Get Mystery Box with random crypto!

መፅሐፍት

Logo of telegram channel audio_poems — መፅሐፍት
Logo of telegram channel audio_poems — መፅሐፍት
Channel address: @audio_poems
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 42
Description from channel

@Air_me1 ግጥሞን በዚ ይላኩ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages 15

2022-12-03 18:50:33
ጠቢብ ማነው ላሉ
                          
አእላፍ ቃል ቢወጡ ፤ ዜማ ቢደረደር
የሰው ልጅ ሃሳቡ ፤ ተዝቆ ቢከመር
ትዝታ ቢወሳ ፤ ጊዜ ላይመለስ
በፍቅር ቢጎዳ
የፈሰሰ ፍቅር ፤ ዳግም ላይታፈስ

ፍጥረቱ ይገርማል
ከቶ ተስፋ አይቆርጥም ፤ አሁንም ይፅፋል
ከመዳፉ መሃል
ከጣቶቹ ጫፎች ፤ ውብ ምስል ይፈልቃል

ሰው ሰውን ያስባለው ፤ ለካ ተስፋ ነበር
ስባሪ ልብ ይዞ ፤ ትዝታ ላይ መሰፍር
ህያው ነኝ እያለ ፤ ተስፋ ይዞ መቀበር
ታድያ
ይህን መሰል ስሜት ፤ ቃላት ቢደረደር
ከንፁህ ሸራ ላይ ፤ ውብ ቀለም ቢሰፍር
እውነት ስሜት ጥሎ ፤ ምን አለ የሚናገር
 
ንፁህ ሰው ካገኙ ፤ ፍፁም ሚዘርፋቸው
ህመምም ስዕል ነው ፤ እንባም ቅኔ ናቸው
ጣት ቀለም ቢያሳምር ፤ አንደበት ቃል ቢቃኝ
ከቶ አንድም ጠቢብ
እነደ ህመም አይስልም ፤ እንደ እንባ አይቃኝ

@MyMessagesss
408 viewsBarkot A, 15:50
Open / Comment
2022-12-01 21:03:58
የናፍቆት ባህርሽ

አመልጣለው ብዬ ፤ ከናፍቆት ባህርሽ ላይ
ተሳፍሬ ነበር ፤ ብዙ መርከቦች ላይ
ያ እርኩስ ትዝታሽ ፤ ማዕበል እያስነሳ
አውጥቶ ይጥለኛል ፤ ሰው ለኔ እንዳይሳሳ
ስለዚህ ከንግዲህ
የናፍቆትሽ ባህር ፤ ወስዶ ከፈለገው
አስኪጥለኝ ድረስ ፤ ምድርን እስከማየው
አይኖቼን ዘግቼ ፤ ከናፍቆት ባህርሽ
ሁሌ እናሳፈፋለው


@MyMessagesss
463 viewsBarkot A, 18:03
Open / Comment
2022-11-28 21:39:48
በፍቅር ሱባኤ
በረሀብ በረሀ በስጋ ጠውልገን
በፍቅር ሰማይ ስር ከሚያፈሰው ዝናብ በመንፈስ አብበን
ከንፈራችን ደርቆ አየተዛዘንን
አናርሰው ነበር እየተቃመስን
እስትንፋስ ሳይቀረን እየተዋዋስን

ከቤታችን ጀርባ ባለች ትንሽ ደብር እቤት
አንዳችን ላንዳችን ስንፀልይ ውለን
ባገኘናት ጉርሻ አፋችን አብሰን
በፍቅር ሱባኤ ደስተኞች ነበርን

ትዝ ይልሻል ወዴ?
ክረምትና በጋን
የአልጋችንን ቦታ ሳንቀይር ረስተን
ሁሌ በጋ መስሎን
ዝናብ የጣለ ቀን
አልጋችን እርሶ እረጥቦ ገላችን
ተቃቅፈን ያደርነው እያንቀጠቀጠን
ለሌላ ያየ ሰው የችግር ቢመስልም
ለኛ ፍቅር ነበር

