Get Mystery Box with random crypto!

Emoji feelings🦋

Logo of telegram channel emoji1619 — Emoji feelings🦋 E
Logo of telegram channel emoji1619 — Emoji feelings🦋
Channel address: @emoji1619
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 811
Description from channel

The channel is about
Feeling 😂😤🤤😭💃❤️💔
photograph¥📷
New musics🎼🎧
Join and share
Ya all much love and respect ❤️🙏🏾🙏🏾
@MilaMilu

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 2

2021-12-07 20:43:42 ​​‍ የጠፋው ሬሳ
ምዕራፍ ሁለት
(ክፍል ሶስት)
፡
...አይኔ ያየውን ማመን አቃተኝ "ባርሳ" ነበረች ድንጋጤና ደስታ በአንድ ላይ ተቀላቀሉብኝ ግን አንዲትም ቃል አልተነፈስኩም እሷም እንደኔ የፊጥኝ ታስራለች ፊቷ ላይ የደም ነጠብጣብ ይታየኛል አይን አይኔን እያየች አንባዋ ቁልቁል ወደ ጆሮዋ ይወርዳል አሁን ያለሁበት ሁኔታ ጥሩ ባይሆንም ግን የተስፋ ጭላንጭል ይታየኛል "በአንበሶች ጉድጓድ የተጣለውን ዳንኤልን ያየ አምላክ አይኑም ክንዱም ለኔ እንደማይዝሉ አምናለሁ" ብዬ ለራሴ አውርቼ ባርሳን እያየሁ ጭንቅላቴን ነቀነኩኝ ፊቴን ከሷ ላይ መልሼ በአቧራ ካደፈው መስታወት አሻግሬ ተመለከትኩ አነስ ምትለዋ ሴት የተለያዩ የህክምና መስጫ መድሃኒቶችን ይዛ አረመኔውን ሰውዬ ካላከምኩህ ብላ ትሟገተዋለች እሱ ደግሞ አለመፈለጉን በምልክት ያሳያታል ምን እንደምትለው ለማወቅ ቢቸግርም ብቻ ብዙ ነገር እያወራችው ነው ከወዲያ ወዲህ እየተንጎራደደ የሆነ ነገር ማብሰልሰል ውስጥ የገባ ይምስላል ግራ እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ የቀኝ እጁን ደግሞ አፉ ላይ አድርጎ ሌባና መሃል ጣቱን ከፍና ዝቅ እያደረገ ይንጎራደዳል ትልቋ ሴትዮ ቁጭ ብላ ትመለከተዋለች ብቻ አንዳች ነገር እያሰበ ነው ትኩረታቸው ወደኛ ሊሆን እንደማይችል በተረዳሁ ጊዜ ወደ ባርሳ ተመለስኩኝ እሷ አሁንም ወደኔ እየተመለከተች ነበር "ባርሳ" ብዬ ጠራሗት እጅግ ዝግ ባለ ድምፅ "ሜርሲ ደና ነሽ ደግሜ አይሻለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከመሞቴ በፊት ስላየሁሽ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ" አለች በእንባ ሳግ በሚቆራረጥና በለዘበ ድምፀት "ሽሽሽሽ እንደዚ አትበይ ባርሳ አይዞሽ ተስፋ አትቁረጪ እስካሁን የቆየሽው ለምክንያት ነው እሱ እኛን ከመግደሉ በፊት ራሳችንን ገለን ልንጠብቀው አይገባም አይዞሽ ባርሳዬ" ስላት ከንፈሯን እየነከሰች እንባዋን ለማቆም መጣር ጀመረች የሷ መበርታት ለኔም አቅም ነው...በድጋሜ አይኔን ወደ ሰዎቹ መለስኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያው አይኔን ወደ ክፍሉ መልሼ የክፍሉን በር ተመለከትኩ ማንም አልመጣም ባርሳን ዝም እንድትል ነግሪያት ለደቂቃዎች ፀጥ አልን ግን አንዳች ነገር አልተከሰተም ለምን እንደው እንጃ ከአይኔ መሰወራቸው ጨንቆኛል "ባርሳ ይሄስ ማነው" ብዬ ጠየኳት አጠገቧ የተኛውን ለማየት ያልተመቸኝን ክፍሉ ውስጥ ያለውን ሌላኛውን ሰው "ባባ ነው" አለችኝ በጣም እንዳዘነች ፊቷ አብዝቶ ይናገራል "ምን ሆኖል በጣም ተጎድቷል እንዴ..." እያልኩኝ ጥያቄዬን ሳልጨርስ ከፍ ባለ ድምፅ "ግደላት" የሚል ድምፅ ሰማሁ አይኔን ወደ መስታወቱ መለስኩኝ ትንሿ ሴትዮ ነበረች ለአረመኔው ሰውዬ ስታወራ የነበረችው ትልቋ ሴት ቁጭ ብላ ትመለከታቸዋለች ወዲያውኑ ሰውዬው እርምጃውን አፍጥኖ በእልህ እኛ ወደነበርንበት ክፍል ሲምዘገዘግ መጣ በሩንም ብርግድ አርጎ ገብቶ ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ ከዛም በራስጌ በኩል ሆኖ የተኛሁበትን አልጋ እየገፋ ወደ ውጪ ይዞኝ ወጣ ባርሳ አይን ላይ ያየሁትን ፍቅርና ፍራቻ ቃል አይገልፅልኝም በትንሿ ሴት መሪነት ወደ ሌላ ክፍል ተወሰድኩኝ ምንም አላልኩኝም ነበር...ክፍሉ ውስጥ ገባሁ እስከዛሬ ያልተመለከትኩት በስለት የተሞላ አስፈሪ እና አሰቃቂ ቦታ ነው ሰውዬው የታሰርኩበትን ቀበቶ መፍታት ጀመረ ልክ እንደጨረሰም አንጠልጥሎ ከአንድ የማይንቀሳቀስ ተለቅ ያለ የብረት ወንበር ላይ አስቀመጠኝ...ወዲያውኑ እጄን ለክንድ ማስቀመጫ ተብሎ ከተሰራበት የወንበሩ ክፍል ጋር አጥብቆ አሰረው ወረድ ብሎም ከመዳፌ ትንሽ ከፍ ብሎ በድጋሜ አሰረኝ እግሬንም እንዲሁ ከወንበሩ ጋር አሰረው አስሮ እንደጨረሰ ከኔ ራቅ ሲል ክፍሉን መመልከት ጀመርኩኝ የተለያዩ የእጅ እና የእግር ጣቶች በየቦታው ተንጠባጥበዋል ጥፍሮችም ጭምር ከተቀመጥኩበት በስተ ቀኝ በኩል ያየሁት ነገር ከምንም በላይ ሰቅጥጦኛል ከአንድ ሰርቢስ ላይ በአንድ ላይ የተቀመጡ የአይን ኳሶች ይታዩኛል በሌላኛው ሰርቢስ ላይ ደግሞ ጆሮና ምላስ ተቀምጧል አጥወለወለኝ አንገሸገሸኝም የማረገውና የምሆነው ጠፋኝ ሆዴ ተላወሰ አስመለሰኝም እዛው በተቀመጥኩበት ራሴ ላይ ለቀኩት ቀና ብዬ ስመለከት ከበላዬ የተለያየ አይነት ቅርፅ ያላቸው መርፌዎች ይታዩኛል ዶክተሮች ለህክምና የሚጠቀሙት መብራትም አለ ሰውዬው ጋውን ለብሶ ወደኔ መጣ የተቀመጥኩበትንም ወንበር ትንሽ ከፍ አድርጎ ወደሗላ አንጋለለው አሁን ካሁን ወደኩኝ ስል ወንበሩ ግን አልወደቀም ነበር አሁን ለመወራጨትም ሆነ ለምንም የማያመች አቀማመጥ ነው ያስቀመጠኝ ዶክተሮች ለቀዶ ጥገና የሚጠቀሙበትን መብራት አበራው አይኔ እሱን መመልከት አልቻለም ነበር ጨፈንኩት ይህ ሰው ሊያሰቃየኝ እንደፈለገ ግልፅ ነው በቀሉን ለመመለስ ይመስላል ከዛም ክፍሉ ውስጥ ይበራ የነበረውን መብራት አጠፋው አይኔን ከፍቼ ግራ ቀኜን ስመለከት አንዳች አልታየኝም የመብራቱ ጉልበት ከፍተኛ ነበር እዛው ባለሁበት አንደበቴን ዘግቼ ፀጥ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ ከሰከንዳት በሗላ ሰውዬው ወደኔ ሲመጣ የእግር ኮቴው ተሰማኝ...ይቀጥላል
54 views17:43
Open / Comment
2021-12-07 07:56:46 ​​‍ የጠፋው ሬሳ
(ምዕራፍ ሁለት)
ክፍል-ሁለት

