Get Mystery Box with random crypto!

Corporate Lawyer

Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer C
Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer
Channel address: @henoktayelawoffice
Categories: Loans, Taxes and Laws
Language: English
Subscribers: 461
Description from channel

⌚️10-11
⚖️" "⚖️

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 2

2022-07-15 08:36:55 በፍትሐብሄር ክርክር #የሰነድ_ማስረጃ ማቅረብ የሚቻለው መቼ ነው

በአብዛኛው ፍ/ቤቶች የጽሑፍ ማስረጃዎች ከክስ ጋር ወይንም ከመከላካያ መልስ ጋር አብሮ ካልቀረበ መቅረብ አይችልም በሚል ሲከለክሉ ይታያል፡፡ ነገር ግን በሥነ-ሥርዓት ህጋችን ግን ከክስ ማመልከቻ ወይም ከመከላካያ መልስ በኋለ ክስ ከመሰማቱ በፊት ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ ያልቀረበ የጽሑፍ ማስጃዎች ካሉ መቅረብ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡

# ሀ . የፅሑፍ ማስረጃዎች በሙሉ ክርክሩን መስማትና ምስክሮችን መመርመር ከመጀመሩ በፊት ተጠቃለው መግባት አለባቸው፡፡

# ለ . በመጀመሪያ ደረጃ ከሳሹ ከክስ ማመልከቻው ጋር ተከሳሹ ደግሞ ከመከላከያ መልሱ ጋር ይጠቅመናል የሚሉትንና በእጃቸው የሚገኙትን ወይም ሊያቀርቡ የሚችሉትን የጽሑፍ ማስረጃ በሙሉ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው (ቁ.223(1)) (ለ) እና 234 (1)፡፡

# ሐ . በሁለተኛ ደረጃ ተከራካሪ ወገኖች ለማቅረብ የሚችሉትንና ይጠቅማናል የሚሉትን ወይም ፍርድ ቤቱ እንዲቀርብ የጠየቀውንና አስቀድመው ፍርድ ቤት ያላቀረቡትን የፅሑፍ ማስረጃ ሁሉ በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ማቅረብ አለባቸው
(ቁ. 137 (1)) ፡፡

# መ. ማንኛውም አቤት ባይ ሰነዶችን ከአቤቱታው ጋር በማያያዝ ወይም ከቀነ ቀጠሮው በፊት ወይም በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ካላቀረበ በቀር ማስረጃዬ ከፍርድ ቤቱ መዝገብ ጋር ይያያዝልኝ ወይም ለማቅረብ ይፈቀድልኝ በማለት ለማመልከት አይችልም (137(3)፡፡

# ሠ . መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች ከተከራካሪዎች ወገኖች ባንዳኛው
ጉድለት ወይም በቂ ባልሆነ ምክንያት ሳይቀርቡ የቀሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ወዲያው ፍርድ ይሰጣል (ቁ. 256(1))፡፡

# ረ . ከላይ በ “መ” እና “ሠ” ሥር የተጠቀሱት አጠቃላይ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ከአቤቱታ ጋር ወይም በመጀመሪያ ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ የፅሁፍ
ማስረጃ በሌላ ጊዜ ሊቀርብ የሚችልበት ልዩ ሁኔታዎች (exceptions) አሉ፡፡

እነዚህም፡-
#1. ፍርድ ቤቱ በራሱ አስተያየት ወይም በተከራካሪዎች ወገኖች አመልካችነት
በሌላ ፍ/ቤት ዘንድ የሚገኝ መዝገብ ወይም የጽሑፍ ማስረጃ እንዲቀርብ ማዘዝ
ይችላል (ቁ.148 (11))፡፡

#2. ማስረጃዎቹ ሳይቀርቡ የቀሩት ከባድና በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተረዳ ስለ ክርክሩ አወሳሰንና ማስረጃ ያለመቅረቡ ስላስከተለው ኪሳራ
ተገቢ መስሎ የታየውን ትፅዛዝ በመስጠት ነገሩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ይወስናል (ቁ. 256 (1)፡፡ (ማስረጃው እንዲቀርብ ማዘዝ ይችላል፡፡)

