቀጥር 8 ላይ ሰውንም ለወላጆቹ መልካም እንዲሆን አዘዝን ግን በርሱ እውቀት የሌለው አንዳች ነገር በእኔ ላይ እንድታጋራ ቢያዙህ ፈጽሞ አትታዘዛቸው ሁላቸውንም መመለሻቹ ወደ እኔ ነው ትሰሩት የነበረውን ሁሉ እነግራችኃለው ይለናል ስለዚህ ለቤተሰቦቻችን መልካም መሆን እንዳለ ሆኖ ግን በአላህ ማጋራት የለብንም ወደ እሥልምና መግባታቹ የምታጡት ነገር የለም ወደ እሥልምና ግቡ ነው የምለው አመሰግናለው ።
ትርንጎ




ጥያቄ ስጠይቃቸው ጥያቄ አትጠይቂን ይሉኝ ነበር የሃይማኖት አባቶች ። ሠለምቴዋ ትእግስት በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም በቁጥር 32





የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-





AS_HABULE YAMlNE TUBE
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125
505 views15:56
Open / Comment
2022-01-24 18:56:34 ስሜ ሳልሰልም በፊት ትርንጎ ነበር አሁን ከሰለምኩ በኋላ ሂክማ ነው የምከተለው የነበረው እምነት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነበር ። በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም

ቤተሰቦቼ ግን ሃይማኖታቸው ላይ በጣም ጥብቅ ናቸው የቤተክርስቲያን ሰውም ናቸው ። ወደፊት እንደ እነርሱ እሆናለዉ የሚል ምኞትና ሃሳቡም ነበረኝ።

ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ከቤተሰቦቼ የወረስኩት ሃይማኖት ሰለነበረ እና በስመ ኦርቶዶክስ ስለነበርኩኝ ትክክለኛ ሃይማኖት አድርጌ ነበረ የማስበው በጊዜው ።

እሥልምና ሃይማኖትን እጠላው የነበረዉ ክርስትና ሃይማኖትን የሚቃወም መስሎ ስለሚታየኝና የእሥልምና እምነት ተከታዮችን ደግሞ ነፃነት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ስለሚመስለኝ በተለይ ሴቶቹን ሒጃብ ሲለብሱ ፈልገውት የሚለብሱት አይመስለኝም ነበር የተጨቆኑ መስሎ ነበር የሚታየኝ በዛ ሰአት ።

ማግለል ነገር አልነበረንም እኔ በግሌ እመነታቸው አልወደውም ነበረ ማለቴ እሥልምናቸውን ማለቴ ነው። እሥልምናን የማስበው ዝቅ ብለህ እንድትኖር የሚያስገድድ ነፃነት የሌለዉ እና አዲስ መጤ አድርጌ ስለማስበዉ በዛ ሰአት ሳላውቀው የምጠላው ነገር ቢኖር እሥልምና ነበር ።

አሁን ላይ ግን አልሃምዱሊላህ የጠላውትን ያክል ወድጀዋለው አንድን ነገር ደግሞ ሳናውቅ መጥላት እንደሌለብን ከዚህ ተምሪያለው አልሃምዱሊላህ።

ክርስትና ሃይማኖት ስህተት ነው በዚህ ማመን የለብኝም ብየ እንድወስን ያደረጉኝ ምክንያቶች ብዙ ናቸው ። ሁሉም እምነቶች የየራሳቸው የሆነ መመሪያ አላቸ። የክርስትና እምነት መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያዘውና የእምነቱ ተከታዮች የሚተገብሩት ነገር የተለያየ ነው ።

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ኢየሱስ እኔ አምላክ ነኝ አላለም እኔ ነቢይ ነኝ ነው ያለው። የእምነቱ ተከታዮች ግን ኢየሱስን አምላክ ነው ብለው ነው ። የሚያምኑት ክርስትና እምነት ላይ ብዙ ሰው ሰራሽና ስእላ ስእል ነገሮች አሉ ለነዚያ ሰው ሰራሽና ስእላ ስእል ነገሮች የተለየ ክብር ነው ያላቸው ። ማክበር ብቻ ሳይሆን ይሰግዱላቸዋል ይተናነሱላቸዋል እርዳታ ይጠይቋቸዋል አንድን ነገር እርዳታ የምንጠይቀዉ የምንተናነስለት የምንሰግድለት ከሆነ እንደ አምላክ ተጠቅመነዋል ማለት ነው ።