፡
...አይኑ ደም መስሎ በእጁ በደም የተጨማለቀ ቢላ ይዞ ፊት ለፊቴ ቆሟል ከጀርባው የሚንጠባጠበው ደም ወለሉን አጨቅይቶታል በሱሪው ላይ ሳይቀር ይፈስ ነበር ይህ ሰው በሰው ሀይል የሚሞት አይደለም ብዬ ደመደምኩ ከንፈሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ ቀስ እያልኩ ወደሗላ ለመሸሽ መሞከር ጀመርኩኝ እዛው የቆመበት ቦታ ሆኖ አይኑን እኔ ላይ ተክሎ አንገቱን ወደ ግራ ወደቀኝ እያደረገ ይመለከተኝ ጀመር እንዴት ፈጥኖ እርምጃ እንዳልወሰደብኝ አንገቴንም እንዳልቀላው ግርምት ሆኖብኛል አራቴ እንደተራመድኩ እሱን የጣልኩበት ጠረጴዛ ጋ ደረስኩ ከዚ በሗላ ለመሸሽም አመቺ አይደለምና ዝም ብዬ በፍርሃት ተውጬ ቆምኩኝ ፀጉሬ ተፈቶ በከፊል ፊቴን ሸፍኖታል የድነሸጋጤ ላብ ያረጠበው ጉንጭና ግንባሬ ላይ ተለጥፏል...ቆሞ ሲመለከተኝ የነበረው አረመኔው ሰው አሁን ወደኔ መምጣት ጀምሯል ይዞት የነበረውን ቢላ ወለሉ ላይ ጥሎ የስንት ሰው አንገት የቀላበትን የደም ጥማተኛውን መጥረቢያ አንስቶ ወደኔ መጠጋቱ ቀጠለ አይኔን ጨፍኜ የአምላኬን ስም ጠራሁ "ዛሬም በአርያም ህያው ሆኖ ስለኔ በሚማልደው ስለ ምድር ሀጢያት በጨካኞች በፈሰሰው ደምህ ነፍሴን ከበደልና ከሀጢያት አንፅተህ በመንግስትህ አስበኝ በልጅህ ልጅነትን አግኝቻለሁና የምህረት አባቴን አንተንም ብቻ በድያለሁና ይቅር በለኝ" ብዬ ፀሎቴን አድርሼ አይኔን ገለጥኩኝ መጥረቢያውን በእልህ አጥብቆ ይዞታል አሁን ነፍሴ መጨነቋን ትታ መች ከስጋዬ እንደምትለይ በጉጉት እየጠበቀች ነው ሞት ፊትለፊቴ ቆሞ ውስጤ ግን ሰላም ይሰማኛል...በቀኝ እጁ የያዘውን መጥረቢያ ወደ ግራ እጁ ቀየረው ከዛም ወደኔ ተጠግቶ በከፍተኛ ሀይል በጥፊ መታኝ አወዳደቄን ስላልተቆጣጠርኩት በጭንቅላቴ ከወለሉ ጋር ተላተምኩኝ እዛው ወለሉ ላይ እንዳለው አይኔን ስገልጥ የማየው ምስል ድብዝዝ ያለ ነበር አይኔ እየተስለመለመ ተከደነ የሚሆነው እስከማይታወቀኝ ድረስ ራሴን ሳትኩኝ...ብቻ እግሬን ይዞ ሲጎትተኝ የሆስፒታሉ መብራት እንደለመደው ሲበራና ሲጠፋ በጭላንጭል ይታየኛል ከደቂቃዎች በሗላ ግን ምንም ማየት አልቻልኩም...ረዘም ላለ ደቂቃ ራሴን መሳቴ የታወቀኝ አምልጬ የየወጣሁበት ሁለቱ ሴቶች ያሉበት ክፍል ራሴን ሳገኝ ነው ይመገቡበት ከነበረው ክፍል ግን የተለየ ነበር እንደነቃሁ ዙሪያ ገባዬን ተመለከትኩ ግን ከሰመመን መንቃቴ መሰለኝ ያስተዋልኩት ነገር የለም አሁንም ራሴን እያዞረኝ ነው በእጆቼ ጭንቅላቴን ልደገፍ እጄን ላነሳ ስል አልንቀሳቀስ አለኝ ከጭንቅላቴ ትንሽ ቀና ብዬ ስመለከት እጄ ከወገቤ ጋር ከተኛሁበት የብረት አልጋ ላይ የፊጢኝ ታስሯል...ሰፋ ያለ ጥቁር ቀበቶ ነበር...ሶስቦታ ላይ ታስሬያለሁ ደረቴ ወገቤጋና እግሬ ጋር ነበር አለለመሞቴ የታወቀኝ አሁን ነው በህይወት መኖሬ እጅግ ደንቆኛል አሁን ዙሪያ ገባዬን ተመለከትኩ እንደኔ የታሰሩ ሁለት ሰዎች ይታዩኛል ነገር ግን ማንነታቸውን መለየት አልተቻለኝም አጠገቤ ካለው ወዲያኛው ክፍል ውስጥ በአቧራ ከነተበው መስታወት አሻግሬ ለመመልከት ሞከርኩ ሁለቱ ሴቶች ከዛ አረመኔ ጋር እየተጨቃጨቁ ይመስለኛል ጠፍሮ የያዘኝን ቀበቶ ለመፍታት ክፉኛ ታገልኩኝ እራሴንም እስክጎዳ ድረስ ተፍጨረጨርኩ ተወራጨሁ ግን ከኔ አቅም በላይ የጠነከረ ነበርና ምንም ማረግ አልቻልኩም አቅሜን ሳውቅ ፍርዴን መጠበቅ ጀመርኩ አረመኔውና ሴቶቹ አሁንም ይጨቃጨቃሉ በኔ ነገር እንደሚሆን ውስጤ እየጠረጠረ ነው ልብሱን አውልቆ የጀርባ ቁስሉን አሳያቸው ትንሿ ሴትም ሁለቱን እዛው ያሉበት ቦታ ትታቸው ክፍሉን ለቃ ወጣች ወዴት እንደሆነ ባላውቅም በድንገት እኔ ከታሰርኩበት ክፍል ውስጥ "ሜርሲ" የሚል ድምፅ ተሰማኝ በአቧራ ከነተበው መስታወት ባሻገር የላኩትን አይኔን እና ቀልቤን መለስ አድርጌ አብረውኝ ከታሰሩት ሁለት ሰዎች መሃል ስለመከት...ይቀጥላል
፡
50 views04:56
Open / Comment
2021-12-06 22:06:05 ​​‍ የጠፋው ሬሳ
(ምዕራፍ ሁለት)
ክፍል አንድ

፡
...በዛው ቅፅበት ወደሌላኛው ጠረጴዛ ስር ቦታ በመቀየሬ አላገኘኝም ነበር...አቋቋሙ ጀርባውን ለኔ ሰቶኝ መቆሙን በተረከዙ ተረዳሁ ከተደበኩበትም ጠረጴዛ ስር ቀስ ብዬ ወደሗላ ለመውጣት ሞከርኩ ከሗላዬ ያለው ነገር ቢኖር ግድግዳ እና ወደ ውጪ የሚያስወጣው መንገድ ብቻ ነው እዚ ቦታ ላይ ቆሜ ሰውዬው በሰከንድ ሽርፍራፊ ቢዞር እና ቢያየኝ የምሸሸግበት አንዳች ነገር የለም...እንቅስቃሴየሰን ለማድመጥ በሚመስል መልኩ በፀጥታ ቆሟል እኔም ካለሁበት ቦታ ፀጥ ብዬ ማሰብ ጀመርኩኝ ከዛም ቀስ አልኩና ገልጦ አይቷቻው ወዳለፈቻው ጠረጴዛዎች ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ቦታ ቀየርኩ ተደብቄ የነበረበት ጠረጴዛ የመጨረሻው ነበርና የመያዝ እድሌ ሰፊ ነበር ቦታ ከመቀየሬ ቅፅበት የመጨረሻውን ጠረጴዛ በእግሩ መትቶ ገለበጠው ወዲያውኑ የያዘውን መጥረቢያ ባለ አቅሙ ወለሉ ላይ አላተመው ይመስለኛል እኔን እንዳገኘኝ እርግጠኛ ሆና ለኔ የሰነዘረው ነው...ነገር የያዘኝ አምላክ ሊተወኝ አይደለምና ተርፌያለሁ...በጣም የተበሳጨ ይመስላል የያዘውን መጥረቢያ በድጋሜ ወርውሮ ከግድዳው ጋር አላተመው...ሰውዬው ከሚፈጥረው ሁካታ በቀር ክፍሉ ጸጥ እንዳለ ነው በጣም በፈጠነ እርምጃ ወደነበረበት ከክፍሉ ሌላኛው ቦታ ሄደ በዚህ ጊዜ ከተሸሸኩበት ስፍራ ወጥቼ ራሴን ሸሽጌ ዙሪያ ገባዬን እየቃኘሁ የያዝኩትን ስለት አሰናድቼ እሱን መከተል ጀመርኩ...አሁንም ቢሆን በላስቲክ የተንጠለጠሉትን መለየት ለኔ ከባድ ነው ድንገት የሰማሁት ድምፅ እርምጃዬን ትቼ እንድቆም አደረገኝ ያ አረመኔ ሰውዬ ያንን የዋይታና የሰቆቃ ጩኸት ድምፅ ከፍቷል ይህን ድምፅ ስሰማ አብዝቼ እረበሻለሁ ጣቶቼ እርስ በእርስ መጨባበጥ አቅቷቸው ይብረከረካሉ ይሄ ድምፅ ድምፅ ብቻ አይደለም አንዳች የድግምት ሃይል አለበት ዋይታው በድንገት ፀጥ አለ ወዲያውኑ የተብረከረኩ ጣቶቼ ፀኑ አብዝተውም ጨበጡ ይህ ዋይታ ተሰምቶ ፀጥ ሲል ድምፅ ሲሰማ የሰውዬውን ፍጥነት አውቀዋለሁ ስለዚም ያለ አንዳች እንቅስቃሴ ባለሁበት ቆምኩኝ ዋይታው ጀመረ ወዲያውኑ አፍንጫዬን በሸፈንኩበት ከፊሉ ጨርቅ ወደ ጆሮዬ የሚመጣውን የዋይታ ድምፅ ላለመስማት ጆሮዬ ውስጥ ጠቀጠኩኝ ከዛም ቀጥ ብዬ ወደሰውዬው አመራሁ ምን እንደሆኑ ያላስተዋልኳቸው የላስቲክ እስሮች ብዛታቸው ወደ ሰላሳ ይጠጋል ወለሉ በእግሬ በርከክ ብዬ አንዱን የፊቴን ክፍል ከወለሉ ጋር አዋድጄ ሰውዬው የቆመበትን ቦታ አየሁት ጀርባውን ሰቶኝ ነው የቆመው በመሃላችን ያለው ልዩነት በጣም ጠቧል ልቤ ከመፍራት ይልቅ የያዝኩትን ቢላ እንድሰነቅርበት ይገፋኛል አንድ ነፍሴ በጥፋም አይገደኝ እያለች ታበረታኛለች ክንዴ ከጎልያድ ክንድ ይልቅ ጉልበታም ነኝ ይለኛል ብቻ አንዳች ሀይል ወደሰውዬው ገፋኝ ያንን አረመኔ ለማጥፋት እግሬ ተንደረደረ ጥርስ እና ጥርሴ በእልህ ተጋጩ የማላውቀው የማልቆጣጠረው ድፍረት ወደፊት ነዳኝ ብዙ ሰው ነፃ እንደሚያወጣ ለሀገሩ ሟች ንጉስ እንደሆንኩም ተሰማኝ አሁን ተጠንቅቄ ተጉዤ ከጀርባው ቆሚያለሁ ቢላውን ጎኔ ላይ ሻጥ አድርጌ አጠገቤ የነበረውን የብረት መዶሻ አንስቼ መሰንዘር ነበር የቀረኝ አደረኩት ጭንቅላቱ ላይ ባለ በሌለ ሃይሌ አሳረፍኩበት ነገር ግን አልወደቀም ነበር ይልቁኑ ዞሮ ሊያየኝ ዳዳው በዚህ ጊዜ ከጎኔ የሻጥኩትን ቢላ አውጥቼ ከማጅራቱ ትንሽ ዝቅ ብሎ ሰነቀርኩበት ከፊቱ የነበረው ጠረጴዛ ላይ በደረቱ ወደቀ ቢላውን ነቅዬ ደጋግሜ ወጋሁት ወጋጋሁት ጨከጨኩት የማቃሰት ድምፅ ያወጣል እንጂ አይጮህም ነበር ነገር ግን ቢላው አላረካኝም የስንቱን ህይወት የቀጠፈበት ያ ነፍሰ በላ መጥረቢያ ብልጭ አለብኝ ቀጥ ብዬም ተወርውሮ ወደ ወደቀበት ስፍራ አመራሁ አነሳሁት እሱ ያረገው እንደነበር መሬት ለመሬት እየጎተትኩ ያንን ሰቅጣጭ ድምፅ እያሰማሁ አንገቱን ቆርጬ ስጋውን ለአሞራ ልመግብ ተዘጋጅቻለሁ መጥረቢያውን ከፍ አድርጌ ትከሻዬ ላይ አስቀምጬ ነፍሱን ከስጋው ልለያት ጠረጴዛው ጋ ስደርስ የማየውን ማመን አቃተኝ ጠረጴዛና ወለሉ በደም ከመጨማለቅ ውጪ ሌላ አንዳች ነገር የለም ሰውዬው በቦታው ላይ አልነበረም በጣም ደነገጥኩኝ አንገቴን ሳላንቀሳቅስ አይኔ እስከቻለው አካባቢዬን ተመለከትኩ እሱ ተኝቶ ከነበረበት ጠረጴዛ አካባቢ የደም ነጥብጣብ አለ የነጠብጣቡ አቅጣጫ ርቆ እንዳልሄዴ ያሳያል ጠረጴዛው ላይ ቢላውም የለም "በቀሉ ይቅርብኝ ራሴን ላድን' ብዬ ከዛ ክፉና አረመኔያዊ ተግባር ከሚፈፀምበት መንደር ተስፋ ቆርጬ ነፍሴን ለማትረፍ እና ለመሸሽ ወስኜ መጥረቢያውን ጥዬ ስዞር...ይቀጥላል