#3. አስፈላጊ መስሎ ከታየው ፍርድ ቤቱ የክርክሩን ጭብጥ ከመያዙ በፊት በተከራካሪዎች ያልቀረበን የፅሑፍ ማስረጃ በትዕዛዝ አስቀርቦ መመርመር
ይችላል (ቁ. 149 (1) )፡፡

#4. ክርክሩ በሚሰማበት በማናቸውም ግዜ ፍርድ ቤቱ በተከራካሪዎቹ ያልቀረበ
ነገር ግን ለክርክሩ ጠቃሚ የሆነ የፅሑፍ ማስረጃ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል
(ቁ.164)፡፡

#5. ምስክሮችን መስቀለኛ ጥያቄ ለመጠየቅ ወይም ምስክሩ ነገሩን ለማስታወስ እንዲችል የሚቀርብ የጽሑፍ ማስረጃ በመጀመሪያ በይቀርብም ክርክሩ በሚስማበት ጊዜ መቅረብ ይችላል (137 (4)) ፡፡
@Henoktayelawoffice

share
4.5K viewsedited  05:36
Open / Comment
2022-07-14 15:33:35
@Henoktayelawoffice
4.4K views12:33
Open / Comment
2022-06-10 10:59:01 Ethio Law ኢትዮ ሕግ pinned «ይዞታ ከመግዛት በፊት ሊደረግ ስለሚገባ ቅድመጥንቃቄ ------------------------- አንዳንድ ሰዋች በተጭበረበረ መንገድ የራሳቸው ያልሆነ ይዞታን በሽያጭ እያስተላለፋ ይገኛሉ።እንዲህ አይነት ተግባር ከቀን ወደ ቀን እየተበራከተ በመምጣቱ በይዞታ ላይ የሚነሱ ክርክሮች በብዛት በየፍርድ ቤቱ ይስተዋላል። የትኛውንም ቤት ወይም ይዞታ ከመግዛት በፊት እነዚህን አምስት ቅድመ ጥንቃቄዋች ማድረግ ሕጋዊ…»
07:59
Open / Comment
2022-06-09 16:43:58 ውል መሰረዝ፤ ማፍረስ እና በስምምነት ማቋረጥ
ውል መሰረዝ
ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንደኛው እንደ ውሉ ባለመፈጸሙና የውሉን ግዴታ በመጣሱ በተዋዋዩ ወይም በፍርድ ቤት ውሉን ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች ቀሪ ማድረግ
ውል የሚሰረዘው ከመሠረቱ ግድፈት ስላለው አይደለም፡፡ ይልቁንም የውል መሠረዝ ምክንያት ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታን ከመፈፀምና ካለመፈፀም ጋር ተያይዞ የሚከሠት ነው፡፡ የውል መሠረዝ ሥርዓትም የራሱ የሆነ አካሄድ አለው፡፡ ይኸውም ውሉን የመሠረዝ ፍላጐት ያለውን ወገን የውሉ ግዴታ ባለመፈፀሙ የተነሳ ከህግ ወይም ከውሉ ከራሱ ባገኘው መብት ተጠቅሞ ውሉን ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆንበት አጋጣሚም ግዴታው ባለመፈፀሙ የተነሳ የደረሰውን ጉዳት ከማረጋገጥ ጋር ተያይዞ የሚታይ እንጂ ጥያቄ አቅራቢው ሁል ጊዜ ተቀባይነት የሚያገኝበት አይደለም፡፡ በመሆኑም የውል ይሰረዝልኝና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በህጉ አግባብ የሚስተናገዱ ስለመሆኑ የፍ/ህ/ቁ. 1784 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በተናጠል መሰረዝ
አንደኛው ተዋዋይ ወገን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን መሠረት በማድረግ ውልን በተናጠል ለመሠረዝ የሚችለው ከሚከተለት ሶስት ሁኔታዎች አንደኛው የተሟላ መሆኑን ለማስረዳት ሲችል ነው፡፡
• የመጀመሪያው ባለዕዳው በውሉ ላይ በተመለከተው መሠረት የውሉን ግዴታ የሚፈፅምበት ቁርጠኛ ጊዜ በውሉ ላይ በግልፅ ተመልክቶ እንደሆነና በውሉ ላይ የተገለፀው ቁርጥ የሆነ የውል መፈፀሚያ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውሉን ለመሰረዝ የሚችል መሆኑን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1775(ለ) ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
• ሁለተኛው ምክንያት ባለዕዳው ውሉን ያልፈፀመበትን ምክንያትና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ዳኞች ባለዕዳው ውሉን የሚፈፅምበት የችሮታ ጊዜ ከሰጡት በኋላ ባለእዳው በዳኛ ውሣኔ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1770 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡
• ሶስተኛው ባለገንዘቡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 በተደነገገው መሠረት ሌላኛው ተዋዋይ (ባለዕዳው) በውል የገባውን ግዴታ የሚፈፅምበትን ጊዜ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆንና በማስጠንቀቂያው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይፈፅም ሲቀር መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ሌላኛው ተዋዋይ ወገን በውሉ መሠረት እንዲፈፅም ለመጠየቅና ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የሚችለው በመጀመሪያ እሱ የበኩሉን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የተዘጋጀ ሲሆን እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1857 በግልፅ ይደነግጋል፡፡