ደግሞ ለበዓል ቀን ፊታችን ሲያበራ
ለስላሳ እንጀራ በወጥ ተፈትፍታ ቤታችን ስትገባ
ሙቀቱ ሲያጅበን የጠጅ እና የጠላ
ሰው ሆንን እያልን
አቅም በአንድ ቀን እንደተላበስን
ስንጮት ያደርነው ቀኑ እስኪነጋ እንቅልፍ ሳየጥለን
የዛች ቀኗን ማግስት ከአልጋችን ወለን
ላንነሳ ምለን

ያሳለፍነው ሁሉ እውነት ትዝ ይልሻል
አውቃለሁኝ ውዴ አዎን አስታውሰሻል
ከቤታችን መሀል የጣልሽው ትዝታሽ አግኝቶ ነግሮሻል
ድሮስ ያለ ፍቅር አሁን ያለሽ ሁሉ መቼ ይጠቅምሻል
ልብሽ ከኔ ኋሏ ብዙ ጠይቆሻል

ያኔ ግን
ከኔ ጋራ ሳለሽ ደሀ እንኳ ብኖንም
ቤታችንን በግንብ ባናንፅ ባናሽቆጠቁጥም
ሆዳችን ለሁሌ ጠግቦልን ባያድርም
የኔና ያንቺ ህይወት አንድ ቀን ተሳስቶ አማሮን አያውቅም

@MyMessagesss
251 viewsBarkot A, 18:39
Open / Comment
2022-11-27 20:21:39 ስንት ጊዜ ይፈጃል ምን ያህል አመታት
ስንት ሰዉ ይበቃል ትዝታን ለመርሳት

ምን የሚሉት ጂኒ ካንተ ጋር አሰረኝ
የትኛዉ መለኮት በፍቅርህ ጠፈረኝ

በየትኛዉ ጥበብ በየትኛዉ ዘዴ
በየትኛዉ ብልሀት አወከዉ የሆዴን

እንጃ................
ጊዜም መልሱ ጠፋበት መሰለኝ
ካንተ ጋር ይነጉዳል ጥያቄ እያጫረኝ

ስንት ዘመን ቀረኝ
ስንት እድሜ ይተርፈኝ
መቼ ያሳርፈኝ

ትዝታህ ጠቢቡ
ትዝታህ ብልሁ

ትዝታህ ብልጥ ወዳጅ
እያሳሳቀ ነዉ አብሮ ሚያሳቅቀኝ
እያጫወተ ነዉ እድሜዬን የቀጨኝ

ወይ እሱ ይተወኝ ወይ አንተ ደግመህ ና
ትዝታህን ዉሰድ እኔን መልስና።
.........................
.........................

ትዝታ ወልዴ

@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
297 viewsTIZITA21, 17:21
Open / Comment
2022-11-27 18:24:49
ያልተስተዋለ እውነት

በሁሉ ንግስ እለት
የኔ ቢጤ ወድቆ ወጣቱ ሲዘምር ሰዉ ይገረማል
አዛውንት ጠውልገው ካህኑም ወዝ ሲይዝ ያኔ ደርሶ ያዝናል
ሰው ብዙ አስተውሎ ብዙ ይናገራል

እኔ ግን እላለው
ሁሉ ምስጢር አለው

አዳፋ ልብስ አርጎ ለማኙ ቢበዛ የተደረደረው
ማፅደቂያ እንዲሆኑ ተብሎ ነው እንጂ
ፈጣሪ አቶ አይደል ለነሱ ሚሰጠው
ደግሞም በዚያ መሐል አምላክ እንዲህ ነበር ለኛ የተዋረደው
በዚያች ክፉ አለም እንዲያ ሞቼ ነበር
አሁን ግን ተነሳው እልል ይበል ምድር
ይላል በወጣቱ ዝማሬ ላይ አድሮ
የሚያገለግለኝስ መቼ ይቀራል ወድቆ
ሲል አምላክ ይታያል
የካህናቱን ፊት በወዝ ቀለም ስሎ
ከቤተ ክርስቲያኑ ውጭው እና ውስጡ
አንድ አለመሆናቸው መቼ የገባው ኑሮ
ከአውደ ምህረቱ ምስጢር ቢገለጥም
የሰው አይን ክፉ ነው
የአለም ገንዘብ እንጂ እውነት አያሳይም