@Emoji1619
58 views19:06
Open / Comment
2021-12-04 21:13:03 ​​ የጠፋው ሬሳ
ክፍል ሀያ-አራት
፡
...ላይ ሊያሳርፈው ሲል ራሴን ከሆስፒታሉ ጥግ ላይ ተኮራምቼ ሳላስበው ይዞኝ ከተመመው የሰመመን እንቅልፍ ጉዞ ተመልሼ ከእንቅልፌ ነቃሁ ደህና መሆኔን አላመንኩም ራሴንም ጠርጥሬ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ደጋግሜ ሰውነቴን እየደባበስኩ ደህንነቴን አረጋገጥኩ...እኔ ብዙ ጊዜ ነፍሴን ያስጨነቃትን ነገር ነው በህልሜ ማየው...እየደባበስኩ ደህንነቴን እየተመለከትኩ ሳለ አይኔ የቅድስቴ በድን ላይ አረፈ እዛው እንደተንጋለለ ነበር ማንም አልነካውም ቀስ ብዬ ተጠጋሁ በእጄም እጇን ነካሁት ገላዋ ከቀረዶ በልጦ ቀዝቅዟል የሷን በድን ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩኝ ሳለ በድንገት የእግር ኮቴ ሰማሁ ወዲያውኑ አጠገቤ ካለው ክፍል ገብቼ ራሴን ከሚመጣው ሰው ሸሸኩኝ እየመጣ የነበረውም ሰው ያ አረመኔ ጨካኝ ገዳይ ነበር በድኑን ሊወስድ እንደመጣ ገመትኩኝ ልክም ነበርኩ ልክ በድኑ ጋ ሲደርስ በርከክ አለና እላዯ ላይ የደረቀውን ደም በጣቱ ፈቅፍቆ ወደ አፉ ሰደደው ቀምሶትም በደም የበለዘ ጥርሱን ፈገግ አደረገ...ከዛም ፀጉሯን ይዞ እያንፋቀቀ መሬት ላይ እየጎተተ ይዟት መሄድ ጀመረ እኔ ካለሁበት ክፍል ትንሽ ራቅ ሲል ርቀቴን ጠብቄ መከተል ጀመርኩኝ በድን ሳይና በደም ስጨማለቅ የመጀመሪያዬ ነው ነገር ግን ከዚህ በፊት ይህን ሁሉ ክስተት እንደተመለከተ ሰው ልቤ ደንዳና ሆኗል...ብቻ አንድ ነገር መሆን አለበት ከዚህ አካባቢ እነዛን ሶስት አረመኔዎች ገድዬ እወጣለሁ ወይ ደግሞ እንደጓደኞቼ እዚሁ እቀበራለሁ ስጋዬንም ይቀራመቱታል እንጂ መቼም ቢሆን አልሸሽም...ትንሽ እንደተጓዘም በህልሜ ወዳየሁት መበለቻ ክፍል ይዟት ገባ ይሄን ሰው ማጥቃት ካለብኝ እንደዚህ ክፍል ሊያመቸኝ የሚችል የለምና እራሴን በጥንቃቄ አዘጋጀሁ ልክ ክፍሉ በር ጋር ስደርስ አንገቴን ወደ ውስጥ አስግጌ ተመለከትኩ ክፍሉ ፀጥ ረጭ ብሏል አንድም ሰው አልነበረም የቅድስቴም በድን የለም ወደ ክፍሉም ዘለቅ ብዬ ገባሁ እስካሁን ያላየሁት የተለየ በር ተከፍቷል ወደሗላም ተመልሼ የሚከተለኝ ሰው አለመኖሩን አረጋገጥኩ በተከፈተው በርም ቀስ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ነገር እጅግ የሚሰነፍጥ ከባድ የስጋ ሽታ ክፍሉ ላይ ሰፎበታል ሽታውን መቋቋም ስላልቻልኩ ወዲያውኑ ተመለስኩኝ ከዛም አንድ ሀሳብ አሰብኩኝ ከውስጥ የለበስኩን ቲሸርት ቀድጄ አፍንጫዬንና አፌን ሸፈንኩበት ወደ ውስጥም አመራሁ አልፎ አልፎ ቢሆን ሽታው ወደ ውስጤ ይገባል ነገር ግን ከመጀመሪያው የተሻለ ነበር ይህ ክፍል የተለየ ክፍል ነው እንደሌሎቹ ያን ያህል ብርሃን የለውም ጨለም ያለ ነው...አሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ውስጥ ገብቻለሁ ነገር ግን ከፊት ለፊቴ ከሚታየኝ የላስቲክ መጋረጃ በቀር አንዳች ነገር አይታይም ወደ ላስቲኩም እርምጃዬን ጀመርኩ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ነው እንቅስቃሴዬን የማረገው ከቅድሙ ይልቅ ሽታው እየበረታ መጣ ቢሆንም ግን ገዳይን ለመግደል ጉዞ ላይ ነኝ ላስቲኩን ገለጥ አድርጌ ወደ ውስጥ ገባሁ አይኔም ቀድሞ ያረፈው ወደላይ ከተንጠለጠሉት በላስቲክ የታሰሩ ነገሮች ላይ ነበር ምን እንደሆኑ ግን መለየት አልቻልኩም በእያንዳንዱ በተሰቀሉት ነገሮች በታች ለሁላቸውም ጠረጴዛ አለ መስመራቸውን ጠብቀው ነበር በረድፍ የተደረደሩት እየተጓዝኩም ወደ መሃላቸው ተጠጋሁ ወደ አንዱም የታሰረ ላስቲክ ቀረብ ብዬ ስመለከት ውስጡ ነጫጭ የስጋ ትሎች ይርመሰመሳሉ ይሄን ባየው ጊዜ በድንጋጤ ወደሗላ ስመለስ ከአንዱ የላስቲክ እስር ጋር ተጋጨሁ ሲንቀሳቀስም ድምፅ አወጣ በሁለት እጆቼም ይዤ ለማቆም ሞከርኩኝ ነገር ግን ያ ክፉ ሰው ድምፁ ወደተሰማበት ቦታ ሲመጣ ኮቴው ተሰማኝ ይሄንንም ባረጋገጥኩ ጊዜ ከአንዱ ጠረጴዛ ስር ተደበኩኝ የሆነ ስለት መሬት ላይ እየጎተተ እንዳለ ከሚሰማው የሚሰቀጥጥ ድምፅ ተረዳሁ እኔም የያዝኩን ስል ቢላ አሰናድቼ መጠበቄን ጀመርኩ ጠረጴዛዎቹ ረዘም ባለ ላስቲክ ስለተሸፈኑ ከስር ያለውን ነገር ካልተገለጠ በቀር በቀላሉ አያሳዩም ይሄ ነገር ትንሽም ቢሆን ሰላም ሰቶኛል መሬት ላይ ሲጎተት የነበረው የስለት ድምፅ አሁን ላይ ወደ ጠረጴዛዎቹ ላይ የተቀየረ ይመስላል...ይህንንም ከምሰማው ድምፀሸ ለይቻለሁ...እየቀረበኝ እንደሆነ ኮቴው ይነግረኛል ውስጤ ግን ቅንጣት ፍራቻ አልነበረበትም ነበር እኔ ያለሁበት ጠረጴዛ እጅግ ተቃርቧል ልቤ ባይፈራም የልብ ምቴ ግን አብዝቶ ጨምሯል በእልህ ከንፈሬን ነክሼ ሁኔታውን መጠባበቅ ጀምሬያለሁ ለሚመጣው ነገር ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነኝ መዳፌ ጠንከር ብሎ ቢላውን ጨብጧል በቀል ውስጤ እንደ ዘይት ይፈላል ቁጭት አንጀቴን ይበላኛል ምሬት ውስጤ ይርመሰመሳል ነገር ግን ሳላስበው እያላበኝ ነበር ከጥቂት እርምጃዎች በሗላ ካለሁበት እና ከተደበኩበት ሰፍራ ደርሷል እኔ ጋር ሲደርስም ቀጥ ብሎ ቆመ ጊዜ ሳያባክን ወዲያውኑ አጎንብሶ ላሲቲኩን ሲገልጠው...ይቀጥላል

እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን

የጠፋው ሬሳ ምዕራፍ አንድ በዚህ መልኩ ተጠናቋል ምዕራፍ ሁለትንም በቅርቡ እንጀምራለን



Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን
70 views18:13
Open / Comment
2021-12-03 17:57:26 ​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል ሀያ-ሶስት

...የማየውን ማመን አቃተኝ ኮቴውን ወይም ድምፁን አልሰማሁኝም ግን አጠገባችን ተገኝቷል ቅድስቴ እንዳለችውም ይህ ሰው በአንድ መናፍስታዊ አገዛዝ ስር እንዳለ ውስጤ አረጋገጠልኝ...ሰውዬውን ከጀርባዋ እንደተመለከትኩት የቅድስቴ ስም ጠርቼ ወደራሴ ጎተትኳት ተያይዘንም እሷ ከላይ እኔ ከታች ሆኜ ወለሉ ላይ ወደቅን አንገቴን ከፍ አድርጌ ስመለከት ሰውዬው የለም ትቶን እንደሄደ አስቤ ደስ አለኝ "አይዞሽ ቅድስቴ ተርፈናል ሌሎቹን ፈልገን ከዚ እንሄዳሀን" አልኳት ነገር ግን መልስ አልሰጠችኝም...አይርገበገብም እንጂ አይኖ ተከፍቷል በጣም ግራ ተጋባሁ ሰውዬው ምንም ሲያረግ አልተመለከትኩትም ነበር እና ምን ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል...ደግሜ ደጋግሜ ስሟን ጠራሁት ግን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠችኝም ነበር ፊቷ ላይ የመጎዳት ነገር አይነበብበትም ቀስ አድርጌ ከላዬ ላይ አንስቼ ወገቧን ደገፍ አድርጌ በጀርባዋ ሳስተኛት የዛገ የሚመስል ስለታማ ብረት በጉሮሮዋ ወጣ ከድንጋጤዬ የተነሳ እጅግ በብዙ ድምፅ ጮውኩኝ ደጋገምኩት አይኔንም ከሷ ላይ መልሼ በዳዴ ከአጠገቧ ሸሸሁ አንዱ ጥግ ላይ ሆኜ ተኮራምቼም አነባሁኝ ያ አረመኔ ሰውዬ እኔን ለምን እንደማይገድለኝ ትንግርት ሆኖብኛል... ቅድስቴ ወለሉ ላይ እንደተንጋለለች ነው እኔ ደግሞ እሷን ማየት ፈርቼ ከአንዱ ጥግ ላይ ነኝ...አሁን መቋቋም የማልችለው ገደብ ያጣ ቁጣ ውስጤ መንፎልፎል ጀመረ ግን ደግሞ የቅድስቴን ሞት ሳይ ጓደኛዬን ያላተረፈ እልህ ብዬም ራሴን አኮማሽሻለሁ...የተቀመጥኩበት ሆኜ ራሴን ከግድግዳው እያጋጨሁ ምንም ሳላወራ መራር እንባዬን አፈሰስኩ አለቀስኩ የእንባ ከረጢቴም እስኪደርቅ ድረስ...ክፉኛ ራስ ምታትም ስቃዬን አበዛው...ሳላስበው እዛው ከተቀመጥኩበት ስፍራ እንቅልፍ አሸለበኝ በስቃይ የዛለ ሰውነቴ ከዚ በላይ የመቆየት አቅም አልነበረውም ነበር...ይመስለኛል ለሰዓታት ያህል ቁጭ ባልኩበት ስፍራ ተኝቻለሁ...እንደነቃሁም እንደምንም ብዬ ወደ ቅድስቴ በድን ዞር አልኩኝ ነገር ግን ቅድስቴ አልነበረችም ነበር ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ አይኔንም ጠራርጌ በድጋሜ ተመለከትኩ ቅድስቴ ፈፅሞ የለችም...እንደ ፈጣሪ ቃል የጓደኞቼ በድን ከአፈር ሳይዋሃድ በሰው አውሬ ተበልቶ አለቀ ይሄ ምነኛ የሚያም እና የማይሽር ቁስል እንደሆነ እኔና እኔ ነኝ የምናውቀው...ቀስ ብዬ በድኗ ወደነበረበት ወለል ተጠጋሁ መሬት ላይ እየጎተተ እንደወሰዳት የደም ምልክቱ ያሳያል የጣልኩትን ቢላ አንስቼ ደሙን እየተከተልኩ ቀስ ባለ እርምጃ መሄድ ጀመርኩኝ እነሱ ወዳሉበት ክፍል በሚወስደው በር በኩል ይጠቁማል የደም ምልክቱ እኔም ያለ አንዳች ፍራቻ በተረጋጋ እና ማስተዋል በሞላበት እርምጃ መጠጋቴን ቀጠልኩ..."ከሞት በላይ ምንም ሊመጣ አይችልም ቀኔ ከሆነ ትንታም ይገለኛል አይደለም ይሄ ክፉ አረመኔ ሰው" እያልኩኝ ውስጤን ለጭካኔ እያነሳሳሁ እና እያጀገንኩ ገዳይን ለመግደል በተጠንቀቅ ራሴን አዘጋጀሁ...የደሙ ምልክት ብዙ ጋውኖች ወደተሰቀሉበት ክፍል ይጠቁማል የሮቤል በድን ወደነበረበት...አሁን በጣም ድንጋጤዬ መጣ እነዛ ንፋስ የሚቆርጡ የሚመስሉ ስለቶች የቅድስቴ ገላ ላይ ሊያርፉ እንደሆነ ገብቶኛል ይሄኔ እርምጃዬን ጨመር አድርጌ ግን ደግሞ ጥንቃቄ ሳይለየኝ ወደ በሩ ተቀረብኩኝ አልተዘጋም ነበር ገርበብ እንዳለ ነው አንገቴን ወደ ውስጥ ቀስ ብዬ ላኩት ሰውዬው ለሮቤል ሲያረግ የነበረውን ሁሉ አድርጓል ከጋወን እስከ ጓንት ድረስ ትጥቁን አማልቷል የቀረው ቢኖር ያ የዋይታ እና የሰቆቃ ነገር ግን እሱን የሚያስደስተው እና ሰላም የሚሰጠው ድምፅ ብቻ ቀርቷል እንደጠበኩትም ያንን የሚሰቀጥጥ የስቃይ ዋይታ ከፈተው አሁን በይበልጥ ከፊል ሰውነቴን ወደ ውስጥ አስገብቼ ሁኔታውን መከታተል ጀመርኩ ለሮቤል እንዳረገው ሁሉ ለቅድስቴም ዘይት ጥዷል እያፏጨ እና እየተንቀሳቀሰ ስለቶቹን መመራረጥ ጀመረ በድንገት ዋይታው ፀጥ አለ ሰውዬውም ከእንቅስቃሴው ተገታ ባለበትም ቦላ በአርምሞ ቆመ እኔም አመሉን ስለማውቀው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረኩም ነበር ትንሽ እንደቆየ ጩኸቱ ጀመረ በዚ ጊዜ የሰውነቴ ክብደት በበሩ ቀድሞ በገባው እግሬ ላይ ስለበር ድካም ተሰማኝና ራሴን ለማሳረፍ ወደነበርኩበት ቦታ ልመለስ ስል አነስ የምትለዋ ሴትዮ ከፊት ለፊቴ ነጭ ጋወን ለብሳ የብረት መዶሻ ይዛ ቆማለች በጣም ደነገጥኩኝ ደነዘዝኩኝም ሴትየዋ ጊዜ አልፈጀችም ነበር ወዲያውኑ በመዶሻው ግንባሬን ስትለኝ በሩን በርግጄ ወለሉ ላይ ተዘረጋሁ እይየተስለመለመ ወደላይ ስመለከት አረመኔው ሰውዬ መጥረቢያውን ከፍ አረጎ መሀል ጭንቅላቴ.............

......ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ አራት እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ


Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን
72 views14:57
Open / Comment
2021-12-03 17:57:05 ​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል ሀያ-ሁለት

፡
...ብልጭ ድርግም በሚለው የሆስፒታሉ መብራት የሆነ ሰው ይታየኛል አሁን ፊቴን አኮሳትሬ ግንባሬን ጨምድጄ እልሄን ሰብስቤ ወደፊት መጠጋቴን ጀመርኩ የጓደኞቼን ደም ለመበቀል ከመፈለጌ የተነሳ ወደኔ እንኳን እስኪመጣ አልጠበኩትም ራሴ ተጠጋሁት የያዝኩትን ቢላ ዘቅዝቄ እጀታውን በማርያም ጣቴ ጋር አድርጌ ስለቱን ወደ ክርኔ አስደግፌ በለዘበ አረማመድ መጠጋቴ ቀጠልኩ ነገር ከኔ ተቃራኒ ጥግ ላይ ያለው ሰው አይንቀሳቀስም ለምን እንደሆነ ባላውቅም እኔ ግን በድፍረት እና በንዴት እየተጠጋሁት ነው...የሆስፒታሉ መብራት ብልጭ ድርግሙን ትቶ ቀጥ ብሎ በራ ጥግ የተመለከትኩት ነገር አይደለም ሊገለኝ ይልቁና በፍርሃት ተሸማቆ ራሱን አሳንሶ ተኮራምቶ ፊቱን ሸሽጎ ተቀምጧል..."እንደ ወንድ ተነስተህ ና እንደ ፈሪ አትሸፋፈን እንደ ገዳይ ፊት ለፊት ውጣ አትርመጥመጥ" አልኩት ንግግሬን በእርጋት ጀምሬ ንዴቴ ሲብስ እየጮውኩኝ ነገር ግን አሁንም ዝምታ ነበር መልሱ...ወደሗላ አድርጌ የነበረውን ስለት ወደ ፊት መልሼ ደረቱ ላይ ለመሰንቀር ወደ ተቀመጠበት ስፍራ ኮቴ ቢስ በሆነ እርምጃ ተጠጋሁት ነገር ግን ከሗላይ በሰከንድ ሽርፍራፊ እጅግ ፈጣን ሰው አለፈ...ከመቅፅበትም ፊቴን መልሼ የያዝኩን ስለታማ ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን አንዳች ያጠቃሁት ፍጡር የለም ከአጠገቤ ያለው የሆስፒታሉ ክፍል አሁን እንደተከፈተ ያስታውቃል እንቅስቃሴውን እንኳን አላቆመም...በጥሞና ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁኝ ግን ማንም አልነበረም ከቆምኩበት ሁለት ከፍል አለፍ ብሎ የሚገኘው ሶስተኛው ክፍል ሲከፈት ተሰማኝ ሆስፒታሉ ፀጥ ብሎ ስለነበር ሲከፈት ያለው የበር ድምፅ ይሰማል "ሲጢጥ" ሲል....አሁን መሃል ላይ ገብቻለሁ ከፊትለፊት የሆነ ሰው አለ ከሗላ ደግሞ ተኮራምቶ የተቀመጠው ፡...ዞር ብዬ ጀርባዬን ቃኘው ማንም ያ ሰው አሁንም ኩርምት እንዳለ ነው የመግደልም አቅም ያለው አልመሰለኝም ልክ እንደኔና ጓደኞቼ ጥቃት የደረሰበት ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ ይሄን ሁላ ማሰላስለው ሲከፈት ድምፁ ወደተሰማኝ በር እያመራሁ በአይኖቼም መለስ ብዬ ጀርባዬን እየተመለከትኩ ነው አሁን ክፍሉጋ ልደርስ አንድ እርምጃ ያህል ቀርቶኛል የቀረኝንም እርምጃ እግሬን አንስቼ ልራመድ ስል መብራቱ ድርግም ብሎ ጠፋ ከመቅፅበትም አጠገቤ ያለው ግድግዳ ላይ ተደግፌ ቁልቁል ወርጄ ድምፄን አጥፍቼ ፀጥ አልኩኝ በጨለማው መሀል የትልቅ ከስክስ ጫማ ድምፅ ተሰማኝ ሰፋ ያለ የእግር አጣጣል እንዳለው ከምሰማው የእግር ኮቴ ተረዳሁ ውስስጤ ፍርሃት የሚባል የለም በቀል እንጂ ነገር ግን ጨለማወው ነገሮችን በብዙ እያከበደብኝ ነው "ቢሆንም ግን ገድዬው ወይ ገሎኝ ከዚ አረመኔ ነፍሰ በላ ጋር እለያያለሁ" አልኩኝ ለራሴ እርምጃው እየቀረበኝ ነው የያዝኩትን ስለት በተጠንቀቅ አዘጋጅቼ እየጠበኩ ነው...በድንገት መብራቱ ፏ ብሎ በራ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነስቼ የእግር ዱካው ይሰማኝ ወደነበረው ስፍራ የያዝኩትን ስለታም ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያውኑ ጎላና ጎርነን ባለ ድምፅ ልብን የሚያርድ ሳቅ ተሰማ ባለሁበት ተንበረከኩ እንደሚዲህ ህፃን ቀዳዴ እየሄድኩ ግራና ቀኜን ተመለከትኩ ነገር ግን ምንም የለም ነበር ሳቁ ሳቅ ብቻ አይደለም አንዳች ሃይል አለው ቁጣዬን ነጠቀኝ እልሄን በፍርሃት ለወጠው በቀሌን የሽሽት አደረገው በጣም ተደነኩኝ አብዝቶም ገረመኝ ካልመጣ ስል የነበርኩት ቤት ልውጣ ብዬ ተጨነኩኝ ጣቶቼ ቢላውን መጨበጥ እስኪያቅታቸው ተብረከረኩ በዛ የውድቅት ምሽት ከየት መጡ የማይባሉ ቁራዎች ሆስፒታሉ ውስጥ ተመሙ ራሳቸውን ከግድግዳ ጋር እያጋጩ ኮሪደሩን በደም አጨቀዩት አብዝተውም ይጮሁ ነበር መሃል ላይ ሆኜ በግንባሬ ከወለሉ ተዋድጄ ሞቴን መጠበቅ ጀመርኩኝ አቀርቅሬ ባለሁበት ጊዜ አንገቴ ላይ ያለው የብር ሃብል ወለሉ ላይ ተመለከትኩት ግንባሬንም ቀና አድርጌ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆነው አንድ አምላክ የተሰቀለበት መስቀል ነበር መስቀሉ ላይም የኔ እና የዓለሙ አዳኝ እንዳላቀረቅር አቀርቅሮ አየሁት ህመሜን ታሞልኝ ተቸንክሮ አየሁት....እሱን ባየው ጊዜ ንዴቴ እና እልሄ መታደስ ጀመረ ስልቱን ጨብጬ በሁለት እግሬ ቆምኩኝ ነገር ግን ሆስፒታሉ በደም ጨቅይቶ የነበረው በቁራ ድምፅ የታወከው ስነሳ ግን ሰላም ነበር...መጀመሪያ ጥግ ላይ ካየሁት ሰው በቀር በድጋሜ ማንም አልነበረም ወደዛም ሰው ቀጥ ብዬ ተጠጋሁ ስደርስም "እባክህ አትግደለኝ እባክህ" እያለች ሳግ እየተናነቃት የምትማፀን ሴት ነበረች "አይዞሽ አልጎዳሽም ተነሺ" ስላት "ሜርሲዬ" ብላ አቀፈችኝ የመየውን ማመን አልቻልኩም ሞቱ ካልኳቸው ጓደኞቼ መሃል ቄድስቴ ነች "ቅድስቴ አንቺ ነሽ እንዴ ተጎዳሽ የሆንሽው ነገር አለ?" ብዬ ጠየኳት ሰውነቷን እየደባበስኩ "ምንም አልሆንኩም ባባን ወስዶታል ባርሳ ደሞ የት እንዳለች አላውቅም" አለችኝ "አታልቅሺ እናገኛቸዋለን" ብዬ አባበልኳትና እጇን ይዤ ወደ መውጫው ሳመራ "ሜርሲዬ ይሄ ለመገለን የሚፈልገው ሰው ትዝ ካለሽ ከወር በፊት ጠፋ የተባለ ሬሳ ነበር ሰዎችም እንደሚሉትም ሞቶ የተነሳ የመናፍስት እጅ ያለበት...እያለች እየነገረችኝ ሳለ ዞር ብዬ የምትለው ገርሞኝ እንግዳ ሆኖብኝም ልሰማ ስቆም ሰውዬው ከየት መጣ ሳይባል የእግሩ ዱካ ሳይሰማ አንዳችም ነገር ሳይታወቀን በንፋስ ፍጥነት ከቅድስታ ጀርባ ቆሟል..............

..........ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ ሶስት እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ አድርሱን


Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን
56 views14:57
Open / Comment
2021-12-03 17:56:39 ​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል ሀያአንድ
፡
...ከፊት ለፊቴ ድንቅር ብላ ቆማለች አፌን በእጆቼ አንስቼ አይኔ እስከተከፈተልኝ ድረስ አፈጠጥኩኝ እሷ ግን ምንም አይነት ነገር ሳታወራ ረጋ ብላ በአትኩሮት ተመለከተችኝ ቁመቷ አጠር ያለ ነበር ከመደንገጤ የተነሳ ቃሎቼ መክነው አንደበቴም ተሳስሮ ነበር ትንሽ ወደ ቀልቤ ስመለስ አይኔን ወደታች ልኬ በእጇ አንዳች ነገር ከያዘች ብዬ ተመለከትኩኝ ነገር ግን ምንም አልያዘችም ነበር በትንሹም ቢሆን ራሴን ማረጋጋት ችያለሁ ቀስ እያለች ወደኔ መጠጋት ጀመረች ቤቱ ያለው አንድ መውጫ እሱንም ደግሞ እሷ ዘግታዋለች ወደሗላ እንዳልሸሽ ጭራሽ ወደ ገዳዩ ነው ምገባው በዚ ግዜ አንዳች ነገር መወሰን እንዳለብኝ ተረዳሁ...እኔም ቀስ እያልኩ እጆቼን ጨብጬ ውስጤን አጠንክሬ ወደሷ መጠጋት ጀመርኩ መሞት እንደው የማይቀር ነው ቀኔ ከሆነ ልሙት ብዬ ራሴን አጀገንኩኝ በጣም ተቀራረብን ሳይቀደሙ መቅደም ነው ራሴን አዘጋጅቻለሁ "እሷ ቀድማ ከመታችኝ ነፍሴን እዚሁ ነው ምነጠቀው ስለዚህ መወሰን አለብኝ" ብዬ ለራሴ ነገርኩት በመሃላችን የአንድ እርምጃ ልዩነት እንደቀረን አሽቀንጥሬ ገፈተርኳት አጠገባችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ሄዳ ተዘረጋች እላዩ ላይ ያለውንም ዕቃ ናደችው ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ የሁካታ ድምፅ ተሰማ ወዲያውኑ ከዛ ቤት በፍጥነት ወጣሁ ገፍትሬ የጣልኳት ሴትዮ "አንድዬ" ብላ ስትጣራ ሰማሁት አሁንም ከዛ ቦታ ለመውጣት የጀመርኩትን ሩጫ አላቆምኩም ዞር ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ላይ ቆሞ እየተመለከተኝ ነው ልክ ደረጃው ጋ ስደርስ በእጁ የያዘውን ወደኔ ወረወረው አንድ ደረጃ ከፍ ብል ኖሮ መጥረቢያው የሗላ ጭንቅላቴ ላይ ይሰነቀር ነበር...ነገር ግን ደረጃውን አልወጣሁትም ነበር "ትረፊ ያላት ነፍስ" አልኩኝ ለራሴ መጥረቢያው እንዳልመታኝ ሲመለከት ሴትየዋን ስጥላት ከወደቀው ዕቃ መሃል ብራማ አብረቅራቂ ቢላዋ ይዞ ወደኔ መገስገስ ጀመረ እኔም ለማምለጥ መሮጤን ቀጠልኩ ደረጃው እንደጨረስኩ ወደ ደረጃው የሚያስገባውን በር ዘጋሁት ነገር ግን ሰውዬው ለመክፈት ቅንጣት አላዳገተውም ነበር መጥረቢያውንም ቢላውንም ይዞ እየተከተለኝ ነው በጣም ፈጣን ነው ሲሮጥ አሁን ኮሪደሩ ላይ ወጥቻለው ከሆስፒታሉ ወጥቼ ወደ ውጪ ልሩጥ ወይስ ወዴት ልደበቅ አልኩና ትንሽ አመነታሁ ከዛም ሌሎቹን የታካሚ መኝታ ክፍሎችን ነበር ዝም ብዬ ከፈትኳቸው ከዛም እኔ ሆስፒታሉ አጠገብ ወዳለው ጫካ ውስጥ ተደበኩኝ የነበርኩበት ቦታ የሆስፒታሉን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ነገር ግን ሰውዬውን አላየሁትም ነበር በጣም ተደናገጥኩኝ ይህ አወዛጋቢ ሰውዬ ወዴት እንደተሰወረ አስደነገጠኝ ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁኝ ሰውዬው አሁንም የለም ነገር ግን ከሆስፒታሉ ውስጥ የጫጫታ እና የዋይታ ድምፅ ተሰማኝ ይህ ሰው ጓደኞቼን አንዳች ነገር እንዳደረጋቸው ጠረጠርኩ ከዛም ካለሁበት ቦታ ስምዘገዘግ ወደ ውስጥ ገባሁ ሁሉንም ክፍሎች ተመለከትኩኝ ማንም አልነበረም ጓደኞቼን ትቼ ከሄድኩበት ስፍራ አጣሗቸው ተንበርክኬም አፌን ከፍቼ ጮውኩኝ የቀረሁት እኔ ብቻ ኀኝ "ወንድ ከሆንክ ና ውጣ እንደ ድመት ተደብቀህ አታድን" ብዬ ጮውኩኝ ደጋግሜም አልኩት ያገኘሁትን ዕቃ ሁሉ ገለባበጥኩኝ ነገር ግን እሱ ዝርም አላለም ነበር ግድግዳውን ታክኬ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ ከዛም ወዲያውኑ ማልቀሴን አቆምኩኝ ከተቀመጥኩበትም ተነሳሁ ቀጥ ብዬ መኪናችን ወደቆመበት ስፍራ አመራሁ ሻንጣዬን አውርጄ የእጅ ባትሪ አውጣሁ የለበስኩትን ቱታ በጅንስ ቀየርኩት ከስክስ ጫማዬንም አደረኩኝ ወፈር ያለ ጃኬት ደረብኩኝ ለምግብ ማብሰያ ከያዝናቸው ዕቃዎች ውስጤ ቢላ አነሳሁ ከዛም ቀጥ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ለመወሰን ወስኛለሁ "ጓደኞቼን አስበልቼ እኔ ቆሜ አልሄድም ወይ እሱ ቆሞ አይሄድም" ብዬ ራሴን የንዴቴ ጥግ ላይ አድርሼ የሚያሳድደኝን ማሳደድ ጀመርኩ የሚፈልገኝን መፈለግ ጀመርኩ የሚያስፈራራኝን ደፈርኩት የሚያስጨንቀኝ ተዳፈርኩት በአንድ ነፍሴ አንድ ጊዜ ማልኩኝ ፍራቻ ከውስጤ ተመንቅሮ ወጣ ደም እንደጠማው መንፈስ ያን ክፉ ሰው እስካገኘው ጊዜው ረዘመብኝ ሴት ነች ወንድን የምትወልደው ሴት ነች የወንድ ልክ ሴትነት ምን እንደሆነ አሳየዋለሁ....የሆስፒታሉ መብራት አሁንም መጣ ቀረት እያለ ነው ነገር ግን ለኔ ምንም ነበር ቀድሞ ጨለማው ያስፈራኝ ነበር አሁን ግን እሱ ከፈራ ይፍራኝ...ጉዞዬን ቀጥያለሁ ሁሉም ክፍሎች እየገባሁ ተመለከትኩኝ ማንም አልነበረም ከጓደኞቼ ጋ የነበርኩበት ክፍልም ገባሁ አሁንም ማንም የለም ነገር ግን አንድ ነገር ቀልቤን ያዘው "ያ ሰው ጓደኞቼ ላይ ጥቃት ካደረሰ እንዴት ደም አልፈሰሰም" ብዬ ራሴን ጠየኩኝ "አምልጠው ቢሆንስ" እያልኩም ከራሴ ጋ ማውራት ጀመርኩኝ ደግሞም ቢያመልጡ እንደዛ አይነት የዋይታ ድምፅ ለምን...ከዛም ከክፍሉ ወጣሁ ወደገባሁበትም ስፍራ ተመለከትኩ ምንም የለም ነገር ግን በተቃራኒው ጥግ ላይ............

............ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል ሁለት እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ



Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን
60 views14:56
Open / Comment
2021-12-01 19:08:53 ​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል ሀያ