ስለሆነም ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ መሠረታዊ ዓላማና ግብ እንደዚሁም የድንጋጌውን የተፈፃሚነት ወሰን ለመረዳት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 ድንጋጌዎች ጋር በማጣመር መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ስንመዝነው አንደኛው ተዋዋይ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 ሌላኛው ተዋዋይ ውሉን እንዲፈፅምለት ለመጠየቅ፤ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 ድንጋጌዎች መሠረት የውል መፈፀሚያ ጊዜ ግልፅ ማስጠንቀቂያ በመስጠትና በፍትሐብሔር ቁጥር 1787 በተደነገገው መሠረት ውሉን በተናጠል ለመሠረዝ በመጀመሪያ በእሱ በኩል በውል የተጣለበትን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ በማስረጃ ለማረጋገጥ የቻለ መሆን እንዳለበት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌዎችን ይዘትና መሠረታዊ ግብ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሕግ አውጭው በውል ለገባው ግዴታ ተገዥ በመሆን በእሱ በኩል ያለውን ግዴታ ያልፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያልቻለ አንድ ተዋዋይ ወገን ሌላኛውን ተዋዋይ ወገን ቀድሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን በተናጠል እንዲሰርዝ በማሰብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን አውጇል ተብሎ አይገመትም፡፡ አንድ ተዋዋይ የውሉን መፈፀሚያ የጊዜ ገደብ በመግለጽ ለሌላኛው ወገን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውል በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው በመጀመሪያ እሱ በውሉ የገባውን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 57280 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 1770፣ 1771፣ 1774፣ 1757፣ 1787
ውል ማፍረስ
በህጉ የተቀመጡት የውል አመሰራረት መስፈርቶችን ያለሟላና ግድፈት ያለበት በመሆኑ የተነሳ የውሉ ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች መቅረት
ውል ማፍረስና ውል መሠረዝ በውል የተቋቋሙት ግዴታዎች ከሚቀሩባቸው መንገዶች ውስጥ የሚካተቱ ቢሆንም ምክንያታቸውና ውጤታቸው የተለያዩ ነው፡፡ የውል ማፍረስ ከውል አመሠራረት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ሲሆነ
ውሉ ከአመሰራረቱ በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱ ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል የውል መሰረዝ ጉዳይ ከውል አመሰራረት ችግር የሚነሳ ሳይሆን ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታውን ካለመወጣት የሚመነጭ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በስምምነት ማቋረጥ /ቀሪ ማድረግ/
ተዋዋይ ወገኖች በውል አቋቁመውት የነበረውን ግዴታ በፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት በስምምነት ቀሪ ሲያደርጉ የተለየ ፎርም መከተል እንዳለባቸው የሚደነግግ አስገዳጅ ድንጋጌ የለም፡፡ የውለታ በተዋዋዮች ስምምነት መቋረጥ (terminate) መደረግ ከውል መፍረስ ወይም ከውል መሠረዝ የተለየ ባህሪና ውጤት ያለው መሆኑን አግባብነት ያላቸውን የፍታብሔር ድንጋጌዎች ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ እንደዚሁም ውል በስምምነት ቀሪ ማድረግ (termination of contract) ውልን ከማሻሻል (ውል ከመለወጥ) (variation of contract) እና ውል ከመተካት (Novation of contract) የተለየ ባህሪ፣ ይዘትና ውጤት ያለው መሆኑን፣ የፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን፣ የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1722 እና የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1826 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
የውሉ በተዋዋዮቹ ፈቃድና ስምምነት መቋረጥ (ቀሪ) መሆን የተዋዋይ ወገኖች የወደፊት የውል የመፈፀም ግዴታ የሚያስቀር መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል፡፡ እንደዚሁም የውሉ መቋረጥ /ቀሪ/ መሆን ያለፈውን ሁኔታ የማይነካ መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 3 ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የውል ቀሪ መሆን (termination of contract) ተዋዋዮቹ በውል አቋቋመውት የነበረውን መብትና ግዴታ ቀሪ የማድረግ ውጤት የሚኖረው መሆኑን ከፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1807 /ለ/ ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 63063 ቅጽ 14፣ ፍ/ህ/ቁ. 1682-84፣ 1722
በአብላጫ ድምፅ የተሰጠ
@Henoktayelawoffice Join
2.9K views13:43
Open / Comment
2022-06-09 16:28:16 ይዞታ ከመግዛት በፊት ሊደረግ ስለሚገባ ቅድመጥንቃቄ
-------------------------
አንዳንድ ሰዋች በተጭበረበረ መንገድ የራሳቸው ያልሆነ ይዞታን በሽያጭ እያስተላለፋ ይገኛሉ።እንዲህ አይነት ተግባር ከቀን ወደ ቀን እየተበራከተ በመምጣቱ በይዞታ ላይ የሚነሱ ክርክሮች በብዛት በየፍርድ ቤቱ ይስተዋላል።
የትኛውንም ቤት ወይም ይዞታ ከመግዛት በፊት እነዚህን አምስት ቅድመ ጥንቃቄዋች ማድረግ ሕጋዊ ይዞታ ለመግዛት ያግዛል።
ይህንንም መረጃ ከዚህ video ማግኘት ይችላሉ። #subscribe