ክርስትና እምነት ላይ አምላካችን የሚሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አይደለም ስግደታቸው ጸሎታቸው ሌሎችም ተጨማሪ ነገሮች አሉ መለኮታት ሰማእታት የሚሉዋቸው ። ነገሮች መለኮታት ከሚሎዋቸው መካከል አንደኛዋ መርየም ናት በመርየም ተሰይሞ ቤተክርክቲያን ይሰራል ስእልዋን ያስቀምጣሉ በቤታቸው ላይ በዚያም ስእል መሠረት ይሰግዱላታል ይለምኗታል እርዳታን ይጠይቋታል። ይሄ ምን ማለት ነው .? አንድን ነገር እርዳታ የምንጠይቀዉ የምንሰግድለት ከሆነ እንደ አምልኮ ተጠቅመነዋል ማለት ነው ።

መርየም አለይሂሰላም ሞታለች ስለሆነም እሷን እርዳታ መጠየቅ ለእርሷ መስገድ መተናነስ እኔ ላምንበት አልችልም ለሞተ አካል ይቅርና በሂወት ላለ ፍጡር መስገድም ሆነ መተናነስ ምንም እሚጠቅመው ነገርም የለም በመቀጠል ደግሞ መላኢካዎችን ይስሉዋቸዋል መላኢካው ሚካኤል መላኢካው ገብርኤል እያሉ ስእላቸውን ይስላሉ መላኢኮች ምን አይነት ቅእፅ እንዳላቸው ምን እንደሚመስሉ የት አይተው ሊስሉዋቸዉ ቻሉ ነዉ የእኔ ጥያቄ ። እና ለመለኢካዎችስ መስገድ መለመን ለምን አስፈለገ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ካሉ ስግደታቸውና ጸሎታቸዉ ለምን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አልሆነም የሚል የእኔ ጥያቄ ነበር አንድን ነገር በስእል ነገር ማስመሰልና መሳል መለኮታዊ ከሆነ እምነት የሚጠበቅ አይደለም ይሄ ሊያሳምነኝ ስላልቻለ ወደ እሥልምና ሃይማኖት ገብቻለው ።

እሥልምና እምነት ትክክለኛ እምነት ነው ብየ እንዳምን ያደረጉኝ ምክንያቶች ብዙ ናቸው ። በመጀመሪያ ግን ስለ እሥልምና ሃይማኖት እንዳጠና መነሻ ነጥብ ሆኖኛል ብየ የማነሳዉ ነገር መሃላ ነዉ መሃላ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ ስንመለከት በብዙ ነገሮች ነበር መሃላችንን የምንፈፅመው ለምሳል :- በማርያም በገብርኤል በሚካኤል በብዙ ነገሮች የእሥልምና እምነት ተከታዮችን በምመለከትበት ጊዜ ደግሞ ሁሉም የእሥልምና እምነት ተከታዬች መሃላቸውን የሚፈጽሙት በአንድ አላህ ብቻ ነው ። ያ ነገር ለእኔ ጥያቄ ሆኖብኝ ነበር እኛ ክርስቲያኖች በብዙ ነገር ነው መሃላችንን የምንፈጽመው ሙሥሊሞች ደግሞ በአንድ ነገር ብቻ መሃላቸውን የሚፈፅሙበት ሚስጥር ምንድን ነው ብዬ አስብ ነበር ምክንያታቸውን ለማወቅ የምጠይቀውና የሚያስረዳኝ ሰው በጊዜው በቅርቤ አልነበረም እና የተጠቀምኩት አማራጭ ማንበብ ነው ።