፡
....ሰውዬው ነበር እሱ ነገር ግን አልተመለከተኝም ነበር...ወደ ውስጥ ሲገባ ውጪ ላይ አንዳች የረሳው ነገር ያለ ይመስል ወደሗላ እየተመለከተ ነበር እኔም ይሄን ቅፅበት ተጠቅሜ ተደብቄ ወደ ነበረበት ስርቻ ተመለስኩ ግን ወደ ውጪ ሲመለከት የነበረው ሰውዬ ወዲያውኑ ከውስጥ አንዳች ነገር በልቡን የሳበው ይመስል በፍጥነት ዞረ ይመስለኛል ስደበቅ ያሰማሁት ኮሽታ ነው...ለደቂቃዎች በአፍንጫው እያነፈነፈ ቤቱ ውስጥ የገባውን እንግዳ ነገር ማሰስ ጀመረ ቅርቤ ስለነበር ይበልጥ ሰውዬውን መመልከት ቻልኩኝ ሁለቱም አይኖቹ ትክክል አይደሉም አቀማመጣቸውም ይለያል ከአይኖቹ ይልቅ አፍንጫውን አብዝቶ ይጠቀምበታል ነገር የአይኑ ብሌኖች ምስል ይከስቱ አይከስቱ እንጃ...በዚ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሰውዬውን እየተመለከትኩት ሳለ በዕድሜ አነስ የምትለዋ ሴት "ለምን እዚጋ ቆም አንድዬ" አለችው በማይገባ ቋንቋ የሆነ ነገር ብሎ መለሰላት "ምንም የለም ሁሉም ሰላም ነው እናትህ እንደ ድሮው ፀጉርህን ልታበጥርልህ ነው ና ወደ ውስጥ እንግባ" አለችው እያባበለችና የሚወደውን ነገር እየነገረችው እሱም በሃሳቧ ተስማምቶ እቅፍ አርጓት ወደ ውስጥ ገቡ...ውስጤ ለሰውዬው እንደ ማዘን አረገው በሆነ አንዳች ክፉ ክስተት እና ገጠመኝ ለዚ እንደተዳረጉ ለማሰብ ሰከንድ አልፈጀብኝም "ብቻ ከዚ በፊት መልካም ቤተሰቦች የነበሩ እሱም መልኩና አስተሳሰቡ ልቡም ጨካኝ ሳይሆን ሩሩህ ሰው ነበር" እያልኩኝ ከራሴ ጋር ስለ ሰውዬው መነጋገር ጀመርኩ ከዛም ከተደበኩበት በጥንቃቄ ተነስቼ ከኔ ቀጥሎ የሚከሰተውን ትዕይንት ወደሚያሳየኝ የመጋረጃ ሽንቁር ተጠጋሁ ወዲያውኑ ትልቋ ሴትዮ ባለመደገፊያ የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጣለች እሱ ደግሞ አነስተኛ ወንበር ላይ ጀርባውን ሰጥቷት እግሯ መሃል ተቀምጧል በያዘችው ማበጠሪያ ሉጫ ፀጉሩን ወደሗላ በማበጠሪያ ታስተኛዋለች አንዳች አትናገርም ቃልም አይወጣትም ነገር ግን ከአይኗ የሚፈሰው እንባ ከእልፍ ድምፅ አልባ ቃላት የበለጠ ይናገራሉ በሚወርደው የእንባዋ ቦይ ላይ ብዙ ብሶቶቿ እና ችግሮቿ በግልፅ ይነበባሉ ፊቷ እንኳን እንደሚያለቅስ ሰው አልተኮማተረም አልተጨማደደም የማትናገረው ውስጧ ሚብሰለሰል እያደር ሚበላት ግን የማታከው አንዳች ነገር እንዳለ አሰብኩኝ..."አንዳንዴ ጥፍር ደርሶ የማያከው ቆዳ ስጋና አጥንትን አልፎ ከውስጥ የሚበላ ክፉ እከክ" አለ አልኩኝ ለራሴ ደሞም ልክ ነበርኩ በሴትየዋ ሁኔታ ከገባሁበት ሰመመን ስነቃ ሳላስበው ጉንጬ በእንባ ርሷል በጣም ደነገጥኩኝ ግራም ተጋባሁኝ እንዴት ሊሆን እንደቻለም ለራሴ ገረመኝ ግን በቃ ሆነ ልቤ እና አይኔ ተስማምተው በአንድነት አዘኑ በእንባዬም ገለፁት..."ግን የእውነትም እጅግ ያሳዝናሉ አንጀትም ይበላሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ስጋ ይበላሉ እዚህ ቤተሰብ ላይ የተከሰተው አንዳች ክፉ ገጠመኝ ምን ሊሆን ይችላል እንዴትስ ሊሆን ቻለ" እያልኩኝ ራሴን መጠየቄን ተያያዝኩትን ከራሴ ንግግር ተመልሼ በድጋሜ አይኔን በመጋረጃው ሽንቁር ወደ ውስጥ ሰደድኩት ትልቋ ሴትዮ ፈትል የሚመስለው ነጭ ፀጉሯ ከጀርባዋ ላይ ተንጋሏል ከፊት ያለው የፀጉሯ ክፍል አልፎ አልፎ ጥቁር ጣል ጣል ብሎበት የተለየ ውበት ሰጥቷታል ለረጅም ደቂቃዎች ያለማቋረጥ ማበጠሯን ተያይዛዋለች አነስ የምትለዋ ሴትዮ ግን ሰውዬውን ካስገባች በሗላ ደግሜ አልተመለከትኳትም ከነሱጋ አለመሆኗ ቢያስገርመኝም "ለምን" ብዬ ምጠይቀው ሰው የለ ግን ከአይኔ መሰወሯን አልወደድኩትም ውስጤ ተረብሿል... ነገር ግን ቀልቤ አሁንም እናትና ልጁ ላይ ነው...ከዛም እሱ በተራው ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብቶ ውሃና የእግር መታጠቢያ አምጥቶ ቀስ እያለ አጠባት ከዛም ቅባት ነገር ይመስለኛል አነስቶ ከእናቱ ትይዩ ባለው የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጦ በእርጋታ ያሻት ጀመር እሷም ፈገግ እያለች አይን አይኑን ትመለከተዋለች ነገር ግን አሁንም አይኗ ከማንባት አልቦዘኑም ነበር ያለመታከት ያነባሉ የእግር ጣቶቿን አንድ በአንድ እያረገ ዘና እንድትል የተቻለውን ይጥራል ደግሞም ከተቀመጠበት ተነስቶ ጉንጯ ላይ ሚንከራተተውን እንባ በመዳፉ ጠርጎ ግንባሯን ይስማታል...ምን አለ አንዳች ነገር ተከስቶ ወደ ቀድሞው በመለስኳቸው ብዬ ተመኘሁ...እዚ ቦታ ላይ ከዚ በላይ መቆየት እንደሌለብኝ ግልፅ ነው ቶሎም ተመልሼ ጓደኞቼን ከዚ አካባቢ ይዤ መሄድም እንዳለብኝ ግልፅ ነው...የውስጡን ትዕይንት ከምከታተልበት የመጋረጃ ሽንቁር አይኔን አንስቼ ወደ በሩ ስዞር አነስ ምትለዋ ሴትዮ...............

...........ይቀጥላል..........

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ



Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን
81 views16:08
Open / Comment
2021-12-01 19:08:23 ​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል አስራ ዘጠኝ

...ያ ሁካታ እና ጨዋታ በድጋሜ ፀጥ አለ በጣም ደነገጥኩኝ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደምንም ተረጋግቼ አንድ ስርቻ ጋር ተሸጎጥኩ አሁንም ፀጥታው እንደቀጠለ ነው ይመስለኛል ጆሯቸውን ቀስረው በድጋሜ የኔን ድምፅ እየጠበቁ ነው ማንም ከተቀመጠበት የተነሳ የለም...በዚህ ሰዓት ከተደበኩበት ቦታ ቀስ ብዬ በጥንቃቄ ተነሳሁ ልወጣ በሩ አካባቢ ስደርስ ሰውዬውም ሊወጣ ነው መሰለኝ ከወንበሩ ተነሳ ወዲያውኑ ወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ እጅግ በጣም ደነገጥኩኝ ይባስ ብሎ ሰውዬው ሊወጣ ብሎ ወደሗላ መለስ አለ የጠረጠረው እንዳች ነገር እንዳለ ተሰማኝ "በቃ ከዚህ በሗላ ማምለጥና መትረፍ አይታሰብም" ብዬ ለራሴ ነግሬ ጭንቅላቴን ጉልበቴ መሀል አስገብቼ የሚሆነውን መጠባበቅ ጀመርኩ እዛው በቃረቀርኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ከዛም እንደምንም ድፍረቴን ሰብስቤ ፍራቻዬን ተቋቁሜ ከአንገቴ ቀና ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ጋር አልነበረም በጣም ግራ ገባኝ ሲራመድ እንኳን ኮቴ አልተሰማኝም ነበር አሁን የባሰ ጭንቅ ሆነብኝ ሰውዬው ከየት እንደሚመጣ ለመገመትም ከበደኝ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ከተደበኩበት ተነስቼ ቅድም ውስጥ ያለውን ነገር እመለከትበት ወደነበረው የመጋረጃው ሽንቁር ተጠጋሁ ሁለቱ ሴቶች እንደነበሩት ናቸው በአርምሞ ሆነው የሮቤልን አካል ይመገባሉ ቀና ብለው እንኳን አይተያዩም ነበር ግን ከዛ አረመኔ ሰውዬ የተሻለ የተስተካከለ የፊት አቀማመጥ እና ጤናማነት ይታይባቸዋል በድንገት አይኔ ተወርውሮ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለው ሁለት የህፃናት ፎቶ ላይ አርፎ ቀረ "እነዚህ ብላቴናዎች ማን ሊሆን ይችላሉ" ብዬም አሰብኩ በድጋሜ በዛች ሽንቁር ዙሪያ ገባውን መቃኘት ጀመርኩ በድጋሜ አንድ ፎቶ ተመለከትኩ አንዲት መልከ መልካም እናት በጨርቅ የተጠቀለለ ልጅ አቅፋ ከሆስፒታሉ መግቢያ ላይ ቆማ ያሳያል በእርግጥም ሆስፒታሉን አውቀዋለሁ አሁን ያለንበት ቦታ ነው በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር "ህፃን ታቅፋ ፎቶ ላይ ያለችው ሴት ማን ልትሆን ትችላለች" ብዬ ራሴን ጠየኩ ዳሩ መላሽ ባላገኝም በድጋሜ አይኔን ወርወር አድርጌ ሌላ ነገር ማየቴን ቀጠልኩ ፎቶዎቹ በአጠቃላይ ጥቁርና ነጭ ቀለመሸ ያላቸው ናቸው...አይኔን ግድግዳው ላይ ሳንከባልል አንድ መልከ ሸጋ ብላቴ ያለበትን ፎቶ ተመለከትኩ ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ቢከብድም ገዳዩ ሰውዬ ይሆን እንዴ ብዬም አሰብኩ ግን የማውቀውን የፊቱን ገፅታ እና አቀማመጡን ሳስበው ፈፅሞ ሊሆን እንደማይችል ደመደምኩ ግን እነዚ የፎቶ ስብስቦች ያለ ምክንያት እንዳልተሰደሩም ተገንዝቤያለሁ በድንገት በዕድሜ ጠና ያለችው ሴትዮ ተነስታ ስመለከት ወደነበረው መልከ መልካሙ ብላቴና ፎቶ ጋር ጠጋ ብላ በእጆቿ እየዳበሰች በስስት አይን እየተመለከተች ድምፅ ሳታሰማ የእንባዋን ጎርፍ በጉንጯ ላይ ታወርደዋለች ከዛው ሌላኛዋ ሴት ተነስታ ከሗላ በኩል እቅፍ አርጋ የፊቷን የግራ ክፍል ጀርባዋ ላይ አስደግፋ ዝም ብላ አብራት ቆመች ከደቂቃዎች በሗላም ሴትየዋ ማልቀሷን አቆመች ወደነበሩበትም ተመለሱ ግን አሁንም ፊቷ አልተፈታም ነበር ሁለት እጆቿን በእልህ ጨብጣ ከንፈሯን ነክሳ በፍጥነት መተንፈስ ጀመረች ምን ሆነች ሳይባል በድንገት ተነስታ የክፍሉን ዕቃ አመሰችው በዚ ጊዜ ሰውዬው ድምፅ ሰምቶ ሊመጣ ይችላል ብዬወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ አሁን ንግግር ጀምረዋል "እባክሽ እባክሽ ተይ ተረጋጊ" ትላለች በዕድሜ አነስ የምትለዋ "ልጄን ልጄን ልጄን በሉብኝ አንድዬን የአይኔን ማረፊያ የፈጣሪዬን ስጦታ በሉብኝ" እያለች ድምፇን ከፍ አርጋ አምርራ ታለቅሳለች "ራስሽን አትጉጂ እባክሽን ተረጋጊ መድሃኒትሽን መውሰድ አለብሽ እንዲ መሆን የለብሽም የባሰ ታስጨንቂዋለሽ" አለቻት "ማነው ሚጨነቀው" ብዬ ወዲያውኑ ራሴን ጠየኩ "ሴትየዋ ልጄን በሉብኝ ብላ ነው ምታለቅሰው በሉብኝ ማለት ደግሞ ገደሉት ይመስለኛል እና ስለየትኛው ሰው እና ስለየትኛው ልጅ ነው እንደዚ ካየሽ ይጨነቃል" የምትለው ብዬ ከራሴ ንግግር ጀመርኩ የዚህ ቤተሰብ ውስብስብ ታሪክ ይበልጥ ዘልቄ እንዳውቃቸው አጓጓኝ ግን መሞትም እንዳለ አልዘነጋሁትም በድጋሜ ከተደበኩበት ተነስቼ ወደመጋረጃው ሽንቁር አመራሁ አሁን ፀጥታው ተመልሶ ነግሷል ሴትዬዋ መሬት ላይ ተኝታለች በዕድሜ አነስ የምትለው ደግሞ በተኛችበት ፀጉሯን እየደባበሰች ታፅናናታለች የሴትየዋ ጉዳት ከባድ እንደነበር መገመት ቀላል ነው ልጇን ምንም ያርጉት ምንም በብዙ ተጎድታለች ሰው ነችና አሳዘነችኝ አነስ የምትለዋ ሴት መድሃኒቱን እንድትውጥ አድርጋ አረጋጋቻት እዛው ቆሜ በመጋረጃው ሽንቁር እየተመለከትኩኝ ሳለ በድንገት በሩ ተከፈተ ስዞር.............