2.3K viewsedited  13:28
Open / Comment
2022-06-08 06:17:57 ያልታተሙ የሰበር ውሳኔዎች
2.8K views03:17
Open / Comment
2022-06-07 20:18:24



#subscribe
660 viewsedited  17:18
Open / Comment
2022-06-05 18:48:26 Watch "ባለአንድ አባል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማቋቋም በአዲሱ የንግድ ሕግ ተፈቀደ ።
አንድ ሰው ብቻውን ኩባንያ መመስረት የሚችልበት የሕግ አግባብ ምንድ ነው?"
on YouTube




ከዚህ ቀደም በነበረው የንግድ ሕግ አንድ ሰው ከሌሎች ሰዋች ጋር ካልተጣመረ በቀር ማህበር ወይም ኩባንያ ማቋቋም አይችልም ነበር።
አዲሱ የንግድ ሕግ አንድ ሰው ብቻውን ኩባንያ ማቋቋም የሚችልበትን አግባብ አመቻችቷል።
ባለአንድ አባል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማለት ምን ማለት ነው?እንዴት ማቋቋም ይቻላል?
ባለአንድ አባል ሀላፊነቱ የተወሰነ ማህበር ለማቋቋም ምን ያህል ካፒታል ያስፈልጋል?
በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማራ ነጋዴ ንግዱን ወደ ድርጅት እንዴት ማሳደችግ ይችላል?
በዚህ video ላይ ምላሹን ያገኛሉ
1.1K viewsedited  15:48
Open / Comment
2022-06-04 14:42:20

1.8K views11:42
Open / Comment
2022-06-03 18:33:29 https://www.bbc.com/amharic/59633486
1.1K views15:33
Open / Comment