ሳነበው የነበረዉ መጽሐፍ ቁርኣን ተፍሲር በአማረኛ ነበር ከዚያም በፊትም ነበረኝ ይህ መጽሐፍ በምሰራባቸው ሰዎች ሙሥሊሞች ስለሆኑ እና እኔም ሙሥሊም ስለመሰልኳቸው ገዝተው አምጥተውልኝ ነበር እና አነበውም ነበር ግን የማነበው ዝም ብየ እንደመዝናኛ ስለነበር ለማወቅም ፍላጎቱ ስላልነበረኝ ትኩረትም ስለማለሰሰጠው ምንም አይገባኝም ነበር ነገር ግን የመሃላው ጉዳይ ጥያቄ ለነበረብኝ ምናልባት መልስ ባገኝ ብየ ነበር ማንበብ የጀመርኩት እና አንስቸ እያነበብ እያለ ሱረቱል ኢኽላስን በማነብበት ሰአት ለጥያቄየ መልስ ያገኘሁበት ጊዜ ነበር ሱረቱል ኢኽላስም እንደዚ ነበር የሚለው "በል እርሱ አላህ አንድ ነው
የሁሉ ነገር መጠጊያ ነው
አለወለደም አልተወለደም
ለእርሱም አንድም አምሳየ የለውም ይላል።

ሱብሃነአላህ የመጀመሪያው አያ ላይ በል እርሱ አላህ አንድ ነው ነበር የሚለው በቃ ሙሥሊሞች መሃላቸውን ሲፈፅሙ የነበረው በአንድ ነገር ነው እርሱም በአምላካቸው አምላካቸው አላህ አንድ ስለሆነ ነው ብየ አሰብኩ።

ክርስትና ሃይማኖት ላይ እያለዉ ጥያቄ ሆኖብኝ የነበሩ ነገሮችን እሥልምና ሃይማኖት ላይ መልስ አግኝቼላቸዋለው ክርስትና ሃይማኖት ላይ ለመላእክታት ለመርየም የሚሰጡት ክብር ወሰን ያለፈና ከሚገባው በላይ ነው ። ወደ መላእክታት ይጸልያሉ ወደ ወርየም ይፀልያሉ ማርያም ሆይ ድረሺልኝ ገብርኤል ሆይ ጠብቀኝ ሚካኤል ሆይ ሃሳቤን አሟላልኝ እያሉ ለአምላክ ብቻ የሚገባውን ክብርና አምልኮ ለእርነሱ ሲሰጡዋቸው እመለከታለው እሥልምና ሃይማኖት ላይ ግን የሚገባቸውን ክብር ቢሰጣየውም እንደ ክርስትና ሃይማኖት ግን ወሰን ያለፈ አይደለም ለምሳሌ ብንመለከት መርየም አለይሂሰላምን አምላካችን አላህ የሙዕሚኖች ምሳሌ አድርጎ በቁርኣን ላይ ይጠቅሳታል ሱሩተል ተህሪም ቁጥር 12 ላይ የ ኢምራን ልጅ መርየምን ያቺን ጥብቅ የሆነችውን ምሳሌ አደረገ በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፋን በጌታዋ ቃላትና መጽሐፍትም አረጋገጠች ከታዛዦችም ነበረች ይላል ስለዚ የሙዕሚኖች ምሳሌ አድርጎ ይጠቅሳታል እንጅ ወደ እርሷ እንድንጸልይና ወደ እርሷ እንድናመልክ አልተፈቀደልንም አምልኮ የሚገባው አምላካችን አላሁ ሱብሀነሁ ወታአላ ብቻ እንደሆነ ተረድቻለው በመቀጠል ደግሞ የክርስትና ሃይማኖት ላይ ያለው ለረሱል አሚን አለይሂ ወሰላቱ ወሰላም የተለየ ክብር ስለሚሰጡ እነርሱን የሚያመልኩት ይመስለኝ ነበር ።
488 views15:56
Open / Comment
2022-01-20 19:46:57 ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ለሚዲያ ፍጆታ የሚያውለው ማስመሰል እንጂ እምነታችን የሚፈቅደው ተግባር አይደለም!