ታድያ ይህ ያልገባው የዘመኑ ኗሪ
አምላክ ሊያዳላ ነው ብሎ ተናጋሪ
አይኑ በእውነት አስተዋልኩኝ ካለ
ለወቀሳ ሩጦ ምስጢር ካልተማረ
ጥያቄዬ ይሄ ነው
ለሱ ያልታየው እውነት ለምን ለኔ ታየ?

@MyMessagesss
394 viewsBarkot A, 15:24
Open / Comment
2022-11-27 17:02:21
Join

@eyobzmariam
@eyobzmariam
@eyobzmariam
435 viewsEyob Z Mariam, 14:02
Open / Comment
2022-11-24 14:20:19
ትችይበታለሽ
                  By  አቤል
ትችይበታለሽ
እለት ተእለት ላይ ቁንጅና መጨመር
የራቀሽን ሁሉ በትዝታ ማሰር
እንደጋለሞታ ዓይንሽ ማሳመር

ትችይበታለሽ
ከእብደት ገበያ ገላሽን መቸብቸብ
ኪስሽ እንደሞላ ክብርሽን መሰብሰብ
ባለቤት ለማጥመድ ስራሽን ማራቀቅ
ከውርጩ ገላሽ ውስጥ
ሞቃት ቃላት ማፍለቅ

ትችይበታለሽ
ክፉ ክፉን ሁሉ ትኖሪበታለሽ
እኔ በበኩሌ አነድ እውነት ልንገርሽ

ከእለታት አድቀን ልክ እንደ ብርሌ
በዳሌሽ እያሰብሽ ጭንቅላትሽ ጠቦ
ሁሉም ሲጨርስሽ ከጠጅሽ ጠትቶ
የሰከረ ለታ ጥሎ ይሰብርሻል
የቻልሻቸው ሁሉ ያኔ ያቅቱሻል



@MyMessagesss
388 viewsBarkot A, 11:20
Open / Comment
2022-11-23 20:41:08
Join

@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
310 viewsEyob Z Mariam, 17:41
Open / Comment
2022-11-23 07:21:21
አስታውስሻለው

ሰማይ ተገላልጣ የተሳለች እለት
የፀሃይ እጆቿ
ከወንዜ ጎተራ ለደመና ስትሰርቅ
በአይኖቿ ስለት  ምድሬ ሲሰነጠቅ

አስታውስሻለው

ባዶ ሲሆን ምድሬ
ከልቦናዬ ላይ አንቺን እዘራሻለው
ከትዝታሽ ፍሬ የቀን ጎዶሎዬን
ከልቦናዬ ላይ እከምረዋለው
ዛሬ ባላይሽም
ትናንት ላይ ቆሜ እጠይቅሻለው

ከእልፊት ቀናቶች ከአመታት ኋላ
እደምትለይኝ ከእቅፌ ጉያ
ይሆን ወይ አውቀሽው
የትዝታሽ ነፍስስ
ለምን ነው ሲጠየቅ ከቶ ማይመልሰው ?
ከፈገግታሽ ውጪ ፊትሽን ማይገልጠው ?
ሁሌ በሳቅ ዓለም መኖርን ሚመርጠው
ከቶ ለምንድነው ?

ብቻ የኔ ዓለም

የሰማይ መገለጥ የፀሃይ መበርታት
ያለኝን ሲወስደው
ምግባሬ ሲጠፋኝ

አስታውስሻለው

@MyMessagesss
561 viewsBarkot A, 04:21
Open / Comment