............ይቀጥላል..........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ



Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን
76 views16:08
Open / Comment
2021-11-30 20:45:06 ​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል አስራ ስምንት

፡
...በድጋሜ "እርዱኝ አድኑኝ" ብሎ ድምፅ አወጣ በዚ ሰውዬው ቡታጋዙ ላይ ተጥዶ የነበረው የሚፍለቀለቅ ዘይት ከመቅፅበት አንስቶ ከፊቱ ጀምሮ እስከ እግሩ ድረስ ደፋበት ሮቤል አምርሮ ክፉኛ ጮኸ ግን ድጋሜ አልጮኸም ነበር ለዘላለሙ በዛው አሸለበ...ይሄን መቆጣጠር አልቻልኩም በዘይት የተጠበሰው የስጋው ሽታ ወደኔ ሲመጣ አጥወለወለኝ ሊያስመልሰኝም ዳዳሁ በብዙ ተፈታተነኝ...እንዳጋጣሚ ሰውዬው ለምን እንደሁ እንጃ ከክፍሉ ወጣ እኔም የሱን አለመኖር ጠብቄ ሚተናነቀኝን አስወጣሁት ከአንድ ደቂቃ በሗላ ሶስት ነጫጭ ሳህን አምጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ምንም አልገባኝም የሩቤል አስክሬን ድርቅ ብሏል አንደበቱ ሊጮህ እንደተከፈተ በዛው ስላሸለበ አልተዘጋም ይሄ ሁሉ ነገር ሲደረግ አይኔን ገልጬ ማየቴ ራሴን እንደ ጨካኝ እንዳይ አድርጎኛል በሌላ በኩል ደግሞ ይሄን ሁላ ትዕይንት መቋቋሜ መልሶ ለራሴ ይደንቀኛል ሰውዬው አሁንም ከዘፈኑ እኩል እየተንቀሳቀሰ ሚከውነውን ይከውናል አንድ ተለቅ ብሎ ስፋት ያለው የሚያብለጨልጭ ስለታም ቢላ እና አነስተኛ ቢላ ይዞ ወደ ሮቤል በድን ተጠጋ ሊሆን ያለውን ማሰብ ለኔ ከባድ ነበር ይህ ከገመትኩት በላይ ክፉና አረመኔ ነው ሰው መባል ሁሉ የለበትም ሰይጣን ስጋ ለብሶ እንጂ...ሰውዬው መለስ ብሎ አነስ ያለ ወንበር ይዞ ወደ በድኑ ተመልሶ ጠጋ ብሎ ተቀመጠ ከዛም በትንሿ ቢላ አስክሬኑን መክፈት ጀመረ ለሚመለከተው የሚያክም እንጂ የሚበልት አይመስልም ዘየት በደንብ ያገኘውን የሰውነት ክፍል እየመረጠ መቁረጥ ጀመረ የቆረጠውንም የሰው ስጋ ባመጣቸው ሳህኖች ላይ እያስተካከለ መደርደር ጀመረ...ሲለው ደግሞ መሀል መሀል ላይ ከሚቆርጠው ስጋ እየቀመሰ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ይደነቃል ይሄን መመልከት ምነኛ አለመታደል ነው ግን ከቤት ወደዚ የመጣሁበትን ቀን አምርሬ ጠላሁት ሲበዛም ረገምኩት...ሰውዬው አሁንም እየቆራረጠ ነው ከትንሽ ደቂቃ በሗላ ሁለቱን ሳህኖች አንስቶ ከክፍሉ ወጣ ብዙም ሳይቆይ በድጋሜ ተመልሶ አንደኛውን ሳህን ይዞ ወጣ እኔም የሚሄድበትን ለመመልከት ብዙ ሳይረቅ ወደ በሩ ተጠጋሁ ሆስፒታሉ ውስጥ ከሚገኝ አንዱን በር ከፍቶ ሲገባ ተመለከትኩት የከፈተውንም በር ሳይዘጋ ወደ ውስጥ አመራ እርምጃዬን አጥፍቼ ያለውን ነገር ለመመልከት ወደ ውስጥ ገባሁ ግን ክፍሉ ባዶ ነበር በጣም ደነገጥኩኝ ወጥመድም መሰለኝ እዛው በቆምኩበት በድንጋጤ እያለከለኩ ተዟዟርኩኝ ግን ማንም አልነበረም የት እንደተሰወረ ግራ ሆነብኝ ነገር ግን የቆምኩበት ወለል እስካሁ ከረገጥኩት የወለል ድምፅ ይለያል ግድግዳ እና ጣሪያ ላይ ሲያማትር የነበረው አይኔን ቁልቁል ወደ ወለሉ ወረወርኩት እውነትም የቆምኩበት ወለል የተለየ ነበር ከላዩ ላይ ወረድኩና በጉልበቴ በርከክ ብዬ ጆሮዬን ላዩ ላይ ደቀንኩና ማዳመጥ ጀመርኩ በጣቶቼም ቆረቆርኩት ከሰማሁት ድምፅ በመናሳት ከታች የሆነ ክፍል እንዳለ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ ውስጥ ያለውን ነገር ገብቶ ለመመልከት ወሰንኩኝ ከዛም ወለል መሳይ በሩን ለመክፈት መታገል ጀመርኩኝ ግን ብዙም አድካሚ አልነበረምና ተከፈተልኝ ቁልቁል ስመለከት ውስጡ ብዙም ብርሃን አልነበረውም ቢሆንም ግን የመመልከት ሀሳቤን አላስቀየረኝም ቀስ ብዬ እግሬን ከደረጃው ላይ አሳረፍኩ በአንድ እጄ በሩን ይዤ በጥንቃቄ ቁልቁል መውረድ ጀመርኩ አልፎ አልፎ ከሚታይ ወጋገን በቀር ክፍሉ ጨለማ ነው እቃ ነገር ጥዬ እራሴ ላይ ወጥመድ እንዳልሆን በጥንቃቄ መራመድ ጀመርኩ ወደፊት በተጠጋሁ ቁጥር ብርሃን እየበዛ መጣ ትንሽ እንደተራመድኩ የሚሳሳቁ የሰዎች ድምፅ ተሰማኝ "ያ ክፉ ሰው ብቻውን አልነበረም ሌሎች የሚያግዙት ሰዎች" አሉ አልኩኝ ለራሴ እርምጃዬን ጠብቄ ወደፊት መሄዴን ቀጠልኩኝ ጨዋታቸው ደርቷል ምን እንደሚባባሉ ግልፅ ባይሆንም ሳቃቸው ግን ይሰማል በነሱ ሁኔታ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሳለ በድንገት ሳላስበው በእግሬ መሬት የነበረ ጣሳ ረገጥኩኝ የፈጠረው ድምፅ ለተንኮል ከፍ ያለ ነበር የደራው ጨዋታቸው እና የሞቀው ሳቃቸው በአንድ ጊዜ ፀጥ አለ በር ሲከፈት ያለው ድምፅ ተሰማኝ የሆነ ሰው ነገሩን ለማጣራት እየመጣ ይመስለኛል እንደዚ ባሰብኩ ጊዜ ከአካባቢው መራቅ ነበረብኝና የሆነ ጥግ ላይ ተደበኩ ግን ማንም አልመጣም ነበር በድጋሜ ቀስ ብዬ ወደፊ ተጠጋሁ ቅድም ሲከፈት የሰማሁት በር ይመስለኛል ከፊት ለፊት ክፍት ሆኖ ይታየኛል ጨዋታው በድጋሜ ደርቷል እየቀረብኩኝ ስሄድ ድምፃቸው ግልፅ እየሆነ መጣ ከእርምጃዎች በሗላ ወደ ክፍቱ በር ደረስኩ አንገቴን አስግጌ ውስጡን ስመለከት የተቀዳደና በደም የመነቸከ ነጭ መጋረጃ ተመለከትኩ ሰዎቹም ከመጋረጃው ጀርባ እንዳሉ ተረዳሁ ቀስ ብዬ ተጠጋሁና በቀዳዳው መመልከት ጀመርኩ ሰውዬው ጀርባው ለኔ ሰጥቶ ነው የተቀመጠው በሱ በስተቀኝ በኩል ተለቅ ያለች አሮጊት ትታየኛለች ከሷ ሴትዮ በመቀጠል ደግሞ ከሁለቱም በዕድሜ ምትበልጥ ሴት ከሱ ፊት ለፊት ተቀምጣለች በድንገት አይኔ የሚመገቡት ነገር አረፈ እሱን ባየው ጊዜ ሳላስበው ድምፅ አወጣሁ........

...........ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል አስራ ዘጠኝ
እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ



Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን
75 views17:45
Open / Comment