አዎ ይሄ "አንድነት" ነው። ኢስላምን በመናድ የእምነትን አጥር በማፍረስ የሚፈፀም ዝብርቅርቅ ህብረት። በዚህ አይነት ተግባር ሙስሊሙም ክርስቲያኑም አይጠቀምም። አብሮ የመኖር እሴትም አይዳብርም። አገርም አታተርፍም። ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ለሚዲያ ፍጆታ የሚሰራው የማስመሰል ስራ ሲኖር የዋሃንን ለዚህ አይነት ጥፋት ያሰልፋል። ደግሞ "ሰላም ይህ ነው" ይባልልናል። እንዲያውም እውነቱን እንናገር ከተባለ ሃይማኖት በዚህ መልኩ የፖለቲከኛና የጋዜጠኛ መጫወቻ ከሆነ ወዲህ ነው ይበልጥ ሰላም ያጣነው። ሁሉም የእምነቱን አጥር ጠብቆ ሰላም ማስከበር እንደሚቻል ያልተረዳ አካል ስለ ሰላም የማውራት አቅም ላይ ገና አልደረሰም።

እንዲህ አይነቱ ኢስላም የማይፈቅደውን ተግባር የምንኮንነው ሰላምና መቻቻል ስለማንፈልግ አይደለም። በፍፁም! እንዲያውም ከሰላም ይበልጥ አትራፊዎቹ እኛ፣ በሰላም መጥፋት ይበልጥ ተጎጂዎቹም እኛ ነን ብለን እናምናለን። ታዲያ እንዲህ አይነቱን የማደበላለቅ አካሄድ የምንቃወመው ሃይማኖታችን ጋር የሚጋጭ ተግባር ስለሆነ ነው።

ስለዚህ የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅና በመልካም ተባብሮ የመኖር እሴት ለማጎልበት አንድ ሺ አንድ አማራጭ መጠቀም ሲቻል ሁሌ በአል እየጠበቁ ሙስሊሙ ታቦት እንዲሸኝ፣ መስቀል እንዲያከብር ማድረግ ወይም መጣራት ወይም ደግሞ እንዲህ አይነቱን ተግባር የመቻቻል ማሳያ አድርጎ መሳል የራሱ አፍራሽ ገፅታ አለው። ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ተግባር በኢስላም በእጅጉ የተኮነነ ስለሆነ እምነቱ የሚጠይቃቸውን የማንቃት ስራ የሚሰሩ ሙስሊሞችን በጠርዘኝነት እንዲሳሉ ቀዳዳ ይከፍታልና።

ዛሬም ከአንዳንዶች እያስተዋልን ያለነው ይሄንኑ ነው።
ከዚህ ይልቅ ዜጎች አብረው ለሰላም እንዲተጉ፣ በችግራቸው እንዲረዳዱ፣ ከተንኳሽና ፀብ ጫሪ ተግባራት እንዲታቀቡ፣ በየቤተ እምነቱ አድፍጠው ወጣቱን ለግጭት እያነሳሱ ያሉ ሰባኪዎች ስርአት እንዲይዙ፣ በአል በመጣ ቁጥር እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ገፊ ምክንያቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ ከምንጫቸው እዲደርቁ ማድረግ ላይ መስራት ነው የሚበጀው። እንጂ ባዶ መሸነጋገል፣ መሸዋወድ የትም አያደርሰንም።

@ኢብኑ ሙነወር
459 views16:46
Open / Comment
2022-01-20 19:46:34
439 views16:46
Open / Comment
2022-01-13 15:27:04 "መስጊድህን አፍርሼ ቤተ ክርስቲያን ባልሰራ እምዬ ማርያም አትለመነኝ"
=
የኃይለ ስላሴ አባት ራስ መኮነን ወልደ ሚካኤል ሃረርን ሊወር ሲዘጋጅ በአሚር ኑር ላይ የፎከረው ነው። ፎክሮም አልቀረ እድሜ ጠገቡን የፈረስ መጋላ መስጅድ አፍርሶ መድሃኔያለም የተሰኘ ቤተ-ክርስትያን በቦታው ገነባ። ይህም ሳይበቃ የቁርአን መማሪያ ማእከላትን ፈርሰው በምትካቸው ስላሴ ቤተ ክርስቲያን፣ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እና ቁልቢ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ተገንብተዋል።
.
እና ታሪክ እየፈጠራችሁ ያም የኛ ይሄም የኛ የምትሉ ሁሉ! የደረቀ ቁስል ባትነካኩ መልካም ነው። ይሄ በሙስሊሙ ብቻ አይደለም የሚነሳው። በአሁኑ ሰዓት በሰፊው ከሚታወቁት አብያተ- ክርስትያናት ውስጥ ከሌሎች ቀደም ብሎ ከነበሩ ልማዳዊ እምነት ቦታዎች ተነጥቀው የተሰሩት ብዙ ናቸው። የታደሰ ታምራትን Church & State መፅሀፍ መመልከት ይቻላል።
ስለዚህ ታሪክ እያጣቀሱ ያም የኔ ነው፣ ይሄም የኔ ነው ማለት መዘዙ ብዙ ነው። ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄ ያነሳሉና። በርግጥ አብዮት አደባባይ ከስም ባለፈ የቤተ-ክርስትያን ንብረት አይደለም። ካርታ ብለው የሚያቀርቡትም ከእምነት ተቋም የማይጠበቅ አይን ያወጣ ማጭበርበር ነው። ባለቤትነትን የሚያሳይ ካለመሆኑም ጋር መሀተም የለውም። ህጋዊ የባለቤትነት ሰነድ የላቸውም እንጂ ቢኖራቸው እንኳ መነጠቅ ነው ያለበት። ምን ሲባል ነው አደባባይ የአንድ ሃይማኖት ንብረት የሚሆነው? ጭራሽ አደባባይ እናስፈቅድ እንዴ? ሆ!
እንዲያውም የምታነሱት የአፄው ዘመን ታሪክ ቤተ ክርስትያን ምን ያክል ምዝበራና ብዝበዛ ላይ እንደነበረች የሚያሳይ፣ የዚያ የጭቆና ዘመን ጠባሳ ማሳያ ነው። ሊታፈርበት ሲገባ ጭራሽ ጅብድ?! "ያልፈሳንበት ዳገት የለም" አለች አሉ አህያ። ቤተ ክርስትያን ምዝበራና ብዝበዛ ላይ ስለነበረች እኮ ነው አፄ ቴዎድሮስ ጋር ተፋጣ ጳጳሱን እስከሚያስር፣ ካህናትን እስከሚያባርር፣ መሬት እስከሚነጥቅ የደረሰው። ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋር ተበደልኩ ባዩዋም እሷው ሆናለች። "እናትና አባቱን የገደለ ሰው ትዝ ይለኛል። የፍርድ ውሳኔ ሊሰጥበት ሲል 'እናትና አባት የሌለኝ ሰው ነኝና ምህረት ይደረግልኝ' አለ" የሚል አባባል ነበር። ይህንን ነውረኛ ተግባር ግን በደንብ አልገልፅልኝ አለ።

ብቻ መስቀል አደባባይ ተብሎ ስለተሰየመ የኛ ነው ካሉ ነገ ከነገ ወዲያ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍል ከተማ፣ ጨርቆስ፣ አቦ፣ ሀናማርያም፣ ቀጨኔ፣ አማኑኤል፣ ... ጎዳናና አደባባዩን ሁሉ ካላስረከባችሁን አይሉም አይባልም። ስለዚህ ሳይቃጠል በቅጠል!
በነገራችን ላይ ቅዳሴና አዛኑ የሚለው ዘፈን ባዶ ኳኳታ እንጂ መሬት ላይ ብዙ መገፋፋት ነው ያለው። ለቤተ ክርስቲያን በ100 ሜትር ርቀት ላይ እንዴት የመስጂድ ቦታ ይሰጣል ብለው እነ ምህረታብ ሲፈጥሩት የነበረው አካኪ ዘራፍ እሩቅ አይደለም።
ባጭሩ መንግስት በለሰለሰ የዲፕሎማሲ ቋንቋ ቢነግራቸውም እየገባቸው አይደለም። ጭራሽ ወደ ግርግርና ሙስሊሙን ወደ መተንኮስ እየሄዱ ነው። በየዘርፉ ያሉ አካላትም ያጋደለ ፅሁፍ እየፃፉ ጫና በመፍጠር ላይ እየተረባረቡ ነው። መንግስት ሆይ! በዚህ የአደባባይ ጉዳይ በነሱ ጩኸት ተሸንፈህ ታሪካዊ ስህተት እንዳትፈፅም። ሰዎቹ ለወቅታዊ ብሶታቸው ማባበያ አድርገህ እንድታቀርብላቸው ነው የሚፈራገጡት። እንዲያውም ህዝባዊ ተቋማት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል፣ አማኑኤል ሆስፒታል፣ ከሚሉ ስያሜዎች መውጣት ነበረባቸው።
=
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
409 views12:27
Open / Comment